አንድ የንግድ ምልክት አንድ ዓይነት ወይም ተመሳሳይ የሆኑ የላላ ዔቃዎችን አገልግልችን በሚመለከት በሚገባ በሚታወቅ ወይም ኢትዮጵያ ዉስጥ ግልጋልት ላይ ከዋለ የንግድ ምልክት ጋር አንድ ዓይነት ወይም ሉያሳስት በሚችል ደረጃ ተመሳሳይ ከሆነ ወይም ትርጉሙን ከያዘ መመዝገብ የላለበት ስለመሆኑ የንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 501/1998 አንቀጽ 7(2)፤ 36(1)
No summary available.
ቀን - 21/09/2010 ዳኞች፡- ተኽሉት ይመሰል ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራዉ አብዬ ካሳሁን አመልካች፡- ደርሂም ኢንደስትሪስ ካምፓኒ ሉሚትድ-ጠበቃ አብደላ አሉ ቀረቡ ተጠሪ፡- አሁጃን ኢንደስትሪስ -ጠበቃ ያሬድ ለገሰ ቀርበዋል **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል
**
ጉዲዩ የንግድ ምልክት ፈራሽ ላሆን ስለሚችልበት ሁኔታን የሚመለከት ነዉ።
ክርክሩ የተጀመረዉ በኢፋዱሪ የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ሲሆን፣ ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
ተጠሪ ለጽ/ቤቱ ያቀረበዉ አቤቱታ ይዘትም በአጭሩ፡- ለፍራፍሬ መጠጦችና ጭማቂዎች ወዘተ የሚያገለግለዉና በስሙ ተመዝግቦ የሚታወቀዉን RANI የሚባለዉን የንግድ ምልክት በንግድ ምልክት እና ምዝገባ ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 501/1998 አንቀጽ 36 ስር የተመለከቱትን የምዝገባ መስፈርት ከመሰረቱም ባልተሟላበት ሁኔታ በተከሳሽ ስም መመዝገቡ ተገቢ ባለመሆኑ ፈራሽ ላሆን ይገባል ሲል ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነዉ። አመልካች በበኩለ የመጀመሪያ መቃወሚያዎች ናቸዉ የሚላቸዉን ክርክሮች በማስቀደም፣ ከፍሬ ነገር ጋር በተያያዘም የንግድ ምልክቱ በከሳሽ ስም ተመዝግቦ የነበረ ቢሆንም በወቅቱ ባለማደሱ ምክንያት መብቱና ማጣቱን፤ በተከሳሽ ስም ሉመዘገብwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የቻለዉም በአዋጅ ቁጥር 501/1998 ተፈቅድለት መሆኑን ጠቅሶ ሉሰረዝ አይገባዉም በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩ የቀረበለት ጽ/ቤትም በዚህ መልኩ ከግራ ቀኝ የቀረበዉን ክርክር መሰረት የቀረቡትን ማስረጃዎች በመመርመር እንዱሁም አስፈላጊዉን የማጣሪያ ጥናት ማድረጉን ጠቅሶ በንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 501/1998 አንቀጽ 7(2) እና 36 መሰረት ለአመልካች ለመጀመሪያ ጊዜ የተመዘገበዉ RANI የንግድ ምልክት ምዝገባ መጀመሪያዉንም ቢሆን በሦስተኛ ወገን የቅድሚያ መብት ምክንያት ሉመዘገብ የማይገባ ስለመሆኑ ፈራሽ ነዉ በማለት ወስኗል። አመልካች ይህን ዉሳኔ ባለመቀበል ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረበ ቢሆንም ከፍተኛ ፍርድ ቤቱም የጽ/ቤቱን ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበዉም በዚህ ዉሳኔ ላይ ቅር በመሰኘት ሲሆን፣ አመልካች በቀን 08/10/09 ዓ.ም ተዘጋጅቶ በጠበቃዉ አማካይነት በቀረበ 4 ገጽ የሰበር አቤቱታ በአዋጁ መሰረት በስሙ ተመዝግቦ የሚገኘዉ RANI የንግድ ምልክት እንዱሰረዝ በሚል በጽ/ቤቱ ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፀንቶ የተወሰነዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ የሚልባቸዉን ምክንያቶች በመዘርዘር ታርሞ ይወሰንለት ዘንድ ዲኝነት ጠይቋል። አቤቱታዉ ተመርምሮ ያስቀርባል በመባለም ተጠሪ በተደረገለት ጥሪ መሰረት ቀርቦ ግራ ቀኝ ክርክራቸዉን በጽሐፍ ተለዋዉጠዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተመለከተዉ ነዉ። እኛም በአመልካች ስም የተመዘገበዉ የንግድ ምልክት እንዱሰረዝ በሚል የተሰጠዉን ዉሳኔ አግባብነት ከግራ ቀኝ ክርክር እንዱሁም ስለጉዲዩ ከሚደነግጉ ህጎች አንፃር መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምረናል። ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለዉ ራኒ (RANY) የንግድ ምልክት በአመልካች ስም በ22/01/99 ዓ.ም ከመመዝገቡ በፉት በተጠሪ ስም ከ16/11/80 ዓ.ም እስከ 16/10/86 ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ አእምሯዊ ጽ/ቤት ተመዝግቦ የነበረ ስለመሆኑ አመልካች አይክድም። አመልካች ይህን ሳይክድ የንግድ ምልክቱ በተጠሪ ጥያቄ ምክንያት ሉፈርስ አይገባዉም በማለት አጥብቆ ከሚከራከርባቸዉ ነጥቦች ዉስጥ አንደ የንግድ ምልክቱ በተጠሪ ስም ቢመዘገብም በወቅቱ ባለመታደሱ ተጠሪ መብቱን አጥቷል በማለት ሲሆን፤ ተጠሪ በበኩለ ምዝገባዉ ከመሰረቱም ስለ 3ኛ ወገኖች የቅድሚያwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
መብት በተመለከተ በአዋጅ ቁጥር 501/98 አንቀጽ 7(2) ስር የተመለከተዉን ድንጋጌ የማያሟላ መሆኑን በመግለጽ እንዱፈርስ መወሰኑ በአግባቡ ነዉ በማለት ይከራከራል።
በመሰረቱ የኢፋዱሪ አእምሯዊ ጽ/ቤት አንድን የንግድ ምልክት ከመመዝገቡ በፉት ማጣራት የሚገባቸዉን ሁኔታዎች አዋጁ በአንቀጽ 6 እና 7 ስር የሚደነግግ ሲሆን፣ አስፈላጊ ሁኔታዎችን ከመሰረቱ ሳያሟላ የተደረገ ምዝገባ ፈራሽ ላደረግ እንደሚገባዉም የአዋጁ አንቀጽ 36(1) ድንጋጌ ያስገነዝባል። ለተያዘዉ ጉዲይ አግባብነት ያለዉ የአዋጁ ድንጋጌ በአንቀጽ 7(2) ስር የተመለከተዉ ነዉ። በዚህ ድንጋጌ መሰረት የንግድ ምልክቱ አንድ ዓይነት ወይም ተመሳሳይ የሆኑ የላላ ዔቃዎችን አገልግልቶችን በሚመለከት በሚገባ በሚታወቅ ወይም ኢትዮጵያ ዉስጥ ግልጋልት ላይ ከዋለ የንግድ ምልክት ጋር አንድ ዓይነት ወይም ሉያሳስት በሚችል ደረጃ ተመሳሳይ ከሆነ ወይም ትርጉሙን ከያዘ መመዝገብ የለበትም። ከዚህ አንፃር ሲታይ በተጠሪ ስም የሚታወቅ ራኒ (RANY) የንግድ ምልክት ምርት ወደ አገር ዉስጥ መግባት ከጀመረ ረጅም ጊዜ እንዲስቆጠረና ምርቶቹም የአመልካች እንደሆኑ ጽ/ቤቱ በአዱስ አበባ የተለያዩ የገበያ ማዔከላት እንዱሁም ድሬዲዋን ጨምሮ በላልችም ከተሞች ባደረገዉ ጥናት ያረጋገጠ መሆኑን ተገንዝበናል። ይህም ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ የንግድ ምልክት በተጠሪ የሚታወቅ መሆኑን የሚያሳይ ነዉ። በመሆኑም ራኒ (RANY) የሚባል የንግድ ምልክት ከመሰረቱም በአመልካች ስም የተመዘገበዉ በአዋጅ ቁጥር 501/98 አንቀጽ 7(2) ስር የተመለከቱትን ሁኔታዎች ሳያሟላ በመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 36(1) መሰረት በተጠሪ ጥያቄ መሰረት እንዱፈርስ መደረጉ በአግባቡ ነዉ። ከዚህ አንፃር ሲታይ በኢፋዱሪ የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጸንቶ የተወሰነዉ ዉሳኔ ከፍ ሲል የተመለከቱትን የአዋጁን ድንጋጌዎች የተከተለ ነዉ ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ስላልተገኘ ተከታዩ ተወስኗል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ቁ/174339 በቀን 14/07/09 ዓ.ም በዋለዉ ችልት፣ በኢፋዱሪ የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት የሰጠዉን ዉሳኔ በማጽናት፣ የሰጠዉ ፍርድ በፍ/ሥ/ሥ/ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ።