ማንኛዉም የቴላኮሙንኬሽን ድርጅት የቴላኮሙንኬሽን መስመር ሲዘረጋ መስመሩ የባለይዞታን ወይም የላላ ህንጻ ላይ የሚዘረጋበት አስገዲጅ ሁኔታ ሲኖር አስቀድሞ ለባለይዞታዉ ወይም ለባለህንጻዉ በማስታወቅ የባለይዞታዉ ወይም የባለህንጻዉ ተቃዉሞ እንዲለ ሰምቶ ተገቢዉን የመወሰን ስልጣን ለኤጀንሲዉ የተሰጠ ስለመሆኑ የቴላኮሙንኬሽን ድርጅት የአንድ ባለይዞታ ይዞታ ውስጥ ገብቶ በቋሚነት ኮንቴነር ከተከለ ለተጠቀመበት ይዞታ ተገቢዉን ካሳ ለባለይዞታው የመክፈል ግዳታ አለበት የቴላኮሙንኬሽን አዋጅ ቁ/49/89 አንቀጽ 18፣20/1/፣22/2/፣እና አዋጅ ቁ/455/97 አንቀጽ 6 www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XXIV የ
No summary available.
የሰ/መ/ቁ/144901 ሐምል 12 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች፡ ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንዲሻዉ አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች፡- ኢትዮቴላኮም የሰሜን ምስራቅ ሪጅን ተጠሪ፡- ወ/ሮ በለጡ ወልደ ተገኝ መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ በመሆኑ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
በዚህ መዝገብ የቀረበዉ ጉዲይ አመልካች በተጠሪ ይዞታ ላይ የተከለዉን ኮንቴነር እንዱያነሳ የቀረበዉን ክስ መነሻ በማድረግ የአማራ ክልል ጠ/ ፍርድ ቤት አመልካች የተጠሪ ይዞታ ለተጠቀመበት ተገቢዉን ካሳ እንዱከፍል መወሰኑን ተከትል ዉሳኔዉ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል እንዱታረም የቀረበ አቤቱታ ነዉ።
የጉዲዩ አመጣጥ ባጭሩ ሲታይ ክርክሩ የተጀመረዉ በደቡብ ወል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን ተጠሪ ያቀረበችዉ ክስ ይዘት ባጭሩ ያለተጠሪ ፈቃድ ለጊዜዉ ነዉ በሚል አመልካች በተጠሪ ይዞታ ዉስጥ ገብቶ የቴላ ሳጥን/ኮንቴነር/ በመትከለ ይዞታየን ለመጠቀም አልቻልኩም በሚል ያጣሁትን ጥቅም ግምት ብር 20,700 ከፍል ሳጥኑን እንዱያነሳ እንዱወስን በማለት ዲኝነት የጠየቀች ሲሆን አመልካች በበኩለ ፍርድ ቤት ጉዲዩን የመዲኘት ስልጣን የለዉም የሚልና ላልች የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የሚላቸዉን መከራከሪያዎች አንስቶ በፍሬነገር ረገድም ሳጥኑ የተተከለዉ በከተማ አስተዲደር ተፈቅድ ስለመሆኑ ገልጾ ክሱ ዉድቅ እንዱደረግ ተከራክሯል።
ጉዲን በመጀመሪያ የዲኝነት ስልጣን ያከራከረዉ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካችን የመጀመሪያ መቃወሚያ ዉድቅ ካደረገ በኋላ ስለጉዲዩ ከከተማዉ አስተዲደር መግለጫ ጠይቆ ከተማዉ አስተዲደር አመልካች የተጠሪ ይዞታ ዉስጥ ገብቶ 9.20 ካ.ሜ ተጠቅሞ የቴላ ሳጥን መትከለንና በዚህ ይዞታ ላይ እንዱተክል ከተማ አስተዲደሩ እንዲልፈቀደለት ስላላረጋገጠ አመልካች ለተጠቀመዉ ቦታ በአካባቢዉ የሉዝ ዋጋ ለተጠሪ እንዱከፍል ዉሳኔ ሰጥቷል።አመልካች በዚህ ዉሳኔ ቅር ተሰኝቶ ለክልለ ጠ/ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርቦ ፍ/ቤቱም ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ አመልካች ለተጠሪ በአዋጅ 49/89 እና 455/97 መሰረት ካሳ የመክፈል ግደታ አለበት በሚል ካሳ መጠን ላይ የስር ፍርድ ቤት አጣሪቶ እንዱወስን መልሶለታል።
ለዚህ ሰበር ችልት አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ላይ ሲሆን የአመልካች አቤቱታ ይዘት ባጭሩ የዲኝነት ስልጣን አስመልከቶ በስር ፍርድ ቤት የቀረበዉ መቃወሚያ መታለፈ ተገቢ አለመሆኑ፣ክሱ በይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑ እና በፍሬነገር ረገድ አመልካች ክስ ያቀረበችበት ይዞታ ለመሰረተ ልማት ዝርጋታ የተፈቀደ ሆኖ አመልካች ኋላ ላይ በቆርቆሮ አጥር ወደ ይዞታዋ ያስገባች ስለመሆኑ የተተከለዉ ሳጥን በከተማ አስተዲደር ተፈቅድ በቋሚነት የሚቀመጥ እንጂ በጊዜያዊነት አለመሆኑንና ተጠሪ ኮንቴነሩ እንዱነሳ ያቀረቡት ጥያቄ ተገቢነት እንደላለዉ በመዘርዘር በመጨረሻም ተጠያቂዉ የከተማዉ አስተዲደር መሆን አለበት በሚል የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ እንዱታረም ጠይቋል።የአመልካች ሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አከራካሪዉ መስመር የተዘረጋዉ ከ5 ዓመት በፉት መሆኑንና ተጠሪ ይዞታዉን ከዚያ በኋላ አስፊፍተዉ የያዙት ነዉ በማለት አመልካች ያቀረበዉ ክርክር በስር ፍርድ ቤት መታለፈን አግባብነት ለመመርመር ጭብጥ ተይዞ ተጠሪ መልስ እንዱትሰጥ ተደርጓል።ተጠሪ መጥሪያ ተልኮላት መልስ አላቀረበችም።በዚሁ መልስ የማቅረብ መብት ታልፍ መዝገቡ ተመርምሯል።
መዝገቡን መርምረን እንደተገነዘብነዉ አመልካች ክስ በቀረበበት ይዞታ ላይ ኮንቴነር መትከለ አልተካደም።አመልካች አጥብቆ የሚከራከረዉ በአዋጅ ቁ/49/89 መሰረት ጉዲዩ መታየት ያለበት በራሱ በአመልካቹ ድርጅት መሆን እንዲለበትና ድርጊቱም የህግ ድጋፍwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ያለዉ ስለመሆኑ ነዉ። በመሰረቱ ማንኛዉም የቴላኮሙንኬሽን ድርጅት የቴላኮሙንኬሽን መስመር ሲዘረጋ የከተማዉን ፕላን ተከትል የመዘርጋት ሃላፉነት እንዲለበት የቴላኮሙንኬሽን አዋጅ ቁ/49/89 አንቀጽ 22/2/ በግልጽ ያስገነዝባል።ከዚህ ባሻገር መስመሩ የባለይዞታን ወይም የላላ ህንጻ ላይ የሚዘረጋበት አስገዲጅ ሁኔታ ሲኖር አስቀድሞ ለባለይዞታዉ ወይም ለባለህንጻዉ በማስታወቅ የባለይዞታዉ ወይም የባለህንጻዉ ተቃዉሞ እንዲለ ሰምቶ ተገቢዉን የመወሰን ስልጣን ለኤጀንሲዉ የተሰጠ ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 18 በዝርዝር ተመልክቷል።
በተያዘዉ ጉዲይ አመልካች በተጠሪ ይዞታ ዉስጥ ገብቶ ኮንቴነር መትከለና ይዞታዉ የተጠሪ ህጋዊ ይዞታ ስለመሆኑ ደግሞ የከተማዉ አስተዲደር ያረጋገጠ ስለመሆኑ በስር ፍርድ ቤት የተረጋገጠ ፍሬነገር ነዉ ።አመልካች ኮንቴነር የተከልኩት በከተማዉ አስተዲደር ፈቃድ ነዉ በማለት የተከራከረ ቢሆንም ከተማዉ አስተዲደር አመልካች ኮንቴነር የተከለበት ይዞታ የተጠሪ የግል ይዞታ እንጂ ለመሰረተ ልማት ዝርጋታ የተፈቀደ ይዞታ አይደለም በማለት ምላሽ መስጠቱንም በስር ፍርድ ቤት የተረጋገጠ ፍሬነገር ነዉ።ስለሆነም አመልካች ኮንቴነር ከተከለ በኋላ ተጠሪ ቦታዉን አስፊፍተዉ በመያዝ ወደ ይዞታዋ አስገብታለች የሚለዉ ነጥብ የፍሬነገር ክርክር በስር ፍርድ ቤት ያልተነሳና በማስረጃ ያልተረጋገጠ ፍሬነገር በመሆኑ በዚህ ረገድ የቀረበዉ ክርክር ተገቢነት ያለዉ ሆኖ አላገኘንም ። አመልካች በአዋጁ መሰረት ጉዲዩ በኤጄንሲዉ በኩል እንዱታይ ለማድረግም አስቀድሞ ለተጠሪ የሰጠዉ ማስታወቂያ ስለመኖሩ ካለማስረዲቱም በተጨማሪ ጊዜያዊ ነዉ እያለ ተጠሪ እንዱጠባበቁ ያደረገ ስለመሆኑ በስር ፍ/ቤት ክርክር የተቀረበበት ነዉ።
በመሆኑም አመልካች በተጠሪ ይዞታ ላይ የተከለዉ ኮንቴነር በቋሚነት የሚቀጥል እስከሆነ ድረስ በአዋጁ አንቀጽ 20/1/ መሰረት ተገቢዉን ካሳ ለተጠሪ የመክፈል ግዳታ አለበት። ስለዚህም የአማራ ክልል ጠ/ፍ/ቤት በስር ፍርድ ቤት የተረጋገጠዉን ፍሬነገር መሰረት በማድረግ አመልካች ለተጠቀመበት የተጠሪ ይዞታ ተገቢዉን ካሳ እንዱከፍል ዉሳኔ መስጠቱና የካሳዉ መጠን ተጣርቶ እንዱወሰን ለስር ፍርድ ቤት መመለሱ በአዋጅ ቁ/49/89 አንቀጽ 20/1/ እና አዋጅ ቁ/455/97 አንቀጽ 6 መሰረት ተገቢ ሆኖ ስላገኘንwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ዉሳኔዉ መሰረታዊ ህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ የሚባልበት ምክንያት አላገኘንም።በዚህ አግባብ ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል።
ዉ ሳ ኔ።
1ኛ/የአማራ ብ/ክ/ጠ/ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ/01-0471 በ03/09/09 ዓ.ም የሰጠዉ ፍርድ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁ/348/1/ መሰረት ጸንቷል።
2ኛ/በዚህ መዝገብ ላይ በጥር 9 ቀን 2010 ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረዉ እግድ ትእዛዝ ተነስቷል።ይጻፍ።