አንድ ሰው መብቴን ይነካል በሚል የመቃወም አቤቱታ ያቀረበበት ዉሳኔ በልላ አግባብ ከተሻረ እና መብትን ሉነካ የሚችል ዉሳኔ በላለበት የሚቀርብ የመቃወም አቤቱታ ተቀባይነት የላለው ስለመሆኑ ፍ/ሥ/ሥርዓት ህግ አንቀጽ 358ፍ/ሥ/ሥርዓት ህግ አንቀጽ
No summary available.
ቀን - 30/09/2010 ዳኞች፡- ተኽሉት ይመሰል ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራዉ አብዬ ካሳሁን አመልካቾች፡-
አቶ ቡልቻ ቱለ - ቀርበዋል።
ወ/ሮ ወርቄ አብዱሳ - ቀርበዋል።
ተጠሪ፡- አቶ ተመስገን ሙላቱ - አልቀረበም።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል
** ::
ጉዲዩ የተጀመረዉ በኦሮሚያ ብ/ክልላዊ መንግስት መስተዲደር በጉቶ ጊዲ ወረዲ ፍርድ ቤት ሲሆን 2ኛ አመልካች በፍ/ሥ/ሥ/ህጉ አንቀጽ 358 መሰረት ያቀረቡትን የመቃወም አቤቱታ መሰረት ያደረገ ነዉ። 2ኛ ተጠሪ ያቀረቡት መቃወሚያ ይዘትም በአጭሩ በኡኬ ከተማ ቀበላ 01 የሚገኘዉን እና አዋሳኞቹ በአቤቱታዉ ላይ የተመለከቱትን ቤት እና ይዞታ በተመለከተ የወረዲዉ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/29375 የሰጠዉ ዉሳኔ መብታቸዉን የሚነካ መሆኑን ጠቅሰዉ ወደ ክርክሩ ገብተዉ ተከራክረዉ እንዱወሰንላቸዉ መጠየቃቸዉን የሚያሳይ ነዉ። የወረዲዉ ፍርድ ቤትም በዚህ መልኩ በቀረበዉ አቤቱታ መነሻነት የግራ ቀኝ ክርክር ከሰማ በኋላ ቀደም ሲል ሰጥቶ የነበረዉን ዉሳኔ በመሻር ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቤት እና ይዞታ አመልካቾች በጋራ የሰሩት ነዉ በማለት ወስኗል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ተጠሪ ይህን ዉሳኔ ባለመቀበል ለምሥ/ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ሲሆን፣ ይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት የይግባኝ መዝገቡን አስቀርቦ የግራ ቀኝ ክርክር ከሰማ በኋላ በወረዲዉ ፍርድ ቤት የተሰጠዉን ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል። ተጠሪ ይህ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት መሆኑን ጠቅሶ ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታዉን ያቀረበ ሲሆን፣ ሰበር ሰሚዉ ችልት በበኩለ ተጠሪዎች ባልና ሚስት መሆናቸዉን እና 2ኛ ተጠሪ ጉዲዩ መብቴን ይነካል የሚትል ከሆነ ክርክርሩ በሂደት ላይ በነበረበት ወቅት ጣልቃ ገብታ መከራከር እየቻለች ይህን ሳታደርግ ቀርታ ዉሳኔ ከተሰጠ በኋላ ያቀረበችዉን የመቃወም አቤቱታ በመቀበል የወረዲዉ እና የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ በማለት ሽሯል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበዉም ይህኑን ዉሳኔ በመቀበል ለማስለወጥ ሲሆን፣ አመልካቾች በቀን 09/02/2010 ዓ.ም ተዘጋጅቶ በጠበቃቸዉ አማካይነት በቀረበ 4 ገጽ የሰበር አቤቱታ በኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ የሚለባቸዉን ምክንያቶች በመዘርዘር ታርሞ ይወሰንላቸዉ ዘንድ ዲኝነት ጠይቀዋል። አቤቱታዉ ተመርምሮ ያስቀርባል በመባለም ተጠሪ በተደረገለት ጥሪ መሰረት ቀርቦ ግራ ቀኝ ክርክራቸዉን በጽሐፍ ተለዋዉጠዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸዉ ሲሆን፣ ይህ ችልትም ለአቤቱታዉ ምክንያት የሆነዉን ዉሳኔ ከግራ ቀኝ ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል። ከፍ ሲል እንደተመለከተዉ 2ኛ አመልካች ለወረዲዉ ፍርድ ቤት ላቀረቡት የመቃወም አቤቱታ መሰረት ያደረገችዉ የወረዲዉ ፍርድ ቤት በ1ኛ አመልካች እና በተጠሪ መካከል የተደረገዉን ክርክር መሰረት በማድረግ በመ/ቁ/29375 በቀን 07/06/08 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ መብቴን ይነካል በማለት ነዉ። የክርክሩ መነሻ ተጠሪ በ1ኛ አመልካች ላይ ያቀረበዉ ክስ ሲሆን፣ተሰጥቶ የነበረዉ ዉሳኔም 1ኛ አመልካች ቤትና ቦታዉን ለተጠሪ ይልቀቅ የሚል ስለመሆኑ ከግራ ቀኝ ክርክር መገንዘብ ይቻላል። ይሁንና 1ኛ አመልካች ይህን ዉሳኔ ባለመቀበል ለምሥ/ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበዉ ይግባኝ ተቀባይነትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ባለማግኘቱ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረበ ሲሆን፣ይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/209425 በቀን 30/06/09 ዓ.ም በዋለዉ ችልት በወረዲዉ እና በከፍተኛ ፍርድ ቤቶች የተሰጡትን ዉሳኔዎች በመሻር መወሰኑን ተመልክተናል። አመልካቾች በዚህ ችልት ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ አጥብቀዉ ከሚከራከሩባቸዉ ነጥቦች ዉስጥ አንደ ለመቃወም አቤቱታዉ ምክንያት የሆነዉ ዉሳኔ መሻሩን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበን እያለ ችልቱ ይህን ሳያጣራ ዉሳኔ መስጠቱን ሲሆን፣ ተጠሪም በጽሐፍ በሰጠዉ መልስ ቀደም ሲል በስር ፍርድ ቤት ተሰጥቶ የነበረዉ ዉሳኔ በይግባኝ መሻሩን በተመለከተ ክድ ካለመከራከሩም በላይ ይህ ችልትም የዉሳኔዉን ግልባጭ አስቀርቦ ተመልክቶታል።
በልላ በኩል አንድ ሰዉ ዉሳኔ ከተሰጠ በኋላ የመቃወም አቤቱታ መቅረብ የሚችለዉ መብቱን የሚነካ ዉሳኔ ሲኖር ብቻ ስለመሆኑ በፍ/ሥ/ሥርዓት ህግ አንቀጽ 358 ስር በግልጽ ተመልክቷል። ይህም ማለት የመቃወም አመልካች አቤቱታ ተቀባይነት ያለዉ መሆን አለመሆኑን በመወሰን ረገድ ፍርድ ቤቶች ግምት ዉስጥ እንዱያስገቡ ከሚጠበቅባቸዉ ሁኔታዎች ዉስጥ አንደ የመቃወም አመልካችን መብት የሚነካ ዉሳኔ መኖር አለመኖሩን ነዉ። የተያዘዉን ጉዲይ በተመለከተ 2ኛ አመልካች ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን የመቃወም አቤቱታ ለወረዲዉ ፍርድ ቤት አቅርባ ጉዲዩ በክርክር ባለበት ወቅት ለመቃወም አቤቱታዉ ምክንያት የሆነዉ ዉሳኔ በ1ኛ አመልካች ይግባኝ ባይነት በዞን እና በጠቅላይ ፍርድ ቤት በሂደት ላይ የነበረ መሆኑን ነዉ። ጉዲዩ በከፍተኛ ወይም በጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ በሂደት ላይ እያለ በጎን ለወረዲዉ ፍርድ ቤት የቀረበዉ የመቃወም አቤቱታ ከመነሻዉም ተቀባይነት ያለዉ አይደለም። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ለዚህ ሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነዉ ጉዲይ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ከመቅረቡ በፉት ለመቃወም አቤቱታዉ ምክንያት የሆነዉ ዉሳኔ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ተሽሯል። አመልካቾች ይህን ለሰበር ሰሚዉ ችልት ገልፀዉ መከራከራቸዉን ከክርክሩ መገንዘብ ተችሎል። በመሆኑም የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የ2ኛ አመልካችን መብት ነክቷል ተብል ለመቃወም አቤቱታዉ ምክንያት የሆነዉ ዉሳኔ የተሻረ መሆን አለመሆኑን ማጣራት ነበረበት።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በበኩላችን እንደተመለከትንዉ 2ኛ አመልካች ላቀረቡት የመቃወም አቤቱታ ምክንያት የሆነዉ ዉሳኔ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተሽሯል። በመሆኑም ለመቃወም አቤቱታ ምክንያት የሚሆን ዉሳኔ የለም። የተሻረን ዉሳኔ መነሻ በማድረግ የሚቀርብ የመቃወም አቤቱታ አይኖርም። ስለሆነም የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ለመቃወም አቤቱታዉ ምክንያት የሆነዉ ዉሳኔ መሻሩን እና የ2ኛ አመልካቸን መብት ሉጎዲ የሚችል ዉሳኔ አለመኖሩን አረጋግጦ የቀረበን የሰበር አቤቱታ ባለመቀበል እንዱሁም ይህኑን መሰረት በማድረግ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡትን ዉሳኔዎች በመሻር መወሰን ሲገባዉ ይህን ባለማድረግ የ2ኛ አመልካች የመቃወም አቤቱታ አቀራረብ ስነ ስርዓታዊ አይደለም በሚል መንፈስ የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ተከታዩ ተወስኗል።
የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/261961 በቀን 29/01/2010 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ፤ እንዱሁም የጉቶ ጊዲ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/29375 በቀን 10/04/09 ዓ.ም በዋለዉ ችልት እና የምስ/ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/42673 በቀን 23/06/09 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጡት ዉሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
2ኛ አመልካች መብቴን ይነካል በሚል የመቃወም አቤቱታ ያቀረቡበት ዉሳኔ በልላ አግባብ ስለተሻረ እና መብቷን ሉነካ የሚችል ዉሳኔ ስለላለ የ2ኛ አመልካች የመቃወም አቤቱታ ተቀባይነት የለዉም።
የሰበር አጣሪ ችልት በቀን 13/02/2010 ዓ.ም የሰጠዉ የዔግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
በዚህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.