No summary available.
መጋቢት 25 ቀን 2010 ዓ/ም ዳኞች፡- ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ ፈይሳ ወርቁ ጰውልስ ኦርሺሶ አመልካች፡- በሰሜን ወል ዞን የቆቦ ጊራና ሸለቆ ልማት ፕሮግራም-የቀረበ የለም።
ተጠሪዎች፡-
2 አቶ ወንድወሰን ተፈራ 3 አቶ ተስፊየ ጭቋላ በላለበት የታየ ነው።
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
የነገሩ አመጣጥ ተጠሪዎች ያለአግባብ እንዱከፈል ያደረጉትን ገንዘብ እንዱከፍለ ተብል የቀረበ ጉዲይ ነው። ክርክሩ የጀመረው በሰሜን ወል መስተዲደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። የአሁን ተጠሪዎች የሥር ከ1ኛ እስከ 3ኛ የተጠቀሱ ተከሳሾች ናቸው። በሥር ፍርድ ቤት የአሁን አመልካች የአሁን ተጠሪዎችን ጨምሮ በ16 ተከሳሾች ላይ ከስ ያቀረበባቸው ሲሆን 25 ጣልቃ ገቦች ወደ ክርክሩ በመግባት ተከራክረዋል። የአሁን አመልካች /የሥር ከሳሽ/ በቀን 23/12/2005 ዓ/ም ጽፍ ባቀረው ክስ የአሁን 1ኛ ተጠሪ የአመልካች ፕሮጀክት ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ፣ የአሁን 2ኛ ተጠሪ የመስኖ ልማት ዋና የሥራ ሂደት መሪ እና የአሁን 3ኛ ተጠሪ ደግሞ የግዢ፣ ፊይናንስ፣ ንብረት እና የሰው ኃይል አስተዲደር ደጋፉ የሥራ ሂደት መሪ ሆነው ሲሰሩwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ከግዢ መመሪያና ደንብ ውጪ ለ6 ሞተር ሳይክልች ግዢ ብር 158,850 እንዱከፈል በማድረጋቸው፣ ለባለሙያዎች ለሥልጠናና ለትምህርታዊ መስክ ጉብኝት ለአንድ ሰራተኛ በቀን የሚከፈለው ብር 70 ሆኖ እያለ በቀን ብር 200 የውል አበል ለ56 ቀን ብር 47,580 ያለአግባብ እንዱከፈል በማድረጋቸው፣ መልቀቂያ ተሰጥቶ የተሰናበተውን አንድ ሰራተኛ ያለ ምንም ማስታወቂያ በድጋሚ እንዱቀጠር በማድረግ ለሶስት ወር ብር 2,562 እንዱከፈል በማድረጋቸው፣ በ1994 ዓ/ም በወጣው የጽ/ቤቱ የሰራተኞች መተዲደሪያ ማኑዋል መሰረት ጊዜያዊ የቅጥር ሰራተኛ የሥራ ስንብት ክፍያ የሚከፈለው የሥራ ውለ ሲቋረጥ ብቻ መሆኑ በግልጽ ተደንግጎ እያለ ተከሳሾች /ተጠሪዎች/ ግን ለ17 የጽ/ቤቱ ሰራተኞች ከጊዜያዊ ወደ ቋሚ ቅጥር ተሸጋግረው የተሻለ ጥቅም አግኝተው እያለ ከሥራ እንደተሰናበቱ በመቁጥር ለአገልግልት ካሳ ክፍያ በማለት በድምሩ ብር 17,588.02 /አስራ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ሰማኒያ ስምንት ብር ከዜሮ ሁለት ሳንቲም/ ያለአግባብ እንዱከፈል በማድረጋቸው እንዱሁም ላልችንም የማይገቡ ክፍያዎችን እንዱከፈለ በማድረግ ሥልጣናቸውን ያለአግባብ በመጠቀምና ተገቢ ያልሆነ አሰራር በመሥራት የመንግሥት ገንዘብ እንዱከፈል በማድረጋቸው በወንጀል ተከሰው መቀጣታቸውን ገልጾ በድምሩ ብር 368,335.97 /ሶስት መቶ ስልሳ ስምንት ሺህ ሶስት መቶ ሰላሳ አምስት ብር ከዘጠና ሰባት ሳንቲም/ በነጠላ እና በአንድነት እንዱከፍለ እንዱወሰንባቸው ዲኝነት ጠይቋል።
የአሁን ተጠሪዎችም ለቀረበባቸው ክስ መልሳቸውን በጽሁፍ አቅርበው የተከራከሩ ሲሆን የደቡብ ወል መስተዲደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን መርምሮ በመ/ቁ. 09881 በሆነው በቀን 8/02/2008 ዓ/ም በዋለው ችልት የአሁን ተጠሪዎችን ኃላፉ በማድረግ ብር 350,777.75 /ሶስት መቶ አምሳ ሺህ ሰባት መቶ ሰባ ሳባት ብር ከሰባ አምስት ሳንቲም/ እንዱከፍለ ውሳኔ የሰጠ ሲሆን ለ17 ሰራተኞች የተከፈለውን ብር 17,588.02 /አስራ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ሰማኒያ ስምንት ብር ከዜሮ ሁለት ሳንቲም/ በተመለከተ ሰራተኞቹ በክርክሩ ጣልቃ ገብተው ለመከራከር በጠየቁት መሰረት ወደ ክርክሩ በመግባት አምነው የተከራከሩ በመሆናቸው ለአሁን 2ኛ እና ለ3ኛ ተጠሪዎች እንዱመልሱ ካለ በኃላ በዚህ ረገድ ከቀረበባቸው ክስ ተጠሪዎችን ከኃላፉነት ነፃ በማድረግ ወስኗል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የአሁን አመልካች ጊዜያዊ የቅጥር ሰራተኛ የሥራ ስንብት ክፍያ የሚከፈለው የሥራ ውለ ሲቋረጥ ብቻ ሆኖ እያለ አስራ ሰባቱ ሰራተኞች ከጊዜያዊ ቅጥር ወደ ቀሚ ተሸጋግረው የተሻለ የኢኮኖሚ ዋስትና አግኝተው እያለ የአገልግልት ካሳ በሚል ብር 17,558.02 /አስራ ሰባት ሺህ አምስት መቶ አምሳ ስምንት ብር ከዜሮ ሁለት ሳንቲም/ ያለአግባብ እንዱከፈል በማድረጋቸው ተጠሪዎች በወንጀል ተከሰው ጥፊተኛ ተደርገው ተቀጥተው እያለ የሥር ፍርድ ቤት ይህንን ሳይወስን በዝምታ ያለፈው ያለአግባብ ነው በማለት ለአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርቧል።
የይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍርድ ቤትም የሥር ፍርድ ቤት የሥር ጣልቃ ገቦች ያመኑትን የሥራ ስንብት ክፍያ ለ2ኛ እና 3ኛ መልስ ሰጪዎች /ለአሁን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች/ እንዱመልሱ ወስኖ መልስ ሰጪዎችን /ተጠሪዎችን/ ከኃላፉነት ነፃ ማድረጉ ስህተት ቢሆንም ቅሬታ የቀረበበትን ገንዘብ የሥር ጣልቃ ገቦች የወሰደና የተጠቀሙበት መሆኑ በክርክር ሂደት የተረጋገጠ በመሆኑ ይግባኝ ባይ/አመልካች/ ሉጠይቅ የሚችለው ጥቅም ከመልስ ሰጪዎች /ከአሁን ተጠሪዎች/ ጋር የሚገኝ ባለመሆኑ በውጤት ደረጃ የቀረበውን የይግባኝ አቤቱታ አልተቀበልነውም በማለት በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 337 መሰረት ዘግቶበታል።
አመልካች ውሳኔውንም ሆነ ትዔዛዙን ቅር በመሰኘት ለአማራ ብሓራዊ ክልላዊ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ አቅርበው በቀረበው ጉዲይ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሟል ለማለት አልተቻለም በማለት አቤቱታውን ሰርዞበታል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ውሳኔውን ለማስለወጥ ሲሆን የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም፡- ተጠሪዎች ሥልጣናቸውን ያለአግባብ ተጠቅመው በፕሮጀክቱ ላይ ያደረሱትን ኪሳራ ከህጋዊ ወለድ ጋር እንዱከፍለ በቀረበው ክስ መሰረት በማስረጃ ተረጋግጦ እያለና በ1994 ዓ/ም በወጣው የፕሮጀክቱ ሰራተኞች መተዲደሪያ ደንብ አንቀጽ 17 (5) መሰረት ጊዜያዊ የቅጥር ሰራተኞች የሥራ ስንብት ክፍያ መፈጸም ያለበት የሥራ ውል ሲቋረጥ ብቻ መሆኑ በግልጽ ተደንግጎ እያለ ተጠሪዎች ግን በ23/03/1999 ዓ/ም በቃለ ጉባዓ የጽ/ቤቱ 17 ሰራተኞች ከጊዜያዊ ቅጥር ወደ ቋሚ ተሸጋግረውና የተሻለ የሥራ ዋስትና አግኝተው እያለ ከስራ እንደተሰናበቱ በመቁጥር የአገልግልት ከሳ ክፍያ በማለት በድምሩ ብር 17,558.02 /አስራ ሰባት ሺህ አምስትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
መቶ አምሳ ስምንት ብር ከዜሮ ሁለት ሳንቲም/ የመንግሥት ገንዘብ ያለአግባብ እንድከፈል በማድረጋቸው በኢትዮጵያ ፋዳራላዊ ዱሞክራሲያዊ ሪፐብላክ የወንጀል ህግ አንቀጽ 407 /2/ መሰረት በሰሜን ወል ዞን ክፍተኛ ፍርድ ቤት በወንጀል ተከሰው ጥፊተኝነታቸው ተረጋግጦ ቅጣት ተወስኖባቸዋል። ህግን በመተላለፍ በአመልካች ፕሮጀክት ላይ ያለአግባብ ገንዘብ እንድከፈል አዘው ላደረሱት ጉዲት በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 2035 በጥፊት ላይ የተመሰረተ ውል ሳይኖር ኃላፉነት ያለባቸው በመሆኑና ያለአግባብ የተከፈለ ብር ፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በ
በተመሳሳይ ጉዲይ ላይ የሰጠውን አስገዲጅ የህግ ትርጉም የተላለፈና መሰረታዊ የህግ ጥሰት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱሻርልን እንጠይቃለን የሚል ነው።
የሰበር አቤቱታውን አጣሪው መርምሮ አመልካች በተጠሪዎች ላይ በመሰረቱት ክስ በ1994 ዓ/ም በወጣው የአመልካች ጽ/ቤት የሰራተኞች መተዲደሪያ ማኑዋል መሰረት ጊዜያዊ የቅጥር ሰራተኛ የሥራ ስንብት ክፍያ የሚከፈለው የሥራ ውለ ሲቋረጥ ብቻ መሆኑ በግልጽ ተደንግጎ እያለ ለ17 የጽ/ቤቱ ሰራተኞች ከጊዜያዊ ወደ ቋሚ ቅጥር ተሸጋግረው የተሻለ ጥቅም አግኝተው እያለ ከሥራ እንደተሰናበቱ በመቁጥር የአገልግልት ካሳ ክፍያ በማለት በድምሩ ብር 17,558.02 /አስራ ሰባት ሺህ አምስት መቶ አምሳ ስምንት ብር ከዜሮ ሁለት ሳንቲም/ ያለአግባብ እንዱከፈል በማድረጋቸው በወንጀል ተከሰው ተቀጥተዋል። ይህን ገንዘብ በአንድነትና በነጠላ ይክፈለን በማለት አመልካች ባቀረበው የዲኝነት ጥያቄ ላይ ሥር ፍርድ ቤት በፍርደ ላይ ያለአግባብ የካሳ ክፍያ የወሰደ ጣልቃ ገቦች ይህን አምነዋል። ያመኑትን ገንዘብ ለአሁን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ሉከፍለ ይገባል በማለት የአመልካችን የዲኝነት ጥያቄ የማለፈን አግባብነት ለመመርመር ሲባል አቤቱታው ለሰበር ሰሚ ችልት ይቅረብ ሲል ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎላቸው የአሁን 1ኛ ተጠሪ ቀርበው በቀን 26/05/2009 ዓ/ም የተጻፈ መልስ አቅርበው የተከራከሩ ሲሆን 1ኛ ተጠሪ ላቀረቡት መልስ የአመልካች ወኪል የሆነው የክልለ ዐቃቤ ህግ በቀን 11/07/2009 ዓ/ም የመልስ መልስ አቅርቧል።
የአሁን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በአዱስ ዘመን ጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ባለመቅረባቸው ሰኔ 7 ቀን 2009 ዓ/ም በዋለው ችልት መልስ የመስጠት መብታቸው እንዱታለፍ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የነገሩ አመጣጥና የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተመለከተውን የሚመስል ሲሆን ተጠሪዎች ለ17 ሰራተኞች እንዱከፈላቸው ያደረጉትን ብር 17,558.02 /አስራ ሰባት ሺህ አምስት መቶ አምሳ ስምንት ብር ከዜሮ ሁለት ሳንቲም/ እንዱመልሱ ይገባል ወይስ አይገባም? የሚል ጭብጥ ተይዞ ጉዲዩ እንደሚከተለው ተመርምሯል። የሰበር አቤቱታ የቀረበበትን ገንዘብ ለአስራ ሰባቱ ሰራተኞች እንዱከፈል ማድረጋቸው መመሪያው የጊዜያዊ ሰራተኛ የቅጥር ውል ሲሰረዝ ተገቢውን ጥቅማ ጥቅም ሰራተኛው ያገኛል ስለሚል በመመሪያው መሰረት የተፈጸመ ነው በማለት የአሁን ተጠሪዎች በሥር ፍርድ ቤት ተከራክረዋል።
አመልካች አጥብቆ የሚከራከረው በ1994 ዓ/ም የወጣው የፕሮጀክቱ ሰራተኞች መተዲደሪያ ደንብ አንቀጽ 17 (5) መሰረት ጊዜያዊ የቅጥር ሰራተኞች የሥራ ስንብት ክፍያ መፈጸም ያለበት የሥራ ውል ሲቋረጥ ብቻ መሆኑ በግልጽ ተደንግጎ እያለ ተጠሪዎች ግን በ23/03/1999 ዓ/ም በቃለ ጉባዓ የጽ/ቤቱ 17 ሰራተኞች ከጊዜያዊ ቅጥር ወደ ቋሚ ተሸጋግረውና የተሻለ የሥራ ዋስትና አግኝተው እያለ ከስራ እንደተሰናበቱ በመቁጥር የአገልግልት ከሳ ክፍያ እንዱከፈል ማድረጋቸው ህግን የጣሰ ተግባር ስለሆነ ለሰራተኞቹ ያለአግባብ እንዱከፈላቸው ያደረጉትን ገንዘብ ሉመልሱ ይገባል በማለት ነው።
ይህ የተጠቀሰው መመሪያ ቁጥር 17/5/ ለጊዜያዊ ሰራተኞች የሥራ ስንብት እንዱከፈል የሚፈቅደው ከሥራቸው የተሰናበቱ እንደሆነ ነው። የዚህ መመሪያ ቁጥር 17/5/ ዓላማም ሰራተኞቹ ከሥራ ከተሰናበቱ በኃላ የሚገጥማቸውን የኢኮኖሚ ችግር ለማቃለል ታስቦ እንደሆነ መገመት ይቻላል። ሰራተኞቹ ግን በአመልካች ድርጅት ውስጥ በጊዜያዊነት ይሰሩ ከነበረበት በቋሚነት ተቀጥረው እንዱሰሩ ሲደረግ የሥራ ስንብት እንዱከፈላቸው ማድረግ የመመሪያውን ዓላማና መንፈስ የተከተለ ሆኖ አላገኘነውም። ይህ በእንዱህ እንዲለ ተጠሪዎቹ በዚህ እና በላልችም በፈጸሙዋቸው ድርጊት በወንጀል ተከሰው ጥፊተኛ ተደርጎው ቅጣት ተወስኖባቸዋል። ይህ የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ ለፍትሐብሕር ክርክር ደግሞ በማስረጃነት ቀርቧል። ይህም ማስረጃ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በ
ላይ ከሰጠውwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
አስገዲጅ የህግ ትርጉም አንጻር ላታይ የሚገባው ነው። የሥር ፍርድ ቤቶችም የተያዘውን ጉዲይ ከዚህ አንጻር ያለመመልከታቸው ሲታይ ተገቢ ሆኖ አልተገኘም፡፤
በመጨረሻም የሥር ፍርድ ቤቶች የሥር ጣልቃ ገቦች የሆኑት አስራ ሰባቱ ሰራተኞች ለዚህ የሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነውን ገንዘቡ መወሰዲቸውን ባመኑት መሰረት ለአሁን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች እንዱመልሱ ሲል የሰጠው ውሳኔ ግልጽ ባይሆንም ተጠሪዎች የአመልካች ድርጅት ገንዘብ ከህግ አግባብ ውጪ እንዱከፈል በማድረጋቸው በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 2035 መሰረት ተጠያቂነት አለባቸው። ስለሆነም ተጠሪዎች ተጠያቂነት የለባቸውም ተብል የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ቀጥል ያለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
የደቡብ ወል መስተዲደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.09881 በቀን 08/02/2008 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ፣ የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፍ/ይ/መ/ቁ. 01-03596 በ10/06/2008 ዓ/ም እንዱሁም የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ቁ. 03-14560 ሐምል 6 ቀን 2008 ዓ/ም የሰጡት ትዕዛዝ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 348 /1/ መሰረት ተሽሯል።
ለአስራ ሰባቱ ሰራተኞች ያለአግባብ የተከፈለውን ብር 17,558.02 /አስራ ሰባት ሺህ አምስት መቶ አምሳ ስምንት ብር ከዜሮ ሁለት ሳንቲም/ የአሁን ተጠሪዎች በነጠላና በአንድነት ለአመልካች ሉከፍለ ይገባል ተብል ተወስኗል።
ተጠሪዎች ለአመልካች የከፈለትን ገንዘብ ከአስራ ሰባቱ ሰራተኞች ላይ የመጠየቅ መብታቸውን ይህ ውሳኔ አይከለክልም ብለናል።
የዚህን ችልት ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
የውሳኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይድረሳቸው።
ጉዲዩ ውሳኔ ስላገኘ መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡
No topics extracted.