በአንድ ክስተት ከሁለት በላይ በሆኑ ሦስተኛ ወገኖች ላይ ጉዲት መድረሱ በመድን ሰጪና ተቀባይ መካከል በተደረገ የመድን ዉል መሰረት የመድን ሰጪዉ ግዳታ የኃላፉነት መጠን በመድን ዉለ ላይ ከተመለከተዉ መብለጥ የላለበት ስለመሆኑ የንግድ ህግ አንቀጽ 665(2)
No summary available.
ቀን - 28/03/2011 ዳኞች፡- ተኽሉት ይመሰል ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራዉ ፀሐይ መንክር አመልካች፡- የኢትዮጵያ መድን ድርጅት - አልቀረቡም።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ መብራቴ ጤናዉ - አልቀረቡም።
ጣ/ገብ ተጠሪ፡- አረብ ኮንትራክተርስ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በአንድ ክስተት ከሁለት በላይ በሆኑ ሦስተኛ ወገኖች ላይ ጉዲት መድረሱ መድን ሰጪዉ በመድን ዉለ ላይ ከተመለከተዉ የኃላፉነት ጣሪያ በላይ እንዱከፍል ምክንያት የሚሆን መሆን አለመሆኑን የሚመለከት ነዉ።
ክርክሩ የተጀመረዉ በኦሮሚያ ክልል ምዔራብ ጉጂ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን፣ ተጠሪ በቀን 10/04/09 ዓ.ም አዘጋጅተዉ በጣ/ገብ ተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ቁጥሩ 3- 69511 የሆነዉ የተከሳሽ ተሽከርካሪ ወደ ኋላ ተንሸራትቶ በንብረታቸዉ ላይ በብር 150,800.00 የሚገመት ጉዲት ያደረሰ መሆኑን ጠቅሰዉ ተከሳሽ ይህኑን ገንዘብ እንዱከፍላቸዉ ይወሰንላቸዉ ዘንድ ዲኝነት ጠይቀዋል። ጣ/ገብ ተጠሪ ለቀረበበት ክስ በሰጠዉ መልስ ጉዲት መድረሱን ሳይክድ፣ የደረሰዉ ጉዲት ግምቱ የተጋነነ ነዉ የሚልባቸዉን ምክንያቶች በመዘርዘር የተከራከረ ሲሆን፣ አመልካች በክርክሩ ጣልቃwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
እንዱገባ በማለትም ጠይቋል። አመልካችም በክርክሩ ጣልቃ በመግባት፣ በከሳሽ የተጠየቀዉ ጉዲት መጠኑ በባለሙያ ተገምቶ ያልቀረበ መሆኑን፣ እንዱሁም በተመሳሳይ ጉዲይ በልላ መዝገብ በክርክር ላይ ያለ መሆኑን እና የኃላፉነት መጠኑ ከብር 100,000.00 ስለማይበልጥ ፍርድ ቤቱ ይህኑን ግምት ዉስጥ እንዱያስገባ በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩ በመጀመሪያ የቀረበለት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ከግራ ቀኝ በዚህ መልኩ የቀረበዉን ክርክር እና ማስረጃ ከሰማ በኋላ በደረሰዉ አደጋ ምክንያት በተጠሪ ላይ የደረሰ ጉዲት በብር 130,800.00 ስለመሆኑ መረጋገጡን ጠቅሶ፣ አመልካች በመድን ዉለ በተመለከተዉ ጣሪያ ልክ ብር 100,000.00 እንዱከፍል፣ ቀሪዉን ለዲኝነት የተከፈለዉን ገንዘብ ጨምሮ የአሁን ጣ/ገብ ተጠሪ እንዱከፍል በማለት ወስኗል።
አመልካች ይህን ዉሳኔ ባለመቀበል ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበዉ ይግባኝም ተቀባይነት አላገኘም።
አመልካች በቀን 06/03/2010 ዓ.ም በወኪለ አማካይነት ባቀረበዉ አራት ገጽ የሰበር አቤቱታ በግራ ቀኝ መካከል በተደረገዉ የመድን ዉል መሰረት አመልካች በአንድ ክስተት በሦስተኛ ወገን ላይ ለደረሰ ጉዲት ለመክፈል የገባዉ ግዳታ እስከ ብር 100,000.00 ብቻ መሆኑን፤ በተመሳሳይ አደጋ ምክንያት ንብረትነቱ የአቶ አርአያ ገ/መድህን የሆነዉ የሰ/ቁጥሩ 1-33616 በሆነዉ ባጃጅ ተሽከርካሪ ላይ ጉዲት መድረሱን ተከትል በመ/ ላይ ክስ ቀርቦ አመልካች ብር 54,951.00 እንዱከፍል መወሰኑን፤ ይህም አመልካች በአንድ ክስተት ሉከፍል ከሚገባዉ ጣሪያ በላይ ብር 54,951.00 እንዱከፍል መደረጉን የሚያሳይ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት ይህኑን ግምት ዉስጥ እንዱያስገባ አመልካች ያቀረበዉን ክርክር ዉድቅ በማድረግ አመልካች መክፈል ከሚገባዉ በላይ እንዱከፍል የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ በማለት ታርሞ ይወሰንለት ዘንድ ዲኝነት ጠይቋል። አቤቱታዉ ተመርምሮም አመልካች በመድን ዉለ ከተመለከተዉ ጣሪያ በላይ እንዱከፍል የመወሰኑን አግባብነት ግራ ቀኝ በተገኙበት ለመመርመር ሲባል ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ በተደረገላቸዉ ጥሪ መሰረት ቀርበዉ ግራ ቀኝ ክርክራቸዉን በጽሐፍ ተለዋዉጠዋል። በዚህ መነሻነት መዝገቡ ከተመረመረ በኋላ፣ በስር ተከሳሽ የነበረዉ በዚህ ችልት ተጠሪ ሆኖ ጣልቃ እንዱገባwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ማድረጉ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በተደረገለት ጥሪ መሰረት ጣ/ገብ ተጠሪ በቀን 24/01/2011 ዓ.ም ተዘጋጅቶ በቀረበ መልስ በዚህ ችልት በሚደረግ ክርክር ጣልቃ እንዱገባ የተደረገበት አግባብ ኢ-ስነስርዓታዊ መሆኑን፣ እንዱሁም የአመልካችን የኃላፉነት መጠን በተመለከተ በስር ፍርድ ቤት የተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት አለመሆኑን ጠቅሶ ተከራክሯል።
ከስር ጀምሮ የክርክሩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ሲታይ ከፍ ሲል የተመለከተዉን ሲመስል፣ ይህ ችልትም መዝገቡን ለማስቀረብ የተያዘዉን ጭብጥ፣ ከግራ ቀኝ ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል።
አመልካች ለዚህ ችልት ባቀረበዉ የሰበር አቤቱታ አጥብቆ የሚከራከረዉ በጣ/ገብ ተጠሪ ተሽከርካሪ ምክንያት በአንድ ጊዜ የሚደርስ አደጋ ከሁለት እና ሁለት በላይ ሰዎች ላይ ጉዲት ቢደርስም የኃላፉነቱ መጠን ከብር 100,000.00 ሉበልጥ እንደማይገባ፣ ይሁንና በተሽከርካሪዉ አማካይነት በተፈጠረ አደጋ ምክንያት ከተጠሪ ላላ በሦስተኛ ወገን ላይ ለደረሰ ጉዲት ተከስሶ ብር 54,591.00 እንዱከፍል መደረጉን እና ይህም ለተጠሪ እንዱከፈል ከተወሰነዉ የገንዘብ መጠን ጋር ሲደመር የአመልካችን ኃላፉነት በመድን ዉለ ከተመለከተዉ በላይ ብር 154,951.00 የሚያደርስ መሆኑን ነዉ። ያስቀርባል የተባለዉም ይህኑን ለማጣራት ነዉ። በመሆኑም በዚህ መዝገብ ላይ የሚሰጥ ዉሳኔ በጣ/ገብ ተጠሪ መብት ላይ አለታዊ ወይም አዎንታዊ ዉጤት ሉያስከትል ይችላል።
ይህኑን ግምት ዉስጥ በማስገባት አመልካች ጣ/ገብ ተጠሪን ተጠሪ ማድረግ ሲገባዉ አላደረገም። ይህ በመሆኑም ጣ/ገብ ተጠሪ በዚህ ችልት እየተደረገ ባለዉ ክርክር በተጠሪነት እንዱቀርብ መደረጉ በፍ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 40(5) መሰረት በአግባቡ በመሆኑ ጣ/ገብ ተጠሪ በዚህ ችልት በተጠሪነት መጠራቱ ከስነ ስርዓት ዉጪ መሆኑን በመግለጽ የሚያቀርበዉ ክርክር ተቀባይነት ያለዉ አይደለም።
ወደ ዋናዉ ጉዲይ ስንመለከት ከላይ እንደተገለጸዉ በግራ ቀኝ መካከል በቀን 24/03/2008 ዓ.ም በተደረገ የሦስተኛ ወገን መድን ዉል በፉደል “ሰ“ ለንብረት ጉዲት ካሳ በሚል በተመለከተዉ ርዔስ ስር በአንድ ክስተት በሦስተኛ ወገን ላይ ለደረሰ የንብረት ጉዲት ካሳ የአመልካች ኃላፉነት እስከ ብር 100,000.00 ስለመሆኑ በግልጽwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ተመልክቷል። በጣ/ገብ ተጠሪ ተሽከርካሪ በተፈጠረዉ አደጋ ምክንያት በተጠሪ ንብረት ላይ በብር 130,800.00 የሚገመት ጉዲት የደረሰ ሲሆን፣ በተመሳሳይ አደጋ በአቶ አርአያ ገ/ማርያም የባጃጅ ተሽከርካሪ ላይ መድረሱን ተከትል በጉጂ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ ክርክር ተደርጎ ፍርድ ቤቱ በአደጋዉ ምክንያት በባጃጁ ላይ ለደረሰ ጉዲት ብር 54,951.00 አመልካች እንዱከፍል መወሰኑን እና በዉሳኔዉ መሰረትም የተፈጸመ ስለመሆኑ ከግራ ቀኝ ክርክር ለመረዲት ተችሎል። ይሁንና ይህ መሆኑ የአመልካችን የኃላፉነት ጣሪያ ከፍ ሲል በተመለከተዉ አግባብ በግራ ቀኝ መካከል በተደረገ የመድን ዉል ከተመለከተዉ ከብር 100,000.00 በላይ ሉያደርግ አይችልም። ስለሆነም የስር የጉጂ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ለተጠሪ ሉከፍል የሚገባዉን የካሳ መጠን ሲወስን ይህኑን ግምት ዉስጥ ማስገባት ነበረበት። ፍርድ ቤቱ ይህን ባለማድረግ በአንድ በኩል አመልካች ለአቶ አርአያ ገ/መድህን 54,951.00 እንዱከፍል ወስኖ እያለ በልላ በኩል ለተጠሪም .00 እንዱከፍል በማድረግ የአመልካችን የኃላፉነት መጠን እስከ ብር 154,951.00 ሉያደርስ የሚችል ዉሳኔ መስጠቱ በግራ ቀኝ መካከል የተደረገዉን የመድን ዉል እንዱሁም የኢንሹራንስ ሰጪዉ ግዳታ የኃላፉነት መጠን በመድን ዉለ ላይ ከተመለከተዉ መብለጥ እንደላለበት በንግድ ህጉ አንቀጽ 665(2) ስር የተመለከተዉን ድንጋጌ ያላገናዘበ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ብለናል። ተከታዩ ተወስኗል።
በጉጂ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 24/09/2009 ዓ.ም ተሰጥቶ በኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 14/02/2010 ዓ.ም በዋለዉ ችልት በትዕዛዝ የፀናዉ ዉሳኔ በፍ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንጽ 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
አመልካች በልላ መዝገብ ላይ በተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረት ለአቶ አርአያ ገ/መድህን የከፈለዉ ብር 54,951.00 ተቀንሶ፣ አመልካች ለተጠሪ ብር 45,049.00 (አርባ አምስት ሺህ አርባ ዘጠኝ ብር) ሉከፍል ይገባል ተብሎል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ጣ/ገብ ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ለተጠሪ ሉከፍል ይገባል ተብል በተወሰነዉ ላይ ብር 54,951.00 ተጨምሮ ብር 85,751.00 (ሰማኒያ አምስት ሺህ ሰባት መቶ ሀምሳ አንድ ብር) ለተጠሪ ይክፈል ብለናል።
የዲኝነት እና ኪሳራ ክፍያን በተመለከተ በስር ፍርድ ቤት የተሰጠ የዉሳኔ ክፍል አልተነካም።
በአጣሪ ችልት ተሰጥቶ የነበረዉ የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
በዚህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ።
No topics extracted.