የመንግስት ቤት ህጋዊ ተከራይ የሆነ ወላጅ የኮንደሚኒየም ቤት በደረሰው ጊዜ ከመንግስት የተከራየውን ቤት ለመንግስት የማስረከብ ግዳታ ያለበት በመሆኑ የወረዲው አስተዲደር ፅ/ቤት የመንግስት ቤቱ ውስጥ ለሚኖሩ ለተከራዩ ልጆች ቤቱን ለቀው እንዱወጡ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ የሁከት ተግባር የማይስብለው ስለመሆኑ የተሻሻለው የመንግስት ቤቶችን ለማስተዲደር የወጣው መመሪያ ቁጥር 4/2009 ዓንቀፅ 15(ሐ(መ))
No summary available.
የሰበር መዝገብ ጥቅምት 30 ቀን 2011 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው በዔውቀት በላይ እንዲሻው አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች፡- አዱስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዲ 9 ኮ/ቤቶች ልማት ጽ/ቤት ተጠሪዎች፡- አቶ ሻወል ወልዳ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር ጉዲይ የመንግስት ቤትን የሚመለከት ክስን መነሻ ያደረገ ክርክር ሲሆን በአዱስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪ ከሳሽ የአሁኑ አመልካች ደግሞ ተከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ እንደነበር መዝገቡ ያመለክታል። የአዱስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት፣ የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት እና ሰበር ሰሚ ችልት ይህንን ጉዲይ በማየት ዉሳኔ መስጠታቸዉ ከመዝገቡ መገንዘብ ይቻላል።
በስር ፍርድ ቤት የአሁን ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ያቀረቡት ክስ ይዘት፡- በአዱስ አበባ ከተማ አዱስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዲ 09 የቤት ቁጥር 447 የሚገኘውን የመንግስት ቤት ከተከሳሽ ላይ ከ1967 ዓ/ም በፉት የከሳሽ ወላጅ አባት አቶ ወልዳ ብራሮ ተከራይተው እንደነበሩ፤የከሳሽ አባት እና እናት በዚሁ ለክሱ ምክንያት በሆነው ቤት ውስጥ አብረው ሲኖሩ ከሳሽን ጨምሮ 7 ልጆች እንደወለደና ከሳሽ እዚሁ አከራካሪው ቤት የሚኖር መሆኑ ቤቱን የተከራዩት አባቱ መስከረም 1 ቀን 1982 ዓ/ም ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።ከሳሽ ወላጅ አባቴ ወራሽ መሆኔን በፍ/ቤት ተወስኖ ለክሱ ምክንያት የሆነው ቤት ከእናቴ ጋር አብሬ የምኖር ስሆን እናቴ ከወንድሞቼና እህቶቼ ጋር 2 ክፍል እኔ ደግሞ 4 ክፍል ይዘን እየኖርንበት እንገኛለን።ወላጅ አባቴ በሞት ከተለየwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በኋላ የኪራይ ውለን በእናቴ ስም በማድረግ ገንዘብ እየሰጠሁኝ ኪራይ ስከፍል ቆይቻለሁ ቤቱንም እንዲይፈርስ ብዙ ገንዘብ በማውጣት አሳድሸዋለሁ።ይህ በእንዱህ እንዲለ እናቴ ኮንደሚኒየም ቤት ስለደረሳት ተከሳሽ በ3 ቀናት ውስጥ ቤቱን እንድናስረክብ የማናስረክብ ከሆነ ግን ቤቱ እንደሚታሸግ የሚገልፅ ማስጠንቀቅያ የሰጠን በመሆኑ ይህን ተግባር በከሳሽ ላይ ሁከት መፍጠር ስለሆነ የተፈጠሩብኝ ሁከት እንዱወገድልኝ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል ። ተከሳሽ ለቀረበው ክስ በሰጠው መልስ ከሳሽ አከራካሪ በሆነው ቤት መብት የለውም ።አከራካሪ የሆነው ቤት ህጋዊ ተከራይ ወ/ሮ ፈለቀች ቂጫ ስለሆኑ እሳቸው ኮንደሚኒየም ቤት የደረሳቸው ስለሆነ ቤቱን ለቀዋል ስለሆነም በመመሪያ ቁጥር 3/2003 እና በተሻሻለው መመሪያ ቁጥር 3/2007 መሰረት ቤቱ ለመንግስት ማስረከብ ስለሚገባቸው ይህን ለማስፈፀም ማስጠንቀቂያ ደብዲቤ መስጠታችን የሁከት ተግባር አይደለም በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ክሱንና በግራ ቀኙ የቀረበውን ማሰረጃ ተመልክቶ እና አጠቃላይ ክርክሩን ከመረመረ በኋላ ተከሳሽ ለከሳሽ አከራካሪው ቤት ለቀው እንዱወጡ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ የሁከት ተግባር ስለሆነ ሁከት ሉወገድ ይገባል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
በዚሁ ውሳኔ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሲሚ ፍርድ ቤት እንዱሁም አቤቱታቸውን ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበው ፍርድ ቤቶቹ የአመልካችን አቤቱታ ባለመቀበል ሰርዘውታል። አሁን የቀረበው ቅሬታ በዚሁ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን አመልካች በቀን 14/07/2010 ዓ/ም የተፃፈ አቤቱታ አቅርቧል የአቤቱታው ይዘት፡- አከራካሪው የሆነው መኖሪያ ቤት ተከራይ የነበሩት የተጠሪ አባት ከሞቱ በኋላ ወደ ተጠሪ እናት ተላልፍ በተጠሪ እናት ስም ኪራይ ሲከፈልበት የቆየ ሲሆን የተጠሪ እናት ኮንድሚኒየም መኖሪያ ቤት ሲደርሳቸው ቤቱን ለአመልካች ማስረከብ ሲገባቸው ልጃቸው ለሆነው ተጠሪ እንዱኖሩበት መደረጉ እና የስር ፍርድ ቤቶችም ውሳኔ መስጠታቸው ከመመሪያው ውጪ እና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ውሳኔ መሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት አቅርበዋል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በሰበር ችልት ላታይ ይገባዋል በመባለ ተጠሪ ቀርበው የጽሁፍ ክርክራቸውን ተለዋውጠዋል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ከላይ ባጭሩ የገለፅነው የጉዲዩን አመጣጥ ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር ችልቱ ከተያዘው ጭብጥ፤ ቅሬታ ከቀረበበት ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
እንደመረመርነው አከራካሪው የሆነው በአዱስ አበባ ከተማ አዱስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዲ 09 የቤት ቁጥር 447 የሚገኘውን የመንግስት ቤት ተከራይ የነበሩት የተጠሪ ( ከሳሽ) ወላጅ አባት አቶ ወልዳ ብራሮ እንደነበሩ እሳቸው በ1982 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ የኪራይ ውለ የከሳሽ እናት ወደ ሆኑት ወ/ሮ ፈለቀች ጫካ እንደተዛወረ የኪራይ ውለም በሳቸው ስም እንደሚከፈል ተጠሪ ከነ ቤተሰቦቹ በተጠቀሰው ቤት ውስጥ የሚኖር መሆኑ በስር ፍርድ ቤቶች ፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ ጉዲይ ነው።
የመንግስት ቤቶች ለማስተዲደር የወጣው መመሪያ ቁጥር 3/2007 ስር እንደተመለከተው ማንኛውም የመንግስት ቤት ተከራይ የኮንደሚኒየም ቤት ባለእድል ሲሆን ቤቱን ለቆ ማስረከብ እንዲለበት ተደንግጓል።የስር ፍርድ ቤት ለውሳኔው መነሻ ያደረገው ነጥብ ተጠሪ በአባታቸው በኩል የተከራይነት መብት አላቸው በማለት ሲሆን በመመሪያው እንደተጠቀሰው ወላጅ አባት ሲሞት የተከራይ መብት ወደ እናት (ሚስት) እንደሚተላለፍ የሚያሳይ ነው ። በዚህ መሰረትም የቤቱ ተከራይ የነበሩት አቶ ወልዳ ብራሮ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ ባለቤታቸው የሆኑት ወ/ሮ ፈለቀች ጫካ ህጋዊ ተከራይ እና የኪራይ ገንዘቡም በስማቸው የሚከፈል መሆኑ ተጠሪ ግን ቤቱ ውስጥ መኖሩ እንጂ ከአመልካች ጋር ህጋዊ ውል ያለው ስለመሆኑ የቀረበ ማስረጃም ሆነ ክርክር የለም ። ተጠሪ አጥብቆ የሚከራከረው የተሻሻለው መመሪያ ቁጥር 4/2009 ዓንቀፅ 15(ሐ(መ)) ውለ ከኔ ጋር እንዱቀጥል ይደግፈኛል በማለት ሲሆን ከመዝገቡ ይዘት ለመረዲት እንደቻልነው በነበረው መመሪያ መሰረት ወላጅ አባት ሲሞት የተከራይ መብት ወደ እናት (ሚስት) እንዱተላለፍ የሚፈቅድ መሆኑ ፣ በዚህ መሰረትም የቤቱ ተከራይ የነበሩት አቶ ወልዳ ብራሮ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ ባለቤታቸው የሆኑት ወ/ሮ ፈለቀች ጫካ ህጋዊ ተከራይ እና የኪራይ ገንዘቡም በስማቸው የሚከፈል መሆኑ ተጠሪ ግን ቤቱ ውስጥ መኖሩ እንጂ ከአመልካች ጋር ህጋዊ ውል የላለው መሆኑ የተሻሻለው መመሪያ ቁጥር 2/2010ም ሆነ ከዚሁ ከተሻሻለው መመሪያ በፉት የነበረው መመሪያ የቤት ተከራይነት መብት ለልጅ የሚተላለፈው ህጋዊ ተከራይ የሆነው ወላጅ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ እንጂ ኮንደሚኒየም ደርሶት ቤቱ ሲለቅ ባለመሆኑ በተያዘውwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ጉዲይ ህጋዊ ተከራይ የነበሩት የተጠሪ እናት ወ/ሮ ፈለቀች ጫካ ኮንደሚኒየም ቤት አግኝተው ከተከራዩት ቤት ከለቀቁ ቤቱ በመመሪያው መሰረት አከራይ ለሆነው አመልካች መመለስ አለባቸው። ስለሆነም አከራካሪ የሆነውን የመንግስት ቤት ህጋዊ ተከራይ የሆኑት የተጠሪ እናት በመሆናቸው እሳቸው የኮንደሚኒየም ቤት ከደረሳቸው ከመንግስት የተከራዩት ቤት ለመንግስት የማስረከብ ግዳታ ያላቸው በመሆኑ እና ተጠሪ አከራካሪው ቤት በተመለከተ መብት ያለው መሆኑ ማስረጃ ያልቀረበ በመሆኑ አመልካች ለከሳሽ አከራካሪውን ቤት ለቀው እንዱወጡ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ህጋዊ ተግባር ነው።
ሲጠቃለል የስር ፍርድ ቤቶች አመልካች ማስጠንቀቂያ መስጠቱ የሁከት ተግባር ነው በማለት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ የሚከተለዉ ተወስኗል።
የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ሰበር ችልት በመ. ታህሳስ 16 ቀን 2010 ዓ.ም የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በማፅናት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 /1/ መሰረት ተሽሯል።
አመልካች አከራካሪውን ቤት በተመለከተ የሰጠው ማስጠንቀቂያ የሁከት ተግባር አይደለም ብለናል።
ግራ ቀኛቸዉ በዚህ ችልት የደረሰባቸዉ ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።
No topics extracted.