አንድ ባለይዞታ ወሰን አልፍ በልላ ሰው ይዞታ ላይ ያለአግባብ በመግባት የሰራው ግንባታ በልላኛው ባለይዞታ ንብረት አጠቃቀም ላይ ጉዲት ያደረሰ መሆኑ በባለሙያ ከተረጋገጠ ባለሙያው ባለበት ተለክቶ በዚያው ልክ ወሰኑን ያለፈዉን ግንባታ እንዱያፈርስ መደረግ ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 1204፣1205፣1225/1/
No summary available.
መ/ቁ159414 ታህሳስ 22 ቀን 2011ዓ.ም ዳኞች፡ ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንደሻዉ አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች፡ አቶ ሚሬሳ ኦብሳ ተጠሪ፡ አቶ ፍቃደ ደበል መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ በመሆኑ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
በዚህ መዝገብ የቀረበዉ ጉዲይ ድንበር ተላልፍ የተሰራ ግንባታ የሚመለከት ነዉ።በስር ፍርድ ቤት ከሳሽ የአሁኑ ተጠሪ ሲሆን የአሁኑ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክሯል።የተጠሪ ክስ ይዘት ባጭሩ አመልካች ከወሰን 50ሳ.ሜ በመራቅ ቤቱን መገንባት ሲገባዉ 75.ሳ.ሜ ወደ ተጠሪ አስጠግቶ ግድግዲ በማቆሙ የቤቱ ፍሳሽ ወደ ተጠሪ ግድግዲ እየፈሰሰ የተጠሪን ግድግዲ አበላሽቷል በሚል አመልካች ግንባታዉን እንዱያፈርስ እንዱወሰን ዲኝነት የጠየቀ ሲሆን አመልካች በበኩለ በራሱ ይዞታ ላይ እንጂ በተጠሪ ይዞታ ላይ ግንባታ እንዲላደረገ በመግለጽ ክሱ ዉድቅ እንዱደረግ ጠይቋል።ክርክሩን በመጀመሪያ የዲኝነት ስልጣን የተመለከተዉ የጎቡ ሰዮ ወረዲ ፍ/ቤት የግራቀኙን ማስረጃ ሰምቶ በተጠሪ በኩል ከቀረቡት ምስክሮች ሁለቱ አመልካች ድንበር አልፍ የሰራዉ ቤት ፍሳሽ የተጠሪ ግድግዲ ላይ የሚፈስ ስለመሆኑ ሲመሰክሩ ሁለት ምስክሮች ማን ድንበር እንዲለፈ እንደማያዉቁ መስክረዋል።በአመልካች በኩል የቀረቡትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ምስክሮች አመልካች ድንበር አላለፈም በመካከላቸዉም 1ሜትር ክፍት ቦታ አለ በማለት በመመስከራቸዉ ፍ/ቤቱ ለጉዲዩ አወሳሰን እንዱረዲ በባለሙያ ታይቶ ዉጤት እንዱቀርብ ትእዛዝ ሰጥቶ የወረዲዉ የመሬት አስተዲደር ጽ/ቤት ባለሙያ አጣርቶ አመልካች ወደ ተጠሪ ይዞታ 9ሳ.ሜ በ13ሜ በማለፍ የገነባዉ ቆርቆሮ ፍሳሽ በተጠሪ ግድግዲ ላይ እየፈሰሰ ጉዲት ማድረሱን መግለጫ በመስጠቱ አመልካች ወሰን አልፍ የሰራዉን እንዱያፈርስና በባለሙያ ተለክቶ1ሜ.በመራቅ እንዱገነባ በማለት ዉሳኔ ሰጥቷል።አመልካች በዚህ ዉሳኔ ቅር ተሰኝቶ ለምስራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት እና ለኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት እንደቅደም ተከተለ ይግባኝ እና የሰበር አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም ተቀባይነት አላገኘም።
ለዚህ ሰበር ችልት አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ላይ ሲሆን የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘት ባጭሩ የግራቀኙ ምስክሮች ቃል ሲታይ የአመልካች ምስክሮች አመልካች ድንበር አለማለፈን ስለመመስከራቸዉ እና በባለሙያ ተለክቶ ከቀረበዉ ሪፖርት ይዘት ባላገናዘበ ሁኔታ የስር ፍርድ ቤት አመልካች1ሜ.ገብቶ እንዱገነባ በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ በተጠሪ ከተጠየቀዉ ዲኝነት ዉጪ ነዉ በሚል ምክንያት ዉሳኔዉ እንዱታረም ጠይቋል።የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ በተጠሪ በኩል በተጠየቀዉ ዲኝነት መሰረት የተወሰነ መሆን አለመሆኑን ለመመርመር እንዱቻል ጭብጥ ተይዞ ተጠሪ መልስ እንዱሰጥ ተደርጓል።በተጠሪ በኩል የቀረበዉ መልስ ባጭሩ በከተማ ፕላን መሰረት በመኖሪያ ቤት መካከል ያለዉ ርቀት 50ሳ.ሜ መሆኑ የሚታወቅ ስለመሆኑና አመልካች 75ሳ.ሜ ወደ ተጠሪ ግድግዲ ተጠግቶ በመስራቱ በድምሩ ከ1ሜ በላይ ስለሚሆን የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ ተገቢ ነዉ በማለት ተከራክሯል።አመልካች በመልስ መልሱ ላይ ክርክር የተነሳበት ይዞታ የገጠር መንደር ስለሆነ በከተማ ፕላን መሰረት ላታይ አይገባም በማለት የተጠሪ ክርክር ዉድቅ እንዱደረግ ጠይቋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራቀኙ ክርክር ይዘት ከላይ ባጭሩ ከላይ የተገለጸ ሲሆን እኛም የግራቀኙን ክርክር የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ እና ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል ሲባል የተያዘዉን ጭብጥ መሰረት በማድረግ አግባብነት ካለዉ ህግ ጋር በማገናዘብ መርምረናል።መዝገቡን እንደመረመርነዉ አመልካችና ተጠሪ በይዞታቸዉ በድንበር የሚዋሰኑ መሆኑ አከራካሪ አይደለም ።ተጠሪ ክስ ያቀረበዉ ከአመልካች በሚዋሰንበትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በምስራቅ በኩል አመልካች 50ሳ.ሜ ወደ ራሱ ይዞታ ገብቶ ግንባታ ማድረግ እየተገባዉ 75ሳ.ሜ ወደ ተጠሪ ይዞታ ገብቶ በመገንባቱ ከአመልካች ቆርቆሮ ጣሪያ ላይ የሚፈሰዉ ፍሳሽ በተጠሪ ግድግዲ ላይ እየፈሰሰ ጉዲት ስላደረሰ ይህንኑ እንዱያፈርስ ዲኝነት የጠየቀ ሲሆን አመልካች ወደ ተጠሪ ይዞታ አልገባሁም በማለት የተከራከረ ቢሆንም ከግራቀኙ ምስክሮች ቃል ባሻገር የባለሙያ መግለጫ እንዲረጋገጠዉ አመልካች 9ሳ.ሜ ስፊት በ13ሜትር ቁመት ወደ ተጠሪ ይዞታ ገብቶ የገነባ ስለመሆኑና ከቤቱ ጣሪያ የሚወርደዉ ፍሳሽ የተጠሪ ግድግዲ ላይ እንደሚፈስና ጉዲት እንዲደረሰ ተገልጧል።
ግራቀኙ የሚከራከሩበት ይዞታ የገጠር መሬት ይዞታ ሆኖ የመኖሪያ መንደር ላይ የተገነባ ቤት ወሰን አጠቃቀም የሚመለከት ስለመሆኑ ከክርክሩ መገንዘብ ተችሎል።ስለሆነም ክርክር የተነሳበት ይዞታና ቤት የሚገኝበት ቦታ በከተማ አስተዲደር የተዋቀረ ባለመሆኑ ጉዲዩ በከተማ አስተዲደር ፕላን መሰረት የሚታይ ባይሆንም በፍ/ብ/ህጉ ስለንብረት አጠቃቀም መብትና ግደታዎች የተደነገገዉን ተመርኩዞ እልባት መስጠት የሚገባ እንደሆነ እንገነዘባለን።በዚሁ አግባብ በፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 1204 እና 1205 ላይ እንደተደነገገዉ ባለሀብቱ ሀብቱን በሚገባ ለመገልገል ሰፉ መብት ያለዉ ቢሆንም በህግ የተጣለ ገደቦች እንደተጠበቁ ስለመሆኑ ያሥገነዝባል።ከእነዚህ ገደቦች አንደ በፍ/ብ/ህጉ አንቀጽ 1225/1/ ላይ እንደተመለከተዉ ባለሀብቱ በሀብቱ በሚገልገልበት ጊዜ የጎረቤቱ ርስት ጥቅም የሚቀንስበትን ወይም የሚጎዲበትን ማንኛዉንም ከመጠን ያለፈ ነገር ከመስራት መጠበቅ እንደሚገባ ያስገድዲል።
በዚህ መዝገብ በተያዘዉ ጉዲይ አመልካች ወሰን በማለፍ ከገነባዉ ቤት ቆርቆሮ /ጣሪያ/ ላይ የሚፈሰዉ ፍሳሽ የተጠሪ ግድግዲ ላይ እየፈሰሰ ጉዲት ማድረሱ በስር ፍርድ ቤት በባለሙያ ታይቶ የተረጋገጠ ስለመሆኑ መዝገቡ ያሥረዲል።ስለሆነም ይህ የአመልካች ድርጊት የተጠሪ ንብረት አጠቃቀም ላይ ጉዲት ያደረሰ በመሆኑ የተጠሪ የዲኝነት ጥያቄ የህግ መሰረት ያለዉ ነዉ።ከዚህ ቀጥል መታየት ያለበት ጉዲይ የስር ፍ/ቤት ዉሳኔ ተጠሪ የጠየቀዉ ዲኝነት እና በማስረጃ የተረጋገጠዉን መሰረት ያደረገ መሆን አለመሆኑን የሚመለከት ነዉ።በመሰረቱ ዲኝነት ላሰጥ የሚገባዉ ከሳሽ ወገን በግልጽ ዲኝነት በጠየቀበት አግባብ እና በተከሳሽ እምነት ወይም በማስረጃ በተረጋገጠ ልክ መሆን እንዲለበት የፍ/ብ/ስ/ስ ህግ አንቀጽ 182፣224፣234፣242 እና 273 ድንጋጌዎችwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ይዘት ያስገነዝባለ።ስለሆነም በዚህ መዝገብ በተያዘዉ ክርክር ተጠሪ ክስ ያቀረበዉ አመልካች 75 ሳ/ሜ ወደ ተጠሪ ይዞታ ገብቶ የደረገዉን ግንባታ እንዱያፈርስ በሚል ዲኝነት የጠየቀ ሲሆን አመልካች ወደ ተጠሪ ይዞታ አልገባሁም በሚል የተከራከረ ሲሆን አመልካች በራሱ ይዞታ ላይ የገነባዉ ቤት ጣሪያ ወደ ተጠሪ ይዞታ ወሰን አልፍ የገባዉ 9ሳ.ሜ ስፊት በ13ሜ.ቁመት መሆኑ በማስረጃ የተረጋገጠ ስለሆነ ፍርድ ቤቱ በዚሁ ልክ ዉሳኔ መስጠት እየተገባ የስር ፍርድ ቤት አመልካች ቤቱን አፍርሶ አንድ ሜትር ገብቶ እንዱሰራ ሲል የሰጠዉ ዉሳኔ በተጠሪዉ ከተጠየቀዉ ዲኝነት ወጪ በመሆኑና ከፍ/ብ/ስ/ስ ህግ አንቀጽ 182/1/ድንጋጌ የሚጻረር በመሆኑ ሉታረም ይገባል ብለናል።በዚሁ አግባብ ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል።
1ኛ/የጎቡ ሳዮ ወረዲ ፍ/ቤት በመ/ቁ11244 ላይ በ26/03/2010 ዓ.ም የሰጠዉ ፍርድ ይህንኑ በማጽናት የምስራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት እና የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት እንደቅደም ተከተል በመ/ ላይ የሰጡት ትእዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁ/348/1/መሰረት ተሻሽሎል።
2ኛ/አመልካች የተጠሪ ይዞታ ላይ ወሰን አልፍ የሰራዉ ቤት 9ሳ.ሜ.ስፊት በ13ሜ.ቁመት ያለአግባብ ወደ ተጠሪ ይዞታ የገባ ስለመሆኑ በባለሙያ በተረጋገጠዉ መሰረት ባለሙያ ባለበት ተለክቶ በዚሁ ልክ ወሰኑን ያለፈዉን ግንባታ እንዱያፈርስ በማለት ወስነናል።
3ኛ/በዚህ ችልት ተሻሽል በተወሰነዉ መሰረት እንዱያስፈጽም ለጎቡ ሳዮ ወረዲዉ ፍ/ቤት ግልባጭ ይተላለፍ ብለናል።ይጻፍ።
4ኛ/በዚህ ፍ/ቤት ለተደረገዉ ክርክር ወጪና ኪሳራ ግራቀኙ የየራሳቸዉን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.