አንድ ሰዉ የኮንድሚኒየም ግዥ ፈጽሟል ልባል የሚችለዉ ከሚመለከተዉ አካል ጋር ስምምነት መፈጸሙ ሲረጋገጥ ብቻ ሲሆን ገዥዉ ቤቱን ለሦስተኛ ወገን በሽያጭ ወይም በስጦታ ማስተላለፍ የሚችለዉ ቤቱን ከገዛ 5 ዓመት ሲሞላዉ ሲሆን ጊዜው የሚቆጠረዉ ዔጣ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ሳይሆን ገዥዉ የቤት ሽያጭ ዉል ከሚመለከተዉ የመንግስት አካል ጋር ከፈጸመበት ቀን ጀምሮ ስለመሆኑ በአ/አ ከተማ አስተዲደር አካላት የአስተዲደሩን አቶ ክብሮም አደራ እና እነ ወ/ሪት ትዔግስት መንገሻ www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XXII የማስተላለፍ ኃላፉነትና አፈፃፀሙን ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁጥር 19/97 አንቀጽ 7(6-ለ)፣14(2)
No summary available.
ቀን - 26/03/2011 ዳኞች፡- ተኽሉት ይመሰል ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራዉ ፀሐይ መንክር አመልካች፡- አቶ ክብሮም አደራ -- ጠበቃ አስቻለው ሽፈራው ቀርበዋል ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል
**
ጉዲዩ በህግ የተመለከተዉ የጊዜ ገደብ ሳይጠናቀቅ የተደረገ የኮንድምንየም ቤት ሽያጭ ዉል እንዱፈርስ በሚል የቀረበን ክስ መነሻ በማድረግ የተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ በማለት አመልካች ያቀረበዉን የሰበር አቤቱታ የሚመለከት ነዉ። ክርክሩ የተጀመረዉ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን፤ 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ፣ አመልካች እና 2ኛ ተጠሪ ደግሞ በቅደም ተከተል 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች በመሆን ተከራክረዋል።
1ኛ ተጠሪ በቀን 21/10/2008 ዓ.ም አዘጋጅታ ያቀረበችዉ ክስ ይዘትም በአጭሩ በአዱስ አበባ ከተማ ቦላ ክ/ከተማ ሰሚት ሳይት ከመንግስት ያገኘሁትን የኮንድሚኒየም ቤት 1ኛ ተከሳሽ ወኪላ ከነበረዉ 2ኛ ተከሳሽ ግንቦት 05 ቀን 2007 ዓ.ም በተደረገ ዉል የገዛሁት ነዉ በማለት ወደ ስሙ እንዱዞር ክስ መስርቶብኛል፤ ይሁንና የአዱስ አበባ ከተማwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ባወጣዉ አዋጅ ቁጥር 19/97 መሰረት አምስት ዓመት ሳይሞላዉ የተደረገ በመሆኑ ምክንያት የሽያጭ ዉለ የህግ ተቃራኒ ነዉ ተብል እንዱፈርስ ይወሰንልኝ የሚል ነዉ።
አመልካች በበኩለ ዔጣዉ የደረሰዉ ሚያዝያ 20 ቀን 2002 ዓ.ም ሆኖ የሽያጭ ዉለ የተደረገዉ አምስት ዓመት ካለፈዉ በኋላ ግንቦት 25 ቀን 2007 ዓ.ም በመሆኑ ዉለ የሚፈርስበት ምክንያት የለም በማለት መልስ ሰጥቷል። 2ኛ ተጠሪም አመልካች ካቀረበዉ ጋር ተመሳሳይ ይዘት ያለዉ ክርክር በማቅረብ ተከራክሯል።
ጉዲዩ በመጀመሪያ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ከግራ ቀኝ በዚህ መልኩ የቀረበዉን ክርክር እና ማስረጃ ከሰማ በኋላ የኮንድሚኒም ቤት የደረሰዉ ሰዉ በሽያጭ ማስተላለፍ የሚችለዉ ቤቱን ከገዛ (በዔጣ ካገኘ) በኋላ አምስት ዓመት ሲሞላዉ ስለመሆኑ የሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ላይ የህግ ትርጉም የሰጠ በመሆኑ ጊዜዉ መቁጠር የሚጀምረዉ ዔጣዉ ከደረሰ በኋላ መሆኑን፤ በዚህም መሰረት ለ1ኛ ተጠሪ ዔጣዉ የደረሰዉ ሚያዝያ 20/2002 ዓ.ም ሲሆን፣ የሽያጭ ዉለ የተደረገዉ ደግሞ ግንቦት 25/2007 ዓ.ም በመሆኑ ዉለ የህግ ተቃራኒ ነዉ ልባል የሚችል አይደለም በማለት የቀረበዉን ክስ ዉድቅ በማድረግ ወስኗል። ይግባኙ በ1ኛ ተጠሪ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በበኩለ 1ኛ ተጠሪ ቤቱን የገዛችዉ ነሐሴ 28 ቀን 2002 ዓ.ም ሲሆን፣ የሽያጭ ዉለ የተደረገዉ ግንቦት 25 ቀን 2007 ዓ.ም በመሆኑ የሽያጭ ዉለ የተደረገዉ በአ/አበባ ከ/አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 19/97 ዓ.ም መሰረት የአምስት ዓመት ጊዜ ያልተጠናቀቀ መሆኑን፣ የስር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዋቢነት የጠቀሰዉ የሰበር ዉሳኔም ለጉዲዩ አግባብነት የላለዉ መሆኑን ጠቅሶ በስር ፍርድ ቤት የተሰጠን ዉሳኔ በመሻር ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ የሽያጭ ዉል ፈርሶ ግራ ቀኙ ከዉለ በፉት ወደ ነበሩበት ሁኔታ እንዱመለሱ ሲል ወስኗል። አመልካች ይህን ዉሳኔ ባለመቀበል ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበዉ ይግባኝም ተቀባይነት አላገኘም።
አመልካች በቀን 22/09/2010 ዓ.ም አዘጋጅቶ ባቀረበዉ አምስት ገጽ የሰበር አቤቱታ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በትዕዛዝ የፀናዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ የሚልባቸዉን ምክንያቶች በመዘርዘር ታርሞ ይወሰንለት ዘንድ ዲኝነት ጠይቋል። አቤቱታዉ ተመርምሮ ያስቀርባልwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በመባለም ተጠሪዎች በተደረገላቸዉ ጥሪ መሰረት ቀርበዉ ግራ ቀኝ ክርክራቸዉን በጽሐፍ ተለዋዉጠዋል።
ከስር ጀምሮ የክርክሩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተመለከተዉ ሲሆን፣ ይህ ችልትም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠዉን ዉሳኔ አግባብነት ከግራ ቀኝ ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል። ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለዉ 1ኛ ተጠሪ ላቀረበችዉ የዉል ይፍረስልኝ ዲኝነት ጥያቄ መሰረት ያደረገችዉ ቤቱን የገዛችዉ ነሀሴ 28/2002 ዓ.ም ሲሆን የሽያጭ ዉለ የተደረገዉ ግን ግንቦት 25/2007 ዓ.ም በመሆኑ በአ/አበባ ከተማ አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 19/97 መሰረት አምስት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ የተደረገ መሆኑን ሲሆን፤ አመልካች እና 2ኛ ተጠሪዎች በበኩላቸዉ ዉለ የተደረገዉ አምስት ዓመት ከሞላዉ በኋላ ነዉ በማለት የሚከራከሩት ቀኑ የሚቆጠረዉ ቤቱ በዔጣ ለ1ኛ ተጠሪ ከደረሰበት ከሚያዝያ 20 ቀን 2002 ዓ.ም ጀምሮ እንጂ ዉለ ከተደረገበት ከነሐሴ 28/2002 ዓ.ም ጀምሮ አለመሆኑን በመጥቀስ ነዉ። ዔጣዉ ለ1ኛ ተጠሪ የደረሰዉ ሚያዝያ 20 ቀን 2002 ዓ.ም ሲሆን፣ ከመንግስት ጋር ዉል የተደረገዉ ነሐሴ 28/2002 ዓ.ም በመሆኑ ላይ ግራ ቀኝ ክርክር የላቸዉም። በመሆኑም ይህ የአምስት ዓመት ጊዜ የሚቆጠረዉ ዔጣዉ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ነዉ? ወይስ ዔጣዉ የደረሰዉ ሰዉ ከሚመለከተዉ አካል ጋር ስምምነት ካደረገበት ቀን ጀምሮ ነዉ? የሚለዉ እልባት የሚያስፈልገዉ ጭብጥ ነዉ።
በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር አካላት የአስተዲደሩን ቤቶች የማስተላለፍ ኃላፉነትና አፈፃፀሙን ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁጥር 19/97 የኮንድሚኒየም ቤት የደረሰዉ ሰዉ ለ3ኛ ወገን በሽያጭ ሉያስተላልፍ የሚችልበትን የጊዜ ገደብ ይደነግጋል። በዚህም መሰረት ገዥዉ ጠቅላላ ዋጋዉን ከፍል ቢያጠናቅቅም፣ ቤቱን ለሦስተኛ ወገን በሽያጭ ወይም በስጦታ ማስተላለፍ የሚችለዉ ቤቱን ከገዛ አምስት ዓመት ሲሞላዉ ብቻ ስለመሆኑ የአዋጁ አንቀጽ 14(2) ድንጋጌ ያስገነዝባል። ይሁንና የቤት ግዥ ተፈጽሟል ልባል የሚችለዉ ዔጣዉ ከወጣ በኋላ ነዉ ወይስ ዔጣዉን ተከትል ከሚመለከተዉ የአስተዲደሩ አካል ጋር ዉል ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ነዉ ለሚለዉ ጥያቄ አዋጁ ምላሽ አይሰጥም። በመሆኑም ቤት ፈላጊዎችን ስለ መመዝገብ እና ቤቶችን ለቤት ፈላጊዎችwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ከማስተላለፍ ጋር በተያያዘ በአዋጁ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ከግንዛቤ ዉስጥ በማስገባት መወሰኑ አስፈላጊ ይሆናል። የከተማ አስተዲደሩ ቤት ፈላጊዎችን በአዋጁ በተመለከተዉ አግባብ ለይቶ ከመዘገበ በኋላ የከተማዉን አስተዲደር ቤቶች ለቤት ፈላጊዎች ስለሚያስተላልፍበት ሁኔታ አዋጁ በአንቀጽ 6 እና 7 ስር ይደነግጋል።
በዚህም መሰረት የማስተላለፉያ መንገድች ሁለት ሲሆኑ፣ የመጀመሪያዉ የቅድሚያ መብትን ከማግኘት ጋር በተያያዘ በአዋጁ የተመለከቱትን ቅድመ ሁኔታዎች ለሚያሟለት ሰዎች ቅድሚያ በመስጠት ሲሆን፤ ሁለተኛዉ በዔጣ ስለመሆኑ ከአዋጁ አንቀጽ 6 እና 7(6-ለ) ስር ከተመለከቱት ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል። በተለይም የአዋጁ አንቀጽ 7(6-ለ) “ኤጄንሲዉ ዔጣ አወጥቶ የሚገዛዉን ቤት ከለየ ቤት ፈላጊ ጋር ባዘጋጀዉ ዉል መሰረት እንዱፈራረም ለጽ/ቤቱ ወይም በሚፈረም መሰረታዊ ዉል መሰረት ለላላ አግባብ ላለዉ አካል ዉክልና ይሰጣል” በማለት ይደነግጋል። በአጠቃላይ ከእነዚህ ድንጋጌዎች መረዲት የሚቻለዉ፣ ዔጣ ከከተማዉ አስተዲደር ጋር የቤት ግዥ ዉል ለማድረግ መብት የሚሰጥ እንጂ እራሱ የቤት ግዥ ዉል አለመሆኑን መገንዘብ ይቻላል። ከዚህም አልፍ የአዋጁ አንቀጽ 7(11) ድንጋጌ፣ ቤት ግዥ ቅድሚያ ክፍያ ፈጽሞ የቤት ሽያጭ ዉል ከተፈራረመ በኋላ ለአበዲሪ ተቋም በዋስትና አስይዞ የቤቱ መግዣ ቀሪ ገንዘብ በተመለከተ ከአበዲሪ ተቋም ጋር ዉል እንደሚያደርግ ሲያመለክት፤
የአዋጁ አንቀጽ 9 የቤት ግዥ ዉል ከመፈረሙ በፉት ቤት ገዥዉ የቅድሚያ ክፍያ የመክፈል ግዳታ እንዲለበት ይደነግጋል። በእነዚህ ሁለቱ ድንጋዎች ስር “የቤት ሽያጭ ዉል ከተፈራረመ” እንዱሁም “የቤት ግዥ ዉል” በሚል ከተገለጹት ሐረጎች መረዲት የሚቻለዉም፣ አንድ ሰዉ የኮንድሚኒየም ግዥ ፈጽሟል ልባል የሚችለዉ ከሚመለከተዉ አካል ጋር ስምምነት መፈጸሙ ሲረጋገጥ ብቻ መሆኑን ነዉ።
በመሆኑም በአዋጁ አንቀጽ 14(2) ስር ገዥዉ ቤቱን ለሦስተኛ ወገን በሽያጭ ወይም በስጦታ ማስተላለፍ የሚችለዉ ቤቱን ከገዛ 5 ዓመት ሲሞላዉ ነዉ በሚል የተቀመጠዉ ጊዜ የሚቆጠረዉ ዔጣ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ሳይሆን፣ ገዥዉ የቤት ሽያጭ ዉል ከሚመለከተዉ የመንግስት አካል ጋር ከፈጸመበት ቀን ጀምሮ ነዉ ማለት ነዉ።
ከላይ እንደተገለጸዉ የስር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሽያጭ ዉለ የተደረገዉ በአዋጁ የተመለከተዉ የአምስት ዓመት ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ነዉ በሚል መደምደሚያ ላይ የደረሰዉ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ላይ የሰጠዉን ዉሳኔwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በመጥቀስ ነዉ። ይሁንና ሰበር ሰሚዉ ችልት በተጠቃሹ መዝገብ ላይ በሰጠዉ ዉሳኔ “ዉለ ከተደረገበት ጊዜ” ካለ በኋላ በቅንፍ ዉስጥ “ዔጣ ከደረሰበት ጊዜ” ጀምሮ ያለ ቢሆንም፣ ጊዜዉ የሚቆጠረዉ ዉለ ከተደረገበት ጊዜ ነዉ ወይስ ዔጣ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ነዉ የሚለዉን ነጥብ በጭብጥነት ይዞ ተገቢዉን ትንታኔ አልሰጠበትም።
በመሆኑም ችልቱ በአዋጁ አንቀጽ 14(2) ስር የተመለከተዉ የአምስት ጊዜ የሚቆጠረዉ ዔጣዉ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2 መሰረት አስገዲጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል ለማለት አይቻልም።
በአጠቃላይ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ የኮንድሚኒየም ሽያጭ ዉል የተደረገዉ በአዋጁ አንቀጽ 14(2) ስር የተመለከተዉ የአምስት ዓመት ጊዜ ከመጠናቀቁ በፉት ነዉ በሚል ምክንያት ሉፈርስ የሚገባዉ ነዉ በማለት በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ፣ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በትዕዛዝ የፀናዉ ዉሳኔ በአግባቡ ነዉ ከሚባል በስተቀር በዚህ ችልት ሉታረም የሚችል መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ባለመገኘቱ ተከታዩ ተወስኗል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ በቀን 30/06/2010 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ፤ እንዱሁም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፍ/ይ/መ/ ላይ በቀን 09/09/2010 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዛዝ በፍ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ።
No topics extracted.