ይግባኝ የማቅረቢያ የመጨረሻ ቀን የመንግስት ስራ ዝግ በሆነበት ቀን ላይ ያረፈ ሲሆንና በቀጣዩ የሥራ ቀን አቶ መሀመድ ሙህዱን እና www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XXVIII ተዘጋጅቶ ሲቀርብ ይግባኙ እንዱከፈት መፍቀድ ሥነሥርዓታዊ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1862፣ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 323/2 ፣326 ዘምዘም አሉ
No summary available.
መስከረም 21 ቀን 2011 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንዲሻዉ አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች:- አቶ መሀመድ በሀዱን-አልቀረበም።
ተጠሪ፡- ዘምዘም አሉ-አልቀረበም።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የይግባኝ ጊዜን የሚመለከት ነው። የፋዳራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍ/ቤት የአሁን አመልካች ያቀረበው ታሕሳስ 16 ቀን 2010 ዓ.ም ላቀረበው የይግባኝ ቅሬታ የይግባኝ ማስፈቀጃ ምክንያት ያቀረበ ቢሆንም የይግባኝ ማስፈቀጃ ምክንያቱ በቂ አይደለም በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 326 መሰረት መዝገቡን ዘግቶታል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህንኑ ትዕዛዝ በመቃወም ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- የፋዳራለ ከፍተኛ ሸሪዓ ፍ/ቤት በመ. በቀን 15/02/2010 ዓ.ም የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም አመልካች የይግባኝ ማመልከቻ አቅርቤ ግልባጩ የተሰጠኝ በቀን 13/04/2010 ዓ.ም በእለተ አርብ ነው፤አመልካች ቅዲሜ እና እሁድ የመንግሥት ሥራ ዝግ ስለሆነ ታሕሣሥ 16 ቀን 2010 ዓ.ም የይግባኝ ቅሬታዬን ለፍ/ቤቱ ያቀረብኩ ቢሆንም ፍ/ቤቱ የይግባኝ ጊዜው አልፎል በማለት የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥሕተትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የጠቅላይ ሸሪዓ ፍ/ቤቱ አመልካች ይግባኙን በቀን 16/04/10 ዓ.ም ማቅረቡን በገለጸበት ሁኔታ የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜው አልፎል በማለት የሰጠውን ትዕዛዝ አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ በዚህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል። ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የተጠሪ መልስ ይዘት በአጭሩ፡- ይግባኝ የተጠየቀበት ውሳኔ የተሰጠው በቀን 15/02/10 ዓ.ም ሲሆን አመልካች ይግባኙን ያቀረበው በቀን 16/04/10 ዓ.ም በመሆኑ በራሱ ቸልተኝነት የይግባኝ ጊዜው ያለፈበት መሆኑን የሚያሳይ ነው፤የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ የሚቆጠረው ቀኖቹን በተከታታይ በመቁጠር እንጂ ቅዲሜ እና እሁድን በመተው አይደለም፤አመልካች በበቂ ምክንያት የተደገፈ የይግባኝ ማስፈቀጃ ያላቀረበ በመሆኑ አቤቱታው ውድቅ ላደረግ ይገባል የሚል ነው።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው። ይህ ችልትም እንዱጣራ የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል።
ይግባኝ የተጠየቀበት ውሳኔ የፋዳራለ ከፍተኛ ሸሪዓ ፍ/ቤት በመ. በቀን 15/02/2010 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሆኑ፤አመልካች ግልባጭ እንዱሰጠው የጠየቀው በቀን 12/04/10 ዓ.ም መሆኑን፤አመልካች የመዝገብ ግልባጭ የተሰጠው በቀን 13/04/2010 ዓ.ም በእለተ አርብ መሆኑ እና ይግባኙን ያቀረበው በቀን 16/04/2010 ዓ.ም መሆኑን የድሬዲዋ ፋዳራል ከፍተኛ ሸሪዓ ፍ/ቤት በቀን 13/04/10 ዓ.ም የጻፈው መሸኛ ደብዲቤ ያሳያል። ከደብዲቤው ይዘት መገንዘብ የሚቻለው ታሕሣሥ 12 ቀን 2010 ዓ.ም እና ታሕሣሥ 13 ቀን 2010 ዓ.ም የሆኑን ሁለቱ ቀናት በአመልካች ጥፊት ያልባከኑ መሆኑን ነው።
በመሰረቱ የይግባኝ አቤቱታ አቀራረብ የሚመራው በሥነ-ሥርአት ሕጉ በተዘረጋው ሥርአት መሰረት ነው። የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 323/2 ድንጋጌ የመጀመሪያ ደረጃው ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ፤ብይን ወይም ትእዛዝ ቅር የተሰኘ ተከራካሪ ወገን የይግባኙን አቤቱታ ለይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ማቅረብ ያለበት ይግባኝ በሚባልበት ጉዲይ ላይwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በተፈረደ በ60 ቀን ውስጥ መሆኑን ይደነግጋል። በዚህ ጊዜ ውስጥ ይግባኙን ያላቀረበ ተከራካሪ ወገን ይግባኙ እንዱከፈት ይግባኝ ማስፈቀጃ ማቅረብ እንዲለበት የዚሁ ሕግ ቁጥር 324 ያስገነዝበናል። የይግባኝ ማስፈቀጃ የቀረበለት ፍ/ቤትም በዚሁ ሕግ ቁጥር 326 መሰረት ይግባኝ ጠያቂው ይግባኙን በጊዜው ለማቅረብ ያልቻለበትን ምክንያት በቂ መሆን አለመሆኑን መርምሮ ይግባኙ እንዱከፈት ሉፈቅድ ወይም ሉከለክል እንደሚችል ከድንጋጌው ይዘት መገንዘብ ይቻላል።
በያዝነው ጉዲይ ይግባኝ አመልካች የፋዳራለ ከፍተኛ ሸሪዓ ፍ/ቤት በመ.
በቀን 15/02/2010 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ መጠየቅ ይችል ዘንድ ግልባጭ እንዱሰጠው የጠየቀው የ60 ቀኑ የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ሳያልፍ በቀን 12/04/10 ዓ.ም ሲሆን የመዝገብ ግልባጭ የተሰጠው ደግሞ በቀን 13/04/2010 ዓ.ም በእለተ አርብ በመሆኑ ይግባኙ የሚቀርብበት የመጨረሻው ቀን የመንግስት ሥራ ዝግ በሆነበት ቀን ላይ አርፎል።አመልካችም በቀጣዩ ቀን ታሕሳስ 16 ቀን 2010 ዓ.ም ይግባኙን አቅርቧል። የሥር ፍ/ቤት አመልካች ያቀረበው ምክንያት በቂ አይደለም በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 326 መሰረት መዝገቡን የዘጋው ቢሆንም የይግባኝ አቤቱታ ማቅረቢያ ጊዜ ከሆኑት ስልሳ ቀናት ውስጥ ሁለቱ ቀናት በአመልካች ችግር የባከኑ ካለመሆናቸው ባሻገር ይግባኝ የማቅረቢያው የመጨረሻ ቀን የመንግስት ስራ ዝግ በሆነበት ቀን ላይ ያረፈ በመሆኑ፤የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1862 ግዳታው የሚፈጸምበት ቀን ከአንድ የበአል ቀን ጋር ከገጠመ በዓል ባልሆነበት በማግስቱ ባለው የሥራ ቀን እንደሚተላለፍ በሚደነግገው አግባብ በተመሣሣይ ሁኔታ አመልካችም ጊዜ ሳያባክን በቀጣዩ የሥራ ቀን ይግባኙን አዘጋጅቶ ያቀረበ ከመሆኑ እና ይግባኝ ሕገ መንግስታዊ ዋስትና ያለው መብት ከመሆኑ አኳያ አመልካች ይግባኙ እንዱከፈት ያቀረበው ምክንያት በቂ ነው ተብል ይግባኙ እንዱከፈት መፍቀድ ሥነ-ሥርዓታዊ ሆኖ አግኝተነዋል። የስር ፍ/ቤትም ጉዲዩን በዚህ አግባብ በማየት ይግባኙ እንዱከፈት መፍቀድ ሲገባው አመልካች ይግባኙ እንዱከፈት ያቀረበው ምክንያት በቂ አይደለም በማለት መዝገቡን መዝጋቱ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የፋዳራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት በመ. ታሕሳስ 30 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥሕ/ቁ 348/1 መሰረት ተሸሯል።
አመልካች ይግባኙ እንዱከፈት ያቀረበው ምክንያት በቂ ምክንያት ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 326/1 መሰረት ይግባኙን እንዱያቀርብ ተፈቅድለታል።
አመልካች የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ከደረሰው ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በአሥር ቀን ጊዜ ውስጥ ይግባኙን ያቅርብ ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ ግራቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።
No topics extracted.