አንድ ተከሳሽ በሕግ አግባብ መጥሪያ የደረሰዉ እና እርሱ በላለበት ዉሳኔ መሰጠቱን ማወቁን አግባብነት ባለዉ ማስረጃ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ በላለሁበት የተሰጠዉ ፍርድ ተነስቶ የመከላከያ መልስ ላቅርብ በማለት የሚያቀርበውን አቤቱታ በህግ በተቀመጠው አንድ ወር ጊዜ ዉስጥ አልቀረበም በሚል ምክንያት ብቻ መከላከያ መልስና ክርክር አቅርቦ የመሰማትና ፍትሕ የማግኘት ሕገ መንግስታዊ መብት መንፈግ ያልተገባና ህጋዊነት የላለው ስለመሆኑ፡የኢ.ፋ.ዳ.ሪ.ሕገ መንግስት አንቀጽ 37፣የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.78፣95 /2/ www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XXV
No summary available.
የካቲት 14 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች፡- 1.ዲኜመላኩ 2. ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) 3. ቀነዓ ቂጣታ 4. ተሾመ ሽፈራዉ 5. ፀሐይ መንክር አመልካች፡- አቶ መሀመድ ከማል - ቀርበዋል ተጠሪ፡- አቶ በቀለ ወልዳ - ከጠበቃ አቶ ምስጋኑ ሙለታ ጋር ቀርበዋል።
ይህ መዝገብ የተቀጠረዉ ለምርመራ ሲሆን ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር ጉዲይ በላለሁበት የተሰጠ ፍርድ እንዱነሳልኝ የሚል አቤቱታ መነሻ ያደረገ ክርክር ሲሆን ለዚህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ.ቁ.06184 በ8/3/2009 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረበዉን አቤቱታ መርምሮ ለመወሰን ነዉ።
የጉዲዩ መነሻ ሲታይ በሆሳዔና ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪ ከሳሽ፣የአሁን አመልካች ደግሞ 1ኛ ተከሳሽ፣በዚህ ችልት የክርክሩ ተካፊይ ያልሆኑት ወ/ሮ ዘምዘም ኑሪ 2ኛ ተከሳሽ ሁኖ ሲከራከሩ ነበር። ከሳሽ ባቀረበዉ ክስ ታህሳስ 9 ቀን 2007 ዓ.ም የተደረገዉ የድርጅት ሽያጭ ዉል እንዱፈጸምልኝ በማለት በጠየቀዉ ዲኝነት፣ 1ኛ ተከሳሽ ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ ተደርጎ፣ 2ኛ ተከሳሽ እንደዉለ ቢፈጸም አልቃወምም በማለታቸዉ ፍ/ቤቱ ጉዲዩን በመመርመር በመ.ቁ.18073 በ4/7/2007 ዓ.ም በሰጠዉ ዉሳኔ በ8000 ካ.ሜ ቦታ ላይ ያረፈዉ የደቄት ፊብሪካ ከነመገልገያ ማሽኖቹ ጭምር ታህሳስ 9 ቀን 2007 ዓ.ም በተደረገ የሽያጭ ዉል መሰረት ለከሳሽ እንዱፈጸም በማለት ወስኗል።
ይህን ዉሳኔ ተከትል 1ኛ ተከሳሽ /የአሁን አመልካች/ ባቀረበዉ አቤቱታ የፍ/ቤቱ መጥሪያ እንዱደርሰኝ ተገቢ ጥረት አልተደረገም፣ መጥሪያ አልደረሰኝም፣ ክርክሩንwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ስላልሰማሁት ተከሳሽ በላለሁበት በጋራ ንብረት ላይ የተሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.78 መሰረት እንዱነሳልኝ በማለት አመልክቷል። በዚህ አቤቱታ ላይ ከሳሽ ባቀረበዉ መልስ ተከሳሽ በቀበላ በኩል መጥሪያ ተልኮለት በቀበላዉ እንደላለ አረጋግጦ ጽፎል፤ በአዱስ ዘመን ጋዜጣም ጥሪ ተደርጎለታል፣ የፍ/ቤቱ መጥሪያ ለ1ኛ ተከሳሽ ሚስት ለሆነችዉ ለ2ኛ ተከሳሽ ደርሷት ቀርበ ስለተከራከረች መጥሪያ ለእርሱም እንደደረሰ ይቆጠራል፤ ተከሳሽ በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ከሳሽ ላይ ላቀረበዉ ክስ ከመልስ ጋር የሆሳዔና ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ በማያያዝ ግንቦታ 12 ቀን 2007 ዓ.ም ስለተሰጠ ተከሳሽ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ዉሳኔዉን ያወቀ ስለሆነ አቤቱታ ያቀረበዉ በ23/10/2007 ዓ.ም ስለሆነ ዉሳኔዉን ካወቀ ከ3 ወር በኋላ ስለሆነ አቤቱታዉ ተቀባይነት የለዉም በማለት ተከራክሯል።
የሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጉዲዩን በመመርመር በሰጠዉ ብይን 1ኛ ተከሳሽ መጥሪያ በቀበላ በኩል ቢላክለትም በቀበላዉ እንደማይኖር ቀበላዉ ደብዲቤ ጽፎል፤
በጋዜጣም ጥሪ ተደርጎለት አልቀረበም፤ በዚህ ጉዲይ የተከሳሽ ባለቤት የሆነችዉ ወ/ሮ ዘምዘም ኑሪ ቀርባ ስለተከራከረች ተከሳሽም ክርክሩን እንደሰማ የሕግ ግምት ያስወስዲል፤ ተከሳሽ ክርክሩን የሰማሁበት በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ከመልስ ጋር በቀረበዉ የሰነድ ማስረጃ ነዉ የሚባል ከሆነ ግንቦት 12 ቀን 2007 ዓ.ም አዉቋል ስለሚያስብል 1ኛ ተከሳሽ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.78 መሰረት አቤቱታዉን ያቀረበዉ ሰኔ 23 ቀን 2007 ዓ.ም ስለሆነ ይህ ደግሞ ከሁለት ወር በላይ ስለሆነ አቤቱታዉ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.78 /1/ መሰረት በአንድ ወር ይርጋ የሚታገድ ነዉ በማለት ዉድቅ በማድረግ ወስኗል። የሀዱያ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት እና የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የቀረበላቸዉን ቅሬታ ዉድቅ በማድረግ የሥር ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካች የካቲት 7 ቀን 2009 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ፡ አመልካች በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.162148 ላይ በነበረን ክርክር በላለሁበት ዉሳኔ መሰጠቱን ያወቅኩት ግንቦት 12 ቀን 2007 ዓ.ም ሳይሆን ግንቦት 22 ቀን 2007 ዓ.ም ትዔዛዙ በደረሰኝ ጊዜ ነዉ። እኔ በላለሁበት ዉሳኔ መሰጠቱን እንዲወቅኩኝ ሰኔ 13 ቀን 2007 ዓ.ም በላለሁበት የተሰጠዉ ዉሳኔ እንዱነሳልኝ ለሆሳዔና ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አቤቱታ ያቀረብኩኝ ቢሆንም የፍ/ቤቱ ሰራተኞች እስከ ሰኔ 22 ቀን 2007 ዓ.ምwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በስብሰባ ላይ የነበሩ በመሆኑ በዚህ ምክንያት ሉዘገይ መቻለን እየተከራከርኩኝ የሥር ፍ/ቤቶች ይህን ሳይቀበለ መወሰናቸዉ ተገቢ አይደለም። አመልካች በባለቤቱ በኩል ክርክር እንዲለ ያዉቃል ለተባለዉ ከባለቤቴ ጋር ተጣልቼ የነበረ እና ባለቤቴ ይህን ድርጅት አሳግዲዉ የነበረ ሲሆን ከተጠሪ ጋር በመመሳጠር እግድ እንዱነሳ በማድረግ ስም ዝዉዉር እንዱደረግ አድርጓል። የሥር ፍ/ቤቶች አመልካች ክርክር እንዲለ ያዉቃል በማለት የጠቀሱት በማስረጃ ባልተረጋገጠ ጉዲይ በመሆኑ፣የሥር ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱሻርልኝ፣ በላለሁበት የተሰጠዉ ዉሳኔ ተነስቶ ተገቢ መከራከሪያ አቅርቤ ዉሳኔ እንዱሰጥ በማለት አመልክቷል።
የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን በማየት ፣አመልካች ከሚስቱ ጋር በጋብቻ ፍቺ ክርክር ጋር ባለበት ሚስቱ መጥሪያዉ ደርሷታል ጉዲዩን ታዉቃለች በመሆኑም አመልካችም ጉዲዩን ያዉቃል ተብል ግምት ተወስድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.78 መሰረት የቀረበዉን የአመልካች ጥያቄ ዉድቅ የመደረጉን አግባብነት፣ ለመመርመር ሲባል አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዱሰጥ ባዘዘዉ መሰረት በ16/5/2010 ዓ.ም የተጻፈ መልስ አቅርቧል። የመልሱም ይዘት በአጭሩ፡ በዚህ ጉዲይ የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ዉሳኔ የሕግ ስህተት ያልተፈጸመበት ስለሆነ አመልካች ያቀረበዉ በማስረጃ ያልተረጋገጠ እና አዱስ የፍሬ ነገር ክርክር ተቀባይነት የላለዉ ስለሆነ ዉድቅ ሆኖ የሥር ዉሳኔ እንዱጸናልኝ ወጪና ኪሳራ እንዱወሰንልኝ በማለት በዝርዝር ተከራክሯል። የአሁን አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኛቸዉን ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንዱሁም አቤቱታዉ ያስቀርባል ሲባል ከተያዘዉ ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለዉ መርምሮታል። የሥር ፍ/ቤት የአሁን አመልካች መጥሪያ ሳይደርሰኝ በላለሁበት የተሰጠዉ ዉሳኔ እንዱነሳልኝ በማለት ያቀረበዉን አቤቱታ ዉድቅ ያደረገዉ በቀበላዉ እንደላለ ተረጋግጧል፣ በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎለት አልቀረበም፣ በሚስቱ ቀርባ ስለተከራከረች ክርክሩን እንደሰማ በሕግ ግምት ይወሰዲል፣ ዉሳኔዉን ካወቀዉ ከአንድ ወር በላይ ስለሆነ አቤቱታዉ ተቀባይነት የለዉም በሚለት ምክንያቶች መሆኑን የሥር ዉሳኔ ግልባጭ ያሳያል።
እንደሚታወቀዉ ስለመጥሪያ አደራረስ ሥርዓት በተመለከተ የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 94--110 ድንጋጌዎች ሥር ተመልክቷል። ከእነዚህ ድንጋጌዎችwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
አቀራረጽና ይዘት መገንዘብ እንደሚቻለዉ የመጥሪያ አደራረስ ሂደት በቅድም ተከተል አራት ደረጃዎች እንዲለት የሚያሳይ መሆኑን ነዉ። እነዚህም አንደኛ መጥሪያዉን ለተከሳሹ ለራሱ ማድረስ /የፍ.ብ.ሥ.ሥ.ሕ.ቁ.95 /3/፣ሁለተኛ መጥሪያዉን ለተከሳሹ ላሰጥ ይችላል ተብል ለሚገመት ሰዉ ማድረስ /አንቀጽ 99-101/፣ ሶስተኛ በፖስታ በኩል ለተከሳሽ እንዱደርሰዉ በማድረግ /አንቀጽ 106/፣አራተኛ በምትክ የመጥሪያ አደራረስ ዘዳን በመጠቀም ለተከሳሹ እንዱደርሰዉ ማድረግ እንደሚቻል /አንቀጽ 105/ ያሳያል። ስለሆነም የመጥሪያ አደራረስ ዘዳዉ ወይም ሥርዓት በዚህ ቅደም ተከተል ካልተፈጸመ ለተከሳሹ መጥሪያዉ በሕጉ አግባብ ደርሶታል ለማለት የሚያስችል አይደለም።
በዚህ አግባብ አሁን ወደ ተያዘዉ ጉዲይ ስንመለስ የሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ለአመልካች መጥሪያ እንዱደርሰዉ የወሰደዉን እርምጃ ማየቱ አስፈላጊ ነዉ። የአሁን አመልካች ቀድም ሲል ሲኖርበት የነበረዉን ቀበላ ዉስጥ እንደማይኖር የተረጋገጠ በመሆኑ እና ከተጠሪ ጋር በፋዳራል ፍ/ቤት ክርክር ላይ እንደነበሩ የሚታወቅ ስለሆነ፣ የሥር ፍ/ቤት ተጠሪ የፍ/ቤቱን መጥሪያ ለአመልካች በአድራሻዉ እንዱደርሰዉ ተገቢዉን ጥረት እንዱያደርግ ማድረግ ነበረበት። ፍ/ቤቱ የመጀመሪያ ደረጃ የመጥሪያ አደራረስ ዘዳ በአግባቡ ሳይፈጸም አራተኛ ደረጃ የመጥሪያ አደራረስ ዘዳ ማለትም ምትክ የመጥሪያ አደራረስ ዘዳ በአዱስ ዘመን ጋዜጣ ጥሪ እንዱደረግለት ማድረጉን የሥር ዉሳኔ ግልባጭ ያመለክታል። ይህ ደግሞ የሥር ፍ/ቤት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.95 /3/ በሚደነግገዉ መሰረት የአሁን አመልካች ክርክሩን አዉቀዉ ቀርበዉ መከራከሪያዉን እንዱያቀርብ ተጠሪ መጥሪያዉን ለአመልካች ለራሱ እንዱያደርስ ተገቢዉን ጥረት እንዱያደርግ ማድረግ ሲገባዉ ይህ ሳይደረግ በጋዜጣ ጥሪ እንዱደረግለት ማድረጉ ከላይ የተመለከቱትን የሥነሥርዓት ሕጎችን የተከተለ ሆኖ አልተገኘም። ስለሆነም የፍ/ቤቱ መጥሪያ ለአመልካች እንዱደርሰዉ ተገቢዉ ጥረት ሳይደረግ በጋዜጣ ጥሪ መደረጉ በሕግ የተመለከተዉን የመጥሪያ አደራረስ ዘዳን ያልተከተለ መሆኑን ያስገነዝባል። በመሆኑም የፍ/ቤቱ መጥሪያ በሕጉ አግባብ ለአመልካች ደርሶታል ክርክሩን አዉቆታል የሚያስብል አይደለም።
በልላ በኩል የሥር ፍ/ቤት በሰጠዉ ዉሳኔ የአሁን አመልካች ሚስት የነበረችዉ የሥር 2ኛ ተከሳሽ ወ/ሮ ዘምዘም ኑሪ በዋናዉ ጉዲይ ቀርባ እስከተከራከረች ድረስ አመልካችwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ክርክሩን እንዲወቀ የሕግ ግምት ያስወስዲል የሚል ድምዲሜ ላይ በመድረስ የአመልካችን አቤቱታ ዉድቅ አደርጓታል። ከፍ ሲል እንደተጠቀሰዉ በዚህ ጉዲይ አመልካች እና ወ/ሮ ዘምዘም ኑሪ ሁለቱም ተከሳሾች የነበሩ ስለሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.95/2/ መሰረት ለእያንዲንዲቸዉ መጥሪያ እንዱደርሳቸዉ መደረግ እንዲለበት ይደነግጋል። የሥር ፍ/ቤት በዚህ አግባብ ትዕዛዝ በመስጠት የሥር 2ኛ ተከሳሽ ወ/ሮ ዘምዘም ኑሪ ለአመልካች የተላከዉን መጥሪያ ፈርማ መቀበሎን የሥር ዉሳኔ የሚያመለክተዉ ነገር የለም። የሥር ፍ/ቤት በሰጠዉ ዉሳኔ ለአሁን አመልካች የተላከዉን መጥሪያ ለወ/ሮ ዘምዘም ስለመሰጠቱ ሳያረጋግጥ ወ/ሮ ዘምዘም ራሳቸዉ ተከሳሽ ስለነበሩ መጥሪያ ደርሷቸዉ ቀርበዉ ስለተከራከሩ አመልካችም ክርክሩን እንደሚያዉቅ የሕግ ግምት እንደሚያስወስድ በመግልጽ መወሰኑ የዉሳኔዉ ግልባጭ ያሳያል። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.101 ሥር እንደተመለከተዉ የፍ/ቤት መጥሪያ የተላከለትን ተከሳሽ ማግኘት ያልተቻለ ወይም መጥሪያ ተቀባይ የሚሆን ወኪል የላለዉ እንደሆነ ከተከሳሹ ጋር አብሮት ከሚኖረዉ አካላ መጠን ከደረሰ ቤተሰቡ ላንደ መስጠት እንደሚቻል ያመለክታል። በዚህ ረገድ የተያዘዉ ጉዲይ ሲታይ የሥር ፍ/ቤት የሥር 2ኛ ተከሳሽ የነበሩት ወ/ሮ ዘምዘም ኑሪ ለአመልካች የተላከዉን መጥሪያ ፈርሞ ስለመቀበላቸዉ ያረጋገጠዉ ነገር ካለመኖሩም በላይ በወቅቱ የአሁን አመልካች ከሚስቱ ጋር በፍ/ቤት የፍቺ ክርክር እንደነበራቸዉ እና በግንኙነታቸዉ መካከል ችግር እንዲጋጠመዉ መገንዘብ ተችሎል። ይህ ከሆነ ደግሞ በአመልካች እና በሚስቱ መካከል በነበረዉ የፍቺ ክርክር ላይ ዉሳኔ ባይሰጥም፣ የፍቺ ክርክር በመኖሩ በመካከላቸዉ ሰላማዊ ግንኙነት ይኖራቸዋል ተብል አይገመትም።
በመሆኑም በዚህ ሁኔታ ወ/ሮ ዘምዘም ኑሪ የፍ/ቤቱን መጥሪያ ለአመልካች በአግባቡ ያደርሳለ ተብል የሕግ ግምት ለመዉሰድ የሚያስደፍር አይደለም። የሥር ፍ/ቤት ይህን ሁኔታ በመገንዘብ ተጠሪ የፍ/ቤቱን መጥሪያ ለአመልካች ለማድረስ ተገቢዉን ጥረት እንዱያደርግ ማድረግ ሲገባዉ ይህን ሳያደርግ ለሚስቱ መጥሪያ ደርሷት ቀርበ ስለተከራከረች ለአመልካችም መጥሪያ እንደደረሰ ግምት በመዉሰድ አመልካች ያቀረበዉን አቤቱታ ዉድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ብለናል።
በመጨረሻም የሥር ፍ/ቤት የአመልካች በላለሁበት የተሰጠዉ ዉሳኔ እንዱነሳልኝ በማለት ያቀረበዉን አቤቱታ ዉድቅ ያደረገበት ምክንያት በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በነበረዉ ክርክር ተጠሪ ከተሰጠዉ መልስ ጋር በቀረበ የሰነድ ማስረጃ ነዉ ያወቅኩኝwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የሚል ከሆነ በዛ ክርክር መልስ የተሰጠዉ ግንቦት 12 ቀን 2007 ዓ.ም ስለሆነ አመልካች አቤቱታዉን የቀረበዉ ሰኔ 23 ቀን 2007 ዓ.ም በመሆኑ የአንድ ወር ጊዜ አልፍበታል በማለት ነዉ። የአሁን አመልካች ባቀረበዉ ክርክር እርሱ በላለበት ዉሳኔ መሰጠቱን ግንቦት 12 ቀን 2007 ዓ.ም እንዲላወቀ እና ግንቦት 22 ቀን 2007 ዓ.ም በችልት ጸሐፉ በኩል ትዕዛዝ ሲደርሰዉ እንዲወቀ በዚህ መነሻነትም ለሥር ፍ/ቤት በጊዜ አቤቱታዉን እንዲቀረበ በመግልጽ እየተከራከረ ይገኛል። በዚህ ረገድ ተጠሪ በቀረበዉ ክርክር አመልካች ግንቦት 12 ቀን 2007 ዓ.ም ችልት ቀርበዉ የመከላከያ መልስና የሰነድ ማስረጃ ተቀብል ዉሳኔ መሰጠቱን አዉቋል የሚል ሳይሆን አመልካች የዉሳኔ ግልባጭ መጠበቅ ሳያስፈልገዉ ማወቅ ይችል ነበር የሚል ነዉ። የሥር ፍ/ቤት አመልካች ግንቦት 12 ቀን 2007 ዓ.ም እርሱ በላለበት ዉሳኔ መሰጠቱን ያወቀ መሆኑን የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት መዝገብ በማስቀረብ ወይም በልላ አግባብ በማጣራት ያረጋገጠ ነገር መኖሩን የሥር ዉሳኔ አያመለክትም። ከሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ ግልባጭ እና ከግራ ቀኛቸዉ ክርክር መገንዘብ እንደሚቻለዉ የአሁን አመልካች ግንቦት 12 ቀን 2007 ዓ.ም በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በችልት ቀርበዉ ተጠሪ ያቀረበዉን የመከላከያ መልስና የሰነድ ማስረጃ በመቀበል፣ እርሱ በላለበት ዉሳኔ መሰጠቱን ግንቦት 12 ቀን 2007 ዓ.ም አዉቆታል ለማለት የሚያስችል ነገር የለም። የሥር ፍ/ቤት በእርግጠኝነት የአሁን አመልካች ግንቦት 12 ቀን 2007 ዓ.ም እርሱ በላለበት ዉሳኔ መሰጠቱን ማወቁን አግባብነት ባለዉ ማስረጃ ባላረጋገጠበት፣ እርሱ በላለበት ዉሳኔ መሰጠቱን በግምት በዚህ ቀን መሰጠቱን አዉቆታል፣ አመልካች በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ አቤቱታዉን ስላላቀረበ ዉድቅ ነዉ በማለት የደረሰበት ድምዲሜ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.78 ዓላማ የሚቃረን ስለሆነ ተቀባይነት የለዉም። በመሆኑም የሥር ፍ/ቤት የአሁን አመልካች በሕግ አግባብ መጥሪያ የደረሰዉ መሆኑን እና እርሱ በላለበት ዉሳኔ መሰጠቱን በእርግጠኝነት ያወቀበት ቀን እስካልተረጋገጠ ድረስ የመከላከያ መልስና ክርክር በማቅረብ የመሰማትና ፍትሕ የማግኘት መብት ሕገ መንግስታዊ መብት ስለሆነ አሳማኝና በቂ ባልሆነ ምክንያት ሉነፈግ አይገባም። በዚህ ረገድ በኢ.ፋ.ዳ.ሪ.ሕገ መንግስት አንቀጽ 37 ፍትሕ የማግኘት መብት ሕገ መንግስታዊ መብት መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።
ሲጠቃለል የሥር ፍ/ቤቶች የአሁን አመልካች በሕግ አግባብ መጥሪያ የደረሰዉ እና እርሱ በላለበት ዉሳኔ መሰጠቱን ማወቁን አግባብነት ባለዉ ማስረጃ ባላረጋገጡበትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
አመልካች በላለሁበት የተሰጠዉ ፍርድ ተነስቶ የመከላከያ መልስ እንዲቀርብ በማለት የቀረበዉን አቤቱታ በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ አልቀረበም በሚል ምክንያት ዉድቅ በማድረግ የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ የሚከተለዉ ተወስኗል።
የሆሳዔና ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ.18073 በ10/3/2008ዓ ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና ይህን ዉሳኔ በማጽናት የሀዱያ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.15040 በ17/5/2008 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዛዝ እና የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚችልት በመ.ቁ.06184 በ8/3/2009 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመባቸዉ ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 /1/ መሰረት ተሽሯል።
የአሁን አመልካች በሕግ አግባብ መጥሪያ የደረሰዉ እና እርሱ በላለበት ዉሳኔ መሰጠቱን ያዉቅ እንደነበር ባልተረጋገጠበት፣ በላለሁበት የተሰጠዉ ዉሳኔ እንዱነሳልኝ በማለት ያቀረበዉ አቤቱታ በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ አልቀረበም በማለት ዉድቅ ማድረጉ በሕግ አግባብ ሆኖ ስላልተገኘ፣የመከላከያ መልስ የመቅረብ የመከራከርና ፍትሕ የማግኘት መብቱ ሉነፈግ ስለማይገባ የሆሳዔና ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ.18073 በ4/7/2007 ዓ.ም አመልካች በላለበት የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.78 (2) መሰረት ሉነሳ ይገባል ብለናል።
የሆሳዔና ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የዘጋዉን መዝገብ በማንቀሳቀስ የአሁን ተጠሪ የቀረበዉ ክስና ማስረጃ ለአመልካች እንዱደርሰዉ በማድረግ አመልካች የመከላከያ መልስ እንዱያቀርብ በማድረግ፣ በሕጉ አግባብ ተከራካሪ ወገኖቹን በማከራከርና በማጣራት ተገቢ ነዉ ያለዉን ዉሳኔ እንዱሰጥበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.341 /1/ መሰረት ተመልሶለታል።
የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ ብለናል።
ግራና ቀኛቸዉ በዚህ ችልት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።
No topics extracted.