አንድ ተከሳሽ የቀረበበት ክስ በይርጋ የሚቋረጥ መሆኑን ከጠቀሰ ከሳሹ ክሱ በሕጉ የተመለከተው ጊዜ ገደብ (ይርጋ) ያላለፈው መሆኑን፣ ጊዜው አልፍ ከሆነም ይርጋውን ሉያቋርጥ የሚችል ሕጋዊ ምክንያት መኖር ያለመኖሩን በተገቢው ማስረጃ ለማስረዲት የሚችልበት እድል ሳይሰጠው የተከሳሽ መቃወሚያ ብቻ መሰረት ተደርጎ ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው ተብል ብይን የሚሰጥበት አግባብ ስነ ስርዓታዊ ስላለመሆኑ ፍ/ብ/ሕ/ቁጥር1000፣1846፣1852እና1853፤የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ ቁጥር 241፣ 244 እና 245(1)
No summary available.
መስከረም 23 ቀን 2011 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውልስ ኦርሺሶ አመልካች፡-
ተጠሪ፡-
ውቢት ዘውዳ- ቀረቡ ።
ትግስት ዘውዳ- ወኪል ደሳለኝ ታምራት ቀረቡ ።
ልቡ በቀለ-ቀረበ።
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካቾች ከወላጅ አባታቸው ከሟች ቄስ በቀለ ሀ/ወልድ በውርስ ሉያገኙ የሚገባውን ይዞታና ግምታቸው ብር 19,000.00 የሚሆኑ ከብቶችን በ25/11/2005 ዓ/ም በተደረገ ኑዛዜ መሰረት የነቀሎቸው መሆኑን ጠቅሰው ኑዛዜው ፈርሶ ድርሻቸውን እንዱያካፍሎቸው ይወሰን ዘንድ የአቀረቡትን የዲኝነት ጥያቄ የሱልልታ ወረዲ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ20/06/2009 ዓ/ም በይርጋ ውድቅ አድርጎ ብይን ሰጥቶ በፉንፉኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በ7/11/2009 ዓ/ም በውሳኔ፣ የኦሮሚያ ብሓረዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር አጣሪ ችልት በመዝገብ በ14/03/2010ዓ.ም. በትዕዛዝ ማጽናታቸውwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት አመልካቾች በ13/06/2010 ዓ/ም የተፃፈ የሰበር አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
አመልካቾች በ12/07/2008 ዓ/ም ያቀረቡት ክስ መሰረታዊ ይዘቱ ሲታይም የአመልካቾችና የ3ኛ ተጠሪ ወላጅ አባታቸው ሟች ቄስ በቀለ ሀ/ወለድ መሆናቸውን፣ ሟች በሕይወት እያለ በ25/11/2004 ዓ/ም ባደረጉት ኑዛዜ አመልካቾችን ከውርስ የነቀለ መሆኑን ጠቅሰው ኑዛዜው ፈርሶ አመልካቾች ከሟቹ የገጠር መሬት ይዞታና ከብቶች ድርሻቸውን እንዱያገኙ ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ለክሱ በሰጡት መከላከያ መልስም ክሱ በይርጋ የሚታገድ መሆኑን፣ የኑዛዜ ወራሽነታቸውም ቀድሞ በፍርድ ያለቀ በመሆኑ አመልካቾች አዱስ ክስ ማቅረባቸው ተገቢ ያለመሆኑን ጠቅሰው የተከራከሩ ሲሆን 3ኛ ተጠሪ ግን የአመልካቾችን ክስ ተገቢ መሆኑን በማመን ተከራክረዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ምስክሮች በመስማትና ለጉዲዩ ተያያዥነት አላቸው ያላቸውን የመ/ ን አስቀርቦ ከተመለከተ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ አመልካቾች ኑዛዜው እንዱፈርስ የጠየቁት ከሶስት አመት በኋላ መሆኑ ተረጋግጧ በማለት ክሱን ውድቅ አድርጓል። አመልካቾች በወላጅ አባታቸው ኑዛዜ ከውርስ የነቀለ መሆኑን ጠቅሰው ያቀረቡት ክስ በይርጋ የታገደ ነው ተብል በተሰጠው የብይን ክፍል ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ የሰበር አቤቱታቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ብይን በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- በአባታቸው በ25/11/2004 ዓ/ም የተደረገው ኑዛዜ ከውርስ የነቀላቸው መሆኑን፣ ይዞታውንም በስምምነት ተካፍለው ሲጠቀሙ የነበረ ከመሆኑም በላይ ክርክሩም እኩል ደረጃ ላይ በማይገኙ ወራሾች መካከል ሁኖ እያለ የበታች ፍርድ ቤቶች ክሱ በይርጋ የታገደ ነው በማለት ብይን መስጠታቸው ያላግባብ ነው የሚል ነው። አቤቱታቸው ተመርምሮም አመልካቾች አከራካሪውን የውርስ ንብረት መጋቢት 13 ቀን 2005 ዓ/ም ተደረገ በተባለ ስምምነት ተካፍለው ሲጠቀሙ የነበረ ከመሆኑ አንጻር ክሱ በይርጋ የታገደ ነው ተብልwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ተብል ጉዲዩ ለዚህ ችልት እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ተጠሪዎች በመቅረባቸውም ግራ ቀኙ በፅሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይሀ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክርና ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነውን ብይን አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች አንጻር እንደሚከተለው መርምሮታል። እንደመረመረውም የችልትን ምላሽ የውርስ ንብረት በስምምነት ክፍፍል ተደርጎበት የነበረ መሆን ያለመሆኑና በተለያዩ መዝገቦች በክርክር ላይ የቆዩት ወገኖች በይርጋው አቆጣጠር ላይ የሚኖረው ሕጋዊ ውጤት ሳይለይ ክሱ በይርጋ የታገደ ነው ተብል ብይን መሰጠቱ ተገቢ ነው? ወይስ አይደለም?
የሚለው ሁኖ አግኝተናል።
አመልካቾች አጥብቀው የሚከራከሩት ወላጅ አባታቸው ከሕግ ውጪ ከውርስ የነቀለና ከውርስ ንብረቶች መካከል የሟችን ይዞታና ባህርዛፍ ከሟች ቄስ በቀለ ሀ/ወልድ ተወላጆች ልጆችና ወራሾች ጋር በሽማግላ ለመከፊፈል ስምምነት አድርገው በስምምነቱ መሰረት ክፍፍል ተደርጎ ይዞታዎቹን በመጠቀም ላይ የሚገኙና የገጠር መሬት ባለይዞታነት ማረጋገጫ ደብተርም ያወጡበት ሁኖ እያለ ክሱ በይርጋ የታገደ ነው መባለ ያላግባብ ነው በሚል ሲሆን 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ደግሞ በአመልካቾች የተጠቀሰው ስምምነት የላለ መሆኑን፣ 3ኛ ተጠሪ ደግሞ የአመልካቾችን ክርክር ደግፈው የሚከራከሩ መሆኑን ተገንዝበናል። 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች አመልካቾች አለ የሚለት ስምምነት የለም ከማለት ውጪ ይህ ክርክር በስር ፍርድ ቤት ያልቀረበ መሆኑን በዚህ ችልት ባቀረቡት የመልስ ማመልከቻቸው ገልፀው ያልተከራከሩ ሲሆን የሥር ፍርድ ቤትም በአመልካቾች በኩል የተጠቀሰው የክፍፍል ስምምነት መኖር ያለመኖሩን በግልጽ ለይቶ ያረጋገጠው ፍሬ ነገር የለም።
በመሆኑም የአመልካቾች የወላጅ አባታቸውን የውርስ ንብረት ድርሻ ለመካፈል ያቀረቡት ጥያቄ የይርጋ ጊዜ ያለፈበት መሆን ያለመሆኑን አመልካቾች በክሳቸው እና በቃል ክርክራቸው ጊዜ የገለጿቸው ፍሬ ነገሮች በተለይም መጋቢት 13 ቀን 2005 ዓ/ም ተደረገ የተባለ የክፍፍል ስምምነት መኖር ያለመኖሩና በዚህ ስምምነት መነሻ ድርሻ ድርሻቸውን ይዘው የሚገኙ፣ የይዞታ ማረጋጋጫ ደብተርም ከሚመለከተው አካል በሕግ አግባብ የተሰጣቸው መሆን ያለመሆኑ በማስረጃ ሳይነጥር ሉወሰን ይችል የነበረ አይደለም።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
አመልካቾች ይዞታውን ሲጠቀሙ የነበረ መሆኑን፣ የወራሽነት መብታቸውን ለማስከበርም በወረዲው ፍርድ ቤት በመ/ ክርክር የነበረ መሆኑን ጠቅሰው ተከራክረዋል። በዚህ ረገድ የቀረበው የአመልካቾች የክርክር ነጥብ ደግሞ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1852 አንጻር ምን አይነት ሕጋዊ ውጤት ሉያስከትል እንደሚችል በስር ፍርድ ቤት በጭብጥነት ተይዞ መታየት የነበረበት መሆኑን ለመገንዘብ ችለናል። አንድ ተከሳሽ የቀረበበት ክስ በይርጋ የሚቋረጥ መሆኑን ከጠቀሰ ክስ አቅራቢ ወገን ክሱ በሕጉ የተመለከተው ጊዜ ገደብ (ይርጋ) ያላለፈው መሆኑን፣ ጊዜው አልፍ ከሆነም ይርጋውን ሉያቋርጥ የሚችል ሕጋዊ ምክንያት መኖር ያለመኖሩን በተገቢው ማስረጃ ለማስረዲት የሚችልበት እድል ሳይሰጠው የተከሳሽ መቃወሚያ ብቻ መሰረት ተደርጎ ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው ተብል ብይን የሚሰጥበት አግባብ ስነ ስርዓታዊ ያለመሆኑን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 241፣ 244 እና 245(1) ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1000፣ 1846፣ 1852 እና 1853 ድንጋጌዎች ጋር አጣምረን በምናነብበት ጊዜ የምገነዘበው ጉዲይ ነው። ስለሆነም በተከሳሽ ወገን በቀረበ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ውሳኔ ከመሰጠቱ በፉት ፍርድ ቤቱ ተገቢ መስል የሚገምተው ማስረጃ እንዱቀርብለት ትዕዛዝ መስጠት ወይም የተቆጠረ ማስረጃ ካለም መስማት የሚችል ስለመሆኑ በስነ ስርዓት ሕጉ በአንቀጽ 245 (1) ከተመለከተው ድንጋጌም የምንችለው ጉዲይ ሁኖ እያለ የሥር ፍርድ ቤት አመልካቾች አለን የሚለትን ስምምነት ሰነድ ትክክለኛነትና ሕጋዊነት አጣርቶና በሕጉ አግባብ ለአመልካቾች የተሰጣቸው የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ካለም እንዱቀርብ አድርጎ እንዱሁም በመ/ በተደረጉ ክርክሮች ይርጋው ሉቋረጥ የሚችል መሆን ያለመሆኑን ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1852 ድንጋጌ አንጻር በመመርመር ሕጋዊ ውጤቱን ሳይለይ የአመልካቾችን የወላጅ አባታቸውን የውርስ ንብረት ድርሻ እንድንካፈል ይወሰንልን የሚለውን ክስ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1000 (1) ድንጋጌን ጠቅሶ ውድቅ ማድረጉ ተገቢውን የክርክር አመራር ስርዓት የተከተለ ሁኖ አልተገኘም። የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ሆነ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር አጣሪ ችልት የስር ፍርድ ቤት ብይን ከላይ የተጠቀሱትን ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ከአመልካቾች የክርክር ነጥቦች ጋር ያላገናዘበ ሁኖ እያለ ማጽናታቸውም ተገቢ ሁኖ አልተገኘም። በዚህም ምክንያት በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ዲኝነት መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በሱልልታ ወረዲ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ20/06/2009 ዓ/ም ተሰጥቶ በፉንፉኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በ7/11/2009 ዓ/ም በውሳኔ፣ በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር አጣሪ ችልት በመዝገብ በ14/03/2010 ዓ.ም. በትዕዛዝ የፀናው ብይን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የሱልልታ ወረዲ ፍርድ ቤት ክርክሩን በመ/ ቀጥል አመልካቾች በወላጅ እናታቸው ድርሻ ላይ ያቀረቡትን ክስ በይርጋ ቀሪ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ ተገቢውን ምላሽ ለመሰጠት በዚህ ችልት የፍርድ ሐተታ ላይ በተመለከተው አግባብ ይዞታው መጋቢት 13 ቀን 2005 ዓ/ም ተደረገ በተባለ ስምምነት በአመልካቾች ተይዞ ቆይቷል ወይስ አልቆየም፣ አመልካቾች ይዞታውን ከኑዛዜ ተጠቃሚዎች ጋር ክፍፍል አድርገው ከሚመለከተው አካል የይዞታ ማረጋገጫ አውጥተውበት ይገኛለ? ወይስ አይገኙም?፣የይዞታ ማረጋገጫ አግኝተው ከሆነ ሰነደ የተሰጣቸው የሕግ አግባብ ምንድን ነው?፣ በመ/ ሲካሄደ በነበሩት ክርክሮች ሲሳተፈ የነበሩ ተከራካሪ ወገኖች እነማን እንደሆኑና በጉዲዮቹ ላይ የተሰጠ የፍርድ ቤት ውሳኔ ይዘቱ ምን እንደሚል፣ እንዱሁም በይርጋው ላይ የሚኖረው ሕጋዊ ውጤት ምን እንደሆነ በመመርመርና በግራ ቀኙ እና አግባብነት ባላቸው ማስረጃዎች ሁለ እንዱጣሩ ካደረገ በኃላ 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ባቀረቡት የይርጋ መቃወሚያ ላይ ተገቢውን ብይን እንዱሰጥ እና ክሱ በይርጋ ቀሪ የሚሆን አይደለም የሚባል ከሆነም በፍሬ ጉዲዩ ረገድ የቀረበለትን ክርክር በአግባቡ አጣርቶ ውሳኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩ ለሱልልታ ወረዲ ፍርድ ቤት በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 341(1) መሰረት መልሰናል። ይጻፍ።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.