አንድ ኑዛዜ ከፀደቀ በኋላ በቀረበ ንብረት ክፍፍል ውስጥ ወራሾች ከአውራሻቸው በውርስ ሉያገኙት ከሚገባው ድርሻ ተገቢውን ያላገኙ መሆኑን ገልጸው በሚከራከሩበት ጊዜ ወ/ሮ ንጋቷ በየነ እና ወ/ሮ ሀረገወይን በየነ www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XXVI ነገሩ ተጣርቶ ከሚለይ በስተቀር ኑዛዜው ፀድቋል በሚል ምክንያት ብቻ የሐብት ድርሻቸውን በተመለከተ የሥረ- ነገር ክርክሩ ቀድሞ ታይቷል ተብል ውድቅ ላሆን የሚችልበት የስነ ስርዓት ሕግ አግባብ የላለ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 5
No summary available.
ግንቦት 29 ቀን 2010 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውልስ ኦርሺሶ አመልካች፡- ወ/ሮ ንጋቷ በየነ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ሀረገወይን በየነ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የውርስ ንብረት ይገባኛል ጥያቄን መነሻ ያደረገ ክርክር የሚመለከት ነው።
ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን፣ ከሣሽ የነበሩት አቶ ብርሃኑ በየነ ሲሆኑ አመልካችና ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ ነበሩ።
አቶ ብርሃኑ በየነ መስከረም 24 ቀን 2008 ዓ/ም በአመልካችና በተጠሪ ላይ ክስ የመሰረቱት ሟች አቶ በየነ ተ/ማሪያም መስከረም 04 ቀን 1997 ዓ/ም የተውት ኑዛዜው በፍርድ ቤት ቀርቦ መጋቢት 19 ቀን 1997 ዓ/ም መፅደቁን ጠቅሰው ኑዛዜ ያረፈበትን በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዲ 2 ክልል ውስጥ የሚገኘውን ቁጥሩ 199 የሆነ ቤት በኑዛዜው መሰረት እንዱከፊፈለ ይወሰነው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
የአሁኑ አመልካችና ተጠሪ በሰጡት መልስም በኑዛዜው መሰረት ክፍፍለ ቢደረግ ተቃውሞ የላላቸው መሆኑን ጠቅሰው ተከራክረዋል። የአሁኗ አመልካች ክፍፍለን የማይቃወሙ መሆኑን የጠቀሱ ቢሆንም ንብረቱ የእናታቸው ድርሻም ያለበት፣ የአሁኗwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ተጠሪ ለብቻቸው ይዘው እየተጠቀሙ ለማከፊፈል ፈቃደኛ ያልሆኑ መሆኑንና የሟች ላላ ተተኪ ወራሽ መኖሩንም ጭምር ገልፀው ተከራክረዋል።
የሥር ፍርድ ቤትም የውርስ አጣሪን ሹሞ ጉዲዩ እንዱጣራ ከአደረገ በኋላ ሪፖርቱ በ22/06/2008 ዓ/ም ለፍርድ ቤቱ የቀረበ ሲሆን በዚህ ሪፖርት ላይም አስተያየት እንዱሰጥበት አድርጎ የአሁኗ ተጠሪና የሥር ከሳሽ ተቃውሞ የላላቸው መሆኑን ሲገልፁ የአሁኗ አመልካች ግን አለኝ የሚለትን ተቃውሞ አቅርበዋል። ከዚህም በኋላ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን መርምሮ ለክፍፍል ጥያቄው መሰረት የሆነው ኑዛዜ በፍርድ ቤት የፀደቀ መሆኑንና ኑዛዜው ሲፅድቅም አመልካች የነበሩ በመሆኑ በኑዛዜው ህጋዊነት ላይ የሚያቀርቡት ተቃውሞ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 5 ድንጋጌ አንጻር ተቀባይነት የለውም፣ አመልካች ላላ የሟች ተተኪ ወራሽ አለ በማለት ያቀረቡት አስተያየትም የቀረበ ወራሽ በላለበትና አመልካች ስለመወከላቸው የሚያሳይ ማስረጃ ባልቀረበበት ሁኔታ ተቀባይነት የላለው መሆኑን ዘርዝሮ የአሁኗ አመልካች ያቀረቡትን ተቃውሞ ውድቅ አድርጎአል።
በዚህም ምክንያት የውርስ አጣሪው ሪፖርት ለሕግና ለሞራል ተቃራኒ አይደለም በማለት አጽድቆታል። ከዚህም በኋላ የአሁኗ አመልካች ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ፍርድ ቤቱም አመልካችንና ተጠሪን ብቻ ከአከራከረ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ የአመልካች ክርክር በፍርድ ቤት የጸደቀውን ኑዛዜ ያላገናዘበ በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 5 ድንጋጌ አግባብ ተቀባይነት የለውም ተብል መወሰኑ ተገቢ ነው በማለት የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ ሙለ በሙለ አጽንቶታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- የበታች ፍርድ ቤቶች ሟች አቶ በየነ ተ/ማሪያም መስከረም 04 ቀን 1997 ዓ/ም ያደረጉት ኑዛዜ የአመልካችና የተጠሪ ወላጅ እናት የሆኑትንና የሟቹ ሚስት የነበሩትን ሟች ወ/ሮ የሺ ብሩ በሚስትነታቸው ያላቸውን ድርሻ የሚያሳጣ የሕግ አግባብ በላለበት ሁኔታ ኑዛዜው መፅደቁ አመልካች የእናታቸውን ድርሻ በተመለከተ ቀድመው ተከራክረው የመጨረሻ ፍርድ እንዲገኙ የሚያስገነዝብ ነው በማለት የሰጡት ውሳኔ የኑዛዜውን ይዘትና የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 5 ድንጋጌን ባላገናዘበ መልኩ ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው።
አቤቱታቸው ተመርምሮም በዚህ ችልት እንዱታይ በመደረጉ ተጠሪ ቀርበው ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ የተደረገ ሲሆን የስር ፍርድ ቤት ዋና መዝገብ ቀርቦ ከመያያዙምwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በተጨማሪ ስለንብረቱ ክፍፍልና የኑዛዜው ይዘት ግራ ቀኙ በቃል እንዱሰሙ ተደርጎአል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን ተመልክተናል።
በሥር ፍ/ቤቶች ከተሰጡት ውሳኔዎች እና አመልካች ለዚህ ሰበር ችልት ካቀረበችው አቤቱታ ይዘት መገንዘብ እንደቻልነው ኑዛዜን በተመለከተ ቀደም ሲል በተደረገው ክርክር የመጨረሻ ውሳኔ አግኝቶአል የሚለው የተጠሪ መቃወሚያ ሟች አቶ በየነ ተ/ማሪያም አከራካሪ ንብረት ላይ ያደረጉት የኑዛዜው ይዘትን የሚመለከት የጉዲዩ ሥረነገር ላይ ክርክር መደረጉን አያመለክትም። አመልካች እና ተጠሪ የእናታቸውን ድርሻ በሚመለከተው የውርስ ሃብቱ ክፍፍል ላይ ተከራክረው የኑዛዜውን ይዘት መሰረት ያደረገ ውሳኔ ተሰጥቶአል የሚል አባባልም የለውም። በአመልካችዋ የሰበር አቤቱታ ጭምር እንደተገለጸው ቀደም ሲል በአቶ ብርሃኑ በየነ በቀረበው የውርስ ሐብት ልካፈል ጥያቄ የግራ ቀኙ ወላጅ አባት ድርሻ የሆነው ቤት ላይ ውሳኔ ተሰጥቶ በዚሁ አውራሽ ድርሻ ላይ ግራ ቀኙ ክፍፍል ያደረጉ መሆኑን የክርክሩ ሂደት የሚያሳይ ቢሆንም የሟች አቶ በየነ ተ/ማሪያም ሚስት የነበሩትና የአመልካችና የተጠሪ ወላጅ እናት ሟች ወ/ሮ የሺ ብሩ በቤቱ ላይ ያላቸውን ድርሻ በተመለከተ ግን ኑዛዜው በፍርድ ቤት ሲፀድቅ በግልፅ ተለይቶ የተጠቀሰ ነገር የለም። ሟች ወ/ሮ የሺ ብሩ ኑዛዜው ባረፈበት መኖሪያ ቤት ላይ ግማሽ ድርሻ /50%/ ያላቸው መሆኑ በውርስ አጣሪውም የውሳኔ ሃሳብ የቀረበበት ሲሆን የአሁኑ ተከራካሪ ወገኖችም ሆነ በስር ፍርድ ቤት ከሳሽ የነበሩት ግለሰብ ያቀረቡት የተለዬ ክርክር ስላለመኖሩ ከክርክሩ ሂደት ለመረዲት ችለናል። ሟች አቶ በየነ ተ/ማሪያም ባደረጉት ኑዛዜም የአሁኗ ተጠሪ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት በሚገኝበት ግቢ ውስጥ ያለትንና በወር በብር 400.00 (አራት መቶ) የሚከራዩትን ሁለት ክፍልችን እንዱወስደ ሲናዘዙ "………ከኔ ድርሻ የሚታሰብ ሁኖ……." የሚል ሐረግ ያሰፈሩበት መሆኑን የኑዛዜው ሰነድ ይዘት ያሳያል። ይህ የኑዛዜው ሰነድ ይዘት ኑዛዜው ሲፅድቅ ክርክር ተደርጎበት ውሳኔ ያረፈበት ስለመሆኑ የሚያሳይ ነገር የላለው ከመሆኑም በላይ የሐረጉ ይዘትና መንፈስ ሟች ወ/ሮ የሺ ብሩ በክፍልቹ ያላቸውንwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ድርሻ የሚያሳጣ መሆን ያለመሆኑን፣ ከላላው የውርሱ ክፍል ላይ በእነዚህ ክፍልች ላይ ወ/ሮ የሺ ብሩ ያላቸው ድርሻ እንዱካካስ ታስቦ የተቀመጠ መሆን ያለመሆኑን የውርስ ንብረቱ ላይ ሟች ወ/ሮ የሺ ብሩ ግማሽ ድርሻ አላቸው ተብል ከቀረበው ክርክርና ማስረጃ አንጻር ታይቶ እልባት ሉያገኝ የሚገባው እንጂ ኑዛዜው በመጽደቁ ብቻ የመጨረሻ ፍርድ አግኝቶአለ ተብል የሚታለፍ ሁኖ አልተገኘም።እንግዱህ የክርክሩ አጠቃላይ ይዘትና ሉታዩ የሚገባቸው ነጥቦች እነዚህ መሆናቸው ከተረጋገጠ በተጠሪ የቀረበው መቃወሚያ ተቀባይነት የሚያገኝበት የሕግ አግባብ አይኖርም።
ከፍ ሲል እንደተመለከተው የተጠሪ መቃወሚያ የተመሰረተው በኋላ የቀረበው ክስ(ጥያቄ) በቀድሞው የኑዛዜ ይጽደቅልን ክርክር የመጨረሻ ውሳኔ አግኝቶአል በሚለው ላይ ነው። ይህን መቃወሚያ ለመወሰን አግባብነት ያለው ድንጋጌ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 5 በመሆኑ ከቀረበው መቃወሚያ ፍሬ ነገር ጋር አገናዝበን ተመልክተናል። በተጠቀሰው ድንጋጌ አባባል በኋላ የቀረበው ጉዲይ ቀድሞ በቀረበው ክርክር የመጨረሻ ውሳኔ አግኝቶአል ልባል የሚችለው በሁለቱም የተነሳው ክርክር ሥረ ነገር እና የተያዘው ጭብጥ አንድ አይነት ከሆነ ነው። በዚህ መዝገብ በያዝነው ጉዲይ የሆነው ግን ከዚህ የተለየ ነው። በቀድሞው ክስ ተነስቶ የነበረው ክርክር የሟች አቶ በየነ ተ/ማሪያም ኑዛዜ ይፀድቅልን የሚል ሲሆን፣ በሁለተኛው ክስ የተነሳው ግን ክስ በተመሰረተበት ንብረት ላይ ሟች ወ/ሮ የሺ ብሩ ድርሻ አላቸው? ወይስ የላቸውም?፣ የሟች አቶ በየነ ተ/ማሪያም የኑዛዜ ይዘት የሟች ወ/ሮ የሺ ብሩን ድርሻ ለላልች ወራሾች የሚያስተላልፊበት የሕግ አግባብ አለ? ወይስ የለም? የሚል ነው። በመሆኑም ተጠሪ ኑዛዜ ፀድቆአል በማለት ያቀረቡት መቃወሚያ የሕግ ድጋፍ ያለው አይደለም።
በአመልካች የእናት ድርሻ እንካፈል በሚል ለቀረበው የዲኝነት ጥያቄ በመከሪከሪያነት ያቀረቡት የክርክሩንና የሟች አቶ በየነ ተ/ማሪያም ኑዛዜ የሚተረጎምበትን አግባብ መሰረት ያላደረገ በመሆኑ አመልካች ከእናታቸው ሉያገኙት የሚገባው የሐብት ድርሻ በተመለከተ የሥረ- ነገር ክርክር ቀድሞ ታይቶአል ልባል የሚችልበት የሕግ አግባብ የለም። እንዱሁም አመልካች ኑዛዜው ከፀደቀ በኋላ በቀረበው ክፍፍል ውስጥ ከእናታቸው በውርስ ሉያገኙት ከሚገባው ድርሻ ተገቢውን ያላገኙ መሆኑን ገልጸው የሚከራከሩ በመሆኑ ይህም ፍሬ ነገሩ ተጣርቶ ከሚለይ በስተቀር ኑዛዜው ፀድቆአል በሚል ምክንያት ብቻ ከወዱሁ ውድቅ ላሆን የሚችልበት የስነ ስርዓት ሕግ አግባብwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የለም። ሲጠቃለልም በእነዚህ ሁለ ምክንያቶች የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ከተጠሪ ጋር ሉካፈለ ስለሚገባው የእናታቸው የውርስ ንብረት ላይ ያቀረቡትን ክርክር ውድቅ ማድረጋቸው የክርክሩን ይዘትና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 5 ድንጋጌ ስር የተመለከቱትን መመዘኛዎችን ያላሟላ በመሆኑ አቤቱታ የቀረበበት የውሳኔ ክፍል መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሁኖ አግኝተናል። በዚህም መሰረት ተከታዩን ወሰነናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ በ25/04/2009 ዓ/ም ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በ08/10/09 ዓ/ም የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሻሽልአል።
አመልካች የእናታቸውን ድርሻ በተመለከተ ያቀረቡት የክፍፍል ጥያቄ ውድቅ የተደረገው ያላግባብ ነው ብለናል።
የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች የሟች ወ/ሮ የሺ ብሩን የውርስ ሃብት በተመለከተ ያቀረቡትን ክርክር በፍርድ ሐተታው ላይ በተመለከተው አግባብ ተመልክቶና በሚገባ አጣርቶ ተገቢውን ዲኝነት እንዱሰጥበት ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 341(1) መሰረት መልሰን ልከንለታል። ይጻፍ።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር መጪና ኪሣራ ግራ ቀኝ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.