በባህላዊ መንገድ የሚታረስ መሬትን በዉል ማከራየት የሚቻለዉ ከ3 ዓመት ላልበለጠ ጊዜ ሆኖ ዉለም ዋጋ የሚኖረዉ በሚመለከተዉ አካል ተመዝግቦ ሲረጋገጥ ብቻ ስለመሆኑ የኦሮሚያ ክልል የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 130/99 አንቀጽ 10(2 እና 3) www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XXI ኤጀንሲን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ ቁ. 179/05 አንቀጽ 8
No summary available.
ቀን፡-ግንቦት 27/2010 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንዲሻዉ አዲነ ኃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች:- አቶ ሀይለ ኪዲኑ ቀረቡ ተጠሪዎች፡-
ለዚህ ሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዲይ በገጠር መሬት የመጠቀም መብትን የሚመለከት ሆኖ የተጀመረው በኦሮሚያ ክልል በጉቶ ጊዲ ወረዲ ፍርድ ቤት ነው።
በዚሁ ፍ/ቤት የአሁኑ 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ የአሁኑ አመልካች ተከሳሽ የነበሩ ሲሆን የአሁኑ 2ኛ ተጠሪ ደግሞ ጣልቃ ገብ ነበሩ። 1ኛ ተጠሪ በአመልካች ላይ አቅርበዉት የነበረዉ ክስ ይዘት፡- ክርክር ያስነሳዉን መሬት በ1989 ዓ.ም በዉሳኔ አግኝቼ እየተጠቀምኩበት የቆየሁ ሲሆን የአሁኑ 1ኛ ተጠሪ መሬቱን በ2005 ዓ.ም ከሕግ ዉጪ ይዞ ስለሚገኝ ይልቀቅልኝ የሚል ነዉ። አመልካች በበኩለ ክርክር ያስነሳዉ መሬት በቤንሻንጉልጉሙዝ ክልል ዉስጥ ይገኝ የነበረ ሲሆን ወደ ኦሮሚያ ከተካለለ በኃላ በጉቶ ጊዲ ወረዲ ግብር እየከፈልኩ ስጠቀምበት የቆየሁት በመሆኑ 1ኛ ተጠሪ መብት የላለዉ በመሆኑ ክስ ዉድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክሯል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ያየዉ የጉቶ ጊዲ ወረዲ ፍ/ቤት የግራቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ አመልካች ክርክር ያስነሳዉን መሬት ለ1ኛ ተጠሪ እንዱለቅ ወስኖ የነበረ ቢሆንም የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ዉሳኔዉን በመሻር አመልካች መሬቱን በኮንትራት ወስጀበታለሁ የሚለዉ የአሁኑ 2ኛ ተጠሪ ወደ ክርክሩ ጣልቃ እንዱገባ ካደረገ በኃላ የመሬቱ ባለይዞታ ማን እንደሆነና በምን መልኩ በአመልካች እጅ እንደገባ አጣርቶ ተገቢዉን እንዱወስን በነጥብ መልሶለታል።
2ኛ ተጠሪ ወደ ክርክሩ ጣልቃ እንዱገባ ተደርጎ በሰጠዉ መልስ ክርክር ያስነሳዉን መሬት ከ1ኛ ተጠሪ በኮንትራት ለ5 ዓመት ወስጄ በመሃል ስታመም ለአመልካች ለ10 ዓመት በኮንትራት የሰጡት እንጂ የአመልካች አይደለም በማለት 1ኛ ተጠሪን በመደገፍ ተከራክሯል።
የወረዲዉ ፍ/ቤት ክርክርና ማስረጃዉን መርምሮ 1ኛ ተጠሪ ክርክር ያስነሳዉ ይዞታ በእጁ አድርጎ ሲያዝበት የነበረ ይዞታዉ ለመሆኑ አላስረዲም በማለት ክስ ለማቅረብ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 33(2) መሰረት መብት የለዉም በማለት ክሱን ዉድቅ በማድረግ ወስኗል። 1ኛ ተጠሪ በዚህ ዉሳኔ ቅር ተሰኝተዉ ያቀረቡትን ይግባኝ የተመለከተዉ የምስራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ግራቀኙን ካከራከረ በኃላ መርምሮ አመልካች ክርክር ያስነሳዉን መሬት ከ2ኛ ተጠሪ ለ15 ዓመት በኮንትራት ወስጄ የያዝኩት ነዉ በማለት የተከራከረ ሲሆን 2ኛ ተጠሪ ደግሞ መሬቱን ከ1ኛ ተጠሪ በኮንትራት ወስጄ ለአመልካች በኮንትራት ሰጠሁኝ ያለ በመሆኑ፤ እንዱሁም በክልለ የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 130/99 መሰረት የኪራይ ዉለ በሚመለከተዉ አካል ያልተመዘገበ በመሆኑ አመልካች መሬቱን ለ1ኛ ተጠሪ ይልቀቅ በማለት የወረዲዉን ፍ/ቤት ዉሳኔ በመሻር ወስኗል። በዚህ ዉሳኔ ቅር ተሰኝተዉ አመልካች ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኝ ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኘም። በመቀጠል ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታ ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኘም። ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚሁ ውሳኔ ላይ አመልካች ቅር በመሰኘታቸዉ ለማስለወጥ ነው።
አመልካች ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ይዘት፡- የአሁኑ ተጠሪ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን መሬት ለአሁኑ 2ኛ ተጠሪ ኮንትራት የሰጠ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ በላለበትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
እና መሬቱን በ01/09/1998 ዓ.ም በተጻፈ የኮንትራት ዉል ከ2ኛ ተጠሪ ተከራይቼ ስጠቀምበት የቆየሁ ስለሆነ ለመክሰስ መብት የነበረዉ 2ኛ ተጠሪ እንጂ 1ኛ ተጠሪ አይደለም። 1ኛ ተጠሪ ይችላል ቢባል እንኳ ክስ በይርጋ ቀሪ ሆኖ እያለ አልፈዉ የስር ፍ/ቤቶች የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ። 2ኛ ተጠሪ ይዞታዉ የራሱ መሆኑን ገልጾ አከራየኝ እንጂ ጠያቂ ሲመጣ መሬቱን እንደምለቅ ባልተዋዋልኩበት እንድለቅ መወሰኑ ስህተት ነዉ። ይዞታዉ የ1ኛ ተጠሪ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ባልቀረበበት መሬቱን ልቀቅ መባላ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ዉሳኔዉ ተሽሮ የወረዲዉ ፍ/ቤት ዉሳኔ ይጽናልኝ የሚል ነዉ።
የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮ በግራ ቀኙ መካከል በተነሳዉ የገጠር እርሻ መሬት ጉዲይ የምስራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የኮንትራት ዉለ ከ1999 ዓ.ም በፉት መፈጸሙ እየታወቀ የክልለን የመሬት አዋጅ ቁጥር 130/99 በመጥቀስ ዉለ ባለመመዝገቡ ፈራሽ ነዉ ሲል የሰጠዉ ዉሳኔ አግባብነት ለመመርመር ሲባል ለሰበር ያስቀርባል የተባለ ሲሆን ግራቀኙ ክርክራቸዉን በጽሁፍ አቅርበዋል።
1ኛ ተጠሪ በሰበር መልሳቸዉ ያቀረቡት ክርክር ይዘት፡- ክርክር ያስነሳዉ መሬት 3 ሄክታር የአርሶ አደር የእርሻ መሬት መሆኑ ተረጋግጦ በክልለ የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 130/99 መሰረት ለዚህን ያህል ጊዜ የአርሶ አደር መሬት ማከራየት አይቻልም ተብል አመልካች መሬቱን እንዱለቅ መወሰኑ ተገቢ ነዉ። በአካባቢዉ ባለመኖሬ እስክመለስ እንዱጠቀምበት ለ2ኛ ተጠሪ ሰጠሁት እንጂ ለላላ 3ኛ ወገን እንዱያከራይ ባለመሆኑ የኪራይ ዉለ አይጸናም። አመልካች መሬቱን በዉል የያዘና የያዘዉም በ1998 ዓ.ም በመሆኑ ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት ያቀረበዉ ቅሬታ ተገቢነት የለዉም በማለት ተከራክሯል። 2ኛ ተጠሪ በበኩለ የ1ኛ ተጠሪን ክርክር በመደገፍ መልስ አቅርቧል።
የግራቀኙ ክርክር ከላይ የተመለከተዉን የሚመስል ሲሆን ከስር ፍ/ቤት ዉሳኔ እና ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል ተብል ከተያዘዉ ጭብጥ ጋር በማገናዘብ መርምረናል። መርምረን እንደተረዲነዉ ግራቀኙን ያከራከረዉ ይዞታ አመልካች ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ግንቦት 01 ቀን 1998 ዓ.ም በተደረገ የኪራይ ዉል ለ15 ዓመት ተከራይቶ የያዘዉ መሆኑን የገለጸ ሲሆን 2ኛ ተጠሪ በበኩለ መሬቱ የ1ኛ ተጠሪ መሆኑን አረጋግጦ ለ5 ዓመት ተከራይቶ በመታመሙ ምክንያት ለአመልካች ለ15 ዓመት ማከራየቱንና መሬቱ ለ1ኛ ተጠሪwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ሉመለስለት እንደሚገባ ተከራክሯል። የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት አመልካች ክርክር ያስነሳዉን መሬት ለተጠሪ ሉለቅ ይገባል በማለት ሲወስን የሰጠዉ ምክንያት አመልካች ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ግንቦት 01 ቀን 98 ዓ.ም ያደረጉት የኪራይ ዉለ፤ የመሬት ኪራይ ዉልን ለመመዝገብ ስልጣን ባለዉ አካል አልተመዘገበም በሚል ነዉ። የዚህን ችልት ምላሽ የሚያሻዉና የአመልካች አቤቱታ ለሰበር ያስቀርባል ሲባል የተያዘዉ ጭብጥ፤ የኪራይ ዉለ ከ1999 ዓ.ም በፉት የተደረገ ሆኖ ሳለ አዋጅ ቁጥር 130/99 በመጥቀስ ዉለ ባለመመዝገቡ ፈራሽ ነዉ መባለ በአግባቡ ነዉ? ወይስ አይደለም? የሚለዉ ነዉ።
በመሰረቱ በክልለ የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 130/99 አንቀጽ 10(2 እና 3) መሰረት በባህላዊ መንገድ የሚታረስ መሬትን በዉል ማከራየት የሚችለዉ ከ3 ዓመት ላልበለጠ ጊዜ ሆኖ ዉለም ዋጋ የሚኖረዉ በክልለ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ተመዝግቦ ሲረጋገጥ ብቻ መሆኑ የተመለከተ ሲሆን ይህ አዋጅ ከመደንገጉ በፉት ሥራ ላይ የነበረዉ አዋጅ ቁጥር 56/94 አንቀጽ 11(2 እና 4) ስር በተመሳሳይ በባህላዊ መንገድ የሚለማን መሬት አርሶ አደሩ ማከራየት የሚችለዉ ከ3 ዓመት ላልበለጠ ጊዜ ሆኖ በአካባቢዉ መሬትን ለማስተዲደር ስልጣን ባለዉ አካል ሲረጋገጥ መሆኑ ተደንግጓል። ከእነዚህ አዋጆች ድንጋጌዎች ይዘት መገንዘብ የሚቻለዉ አዋጅ ቁጥር 130/99 ከመዉጣቱ በፉትም ሆነ በኃላ አርሶ አደሩ በባህላዊ መንገድ የሚያለማዉን መሬት ማከራየት የሚችለዉ ከ3 ዓመት ላልበለጠ ጊዜ ሆኖ ዉለ ዋጋ እንዱኖረዉ በሚመለከተዉ አካል ተመዝግቦ መረጋገጥ የሚገባዉ መሆኑን ነዉ።
በተያዘዉ ጉዲይ አመልካች ክርክር ያስነሳዉን መሬት ለ15 ዓመት ከ2ኛ ተጠሪ ተከራየሁ ከማለቱም በላይ የኪራይ ዉለ በሚመለከተዉ አካል ያልተመዝገበና ያልተረጋገጠ ነዉ።
ይህ ዉል በአዋጅ ቁጥር 56/94 አንቀጽ 11(2 እና 4) ሆነ አሁን ሥራ ላይ ባለዉ አዋጅ ቁጥር 130/99 አንቀጽ 11(2 እና 3) መሰረት ሕጋዊ ዉጤት የላለዉ በመሆኑ 2ኛ ተጠሪን ሉያስገድድ የሚችል አይደለም። ከዚህ በተጨማሪ 2ኛ ተጠሪ ከ1ኛ ተጠሪ ለ5 ዓመት ተከራየሁት የሚለዉን መሬት በላለዉ መብት ለ15 ዓመት ሉያከራይ የሚችልበት አግባብ የለም። ከዚህ አንጻር የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት አመልካች ለ1ኛ ተጠሪ መሬቱን ይልቀቅ ብል መወሰኑም ሆነ በየደረጃዉ ጉዲዩን የተመለከቱት ፍ/ቤቶች ይህንኑ ዉሳኔ ማጽናታቸዉ የሚነቀፍ አይደለም።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ሲጠቃለል አመልካች ክርክር ያስነሳዉን የገጠር መሬት ለ1ኛ ተጠሪ እንዱለቅ የተሰጠዉ ዉሳኔ የሚነቀፍበት በቂ ምክንያት ባለመኖሩ ዉሳኔዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል ለማለት አልተቻለም። በመሆኑም የሚከተለዉ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
በምስራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ጥቅምት 27 ቀን 2010 ዓ.ም ተሰጥቶ፤ በኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ሕዲር 13 ቀን 2010 ዓ.ም በተሰጠ ትዕዛዝ እና በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ሕዲር 27 ቀን 2010 ዓ.ም በተሰጠዉ ትዕዛዝ የጸናዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ጸንቷል።
በጉቱ ጊዲ ወረዲ ፍ/ቤት የተጀመረዉ አፈጻጸም ለጊዜዉ ታግድ እንዱቆይ በዚህ ችልት የካቲት 07 ቀን 2010 ዓ.ም የተሰጠዉ የዔግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
ይጻፍ።
No topics extracted.