በንግድ መደብር ውስጥ የሚገኙ ግዙፍነት ያላቸው እንደ መሳሪያዎች፣ የቤት ዔቃዎችና ሸቀጥ ያለ ወ/ሮ እመቤት ዲኛቸው www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XVIII ባለሀብትነትን ንብረቱን በመግዛት ወይም በልላ አኳኃን ያገኘው ወይም በኑዛዜ የተሰጠው ሰው ንብረቱን በእጁ ባደረገው ጊዜ የሚተላለፍለት ስለመሆኑና ተቃራኒ ማስረጃ እስካልቀረበ ድረስ የእነዚሁ ንብረቶች ባለሀብት ስለመሆኑ በሕጉ ግምት የሚወሰድበት ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1186 (1)፤ንግድ ሕጉ በቁጥር እና እነ አቶ ይስማው ዘገየ ( 2 ሰዎች)
No summary available.
መስከረም 23 ቀን 2011 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውልስ ኦርሺሶ አመልካች፡- ወ/ሮ እመቤት ዲኛቸው - ጠበቃ ተፈራ ኢሬንሳ ቀረቡ ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ በተጠሪዎቹ መካከል የነበረው ጋብቻ በፍቺ ውሳኔ መፍረሱን ተከትል የተነሳ የንብረት ክፍፍል ጥያቄን የሚመለከት ክርክር ሲሆን በስር ፍርድ ቤት ጣልቃ ገብ የነበሩት የአሁኗ አመልካች የሰበር አቤቱታቸውን ለዚህ ችልት ያቀረቡት በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ13/10/2009 ዓ.ም.የተሰጠውን ውሳኔ ሽሮ በአንጻሩ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ04/02/2009 ዓ.ም.የተሰጠውን ውሳኔ በማጽናት የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ በ12/04/2010 ዓ.ም. የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉሻር ይገባል በማለት ነው።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በተጠሪዎቹ መካከል የነበረው ጋብቻ በ07/07/2007 ዓ.ም. በተሰጠ የፍቺ ውሳኔ መፍረሱን ተከትል በአቃቂ ቃሉቲ ክፍለ ከተማ በወረዲ 4 ክልል ከቅደስ ሚካኤል መረዲጃ ዔድር በኪራይ በተገኘው ቤት ውስጥ በሚገኙት የመጠጥ ግሮሰሪ ዔቃዎች እና ገቢ የክፍፍል ጉዲይ ላይ ተጠሪዎቹ በክርክር ሂደት ላይ እያለ የአሁኗ አመልካች የንግድ ፈቃደን በስማቸው አውጥተው ስራውን እያከናወኑ የሚገኙበትን ግሮሰሪ ተጠሪዎቹ እንደራሳቸው ንብረት በመቁጠር የራሳቸው ባልሆነ ንብረት ላይ የክፍፍል ጥያቄ ማቅረባቸው ተገቢ አለመሆኑን ገልጸው በግሮሰሪው ላይ የቀረበው የክፍፍል ጥያቄ ውድቅ ይደረግልኝ ሲለ በጉዲዩ ጣልቃ ገብተው ተከራክረዋል።የአመልካቿ እህት የሆኑት 2ኛ ተጠሪ የጣልቃ ገቧን አቤቱታ ደግፈው የተከራከሩ ሲሆን 1ኛ ተጠሪ በበኩላቸው ተጠሪዎቹ ጣልቃ ገቧን ለመርዲት አምጥተው አብረዋቸው ስላደጉ እንደልጃቸው በመቁጠር የንግድ ፈቃደን በስማቸው ከማውጣታቸው ውጪ ጣልቃ ገቧ ግሮሰሪውን ለመቋቋም የሚያስችል የፊይናንስ አቅም የላላቸው መሆኑን፣የግሮሰሪ ዔቃዎቹ የራሳቸው ስለመሆኑም ያቀረቡት ማስረጃ አለመኖሩን ገልጸው የጣልቃ ገብነት አቤቱታው ውድቅ እንዱደረግ የተከራከሩ መሆኑን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።
ፍርድ ቤቱም ክሱን እና የተጠሪዎቹን ምስክሮች ከሰማ በኃላ የግራ ቀኙን አጠቃላይ ክርክር እና ማስረጃ መርምሮ ጣልቃ ገቧ ከተጠሪዎቹ ጋር እንደልጅ ሆነው በጥገኝነት ይኖሩ የነበረ ስለመሆኑ እና ግሮሰሪውን ያቋቋሙት፣ስራውንም ይሰሩ የነበሩት ተጠሪዎቹ ስለመሆናቸው በ1ኛ ተጠሪ ምስክሮች የተገለጸ መሆኑን፣የግሮሰሪው መገልገያ ቁሳቁሶች ከፉልቹ በ1ኛ ተጠሪ ስም፣ደግሞ በ2ኛ ተጠሪ ስም የተገዙ መሆኑን የሚያመለክቱ ደረሰኞች በ1ኛ ተጠሪ በኩል በማስረጃነት የቀረቡ መሆኑን፣ጣልቃ ገቧ የግሮሰሪ ድርጅቱን ያቋቋሙት ከቤተሰብ በተሰጣቸው ገንዘብ ስለመሆኑ ገልጸው የመሰከሩት የ2ኛ ተጠሪ ምስክር የ2ኛ ተጠሪ ወንድም ከመሆናቸውም በላይ ብቸኛ ምስክርም በመሆናቸው ገለልተኛ ናቸው ለማለት የማይቻል መሆኑን፣የንግድ ፈቃደ እና የግብር ደረሰኞቹ በጣልቃ ገቧ ስም መሆኑ ብቻ ግሮሰሪውን በራሳቸው ስም አደራጅተዋል የሚያሰኝ አለመሆኑን ገልጾ የጣልቃ ገቧን ጥያቄ ሙለ በሙለ ውድቅ በማድረግ ውሳኔ ሰጥቶአል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ይህንን ውሳኔ በመቃወም ጣልቃ ገቧ ባቀረቡት ይግባኝ ሳቢያ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የግሮሰሪው ቁሳቁሶች የተሟለት ለጣልቃ ገቧ ከቤተሰብ አንድ ጊዜ ብር ሃያ ሺህ፣ላላ ጊዜ ደግሞ ብር አስራ አምስት ሺህ በተላከ ገንዘብ ስለመሆኑ በጣልቃ ገቧ አንድ ምስክር የተገለጸ መሆኑን፣የዚህን ምስክር ቃል የሚያስተባብል በ1ኛ ተጠሪ በኩል የቀረበ ማስረጃ ሳይኖር እና በ1ኛ ተጠሪ በኩል የተሰሙት ምስክሮች አንዲቸውም 1ኛ ተጠሪ የግሮሰሪ ዔቃዎቹን ገዝተዋል ወይም ሰጥተዋል የሚል ምስክርነት ባልሰጡበት ሁኔታ የጣልቃ ገብነት ጥያቄው ውድቅ የተደረገው አለአግባብ መሆኑን ገልጾ በዚህ ረገድ የተሰጠውን ውሳኔ በመሻር በንግድ መደብር ውስጥ የሚገኙ ዔቃዎች የንግድ በመደብሩ አካል ተደርገው የሚቆጠሩ ስለመሆኑ በንግድ ሕጉ በአንቀጽ 128 የተመለከተ መሆኑ ገልጾ በአቃቂ ቃሉቲ ክፍለ ከተማ በወረዲ 4 ክልል ከቅደስ ሚካኤል ዔድር በመከራየት አመልካች የግሮሰሪ ንግድ የሚያከናውኑበት የንግድ መደብር ዔቃዎች የአመልካች ንብረት ናቸው በማለት ውሳኔ ሰጥቶአል።
በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት 1ኛ ተጠሪ በተራቸው ባቀረቡት ይግባኝ ሳቢያ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ 2ኛ ተጠሪ በክርክሩ መጀመሪያ ላይ ግረሰሪው የጋራ ንብረት መሆኑን ገልጸው ሲከራከሩ ከቆዩ በኃላ የአመልካቿ ነው በማለት መከራከር የጀመሩት የጣልቃ ገብነት ጥያቄው ከቀረበ በኃላ መሆኑን በማከል በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ የተገለጹትን ፍሬ ነገሮች መሰረት አድርጎ በከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠውን ውሳኔ በመሻር በአንጸሩ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተሰጠውን ውሳኔ በማጽናት ውሳኔ ሰጥቶአል።
አመልካች የሰበር አቤቱታቸውን ለዚህ ችልት ያቀረቡት ይዘቱ ከላይ የተመለከተው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ሲሆን የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ ክርክር የተነሳበት ግሮሰሪ የንግድ ፈቃድም ሆነ ግብሩ እንዱሁም የቤት ኪራይ ውለ ጭምር በአመልካች ስም መሆኑ ባልተካደበት ሁኔታ የተደራጀው በተጠሪዎቹ ነው በሚል ብቻ ንብረቱ የተጠሪዎቹ የጋራ ሀብት ነው ተብል የመወሰኑን አግባብነትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ተጠሪዎቹ ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለክርክሩ ከተያዘው ነጥብ አንጻር መርምረናል።
በዚህም መሰረት ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ግሮሰሪ የተቋቋመበትን የንግድ ቤት ኪራይ ውል አከራዩ የተዋዋለው ከአመልካቿ ጋር መሆኑ፣የንግድ ፈቃደ ከጅምሩ የተሰጠው እና ግብሩም የሚከፈለው በአመልካቿ ስም መሆኑ ያከራከረ ጉዲይ አይደለም።በንግድ ሕጉ በቁጥር 127 (2) (ሀ) እና (ለ) ስር የተጠቀሰው የንግድ ቤቱ ስም እና የሚነገድበት የተለየ የንግድ ማስታወቂያ ሰላዲም የሚታወቀው በአመልካቿ ስም ስለመሆኑ በሰበር አቤቱታው የቀረበው የክርክር ነጥብ በ1ኛ ተጠሪ አልተካደም።አግባብነት ባለው ሕግ እና ደንብ መሰረት የንግድ ፈቃድ የሚሰጠውም ፈቃድ ጠያቂው ለንግድ ስራው የሚያስፈልገውን ካፒታል ጨምሮ ተገቢ መስፈርቶችን መሟላቱ ከተረጋገጠ በኃላ እንደሆነ የሚታመን ነው።እነዚህ ሁኔታዎችም አመልካቿ የግሮሰሪ ድርጅቱን እራሳቸውን ችለው ያቋቋቀሙ መሆኑን መገንዘብ የሚያስችለ ናቸው።የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በውሳኔ ላይ እንደገለጸው በንግድ መደብር ውስጥ ግዙፍነት ያለው እንደ መሳሪያዎች፣የቤት ዔቃዎችና ሸቀጥ እንደሚገኙበት በንግድ ሕጉ በቁጥር 128 ተመልክቶአል።እነዚህ የግሮሰሪው መገልገያ ዔቃዎች በሕጉ ግዙፍነት ያላቸው ተንቀሳቃሽ ንብረቶች ተብለው የሚታወቁ ናቸው።
የዚህ ዓይነቶቹ ንብረቶች ባለሀብትነትም ንብረቱን በመግዛት ወይም በልላ አኳኃን ያገኘው ወይም በኑዛዜ የተሰጠው ሰው ንብረቱን በእጁ ባደረገው ጊዜ የተላለፈለት እንደሚሆን በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1186 (1) ስር ተመልክቶአል።አመልካቿ እነዚህን ንብረቶች በስማቸው በሚታወቀው የግሮሰሪ የንግድ መደብር ውስጥ ይዘው መገኘታቸው ተቃራኒ ማስረጃ እስካልቀረበ ድረስ የእነዚሁ ንብረቶች ባለሀብት ስለመሆናቸው በሕጉ ግምት የሚወሰድበት ነው።2ኛ ተጠሪ ከስር ጀምሮ የአመልካቿን አቋም ደግፈው የሚከራከሩ መሆኑን የመዝቡ ግልባጭም ሆነ የሰበር ክርክራቸው ያመለክታል።አመልካቿ የጣልቃ ገብነት ጥያቄ ከማቅረባቸው አቀድሞ 2ኛ አመልካች ግሮሰሪው የጋብቻ ውጤት መሆኑን አምነው የክፍፍል ጥያቄ አቅርበው ነበር መባለwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ብቻውን የክርክር አቋማቸውን የቀየሩት እህታቸው የሆኑትን አመልካች አለአግባብ ለመጥቀም በማሰብ ነው ከሚል ድምዲሜ ላይ ለመድረስ የሚያስችል አይደለም።
ከስር ጀምሮ አመልካቿን በመቃወም በመከራከር ላይ የሚገኙት 1ኛ ተጠሪ በተመሳሳይ ስያሜ የሚታወቁ ዔቃዎች የተገዙባቸውን ደረሰኞች በማስረጃነት ከማቅረብ በቀር ዔቃዎቹን በራሳቸው ገንዘብ ገዝተው ወደ ግሮሰሪው ያስገቡት እራሳቸው ስለመሆናቸው ያስረደ ስለመሆኑ የመዝገቡ ግልባጭ አያመለክትም።በዚህ አግባብ ካላስረደ ደግሞ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንደገለጸው የዔቃዎቹ ባለሀብት አመልካች ስለመሆናቸው በሕጉ የሚወሰደውን ግምት አስተባብለዋል ልባል አይችልም።በ1ኛ ተጠሪ ምስክሮች በተነገረው መሰረት በግሮሰሪው ውስጥ ይሰሩ የነበሩት ተጠሪዎች መሆናቸው ብቻውን ግሮሰሪው የእነርሱ ነው ከሚል ድምዲሜ ላይ ለመድረስ የሚያስችል አይደለም።የንግድ ቤቱ ኪራይ፣የንግድ ፈቃደ እና ላልችም ባለሀብትነትን የሚያመለክቱ መሰረታዊ ጉዲዮች በአመልካቿ ስም እንዱሆን ያደረግነው ባለን ቤተሰባዊ ግንኙነት ነው ከማለት በቀር እንደክርክራቸው ግሮሰሪው የተቋቋመበት የገንዘብ ምንጭ ሙለ በሙለ የእነርሱ ከሆነ ግሮሰሪው ከተጋቢዎቹ በአንዲቸው ስም እንዱቋቋም ለማድረግ ያልቻለበት አሳማኝ እና ሕጋዊ እና ምክንያት ስለመኖሩ 1ኛ ተጠሪ ከስር ጀምሮ ያቀረቡት ክርክር የለም።በመሆኑም በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተደረሰበት እና በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ተቀባይት ያገኘው ድምዲሜ በክርክሩ የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮች እና ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸውን የሕግ ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገ ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም።
ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቶአል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የሰጠው ውሳኔ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 348 (1) መሰረት ተሽሯል።
የተሰጠው ውሳኔ ፀንቶአል።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
እንዱያውቁት የውሳኔው ቅጂ ለስር ፍርድ ቤቶች ይላክ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቶአል።
ቅ/ሀ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት።
No topics extracted.