የከተማ ይዞታን የማስተዲደር ስልጣን በህግ አግባብ የተሰጠው አካል ስልጣንና ኃላፉነቱን በህግ አግባብ አልተወጣም የሚል ክርክር ያለው ወገን ጉዲዩን ለፍ/ቤት የማቅረብ መብት ያለው ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 37፣ 40(3)(4)፣79(1) www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XXIII እና 78(4)
No summary available.
ሐምል 26 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውልስ ኦርሺሶ አመልካች፡- ወ/ሮ አድና መላኩ ተጠሪ፡- የወልዱያ ከተማ አገልግልት ጽ/ቤት ከክልለ ፍትህ ቢሮ ፍሬህይወት አበባቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ይህ የሰበር አቤቱታ ላቀርብ የቻለው አመልካች የወልዱያ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/4 በቀን 24/02/2009 ዓ.ም ጉዲዩ በቀጥታ ክስ በፍርድ ቤት የሚታይ አይደለም በማለት የሰጠውን ብይን ፣የሰሜን ወል መስተዲድር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 27/04/2009 ዓ.ም በፍርድ፣ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ አጣሪ ችልት በመ/ቁጥር 03-16739 በ27/06/2009 ዓ/ም በትእዛዝ በማጽናታቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለታቸው ነው።
ጉዲዩ የዲኝነት ሥልጣንን የሚመለከት ሲሆን በስር ፍ/ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ ነበሩ። የክሱ ይዘትም፡- በወልዱያ ከተማ 06 ቀበላ ክልል ውስጥ የሚገኘውና አዋሳኙ በክሳቸው የተጠቀሰው ቦታ እንዲላቸውና በዚህ ቦታ ላይ ቤት ያላቸው፣ ባህር ዛፍና ሁለት እግር ጽድ ያፈሩ መሆኑን ይዞታውን ለረዥም ጊዜ ይዘውwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በሚገኙበት ሁኔታ ተጠሪ ህግና መመሪያን መሰረት ሳያደርግ፣ ለአመልካችም 500 ካ/ሜትር ይዞታ ሳይጠብቅላቸው ቦታውን እየሸነሸነ ለግለሰቦች እየሰጠ እንደሚገኝ፣ በቦታው ላይ የሰሩትን ቤት ያለምንም ምክንያት በድዘር መጋቢት ወር 2007 ዓ/ም ያፈረሰባቸውና አቤቱታቸውን ለሚመለከተው አካል አቅርበው የሚመለከታቸው አካላት እንደማንኛውም ባለይዞታ 500 ካ/ሜትር ይዞታ ለአመልካች እንዱጠበቅላቸው አስተዲደራዊ ውሳኔ የሰጡ መሆኑንና በዚህ አግባብ እንዱወሰንላቸው ለተጠሪም ሆነ ለሚመለከተው አካል አመልክተው መፍትሓ ያላገኙ መሆኑን ገልጸው ለክሱ ምክንያት ከሆነው ነባር ይዞታ ላይ 500 ካ/ሜት እንዱጠበቅላቸው፣ ከሕግ ውጪ በድዘር ለፈረሰባቸው ቤት ግምት ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)፣ የባህር ዛፈና የፅደ ግምትም እንዱከፈላቸው እንዱሁም ከ500 ካ/ሜትር በላይ ላለው ይዞታም ካሳ እንዱከፈላው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካችም ጉዲዩ በአዋጅ ቁጥር 721/2004 እና በአዋጅ ቁጥር 455/97 መሰረት በፍርድ ቤት በቀጥታ ክስ የሚታይ ያለመሆኑን፣ አመልካች በቦታው ላይ መብት የላላቸው መሆኑንና ላልች የክርክር ነጥቦችን በማንሳት ተከራክሯል። የሥር ፍርድ ቤትም ስልጣንን መሰረት አድርጎ የተነሳውን የተጠሪን መቃወሚያ መርምሮ አመልካች የከተማ ቦታ ይዞታን እንዱለቁ የተደረጉ በመሆኑ ጉዲዩ መታየት ያለበት በከተማ አስተዲደሩ ስር ለተቋቋመ የመሬት ነክ አቤቱታ ሰሚ አካል ነው እንጂ ለፍርድ ቤት አይደለም የሚል ምክንያት አስፍሮ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን በቀጥታ ክስ የማየት የስረ ነገር ስልጣን የለውም ሲል በብይን የአመልካችን ክስ ውድቅ አድርጎታል። በዚህ ብይን የአሁኑ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለሰሜን ወል መስተዲድር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን አከራክሮ የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ብይን ተገቢ ነው በማለት አጽንቶታል። በመጨረሻም አመልካች የሰበር አቤቱታቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበው በአጣሪው ችልት ተሰርዞባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- የአመልካች ክስ መሰረታዊ ይዘት ከሕግ ውጪ የተወሰደው ቦታና የወደመው ንብረት በሕጉ አግባብ ታይቶ ባለይዞታነታቸው መብት እንዱጠበቅላቸውና ለወደመው ንብረት ደግሞ ካሳ እንዱከፈል የሚያሳይ ሁኖ እያለ የክሱን መሰረታዊ ይዘት ሳይገነዘቡ ጉዲዩ በቀጥታ ክስ በፍርድ ቤት የሚታይ አይደለምwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በማለት መወሰናቸው ያላግባብ ነው የሚል ሲሆን አቤቱታቸው ተመርምሮም አመልካች በሕገ ወጥ መንገድ ቦታዬ ተወስድአል፣ ንብረቴም ወድሟል በማለት ያቀረቡት ክስ በአስተዲደራዊ መልኩ ብቻ የሚታይ ነው በማለት የሥር ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 721/2004 እና የሉዝ ደንብ ቁጥር 103/2004 በመጥቀስ የመወሰናቸውን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለዚህ ችልት የቀረበ ሲሆን ተጠሪ ቀርቦም ግራ ቀኙ በፅሁፍ እንዱከራከሩ ተደርጎአል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባላመልኩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ አና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን ለዚህ ችልት ያስቀርባል ሲባል ከተያዘው ጭብጥ አንጻር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከከርክር ሂደት መገንዘብ የሚቻለው አመልካች ከነባር ይዞታቸው ውስጥ በሕጉ አግባብ ሉጠበቅላቸው የሚገባው ይዞታ መብት ያልተጠበቀላቸው መሆኑንና በይዞታው ላይ የነበሩ ንብረቶችም ኪሳራ ሳይከፈላቸው በድዘር የወደሙባቸው መሆኑን ጠቅሰው ክስ የመሰረቱ መሆኑን፣ ተጠሪ የሚከራከረው ደግሞ ጉዲዩ ከህግ ውጪ የተያዘውን የከተማ ቦታ የማስለቀቅ ጉዲይ በመሆኑ ለተጠሪ በሕጉ ከተሰጠው ስልጣን አንፃር ጉዲዩ የከተማ ቦታን ማስለቀቅ ጉዲዮች አቤቱታ ሰሚ አካል ከሚቀርብ በስተቀር በቀጥታ ክስ በፍርድ ቤት የሚታይ አይደለም በማለት የሚከራከር መሆኑን ነው።
ፍርድ ቤቶች በህግ የሚቋቋሙ በመሆናቸው የዲኝነት ስልጣናቸው የሚመነጨውም ከህግ ነው። የማንኛውም ፍርድ ቤት ስልጣን በህግ ተወስኖ የሚሰጥ በመሆኑ ፍርድ ቤት የቀረበለትን ጉዲይ ተቀብል ከማስተናገደ በፉት ጉዲዩን /ክሱን/ ለማየት በህግ የተሰጠ የዲኝነት ስልጣን ያለው መሆኑን የማረጋገጥ ኃላፉነት አለበት። በህግ የዲኝነት ስልጣን ሳይኖረ የሚሰጥ ውሳኔ የህግ መሰረት ያለው ነው ለማለት አይቻልም።
ወደ ያዝነው ጉዲይ ስንመለስ አመልካች በስር ፍርድ ቤት የጠየቁት ዲኝነት ከነባር ይዞታቸው ውስጥ 500 ካ/ሜትር እንዱጠበቅላቸውና በይዞታው ላይ የነበረው ንብረትም ከሕግ ውጪ በመወደሙ ካሳ ሉከፈለኝ ይገባል በማለት ነው። ተጠሪም ይዞታውን ከሕግ ውጪ በመያዙ መውሰደንና አመልካች በሕግ አግባብ የያዙት ይዞታ ደግሞwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የተጠበቀላቸው መሆኑን ገልጾ ጉዲዩ የከተማ ቦታን ከማስተዲደር ስልጣኑ ጋር የተያያዘና በከተማ ቦታ ማስለቀቅ ጉዲዮች አቤቱታ ሰሚ አካል ቀርቦ ላታይ ይገባል በማለት የሚከራከር መሆኑን ተገንዝበናል።
በመሰረቱ ካሳን አስመልክቶ የሚቀርቡ አቤቱታዎችና ይግባኝ በአዋጅ ቁጥር 455/97 አንቀጽ 11 በግልጽ ተደንግጓል። በከተማ አስተዲደር የከተማ መሬት ማስለቀቅ ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ካለ ካሳውን አስመልክቶ የሚቀርበው ቅሬታ ለዚህ አስተዲደራዊ አካል የሚቀርብ ስለመሆኑ ሕጉ የሚደነግግ ሲሆን የከተማው አስተዲደራዊ አካል ካሳውን አስመልክቶ በሚሰጠው ውሳኔ ላይ ቅሬታ ያለው ወገን ለመደበኛ ፍርድ ቤት ይግባኙን ማቅረብ እንደሚችልም ሕጉ ደንግጎ ይገኛል። እንዱሁም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ስለመሆኑም ሕጉ ይደነግጋል። ሆኖም በአዋጁ መሰረት ይዞታው የተወሰደው ያለአግባብ ነው በሚል መሬት እንዱለቀቅ በተላለፈው ውሳኔ ላይ ቅሬታ ማቅረብ የሚቻልበት ሁኔታ በአዋጁ ውስጥ አልተካተተም።
የሉዝ አዋጅ ቁጥር 721/2004 በአንቀፅ 26(1) ስር አግባብ ያለው አካል ከቦታው ለሚነሳው ንብረት ተመጣጣኝ ካሳ በቅድሚያ እንዱከፈል በማድረግ የከተማ ቦታ ይዞታን ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የማስለቀቅና የመረከብ ስልጣን እንደሚኖረው ሲደነግግ በተጠቃሹ ድንጋጌ ንዐስ ቁጥር አራት ስር ደግሞ አግባብ ያለው አካል በሕገ ወጥ መንገድ የተያዘን የከተማ ቦታ በአዋጁ አንቀጽ 27 መሰረት የማስለቀቂያ ትዕዛዝ በመስጠትና ካሳ መክፈል ሳያስፈልግ የሰባት ቀናት የፅሐፍ ማስጠንቀቂያ ብቻ ለባለይዞታው በአካል በመስጠት ወይም በቦታው በሰፈረው ንብረት ላይ በመለጠፍ የማስለቀቅ ስልጣን እንደሚኖረው ተመልክቶአል። የማስለቀቂያ ትዕዛዝን ወይም ማስጠንቀቂያ የሚመለከቱ አቤቱታዎች አቀራረብን በተመለከተም አዋጁ በአንቀጽ 28 ስር ያሰፈረ ሲሆን በአቤቱታዎች ላይ ስለሚኖረው ይግባኝም በአዋጁ አንቀፅ 29 ስር ሰፍሮ ይገኛል። በመሆኑም አዋጅ ቁጥር 721/2004 በሕገ ወጥ መንገድ የተያዙ የከተማ ቦታዎችን እንዱለቀቁ የሚደረግበት ስርዓት በግልጽ የተመለከተ ሲሆን አግባብ ያለው አካል በሚሰጠው ውሳኔ ላይ ቅሬታውን ለይግባኝ ሰሚው ጉባኤው ማቅረብ እንደሚችል ሕጉ መደንገጉ ጉዲዩ በቀጥታ ወደ ፍርድ ቤት የሚሄድበት አግባብ የላለ መሆኑን የሚያሳይ ነው። ይግባኝ ሰሚው አካል ጉዲዩን የሚያስተናግደውም አቤቱታው በቅድሚያ መሬቱን እንዱለቅ ትዕዛዝwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ለሰጠው አካል ቀርቦ መስተናገደ ሲረጋገጥ መሆኑን በአዋጁ የከተማ ቦታን ማስለቀቅ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ክርክሮችን በተመለከተ የተዘረጋው ስርዓት ያስገነዝበናል።
ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስም አመልካች ክሱን የመሰረቱት የነባር ይዞታ ባለመብትነት እንዱጠበቅላቸውና በተጠሪ የወደመ ንብረት ካሳ እንዱከፈላቸው ሲሆን የክሳቸው መሰረታዊ ይዘት የሚያስገነዝበውም የነባር ይዞታ መብትን የሚመለከቱ ህጎች የጠበቁላቸው መብቶች ሳይከበሩላቸው ሕጉቹ ተጥሰው ይዞታው የተወሰደባቸው መሆኑንና ይዞታው ሲወሰድም በላዩ ላይ የሰፈረው ንብረት የወደመባቸው መሆኑን በመሆኑ ነባር ይዞታን የሚመለከቱ ሕጎችንና የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2035 ድንጋጌን መሰረት በማድረግ ጥያቄአቸውን መመርመርን የግድ የሚል ነው። ተጠሪ የከተማ ይዞታን የማስተዲደር ስልጣን በሕጉ አግባብ የተሰጠው ቢሆንም ስልጣንን እና ኃላፉነቱን በሕጉ አግባብ አልተወጣም የሚል ክርክር ያለው ወገን ግን ጉዲዩን በፍርድ ቤት ወስድ መብቱን ከማስከበር የሚከለከል ያለመሆኑን ከኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት አንቀፅ 37፣ 40(3)(4)፣79(1) እና 78(4) ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ የምንረዲው ጉዲይ ነው።
አመልካች ክሳቸውን ለመደበኛ ፍርድ ቤት ሉያቀርቡ የቻለትም የሚመለከታቸው የከተማው አስተዲደር አካላት የነባር ይዞታ ባለመብትነታቸው እንዱጠበቅላቸው አስተዲደራዊ ውሳኔ ሰጥተው እያለ ተጠሪ ውሳኔውን ባለማክበሩ ምክንያት መሆኑን ከክሳቸው መግለፃቸው ሲታይ በአዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 26ከ፣ 27 እና 28 ድንጋጌዎች በተመለከተው አካል በሚመለከተው አካል በተሰጠው ውሳኔ ቅሬታ አላቸው ለማለት የማያስችል በመሆኑ በተጠቃሹ አዋጅ በተዘረጋው የይግባኝ ጉባኤ መብታቸውን ማስከበር አለባቸው ሉባለ የሚችለበት የሕግ አግባብ የለም። ይልቁንም እሚመለከተው አካል መስኖባቸው እያለ በተጠሪ ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸው ሕጎቹ ተጥሰው የይዞታና የንብረት መብታቸው እንደተነካባቸው አመልካች በክሳቸው መጥቀሳቸውና ተጠሪም በሕጉ አግባብ ስልጣኑን በመጠቀም የወሰደው እርምጃ መሆኑን ጠቅሶ መከራከሩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 246፣ 247 እና 248 ድንጋጌዎች አግባብ የተጠሪ እርምጃ ሕጉን ተከትል የተከናወነ መሆን ያለመሆኑን የሚመለከት ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን ማጣራትን የግድ የሚል በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 721/2004 ወይም አዋጅ ቁጥር 455/97 ድንጋጌዎች አግባብ በተዘረጋው ስርዓት መሰረት በቀጥታ ለፍርድ ቤት ላቀርብ የሚችል አይደለም ወደሚለው ድምዲሜ የሚያደርስ አይደለም። ስለሆነም ከአመልካች ክስwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
መሰረታዊ ይዘት ስንነሳ በስር ፍርድ ቤት የተሰጠው ብይንም ሆነ በክልለ የበላይ ፍርድ ቤቶች ይህንኑ ብይን በማጽናት የተሰጠው ዲኝነት መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተናል። በዚሁ መሰረት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
በወልዱያ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/4 በቀን 24/02/2009 ዓ.ም ተሰጥቶ በሰሜን ወል መስተዲድር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 27/04/2009 ዓ.ም በፍርድ፣ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ አጣሪ ችልት በመ/ቁጥር 03-16739 በ27/06/2009 ዓ/ም የጸናው ብይን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሸሯል።
የወልዱያ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/4 ክርክሩን እንዱቀጥል በማድረግ ከስልጣን ውጪ የቀረቡትን የግራ ቀኙን ላልች የክርክር ነጥቦችን በመመርመርና በማጣራት ተገቢውን ዲኝነት እንዱሰጥበት ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 341/1 መሰረት መልሰን ልከንለታል። ይጻፍ።
በዚኅ ችልት በተደረገው ክርክር ግራ ቀኙ ያወጡትን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻቻለ ብለናል።