የንግድ ማህበር ስለሚፈርስበት አግባብ የንግድ ህግ ቁጥር 217፤218 እና 542 www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XX ቸን ( 2 ሰዎች)
No summary available.
መስከረም 21 ቀን 2011 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውልስ ኦርሺሶ አመልካች፡- ሚሲስ ሲያዎ ድንግ - ጠበቃ ሃፍቶም ከሰተ - ቀረቡ ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። በሥር ፍርድ ቤት የአሁን ተጠሪዎች ከሳሾች አመልካች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል። የተጠሪዎች ክስ ይዘትም አመልካች በሁዋ ኢ ስሜንት የተወሰነ የግል ማህበር ውስጥ ስራ አስኪያጅ ሲሆኑ የተሸሙት ለአራት ዓመታት በመሆኑ፤
ምንም ዓይነት የባለአክስዮኖች ስብሰባ ጠርተው የማያውቁ በመሆናቸው፤ ዓመታዊwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የሑሳብ ሪፖርትም ሆነ የትርፍ ክፍፍል ተደርጎ የማያውቅ በመሆኑ፤ ሽያጭ እየደበቁና ግብር እየሰወሩ በገቢ ሰብሳቢ ቢሮ ድርጅቱ እንዱቀጣ ያደረጉ በመሆናቸው ከስራ አስኪያጅነታቸው ይሻርልን፤የድርጅቱ ሑሳብና ሁኔታ ኦዱት እንዱደረግልን በማለት ክስ አቅርበዋል።
የስር ተከሳሽ የነበሩት አመልካች በሰጡት መልስ የድርጅቱ ባለአክስዮኖች በ03/10/2001፤ 20/07/2002 እና በ23/11/2003 ዓ.ም በተደረጉ ውሳኔዎች ማህበሩ የማቋቋም ውሳኔዎች ተሻሽሎል፤2ኛ ተጠሪ ምንም ገንዘብ አላወጣም፤ስራ አስኪያጅ የማንሳት ጉዲይ በባለአክስዮኖች ስብሰባ ላይ አብላጫ ድምፅ ድጋፍ ሳያገኝ በመቅረቱ ያልተተካ በመሆኑ በፍርድ ቤት ሉወሰን የሚችል አይደለም፤በመመስረቻ ጽሁፍና በመተዲደሪያ ደንቡ መሰረት ስብሰባ የመጥራት ኃላፉነት የሁለም ባለአክስዮኖች ግዳታ ነው፤አመልካች ስብሰባ ተጠርተው ቀርተው አያቁም፤ስብሰባውም እ.ኤ.አ ዱሴምበር 27 ቀን 2014 እና ጃንዋሪ 20 ቀን ተደርጓል፤የሁለም በጀት ዓመት ሑሳብ ተደርጓል፤ትርፍ ክፍፍል ተደርጎ ተጠሪዎች ገንዘብ ወስደዋል፤ከስራ አስኪያጅነት ሉያስነሳ የሚችል ጥፊት አልሰራሁም፤የድርጅቱ ሑሳብ በየዓመቱ ኦዱት ተደርጎ ግብር የሚከፈል ሁኖ እያለ በ3ኛ ወገን የሚመረመርበት ምክንያት የለም በማለት መልስ ካቀረቡ በኋላ ድርጅቱ በስድሳ ሚልዮን ቢቋቋም አመልካችና 1ኛ ተጠሪ እያንዲንዲችን 45% ድርሻ ሲኖረን 2ኛ ተጠሪ ደግሞ 10% ድርሻ ነበራቸው። አመልካችና ተጠሪዎች ባደረግነው ስምምነት ከ14 ሚልዮን በላይ መዋጮ ያዋጣሁ ቢሆንም ተጠሪዎች መዋጮ ያልከፈለ በመሆናቸው በተለያየ ጊዜ በተደረጉ ስምምነቶች መዋጮው እንዱከፍለ /ላላ ግለሰብ እንዱከፍልላቸው ጭምር/ የተስማማ ቢሆንም ምንም ዓይነት መዋጮ አዋጥተው የማያውቁ በመሆናቸው እ.ኤ.አ ጃንዋሪ 22 ቀን 2015 ከተደረገው ስብሰባ ጀምሮ የሑሳብ ሪፖርት ፀድቆ ትርፍ ክፍፍል እንዱደረግ በተያዘው አጀንዲም ምንም ስምምነት መድረስ አልቻለም በስራ አስኪያጅ ይነሳ ጉዲይ ከፍተኛ አለመግባባት ተፈጥሯል፤
በውጭ ኦዱተር የተሰራውን የማህበሩ ሑሳብ ተጠሪዎች ለማጽደቅ እምቢተኛ ሁኗል፤ተጠሪዎች ባቀረቡት ክስ መነሻነትም የማህበሩ ህልውና አደጋ ላይ ወድቋል፤በአጠቃላይ በመዋጮ፤ስራ አስኪያጅ ሹመት፤ትርፍ ክፍፍል፤በኦዱት ሪፖርትና የማህበሩ አመራር ዙሪያ በአባላት መካካል አለመግባባት እና ብርቱ ጭቅጭቅ የተፈጠረ በመሆኑ ማህበሩ እንዱፈርስ እና ንብረት አጣሪ እንዱሾም የተከሳሽ ከሳሽነት አቅርበውwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ተጠሪዎች በበኩላቸው ማህበሩ ሉፍርስ አይገባውም የሚል መልስ ሰጥቷል። ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የቀረበው መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ በፍሬ ነገሩ ላይ የግራ ቀኙ ክርክር ከሰማና ማስረጃ ከመዘነ በኋላ ማህበሩ ሉፍርስ ይገባል?
ወይስ አይገባም? የሚለውን ጭብጥ በማስቀደም የተፈጠረው ግጭት መሰረታዊ ግጭት አይደለም፤አንደ ማህበርተኛ በወሰነው ወይም በሰራው ላላው ደስተኛ ወይም ተጠቃሚ ካለመሆኑ የተነሳ አለመግባባት ነው፤ማፍረስ የመጨረሻ መፍትሓ ነው፤የተጠቀሱ ምክንያቶች አለመግባባት እና ብርቱ ጭቅጭቅ ፈጥሯል የሚባለ አይደለም በማለት ማህበሩ ሉፍርስ አይገባውም፤በመቀጠል አመልካች ከተሾሙ አንስቶ 4 ዓመት ያለፈባቸው በመሆኑ፤ድርጅቱ እንዲልተቀጣ ቢገልጹም የተወሰነ ገንዘብ እንደከፈለ ማመናቸው፤በየዓመቱ ስበሰባ እየጠሩ የሑሳብ እና የስራ ሪፖርት ያቀረቡ ስለመሆናቸው ያቀረቡት ክርክር የለም በማለት ክስራ አስኪያጅነታቸው ሉነሱ ይገባል በማለት ወስኖ የድርጅቱ ሁኔታና ሑሳብ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ በኦዱተር እንዱጣራ ሲል የሰጠው ውሳኔ በመቃወም አመልካች ይግባኛቸው ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ተቀባይነት ሳያገኝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.337 መሰረት በትእዛዝ ሰርዞታል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበውም ይህንኑ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። አመልካች የካቲት 13 ቀን 2010 ዓ.ም በፃፈት አቤቱታ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶችን ዘርዝረው አቅርበዋል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ በመደረጉ ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡበት በታዘዘው መሰረት ሚያዚያ 25 ቀን 2010 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርበዋል። አመልካችም አቤቱታቸው በማጠናከር የመልስ መልስ በመስጠት ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለክርክሩ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር መርምረናል። ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪዎች ባቀረቡት ክስ አመልካች ከስራ አስኪያጅነት ኃላፉነታቸው እንዱነሱ ያቀረቡት መሰረት በማድረግ የማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 10.4 መሰረት ከአራት ዓመት በኋላ ላላ ስራ አስኪያጅ እንደሚመረጥ የተመለከተ መሆኑን በመግለጽ የስር ፍርድ ቤቶችwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የደረሱበት ድምዲሜ ከመሆኑም በላይ በአጣሪው ችልትም በጭብጥነት ያልተያዘ ከመሆኑ አንፃር አመልካች ስራ አስኪያጅ እንዱመረጥ የተሰጠ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት ያለው ሁኖ አልተገኘም። በልላ በኩል አመልካች አጥብቀው የሚከራከሩበት ጉዲይ በማህበሩ አባላት መካከል ብርቱ ጭቅጭቅ ተፈጥሮ እያለ ማህበሩ ሉፍርስ አይገባም በማለት የስር ፍርድ ቤቶች የደረሱበት ድምዲሜ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ሉታረም ይገባል የሚል ሲሆን ተጠሪዎች በበኩላቸው የአመልካችን የማህበሩ ይፍረስ ጥያቄ እና ምክንያት በንግድ ህጉ አንድ ማህበር ስለሚፈርስበት ሁኔታ ከተደነገጉት አንቀጽ 217 እና 218 ጋር በአግባቡ አገናዝበው የሰጡት ውሳኔ እና አተረጓጎም ምንም አይነት የህግ ስህተት የላለበት ስለሆነ ሉጸና ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካቿ ምክንያታቸውን በዝርዝር በመግለጽ ሂሳቡ ተጣርቶ ማህበሩ እንዱፈርስ እንዱወሰን የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ አቅርበዋል።
በቀረበው የዲኝነት ጥያቄ በግራ ቀኙ መካከል ዝርዝር ክርክር ከተደረገ በኋላ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ማህበሩን ለማፍረስ የሚያስችል በቂና ሕጋዊ ምክንያት ያልተገኘ መሆኑን እንዱሁም የንግድ ማህበሮች መቋቋምና በተለያዩ የንግድ፤የኢኮኖሚ ስራዎች ላይ መሰማራት፤ለአንድ ሀገር የኢኮኖሚ እድገትና እንቅስቃሴ ወሳኝ የሆነ ሚና ያላቸው ሲሆን የሀገራት ኢኮኖሚ እድገትም ከንግድ ማህበሮች መቋቋም ጋር የተያያዘ ነው። በመሆኑም የንግድ ማህበሮች መቋቋም፤መስፊፊት ብልም መፍረስ ከማህበርተኞች መብትና ጥቅም አልፍ በሶስተኛ ወገኖች /ሰራተኞች፤ከማህበሩ ጋር የውል ግዳታ በሚገቡ ሰዎች በገንዘብ ጠያቂዎች ወዘተ../መብትና ጥቅም ላይ እንዱሁም በአጠቃላይ የሀገር ኢኮኖሚ እድገትና እንቅስቃሴ ላይ አለታዊ ውጤት የሚያስከትል በመሆኑ የንግድ ማህበራት ጉዲይ በተለይም የንግድ ማህበራት መፍረስ ጉዲይ በአግባቡ እና በጥንቃቄ ላታይ የሚገባው ጉዲይ መሆኑን ገልጾ አመልካቿን ጥያቄ በቀን 15/02/2010 ዓ.ም. በዋለው ችልት በተሰጠ ውሳኔ ውድቅ አድርጓል። ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔን በማጽናት በቀን 29/05/2010 ዓ.ም. በዋለው ችልት ትእዛዝ ሰጥቷል።
በመሰረቱ የንግድ ማህበሮች ከተቋቋሙ በኋላ እንደየአግባብነቱ በማህበርተኞቹ ስምምነት፣ በሕግ በተመለከተው ምክንያትና በፍርድ ቤት ውሳኔ ሉፈርሱ የሚችለwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ሲሆን የንግድ ሕጉ ለሁለም ማህበሮች ተፈፃሚነት ያላቸው የማፍረሻ ምክንያት ያስቀመጠ ከመሆኑ በተጨማሪ እያንዲንደ ንግድ ማህበር ካለው የተለየ ባህሪ አኳያ ለየማህበራቱ ተፈፃሚ የሚሆን ተጨማሪ የማፍረሻ ምክንያቶች አካትቶ ይዟል። በንግድ ሕጉ ስለ ንግድ ማህበሮች በጠቅላላው በሚናገረው ክፍል የሚገኘው ቁጥር 217 ማህበር በሕግ ወይም በስምምነት ሉፈርስ የሚችልበትን ቁጥር 218 ደግሞ በፍርድ ቤት አማካኝነት የሚፈርስበትን ምክንያቶች ያመለክታለ። ማህበሩ የተቋቋመበትን ጉዲይ ከፈፀመ ወይም ለመፈፀም ባልቻለ ጊዜ፣የንግድ ማህበሩ ፀንቶ የሚቆይበት ዘመን ከመድረሱ በፉት ማህበርተኞቹ ማህበሩ እንዱፈርስ ተስማምተው ከወሰኑ፣ማህበርተኞቹ ማህበሩ እንዱቀጥል ካልተስማሙ በቀር ማህበሩ የተቋቋመበት ዘመን ሲያበቃ ማህበሩ ሉፈርስ ይችላል። ማህበሩ የሚቆይበት ዘመን ከመድረሱ በፉት ትክክለኛ ምክንያቶች ኖረውት ከማህበርተኞቹ አንደ ጥያቄ ሲያቀርብ በፍርድ ቤት ውሳኔ ሉፈርስ የሚችል ሲሆን ከማህበርተኞቹ አንደ ተግባሩን (ግዳታዎቹን) ከመፈፀም በብዙ ማስተጓጎል፣በአካል ጉድለት ወይም በማይድን ህመም ምክንያት ወይም በማንኛውም ላላ ምክንያት የማህበሩን ስራ ለመስራት አለመቻለ፣ በማህበርተኞቹ መካከል ብርቱ ጭቅጭቅና አለመስማማት መፈጠሩ እንደትክክለኛ ምክንያት ሉወሰደ እንደሚችለ የንግድ ህግ ቁጥር 218 (2) ድንጋጌ ያመለክታል። ድንጋጌው "ብርቱ ጭቅጭቅና አለመስማማት" የሚለው ሐረግ ምን እንደሚያመላክት የሚያስቀምጠው ግልፅ መመዘኛ የላለ ቢሆንም ሐረጉ ማህበሩ ከተቋቋመበት መሰረታዊ አላማና ከማህበርተኞቹ አብሮ የመስራት አጠቃላይ ሁኔታ አንጻር ታይቶ ሉተርጎም የሚችል መሆኑ የሚታመን ነው።
ስለሆነም ብርቱ ጭቅጭቅ ሲባል በማህበርተኞቹ መካከል ያለ ማንኛውም አለመግባባት ሳይሆን ማህበርተኞች አብረው ለመስራት የማያስችላቸው ወይም ማህበሩ የተቋቋመበትን አላማ ለማሳካት የማያስችለው እና ለስራው አስፈላጊ ከሆነ ጉዲይ ጋር የተገናኘ መሰረታዊ ግጭትና አለመግባባት መኖሩን የሚያመለክት ነው ተብል የሚወሰድ መሆኑ ይታመናል። ሐረጉ በዚህ አግባብ መተርጎም ያለበት ካልሆነ ማህበራት ተገቢው የሕግ ጥበቃ ተደርጎላቸው ለአገር ኢኮኖሚ የሚያበረክቱት ሚና የጎላ አይሆንም። በልላ አገላለፅ ሐረጉ ማህበሩ ተገቢውን ስራ ለማከናወን የሚያስችል ሁኔታ ውስጥ መኖሩን በሚያሳይ መልኩ ካልተተረጎመ ማህበራት ተገቢ ባልሆኑ ምክንያቶች ሁለ እንዱፈርሱwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የማድረግ አጋጣሚን ሁለ ሉፈጥር የሚችል ነው። ይህ ደግሞ የሕጉ መሰረታዊ ዓላማ ያለመሆኑ ይታመናል።
ላላው በተጠቃሹ ድንጋጌ ስር የተጠቀሱት የማህበር ማፍረሻ ምክንያቶች ተዘርዝረው የተጠቀሱ ሳይሆን አመልካች በመሆናቸው በተለይ “ትክክለኛ ምክንያት” የሚለው የድንጋጌው ሃረግ ሰፉና ትርጉም የሚያሻው በመሆኑ በስራ አስኪያጆቹ ግዙፍ ጥፊት ሲፈፀም፣ስራው የሚጠይቀው ቅን ልቦና ሲጠፊ፣ የማህበሩ ገንዘብ ለግል ጥቅም ሲውል፣ለማህበሩ ገቢ መሆን የሚገባው ገንዘብ አለማድረግን የመሰለት ምክንያቶች ከተከሰቱና የተፈጠረው ችግርም ማህበሩን ከማፍረስ ውጪ በልላ ሁኔታ ወይም አግባብ መፍትሓ የማያገኝ መሆኑን ፍርድ ቤቱን የሚያሳምን ከሆነ ማህበሩ ሉፈርስ የሚችልበትን አግባብ የሚያሳዩ ናቸው ተብል ሉወሰደ የሚችለ ምክንያቶች ናቸው።
የተወሰነ አላፉነት ያለው የግል ማህበር የሚፈርስባቸው ምክንያቶችም በንግድ ሕጉ በቁጥር 542 ስር ተመልክቷል። ስለሆነም ፍርድ ቤቱ እንደየ ጉዲዮቹ አግባብነት የሚቀርበውን ምክንያት መከሰቱን በማስረጃ ማረጋግጥና ስለመከሰቱ ከተረጋጋጠ ደግሞ የምክንያቱን በቂነት በአግባቡ ሉመረምር የሚገባው ነው።
በተያዘው ጉዲይ በአመልካች ማህበሩ ሉፈርስ ይገባል በማለት የጠየቁት አባላት የአክስዮን መዋጮ አልከፈለም፤ለማህበሩ ሉዋጣ የሚገባውን ገንዘብ በተመለከተ በተለያየ ጊዜ ስምምነት ላይ የተደረሰ ቢሆንም አባላቱ በስምምነቱ መሰረት መዋጮ አልከፈለም፤የከሳሽ ተከሳሽ ማህበሩ ያላቸውን 55% አብላጫ ድምጽ በመጠቀም ከተከሳሽ ከሳሽ የተለየ አቋም ስለሚይዙ ማህበርተኞች መስማማት የማንችልበት ደረጃ ላይ ደርሰናል፤ አመልካች ስራ አስኪያጅ እንዱሻር እና በፍርድ ቤት ክስ በማቅረባቸው ምክንያት ድርጅቱ አደጋ ላይ ወድቋል። በአጠቃላይ በማህበሩ አስተዲደር እና አካሄድ ዙሪያ በአባላት መካከል አለመግባባት እና ብርቱ ጭቅጭቅ ተፈጥሯል የሚለ ምክንያቶችን መሆናቸው የስር ውሳኔ ግልባጭ ያመለክታል። እንደሚታየው እነዚህ ምክንያቶች ማህበሩን ለማፍረስ የሚያስችለ በቂና ሕጋዊ ምክንያቶች ተደርገው ሉወሰደ የሚችለ አይደለም። በአመልካች የተነሱ ምክንያቶችም ከማህበሩ መፍረስ በመለስ ባለ እርምጃዎች እልባት ማግኘት የሚችለ ጉዲዮች ናቸው። የማህበሩ ሕልውና እንዱቀጥል መደረግ የሚገባው ከመሆኑ በቀር ማህበሩ ሉፈርስ ይገባል በማለት አመልካች ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ባለመገኘቱ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.225884 ጥቅምት 15 ቀን 2010 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ.205876 ጥር 29 ቀን 2010 ዓ.ም በትእዛዝ የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ወጭ እና ኪሳራ የግራ ቀኙን ተከራካሪ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻለ።
መዘገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.