ክርክርን በመስማት ላይ ያለ ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወገን በክርክሩ ጣልቃ እንዱገባ ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ፣ ጣልቃ ለመግባት የሚያስችል ህጋዊ ምክንያት አለመኖሩን ፍርድ ቤቱ ካመነበት ክርክሩ በየትኛዉም ደረጃ ላይ ቢሆን ናይል ትራንዚት ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና እነ ኒያላ ኢንሹራንስ www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XXVII ገቡ ከክርክሩ ዉጪ እንዱሆን ትዕዛዝ ከመስጠት የሚከለክለዉ ነገር የላለ ስለመሆኑ የፍ/ሥ/ሥርዓት ህግ ከአንቀጽ 40-43 ኩባኒያ
No summary available.
ቀን - 30/11/2010 ዳኞች፡- ዲኜ መላኩ ተኽሉት ይመሰል ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራዉ አመልካች፡- ናይል ትራንዚት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ተጠሪዎች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል
**
ጉዲዩ የኢንሹራንስ ዉልን መሰረት በማድረግ በመድን ሰጪዉ የተከፈለን የጉዲት ካሳ መድን ሰጪዉ በመድን ገቢዉ ተተክቶ በተጠየቀ የመዲረግ መብት ጋር በተያያዘ የቀረበን ክርክር መሰረት በማድረግ የስር የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የስር 2ኛ ጣልቃ ገብ የነበሩት አቶ ኪዲኔ ታረቀኝ እና የአሁን 3ኛ ተጠሪ በክርክሩ ጣልቃ ሉገቡ አይገባም በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ በማለት አመልካች ያቀረበዉ አቤቱታ ነዉ።
አመልካች በቀን 23/04/2010 ዓ.ም ተዘጋጅቶ ባቀረበዉ የሰበር አቤቱታ፣ ስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ወደ ክርክሩ እንዱገቡ ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ አመልካች ከፈለገ ከእነርሱ ላይ ክስ መስርቶ ካሳ መጠየቅ ይችላል በሚል ከክሱ እንዱሰናበቱ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነዉ የሚል ነዉ። አቤቱታዉ ተመርምሮ ያስቀርባል በመባለም ተጠሪዎች በየበኩላቸዉ በጽሐፍ በሰጡት መልስ፣ የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት አይደለም የሚለባቸዉንም ምክንያቶችwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በመዘርዘር መልስ ሰጥተዋል፤ አመልካች ያቀረበዉ የመልስ መልስም ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተመለከተዉ ሲሆን፣ እኛም የስር ፍርድ ቤት በዚህ ረገድ የሰጠዉን ብይን አግባብነት እንደሚከተለዉ መርምረናል። ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለዉ የአሁን 1ኛ ተጠሪ በአመልካች ላይ በስር ፍርድ ቤት ባቀረበዉ ክስ፣ አመልካች ከደንበኛዉ ጋር ባደረገዉ የዔቃ አስተላላፉነት ዉል መሰረት የሚጠበቅበትን ግዳታ ባለመወጣቱ ለደንበኛዉ የከፈለዉ የጉዲት ካሳ እንዱተካለት ሲሆን፤ አመልካች በበኩለ የተለያዩ የመጀመሪያ እና የፍሬ ነገር ክርክሮችን ካቀረበ በኋላ የማጓጓዝ ስራዉ የተከናወነዉ በስር 2ኛ ጣ/ገብ በነበረዉ፣ አቶ ኪዲኔ ታረቀኝ፣ በክርክሩ ጣልቃ እንዱገባ የጠየቀ ሲሆን፣ አቶ ኪዲኔ ታረቀኝም በክርክሩ ጣልቃ ገብቶ በመግባት በሰጠዉ መልስ ያሁን 3ኛ ተጠሪ መኪና በጭነቱ ቦታ የነበረ መሆኑን ጠቅሶ በክርክሩ ጣልቃ እንዱገባ በማለት መጠየቁን ነዉ። የስር ፍርድ ቤት የስር 2ኛ ጣልቃ ገብ፣ አቶ ኪዲኔ ታረቀኝ፣ እንዱሁም የአሁን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በክርክሩ ጣልቃ እንዱገቡ በማድረግ ክርክር ከሰማ በኋላ 3ኛ ተጠሪ እና የስር 2ኛ ጣልቃ ገብ ከክርክሩ እንዱወጡ ብይን መስጠቱን ተገንዝበናል።
በመሰረቱ በላልች ሰዎች መካከል በመካሄድ ላይ ባለዉ ክርክር ጣልቃ መግባት ስለሚቻልበት ሁኔታ የፍ/ሥ/ሥርዓት ህጋችን ከአንቀጽ 40-43 ባለት ድንጋጌዎች የተመለከቱ ሲሆን፤ ክርክሩን በመስማት ላይ ያለዉ ፍርድ ቤትም ላላ ሦስተኛ ወገን በክርክሩ ጣልቃ እንዱገባ ትዕዛዝ ከመስጠቱ በፉት ሉገባ የሚገባ መሆን አለመሆኑን በመወሰን ረገድ በድንጋጌዎቹ ስር የተመለከቱትን ሁኔታዎች ግምት ዉስጥ የማስገባት ግዳታ የሚጠበቅበት ሲሆን፤ ይህን የሚያደርገዉም 3ኛዉ ወገን ጣልቃ እንዱገባ ትዕዛዝ ከመስጠቱ በፉት ስለመሆኑ ከየድንጋጌዎቹ አጠቃላይ ይዘት መገንዘብ የሚቻል ነዉ።
ይህ መርህ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ 3ኛ ወገን ጣልቃ እንዱገባ ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ፣ ጣልቃ ለመግባት የሚያስችል ህጋዊ ምክንያት አለመኖሩን ፍርድ ቤቱ ካመነበት ክርክሩ በየትኛዉም ደረጃ ላይ ቢሆን ጣልቃ ገቡ ከክርክሩ ዉጪ እንዱሆን ትዕዛዝ ከመስጠት የሚከለክለዉ ነገር የለም። በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ተጠሪዎች በክርክሩ ጣልቃ እንዱገቡ ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ ወደ ኋላ ተመልሶ ከክርክሩ ዉጪ እንዱሆኑ ትዕዛዝ መስጠቱ ኢ-www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ስነስርዓታዊ ነዉ በማለት አመልካች እያቀረበ ያለዉ ቅሬታ ተቀባይነት ያለዉ አይደለም።
ወደ ክርክሩ እንዱገባ የተደረገዉ 3ኛ ተጠሪ በክርክሩ እንዲይቀጥል አለመደረጉ በአግባቡ ነዉ ወይስ አይደለም የሚለዉን ጭብጥ ስንመለከት፤ የስር 2ኛ ጣልቃገብ፣ አቶ ኪዲኔ ታረቀኝ፣ 3ኛ ተጠሪ በክርክሩ ጣልቃ እንዱገባ ሲጠይቅ በምክንያትነት የጠቀሰዉ ጉዲት የደረሰበትን ማሽነሪ የጫነዉ የ3ኛ ተጠሪ መኪና መሆኑን ነዉ። ከፍ ሲል እንደተገለጸዉ በላልች ሰዎች መካከል በመካሄድ ላይ ባለዉ ክርክር ጣልቃ መግባት ስለሚቻልበት ሁኔታ የፍ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 40-43 ይደነግጋል። የተያዘዉን ጉዲይ በተመለከተ የስር 2ኛ ጣልቃ ገብ ያሁን 3ኛ ተጠሪ በክርክሩ ጣልቃ እንዱገባ ሲጠይቅ፣ በህጉ አንቀጽ 43 መሰረት 3ኛ ተጠሪ ከእርሱ ጋር በድርሻ ካሳዉን ለመክፈል የሚገደድበትን የዉል ወይም የህግ ምክንያት ስለመኖሩ አልገለጸም። አሉያም በአመልካች እና በተጠሪ መካከል ሲደረግ በነበረዉ ክርክር መሰረት ፍትሐዊ ዉሳኔ ለመስጠት የተጠሪዎች በክርክሩ ጣልቃ መግባት፣ በፍት/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 40 መሰረት፣ የግድ መሆኑን የሚያሳይ የህግ ምክንያት አልቀረበም። ከዚህ አንፃር ሲታይ ተጠሪዎችን ከክርክሩ ዉጪ በማድረግ በስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በትዕዛዝ የፀናዉ ብይን በዚህ ችልት ሉታረም የሚችል መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ባለመገኘቱ ተከታዩ ተወስኗል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/111574 በቀን 19/07/09 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ብይን፤ እንዱሁም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/141787 በቀን 29/09/09 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ትዕዛዝ በፍ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 348(1) ፀንቷል።
በዚህ ችልት በቀን 30/05/2010 ዓ.ም የተሰጠዉ የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
በዚህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.