በአንድ ክስ አጠቃል ክስ ማቅረብ የሚቻለው በተቋቋመ መብት ላይ ተመስርቶ እንጂ ዲኝነት በተጠየቀበት ጊዜ ያልበሰለ ወይም ያልተረጋገጠ መብት ጭምር ማቅረብ የማይቻል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 33/2/፤216
No summary available.
ቀን 16/09/2010 ዓ/ም ዳኞች፡- ዲኜ መላኩ ተኽሉት ይመስል ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ አብዬ ካሳሁን አመልካች፡- ኦይል ሉቢያ ኢትዮጵያ ሉሚትድ የቀረበ የለም ተጠሪ፡- አቶ ኃይለ ገ/ሕይወት የቀረበ የለም መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ አከራካሪ የሆነው መሰረታዊ ጭብጥ አመልካች የንግድ ድርጅት ለመረከብ ባቀረበው ክስ ላይ የተቋረጠ ጥቅም አጣምሮ መጠየቅ ይችል ነበር ተብል በፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የተሰጠው ውሳኔ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 216 እና 33(2) ድንጋጌዎች መሰረታዊ ይዘትና መንፈስ ያገናዘበ ነው ወይስ አይደለም? የሚል ነው።
አመልካች ቀደም ሲል በተጠሪ ላይ በመ/ቁ. 76340 ባቀረበው ክስ በአዱስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀበላ 17/18 ክልል የሚገኘውንና በቤት ቁጥር 387 የተመዘገበውን የነዲጅ፣ የዘይት ማደያና የመኪና እጥበት ማከናወኛ የንግድ ድርጅት እንዱያስረክቡት ዲኝነት ጠይቆ እስከ ፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በተደረገው ክርክር አመልካች ንብረቱን እንዱረከብ ውሳኔ መስጠቱን መዝገቡ ያመለክታል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
አመልካች ንብረቱ እንዱረከብ ከተወሰነ በኋላ ከታህሳስ 4 ቀን 2001 ዓ.ም ጀምሮ ድርጅቱን በፍርድ እስከተረከበበት ሰኔ 14 ቀን 2003 ዓ.ም ድረስ ከነዲጅ ጣብያው አገልግልት፣ ከነዲጅ፣ ዘይት ሽያጭ ማግኘት የነበረበት ገቢ በድምሩ ብር 971,394.04 ጥቅም የተቋረጠ በመሆኑ ተጠሪ እንዱከፍለ በኮ/መ/ቁ. 111441 ክስ አቅርቧል። የአሁኑ ተጠሪ ባቀረቡት የመከላከያ መልስ አመልካች መጀመሪያ ባቀረበው ክስ የተቋረጠ ጥቅምና ኪሳራ መጠየቅ እየቻለ ክሱን ነጣጥል ያቀረበ እንደሆነ፤ መጀመሪያ ባቀረበው ክስም የኪሳራ ጥያቄ ወደፉት ለመጠየቅ እንዱፈቀደለት ያቀረበው ጥያቄ በዝምታ የታለፈ በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
216/4/ እና 5(3) መሰረት ውድቅ እንዱደረግ አመልክቷል።
በዚህ አግባብ ክርክሩ የቀረበለትን የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ተጠሪ ያቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ ፍሬ ጉዲዩ ከመረመረ በኋላ ተጠሪ ለአመልካች ብር 912,487.43 ከሰኔ 14 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ 9% ወለድ እንዱከፍለ ሲል ወስኗል። ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኝ ቅሬታቸውን አቅርበው ፍርድ ቤቱም ግራቀኙን ከአከራከረ በኋላ አመልካች የተቋረጠ ጥቅም ለወደፉት እንዱጠይቅ መብቱ እንዱጠበቅለት ያቀረበው ጥያቄ በዝምታ የታለፈ በመሆኑ በድጋሚ ክስ ሉያቀርብ የሚችልበት የሕግ አግባብ አይኖርም በማለት የስር ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ ሽሮአል።
አመልካች የስር ፍ/ቤት ውሳኔ በመቃወም ግንቦት 14 ቀን 2009 ዓ.ም ባቀረበው የሰበር አቤቱታ ንብረቱ ለማስመለስ ባቀረበው ክስ ላይ የተቋረጠ ጥቅም እንዱከፈለው ግልጽ ዲኝነት ባልጠየቀበት እና የክስ ምክንያት ባልበሰለበትና ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ክስ መቅረብ ነበረበት የሚባልበት የህግ ምክንያት የላለ መሆኑን እየታወቀ የስር ፍ/ቤት የዲኝነት ጥያቄው በዝምታ ታልፎል በማለት የደረሰበት ድምዲሜ በሕጉ አግባብ አይደለም ተብል እንዱሻርለት አመልክቷል።
የአመልካች አቤቱታ የመረመረው አጣሪ ችልትም አመልካች ያቀረበው ክስ መብት ሉያቋቁም የሚችል ፍሬ ነገር ባልነበረበት አጠቃለህ ልትከስ ይገባ ነበር ተነጣጥል የቀረበ ክስ ነው ተብል በድጋሚ ላቀርብ አይገባውም የመባለን አግባብነት ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 216 እና 33(2) አንጻር ለመመርመር ጉዲዩ ለዚህ ችልት ያስቀርባል ተብሎል። ተጠሪም ታህሳስ 20 ቀን 2010 ዓ.ም ባቀረበው መልስwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
አመልካች የኪሳራውን ጥያቄ ወደፉት ነጥል ለማቅረብ በውሳኔ እንዱታወቅለት የመጀመሪያው ክስ ላስተናገደው ፍ/ቤት ያቀረበው ጥያቄ ሳይፈቀደለት የታለፈ በመሆኑ የካሳው ጥያቄ ነጥል ማቅረብ አይችልም በማለት የተሰጠው ውሳኔ በአግባቡ ነው ተብል እንዱጸና ጠይቋል። የመልስ መልስም ቀርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት መሆን አለመሆኑን እንደሚከተለው መርምረናል።
እንደመረመርነውም አመልካች መጀመሪያ ባቀረበው ክስ የነዲጅ ጣቢያው እንዱረከብ እንዱሁም የገቢና ትርፍ ማጣት ኪሳራ ወደፉት እንደሚጠይቅ በውሳኔ እንዱታወቅለት ማመልከቱን ከቀረበው ክርክር ተገንዝበናል። ተጠሪ አጥብቆ የሚከራከረው የአመልካች የካሳ ጥያቄ በዝምታ ታልፎል የሚል ነው። በመሰረቱ በአንድ ክስ የሚጠቃለለ ጉዲዮች አጠቃል ክስ ማቅረብ የሚገባ ስለመሆኑ፤ በዚህ አግባብ ያልቀረበው ክስ እንደገና የክስ ምክንያት ላሆን እንደማይገባ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 216 ድንጋጌ መሰረታዊ ይዘት ያስገነዝበናል። ከዚህ ድንጋጌ እንደምንገነዘበው አጠቃል ክስ ማቅረብ የሚቻለው በተቋቋመ መብት ላይ ተመስርቶ እንጂ ዲኝነት በተጠቀበት ጊዜ ያልበሰለ ወይም ያልተረጋገጠ መብት ጭምር ማቅረብ እንደማይቻል ነው። በተያዘው ጉዲይ አመልካች መጀመሪያ ያቀረበው ክስ መሰረታዊ የዲኝነት ጥያቄው የነዲጅ ማደያው መረከብ ስለመሆኑ አጠቃላይ ካደረጉት ክርክር መረዲት ይቻላል። የነዲጅ ጣቢያው የባለቤትነት ጥያቄ ባልተመለሰበት ሁኔታ የጥቅም ማጣት ወይም ኪሳራ መጠየቅ ግምታዊ የዲኝነት ጥያቄ ከሚሆን ውጭ የተረጋገጠ መብት/ጥቅም ቀንሶ ማስቀረትን የሚያሳይ ሆኖ አልተገኘም። አመልካች ነዲጅ ማድያው ለመረከብ ባቀረበው ክስ ለወደፉት የሚጠይቀው መብት መኖሩን ማመለከቱ መጀመሪያ ባቀረበው ክስ ላይ የተቋረጠ ጥቅም እንዱወሰንለት ግልጽ ዲኝነት ጠይቋል ለማለት አይቻልም። አመልካች ያልበሰለ ወይም ያልተረጋገጠ መብት በመጀመሪያ ክሱ ላይ አጠቃል አላቀረበም ተብል በስር ፍ/ቤት መወሰኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 216 ድንጋጌ መሰረታዊ ይዘትና መንፈስ ያላገናዘበ ሆኖ ተገኝቷል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
አመልካች መጀመሪያ ባቀረበው ክስ የነዲጅ ጣቢያው የባለቤትነት መብት አከራካሪ የነበረ ስለመሆኑ የተካደ ጉዲይ አይደለም። የባለቤትነት መብት በሚያከራክርበት ሁኔታ ደግሞ አመልካች ባልተረጋገጠ መብት ላይ ተመስርቶ የገቢና ትርፍ ማጣት ኪሳራ የሚጠይቅበት ሁኔታ አይኖርም። አመልካች መብቱን ወደፉት የሚጠይቅ ስለመሆኑ በክሱ ላይ ማመልከቱ ዲኝነት ጠይቋል የሚያስብል አይደለም። በመሆኑም የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የግባኝ ሰሚ ችልት አመልካች ያቀረበው ክስ ተነጣጥል የቀረበ ነው፤ የፍርድ ቤት ፈቃድ ማግኘቱ አልተረጋገጠም በማለት የስር ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ መሻሩ ከላይ በዝርዝር በገለጽናቸው ምክንያቶች የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
33/2/ እና 216 ድንጋጌዎች መሰረታዊ ይዘትና መንፈስ ያላገናዘበ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ብለናል። አመልካች የገቢና ትርፍ ማጣት ኪሳራ ለመጠየቅ ያቀረበው ክስ እንደገና (በድጋሚ) የቀረበ አይደለም ብለናል። በዚህም ተከታዩን ወስነናል።
348/1/ መሰረት ተሽሯል።
አመልካች በተጠሪ ላይ ያቀረበው የገቢና ትርፍ ኪሳራ ይከፈለኝ የዲኝነት ጥያቄ እንደገና (በድጋሚ) የቀረበ አይደለም በማለት ወስነናል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የተዘጋውን የመዝገብ በመክፈት ግራቀኙ በፍሬ ጉዲዩ ያቀረቡትን ክርክር መሰረት በማድረግ ተገቢ ህጋዊ ውሳኔ ይሰጥበት ዘንድ ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 341 መሰረት መልሰንለታል። የውሳኔ ግልባጭ ይድረስ ብለናል።
በዚህ ችልት የተደረገው ክርክር ያስከተለው ወጪና ኪሳራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.