በባህላዊ መንገድ የሚታረስ መሬትን በዉል ማከራየት የሚቻለዉ ከ3 ዓመት ላልበለጠ ጊዜ ሆኖ ዉለም ዋጋ የሚኖረዉ በሚመለከተዉ አካል ተመዝግቦ ሲረጋገጥ ብቻ ስለመሆኑ የኦሮሚያ ክልል የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 130/99 አንቀጽ 10(2 እና 3) www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XXI ኤጀንሲን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ ቁ. 179/05 አንቀጽ 8
No summary available.
የሰ/መ/ቁ/134343 ግንቦት 27 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች፡ ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንዲሻዉ አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካቾች፡ 1ኛ/አቶ ቴዎድሮስ ዉብሸት 2ኛ/ወ/ሮ ፍሬህይወት ዉብሸት 3ኛ/አቶ ሚካኤል ዉብሸት ተጠሪዎች፡ 1ኛ/የአዲማ ከተማ ቀበላ 06 መስተዲድር ጽ/ቤት 2ኛ/አቶ ሙከሚል ከሉል 3ኛ/ወ/ሮ ዓለም ሃጎስ 4ኛ/ወ/ሮ አይሻ ከድር 5ኛ/አቶ ሻምበል ሃይለ መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ በመሆኑ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
በዚህ መዝገብ የቀረበዉ ጉዲይ በዉርስ የተላለፈ የከተማ ይዞታና ቤት ከመንግስት ቤት ጋር ተቀላቅል ስለሚገኝ የመንግስት ቤት ፈርሶ ለአጠቃቀም በሚያመች አኳኋን ይዞታዉ ስፊት ተስተካክል የይዞታ ማረጋገጫ ለወራሾች እንዱሰጥ የቀረበ የዲኝነትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ጥያቄ የሚመለከት ነዉ።በዚህ ጉዲይ ከሳሾች የአሁኖቹ አመልካቾች ሲሆኑ 1ኛ ተጠሪ ተከሳሽ ከ2-5 ያለት ተጠሪዎች ጣልቃ ገብ በመሆኑ ተከራክረዋል። የአመልካቾች ክስ ይዘት ባጭሩ በአዲማ ከተማ ቀበላ 06 ዉስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር 233.06 የሆነ መኖርያ ቤት ይዞታ ስፊቱ 101 ካ.ሜ ከአያታቸዉ ከወ/ሮ ፀሐይ ካሳ በስጦታ የተላለፈላቸዉ መሆኑን ገልጸዉ ይዞታዉና ቤቱ ከመንግስት ቤት ጋር ተቀላቅል ስለሚገኝ ለ1ኛ ተጠሪ ጉዲዩ በአቤቱታ ቀርቦ ቃለ ጉባኤ ተይዞ የመንግስት ቤት ፈርሶ ይዞታዉ ሰፍቶ ከፉለ ለመንገድ እንዱሆን ላላዉ ለአመልካቾች ይዞታ ተጨምሮ 260 ካ.ሜ ሆኖ የይዞታ ማረጋገጫ እንዱሰጥ ስለተወሰነ በዚሁ መሰረት እንዱፈጸም ዉሳኔ እንዱሰጥ ዲኝነት ጠይቀዋል።
በ1ኛ ተጠሪ በኩል የቀረበዉ መልስ ባጭሩ የከተማ መሬት የማስተዲደርና የመቆጣጠር ስልጣን የአዲማ ከተማ መሬት ልማት ማኔጅመንት ኤጀንሲ እንጂ የተከሳሹ ባለመሆኑ ስልጣን በልላቸዉ የቀበላዉ አመራሮች የተሰጠ ዉሳኔ ወይም ቃለጉባኤ ተፈጻሚነት እንደላለዉ፣አመልካቾች እንዱፈርስ የጠየቁት የመንግስት ቤት የማስተዲደር ስልጣን የመንግስት ቤቶች አስተዲደር አካል በመሆኑና የላልችን መብትና ጥቅም የሚመለከት ስለሆነ ተቀባይነት እንደላለዉ በመግለጽ ክሱ ዉድቅ እንዱደረግ ተከራክሯል።ከ2-5ኛ ላለት ተጠሪዎች ከመንግስት ቤቶቹን ተከራይተዉ የሚኖሩበት መሆናቸዉን ገልጸዉ ክርክሩ መብታቸዉን የሚመለከት በመሆኑ ወደ ክርክር በጣልቃ ገብነት ገብተዉ ቤቶቹ እንዱፈርሱ ዉሳኔ ላሰጥ እንደማይገባ ተከራክረዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ የዲኝነት ስልጣን የተመለከተዉ የአዲማ ወረዲ ፍርድ ቤት አመልካቾች በንብረታቸዉ የመገልገል ህገ መንግስታዊ መብት እንዲላቸዉ እና ይዞታቸዉ ለአጠቃቀም በሚያመች መልኩ ችግሩ እንዱፈታ በቀበላ አመራር ኮሚቴ በተሰጠ ዉሳኔ መሰረት የመንግስት ቤቶች እንዱፈርሱና ለአመልካቾች ይዞታ ተጨምሮ በ260 ካ.ሜ ይዞታ ማረጋገጫ እንዱሰጣቸዉ በማለት ዉሳኔ ሰጥቷል። የቀበላ ቤት ለሚፈርስባቸዉ ሰዎች መስተዲድሩ መፍትሓ እንዱሰጥ የሚል ትእዛዝ ሰጥቷል። በዚህ ዉሳኔ ተጠሪዎች ቅር በመሰኘት ለአዲማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ቅሬታ በማቅረባቸዉ ፍርድ ቤቱ ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ ጉዲዩ የከተማ መሬት ይዞታ ላይ መሬት እንዱሰጥ እና ይዞታ ማረጋገጫ እንዱሰጥ የሚል ከመሆኑ አኳያ ይህምwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የከተማዉ እስታንዲርድና ማስተር ፕላን ጋር የሚታይ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ በዚህ ጉዲይ ላይ የመወሰን ስልጣን የለዉም በማለት የወረዲ ፍርድ ቤት ዉሳኔ በመሻር ተጠሪዎችን አሰናብቷል።አመልካቾች ለኦሮሚያ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ባቀረቡት ይግባኝ ላይ ፍርድ ቤቱ ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ የአመልካቾች ጥያቄ ፍትህ የማግኘት መብት ጥያቄ ነዉ በሚል አስተዲደሩ ባለዉ መመሪያ መሰረት ይዞታ ተስተካክል ማረጋገጫ እንዱሰጣቸዉ በወረዲ ፍርድ ቤት የተሰጠዉ ዉሳኔ በከፍተኛዉ ፍርድ ቤት መሻሩ ተገቢ አይደለም በማለት የከፍተኛዉን ፍርድ ቤት ዉሳኔ በመሻር የወረዲዉን ፍርድ ቤት ዉሳኔ አጽንቷል።በዚህ ዉሳኔ ተጠሪዎች ቅር በመሰኘት ለኦሮሚያ ክልል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ በማቅረባቸዉ ሰበር ችልቱ ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ በቀበላዉ ኮሚቴ በ15/12/06 ዓ.ም የተያዘዉ ቃለጉባኤ አስተዲደራዊ መፍትኄ የሚያመለክት እንጂ በቀጥታ ፍርድ ቤት ቀርቦ የሚፈጸም ባለመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ተቀብለዉ በቃለ ጉባኤ መሰረት ይፈጸም በማለት የሰጡት ዉሳኔ የህግ መሰረት የለዉም በማለት የክልለ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት እና ወረዲዉ ፍ/ቤት ዉሳኔ በሰበር ችልቱ ተሽሯል።
ለዚህ ሰበር ችልት አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ላይ ሲሆን የሰበር አቤቱታቸዉ ይዘት ባጭሩ ጉዲዩ አዱስ ማስረጃ ጥያቄ ሳይሆን በእጃችን ያለዉ ይዞታ በመመሪያዉ መሰረት ይካፈልልን የሚል የፍትህ ጥያቄ ስለሆነ ፍርድ ቤት ማየት አይችልም መባለ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለሆነ እንዱታረም የሚል ሲሆን አቤቱታቸዉ ተመርምሮ የክልለ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልት የስር ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን ማየት አይችለም በማለት የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ መሻሩ ተገቢ መሆን አለመሆኑን ለመመርመር እንዱቻል ጭብጥ ተይዞ ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡ ተደርጓል። በ1ኛ ተጠሪ ወኪል በኩል የቀረበዉ መልስ ባጭሩ በሰበር ችልቱ የተያዘዉ ጭብጥ ላይ ሰበር ችልቱ የሚወስነዉ ሆኖ የአመልካቾች ይዞታ ከቀበላ ቤት ጋር ሳይቀላቀል ማስረጃ ቢሰጣቸዉ ተቃዉም እንደላለዉ ገልጸዋል።ከ2—5 ያለትን ተጠሪዎች በጠበቃቸዉ አማካኝነት የሰጡት መልስ የአመልካቾች ጥያቄ የቀበላ ቤትና ይዞታ ተጨምሮ ይዞታ ተስተካክል ማረጋገጫ እንዱሰጣቸዉ የሚል ስለሆነ በዚህ ጉዲይ የመወሰን ስልጣን የአዲማ ከተማ መስተዲድር ስለመሆኑ በመግለጽ የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ እንዱጸና ተከራክረዋል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የጉዲዩ አመጣጥና ግራቀኙ ክርከር ከላይ ባጭሩ የተገለጸ ሲሆን ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል ሲባል የተያዘዉን ጭብጥ መሰረት በማድረግ አግባብነት ካለዉ ህግ ጋር በማገናዘብ መርምረናል ።መዝገቡን መርምረን እንደተገነዘብነዉ የአመልካቾች የዲኝነት ጥያቄ ከአያታቸዉ በዉርስ ያገኙት የቤት ቁ/233.06 በ101 ካ.ሜ ላይ ያረፈ ቤት ከመንግስት ቤት ጋር የተቀላቀለ ስለሆነ ካርታና ፕላን ማሰራት እንዲልቻለ ጠቅሰዉ ተቀላቅል የሚገኘዉ የመንግስት ቤት ፈርሶ ይዞታቸዉ ላይ 157 ካ/ሜ ተጨምሮ በ260 ካ.ሜ ይዞታ ማረጋገጫ እንዱሰጣቸዉ ነዉ።ለዚህም መነሻ የደረጉት የ1ኛ ተጠሪ በኮሚቴ ጉዲዩን አይቶ ቃለጉባዓ ይዞ ዉሳኔ ስለመስጠቱ ነዉ።ይህን ቃለጉባኤ አስመልክቶ በአንድ በኩል ቀጥታ ፍርድ ቤት ክስ ለማቅብ የሚያስችል መብት የሚሰጥ ነዉ ወይስ አስተዲደራዊ ዉሳኔ ሀሳብ ሆኖ በሚመለከታቸዉ የአስተዲደር አካላት ተቀባይነት ሲያገኝ የሚፈጸም ነዉ የሚል ጥያቄ የተነሳበት በልላ በኩል ደግሞ የቀበላ ቤት እንዱፈርስ እና ለአመልካቾች ተጨማሪ ይዞታ እንዱሰጥ የቀበላዉ ኮሚቴ ተፈጻሚነት ያለዉ ዉሳኔ ለመስጠት የሚያስችለዉ የህግ መሰረት አለዉ ወይ የሚለዉ መሰረታዊ ጉዲይ አከራካሪ ሆኖ ቀርቧል። ስለሆነም እነዚህ አስተዲደራዊ መዋቀር እና ስልጣን ተከትል መፍትሄ ወይም ምላሽ የሚያገኙ ሆኖ አመልካቾች የጠየቁት ዲኝነት በፍርድ ቤት ዉሳኔ የሚሰጥበት ጉዲይ ነዉ የሚለዉ መመርመር ተገቢ ነዉ።
በመሰረቱ የዲኝነት ስልጣን ከህግ የሚመነጭ መሆኑ ልብ ይለዋል።በልላ በኩል ማንኛዉም ሰዉ በፍርድ ሉወሰን የሚገባዉን ጉዲይ ለፍርድ ቤት ወይም ለላላ በህግ የዲኝነት ሰልጣን ለተሰጠዉ አካል የማቅረብና ፍትህ የማግኘት መብት እንዲለዉ የኢ.ፋ.ዳ.ሪ ህገ መንገስት አንቀጽ 37/1/ በግልጽ ደንግጓል።ከዚህ አንጻር አመልካቾች በፍርድ በዲኝነት አካል ሉወሰን የሚገባዉን ጉዲይ ወደ ፍርድ ቤት በማቅረብ ፍትህ የማግኘት ህገ መንግስታዊ መብት ያላቸዉ መሆኑ አከራካሪ አይደለም ።በዚህ መዝገብ የተያዘዉ ጉዲይ ሲታይ የአመልካቾች ጥያቄ በዉርስ ያገኙት ቤትና ይዞታ ላይ የይዞታ ማረጋገጫ የማግኘት መብት ተነፍገዉ ሳይሆን ይዞታቸዉ 101 ካ/ሜ ብቻ በመሆኑ በዚህ ላይ የይዞታ ማረጋገጫ ማሰራት ባለመቻለና ለአጠቃቀም አመቺ ባለመሆኑ ተቀላቅል ያለዉ የቀበላ ቤት እንዱፈረስና ተጨማሪ ይዞታ ተሰጥቶአቸዉ በ260 ካ.ሜ የይዞታ ማረጋገጫ እንዱሰጣቸዉ እንዱወሰን የሚል ነዉ። በዚህ ደግሞ ፍርድ ቤቱ ዉሳኔ ከመስጠቱ በፉት መብትና ጥቅም ያላቸዉ ወገኞች እንዱሁም የከተማ መሬትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ይዞታ አጠቃቀም ላይ የመወሰን ስልጣን በህግ ስልጣን የተሰጣቸዉ የአስተዲደር አካላት ዉሳኔ አስፈላጊ መሆኑ ይታወቃል።በተለይም የክልለ ከተማ መሬት አስተዲደር አካል በአዋጅ ቁ/179/05 አንቀጽ 8 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት እንዱሁም እንዱፈርሱ እየተባለ ያለዉ የቀበላ ቤት የሚያስተዲድረዉ አካል እና በቤቱ ዉስጥ የሚኖሩት ሰዎች እጣፈንታ በሚመለከት ስልጣን በተሰጠዉ አካል ባልተወሰነበት ሁኔታ የአመልካቾችን ጥያቄ ብቻ መሰረት በማድረግ ፍርድ ቤቱ ዉሳኔ ለመስጠት የሚያስችለዉ የህግ መሰረት የለዉም ። አመልካቾች በጉዲዩ ላይ አስተዲደራዊ መፍትሄ ከሚመለከታቸዉ አካላት መጠየቅና ማስወሰን እየተገባቸዉ በአስተዲደር አካል ያልተረጋገጠ መብት ይዘዉ ፍርድ ቤት ዉሳኔ እንዱሰጣአቸዉ ያቀረቡት የዲኝነት ጥያቄ ተቀባይነት የለዉም በማለት የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሟል ለማለት አልተቻለም።በዚሁ አግባብ ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል።
1ኛ /የኦሮሚያ ክልል ጠ/ፍ/ቤት በሰበር መ/ቁ/233806 ላይ በ14/02/09 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁ/348/1/ መሰረት ጸንቷል።ይጻፍ።