የአካል ጉዲት ካሳ በርትዔ ሲወሰን ባጠቃላይ የተጎጂው የመስራት አቅሙ ላይ የደረሰውን የጉዲት መጠን መነሻ በማድረግ አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታዎች በተጎጂው የወደፉት ህይወት ላይ ሉያስከትለ ስለሚችለት አለታዊ ተጽእኖ፤ ወቅታዊ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ እድገት እና ተጨባጭ የገንዘብ /ብር/የመግዛት አቅም በየጊዜው እየቀነሰ መሄደ፤ ወደፉት ሉታጣ የሚችለው ገቢ ከተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር ተገናዝቦ መታየት ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2091 እና 2102 እና 2153(ሀ))
No summary available.
ግንቦት 17 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች፡- ፀጋይ አስማማው አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ አመልካች፡- ወ/ሮ ሚሚ አበበ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ታምራት /ማሙሽ/ ባልቻ - ታልፎል **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ ጉዲይ ክርክሩ በተጀመረበት በምንጃር ወረዲ ፍርድ ቤት ከሳሽ የነበሩት የአሁኗ አመልካች ሲሆኑ ተከሳሽ ደግሞ የአሁኑ ተጠሪ ነበሩ። የአመልካች የክስ ይዘትም ባጭሩ፡- ተጠሪ በቆንጨራ የቀኝ እጃቸውንና የቀኝ ጭንቅላቸውን በመምታት የቀኝ እጃቸው መዲፍ ማጠፉያ አንጓ እንዱቆረጥ በማድረጋቸው በከባድ የሰው መግደል ሙከራ ወንጀል ተከሰው በፍርድ ቤት በተሰጠው ውሳኔ ጥፊተኛ ተብለው የተቀጡ መሆኑን፣ በዚህ የወንጀል ድርጊት በደረሰባቸው የአካል ጉዲት ምክንያትም ስራ ሰርተው ያገኙት የነበረው ገቢ የቀረባቸውና ስራ ስርተው መኖርም ያልቻለ መሆኑን ጠቅሰው ብር 300,000.00(ሶስት መቶ ሺህ ብር) ካሳ እንዱከፈላቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት የተጠየቀበት መሆኑን የሚያሳይ ነው።
የአሁኑ ተጠሪም በሕጉ አግባብ ተጠርተው ባለመቅረባቸው ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ የተደረገ ሲሆን የሥር ፍርድ ቤትም ተገቢ ናቸው ያላቸው የአመልካች እድሜና የገቢ መጠን በማስረጃ እንዱጣሩ ለማድረግ ማስረጃዎቹ ከሚመለከታቸው አካላት እንዱቀርቡwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በማለት ትዕዛዝ ሲስጥ ቆይቶ የአመልካች ጠበቃ ተገቢውን ሉፈጽሙ ባለመቻላቸው በዚህ ረገድ ማስረጃዎችን ያልሰማ ሲሆን በኃላፉነት ረገድ ግን በተጠሪው ላይ በወንጀል ጉዲይ በፍርድ ቤት የተሰጠውን የጥፊተኝነት ውሳኔ መሰረት አድርጎ ተጠሪን ለክሱ ኃላፉ ያደረገ ሲሆን ካሳውን በተመለከተ የአመልካች ጠበቃ በርትዔ እንዱወሰን ያቀረቡትን ጥያቄ ካሳ በርትዔ የሚወሰነው በልዩ ሁኔታ በመሆኑ ተቀባይነት እንደላለውና አመልካችም በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2141 አግባብ የካሳ መጠኑን ለማስረዲት ያልቻለ መሆኑን ጠቅሶ ለአካል ጉዲት የተጠየቀውን ካሳ በማለፍ የሞራል ጉዲት ካሳ ብቻ ብር 1000.00(አንድ ሺህ ብር) አመልካች እንዱከፈላቸው በማለት ወስኖአል። በዚህ ውሳኔ የአሁኗ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበውም ተጠሪ በህጉ አግባብ ተጠርተው ባለመቅረባቸው ጉዲዩ ተጠሪ በላለበት እንዱታይ ከተደረገ በኃላ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን መርምሮ የስር ፍርድ ቤት የጉዲት ካሳ መጠኑ በርትእ ሉወሰን የሚችል አይደለም በማለት የደረሰበትን ድምዲሜ ተገቢነት የላለው መሆኑን ጠቅሶ የአካል ጉዲት ካሳውን በርትእ አስልቶ ብር 40,000.00(አርባ ሺህ ብር) በማድረግ ወስኖአል። ከዚህም በኋላ አመልካች የሰበር አቤቱታቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። አመልካች የአሁኑን የሰበር አቤቱታውን ያቀረቡትም በአካል ጉዲት ካሳ መጠን አወሳሰን ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞአል በማለት ሲሆን አቤቱታቸው ተመርምሮም የካሳ መጠኑ አወሳሰኑን ተገቢነት ለመመርመር ተብል ለዚህ ችልት እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸውም ባለመቅረባቸው መልስ በጽሐፍ የመስጠት መብታቸው ታልፎል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ለክርክሩ በተያዘው ጭብጥ መሰረት ጉዲዩን እንደሚከተለው ተመልክተናል።
በመሰረቱ በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 14 ሥር “ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሰስ በህይወት የመኖር፣የአካል ደህንነትና የነፃነት መብት አለው” ተብል የተቀመጠ ሲሆን አንቀጽ 16 የአካል ደህንነት መብት ምን እንደሆነ ያብራራል።
ማንኛውም ሰው በአካለ ላይ ጉዲት እንዲይደርስበት የመጠበቅ መብት እንዲለው የሃገሪቱ የበላይ ሕግ ያስገነዝባል። መንግስትም ሆነ ማንኛውም ሰው የላላውን ሰው የአካልwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ደህንነት የመጠበቅ የሕግ ግዳታ አለበት። ይህን ህግ በመተላለፍ በሰው አካል ላይ ጉዲት ማድረስ በወንጀል የሚያስቀጣ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ለደረሰው የአካል ጉዲት ተጏጂው ካሳ የማግኘት መብት ይኖረዋል። በህገ-መንግስቱ የተቀመጠው ይህን የሰብአዊ መብት ከሚያረጋግጡ ዝርዝር ሕጏች ውስጥ በፍ/ሕጉ ውስጥ የጉዲት ካሳን አስመልከቶ የተቀመጡት ድንጋጌዎች ይገኙበቸዋል። በዚህም መሰረት አንድ ሰው በጥፊቱ በልላ ሰው ላይ ጉዲት ካደረሰ ላደረሰው ጉዲት ኃላፉ ሆኖ ካሳ ሉከፍል እንደሚገባ የፍ/ሕ/ቁ.
2028 አስቀምጧል። በመሆኑም በመርህ ደረጃ የጉዲት ካሳ ሉከፍል የሚገደደው በጥፊቱ ጉዲት ያደረሰ ሰው ሲሆን በአንዲንድ የተለያዩ ጉዲዮች ደግሞ አንድ ሰው ጥፊት ሳይኖርበትም ኃላፉ እንደሚሆን ከፍ/ሕ/ቁ. 2066 እና ተከታዮቹ መገንዘብ ይቻላል።
ተጠሪ በራሳቸው አድራጎት በአመልካች አካል ላይ ለአደረሱት ጉዲት በወንጀል ተከሰው ጥፊተኛ ተብለው የተቀጡ መሆኑን የክርክሩ ሂደት በግልጽ ያሳያል። በመሆኑም በራሱ ጥፊት በሰው አካል ላይ ለደረሰ ጉዲት ኃላፉ የሆነ ሰው ለደረሰው ጉዲት ካሳ የመክፈል ግዳታ በፍትሐብሕር ሕጉ ግዳታ ተጥልበታል።
ከዚህ በመቀጠል ላታይ የሚገባው የካሳው መጠን ነው። ለጉዲቱ ኃላፉ የሆነ ሰው የሚከፍለው የካሳ መጠን ከጉዲቱ ጋር ተመዛዛኝ ላሆን እንደሚገባ በፍ/ሕ/ን/ቁ. 2090 እና 2091 ስር ተመልክቷል። ወደፉት ይደርሳል ተብል የሚገመት ጉዲት የተረጋገጠ ከሆነ እስኪፈፀም መጠበቅ ሳያስፈልግ ካሳው ሉከፈል እንደሚገባ የፍ/ሕ/ቁ. 2092 ይናገራል። በልላ በኩል ካሳ ከደረሰው ጉዲት ጋር እኩል ሆኖ መመዘን አለበት ሲባል መታየት ያለበት በአጠቃላይ በተጏጂው ላይ ጉዲት በመድረሱ ምክንያት እንደሰው በአጠቃላይ የመስራት ኃይል ቅነሳ አንፃር እንጂ ከጉዲቱ በፉት ሲሰራው የነበረውን ስራ ላለመስራት ጉዲቱ ያስከተለው ልዩ ጫናና የቅነሳ መጠን ግምት ውስጥ በማስገባት አለመሆኑን ለዚህም ምክንያት የሚሆነው እያንዲንደ የሰውነት ክፍል ስራ ለመስራት ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ አንድ ሰው ለመኖር የተለያየ ፊይዲና ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ እንደሆነ ይህ የሰበር ችልት በመ/ቁ. 19338 ትርጉም ሰጥቶበታል።
በመሰረቱ ካሳ የሚከፈለው ጉዲት መኖሩ ሲረጋገጥ ሲሆን የካሳ አተማመን ፣ መጠንና አከፊፈልን በተመለከተ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2090 ፣ 2091 ፣ 2092 ፣ 2095 እና በላልች ድንጋጌዎች የተቀመጠ ሲሆን ከእነዚህ ድንጋጌዎች መገንዘብ የሚቻለውም ካሳውwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በተቻለ መጠን ከጉዲቱ ጋር መመጣጠን ያለበትና በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2141 ድንጋጌ አግባብም ጉዲት የደረሰበት ሰው የጉዲት ካሳ መጠኑን በትክክል ማስረዲት ያለበት መሆኑን ነው። በአደጋ ምክንያት ጉዲት ለደረሰበት ሰው ለደረሰበት ጉዲት ሉከፈል የሚገባው የካሣ መጠን በትክክል ለመወሰን የሚያስችል ማስረጃ ያልቀረበ ወይም የካሣውን መጠን በማስረጃ አጣርቶ ለመወሰን አስቸጋሪ ሁኔታ ሲያጋጥማቸው ዳኞች ካሣውን በፍትብሓር ህግ ቁጥር 21ዐ2 መሰረት በርትዔ ሉወሰኑ እንደሚችለ ተደንግጓል። በዚህ ድንጋጌ የተመለከተው የርትእ መርህ ፍትሕን ለማስፈን ዳኞች በሕግ ከተደነገገው በመውጣት ወይም ሕጉ ራሱ በአንዲንድ ተለይተው በተገለጹ ጉዲዮች ላይ ርትዔን እንዱከተለ ሲፈቅድ ከሕግ ይልቅ ህሉናቸው ትክክል ነው የሚለውን እንዱመርጡ እንዱወስኑ የሚፈቅድ ነው። ስለሆነም ርትዔ የሚያመለክተው የተፈጥሯዊ ሕግጋትን በመጠቀም ፍትሕን መስጠት ሲሆን መሰረታዊ አላማውም በሕግ ያለውን ክፍተትን መሙላት ወይም የሕግን ጥብቅ ደንብ ፍትሐዊ ማድረግ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ርትእ አይነተኛ አላማውና ግቡ ሕግ ትክክለኛ ፍትሕ ላያስገኝ ስለሚችል አከራካሪ ለሆነው ጉዲይ እንደማስረጃዎቹና አከባቢያዊ ነባራዊ ሁኔታዎች በሕግ ድንጋጌ ስር መታጠር ሳያስፈልግ ፍትሕ ለማስገኘት ነው ተብል ይታሳበል። ስለሆነም አስቀድሞ እርግጠኛ በመሆን ደንብ ማስቀመጥ በማይቻልበት ሁኔታ፣ግልጽና ቁልጭ ያል መፍትሓ ለመስጠት የሚቻልበት አጋጣሚ ሲኖር፣ጉዲት አድራሹ ድርጊቱን የፈጸመበት ምክንያት ከቁጥጥሩ ውጭ በሆነ ጊዜ ባደረሰው ጉዲት መጠን ካሳ መክፈል ከህሉና ግምት ውጭ በሚሆንበትና ላልች ተመሳሳይ ችግሮች ሲያጋጥሙ ርትዔ እነዚህን ችግሮች በመቅረፍ ረገድ በሕግ የማይተካ ሚና ያለው መሆኑ ይታመናል።
በመሆኑም ካሳ በርትእ ሲወሰን በዘፈቀደ ላሆን የማይገባው ሲሆን በርትዔ የተሰጠ ውሳኔም በበላይ ፍርድ ቤት ሉሻር የሚገባው ይህንኑ የርትእ መሰረታዊ አላማ እግምት ውስጥ ያላስገባ መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ነው። የበታች ፍርድ ቤቶች በሚሰጡት የካሳ መጠን ላይ ይግባኝ የላለው መሆኑ በመርህ ደረጃ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2152 ስር የተመለከተ ሲሆን ይግባኙ በልዩ ሁኔታ የሚፈቀድባቸው ሁኔታዎች ደግሞ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2153 ስር ተገልጸዋል። ስለሆነም የጉዲት ካሣ መጠን በዝቷል ወይም ያንሣል በሚል ቅሬታ ማቅረብ የሚቻለው በፍትሃ ብሓር ሕግ ቁጥር 2153 ስር የተመለከቱት የተለዩ ሁኔታዎች ማለትም የነገሩን አጋጣሚ ሁኔታ ያለአግባብ በመያዝwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ውሣኔ የተሰጠበት ከሆነ፣ ያለአግባብ የሆነውን የአገማመት ስርዓት በመከተል የተሰጠ ከሆነ፣ የተወሰነው የካሣ መጠን በግልፅ ከአዔምሮ ግምት ውጪ የሆነና የተወሰነውም በማድላት ወይም በዝንባላ መሆኑ በእርግጥ ሆኖ የተገኘ ከሆነ እና የተሰጠው የጉዲት ካሣ በሂሳብ መሣሣት የሆነ እንደሆነ በመሆኑና እነዚህ ነጥቦች ባልተረጋገጡበት ሁኔታ ግን በፍትሐብሕር ሕግ ቁ. 2152 ስር እንደተመለከተው ይግባኝ በሕጉ የተፈቀደ አይደለም። ስለሆነም የጉዲት ካሳ መጠን ውሳኔ በሕጉ በተዘረጋው ስርዓት መወሰን ያለበት ሲሆን ይህም የጉዲት ካሳ ሕግ መሰረታዊ አላማን የሚያሳካ ነው ተብል ይታሳበል። ከዚህ አንጻር ሲታይ ፍርድ ቤቶች የጉዲት ካሳ መጠኑን መወሰን ያለባቸው በሕጉ በተዘረጋው ስርዓት ብቻ እንጂ የጉዲት ካሳ መጠኑ ከፍ የማለቱን ወይም ላላ ግምታዊ የሆነ ምክንያት መሰረት በማድረግ ላሆን አይገባም።
ከፍ ሲል እንደተመለከትነው ተጠሪ በወንጀል ድርጊት በአመልካች ላይ የአካል ጉዲት ያደረሱባቸው ስለመሆኑ ተረጋግጧል። አከራካሪ የሆነው ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ካሳው በርትእ ሉወሰን የሚገባው መሆኑን ከአመነ በኃላ መጠኑን ብር 40,000.00 እንዱሆን በርትእ ሲወሰን እግምት ውስጥ ሉገቡ ይገባቸው የነበሩትን ሁኔታዎች በአግባቡ የያዘ መሆን ያለመሆኑ ነው። በመሆኑም ችልቱ የጉዲት ካሳ መጠኑ በርትዔ ሲወሰን ምን ምን ሁኔታዎችን ማገናዘብ አለበት? የሚለውን ነጥብ መመርመር አስፈላጊ መሆኑን ያመነበት ሲሆን ይህንኑ በአግባቡ ለመመለስም አግባብነት ያላቸውን የህግ ድንጋጌዎች መመልከቱ ተገቢ ይሆናል። በአመልካች ላይ የደረሰው የአካል ጉዲት 40% ስለመሆኑ ተገንዘበናል። ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት አመልካች ላይ 40% የአካል ጉዲት መድረሱን ቢያረጋግጥም አመልካች ከጉልበት ስራ ምን ያህል ገቢ እንደሚያገኙ በማስረጃ አለመረጋገጡን፣በዚህ ስራ የተሰማራ ሰው ገቢ በአመክንዩ በመውሰድ እንዱሁም በአገራችን የአንድ ሰው የእለት ገቢ በአማካኝ ተወስድ ካሳው መሰላት ያለመበት መሆኑን፣ በዚህ ረገድ ግን ግልጽ የሆነ ማስረጃና የሂሳብ ቀመር ያለመቅረቡን ገልጾ ለእነዱዚህ አይነት ችግር ሕጉ መፍትሄ መዘርጋቱን ጠቅሶ ካሳው በርትዔ መወሰን እንደአለበት ከዘረዘረ በኋላ ይህ በሕጉ የተዘረጋው መፍትሓ ስለጉዲቱ ምን ያህል ኪሳራ እንደሚከፈል በትክክል ለመወሰን ያልተቻለ እንደሆነ ዲኞቹ የነገሮቹን ተራ ሁኔታዎችንና ተጎጂውም ያደረገውን ጥንቃቄ አመዛዝነው በመገመት የኪሳራውን ልክ እንደሚወስኑ የሚደንግግ መሆኑን፣ ከዚህ አንጻር ሲታይም ተጠሪ የአመልካችንwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
አንገት ለመምታት ሲሰነዝሩ አመልካች ሲከላከለ የአካል ጉዲቱ የደረሰባቸው መሆኑ በሰነድ ማስረጃ መረጋገጡን በምክንያትነት ይዞ የካሳውን መጠን የወሰነ መሆኑን የውሳኔው ግልባጭ ያሳያል። ይሁን እንጂ ይህ የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ምክንያት ጉዲዩ ወንጀል መሆኑንና የወንጀለ ድርጊት ሲፈፀም አመልካች ሉያደርጉት የሚገባውን ምክንያታዊ ጥንቄቄና በተጠሪ የተሰነዘረው መሳሪያ በአንገታቸው ላይ ቢያርፍ ኖሮ ሉያስከትለው የሚችለውን የከፊ ውጤት ያላገናዘበ ሆኖ ይታያል። ሕጉ ተጎጂው ያደረገው ጥንቃቄ ማመዛዘን የጉዲት ካሳ መጠኑን በርትዔ ሲወሰን ግንዛቤ ውስጥ እንዱገባ የፈለገው የከፊውን ውጤት ለማስወገድ የሚደረገውን ጥንቃቄ ሳይሆን ጉዲቱን በማስከተል ረገድ በተጎጂ በኩል የተደረገውን ያልተገባ ድርጊትን መሆኑን ከድንጋጌው ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። በመሆኑም አመልካች ለሕይወታቸው አደገኛ የሆነውን የተጠሪን ድርጊት በእጃቸው ሲከላከለ በእጃቸውና በጭንቅላቸው ጉዲት መድረሱ በማናቸውም መመዘኛ አመልካች ለጉዲቱ መድረስ ተገቢ ያልሆነ ጥንቃቄ አድርገዋል ወደሚለው ድምዲሜ የሚያደርስ አይደለም። ይህ የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ምክንያት ከፍትሃ ብሓር ሕግ ቁጥር 2153 (ሀ) ድንጋጌ አንጻር ሲታይም ፍርድ ቤቱ የነገሩን አጋጣሚ ሁኔታ ያለአግባብ በመያዝ ውሣኔ የሰጠበት መሆኑን የሚያሳይ እና ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2152 ድንጋጌ አኳያ ሲታይም ለይግባኝና ለሰበር መሰረት የሚሆን የሕግ ጉዲይ ሆኖ አግኝተናል። አንድ የአካል ጉዲት ካሳ መጠኑ በርትዔ እንዱወሰን የግድ የሚል ሆኖ ሲገኝም የጉዲት ካሳ መጠኑ ከደረሰው ጉዲት ጋር ተመጠጣኝ እንዱሆን ተደርጎ ሉወሰነው አይችልም ማለት አይደለም። ምክንያቱም ጉዲት መድረሱ በተጨባጭ እስከተረጋገጠ ድረስ ለተጏጂው ከደረሰበት ጉዲት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ካሳ ሉከፈለው እንደሚገባ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2091 ስር በመርህ ደረጃ ከመቀመጡም በላይ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2153 (ሀ) ድንጋጌ ስር ዳኞች ሉገምቱ የሚገባቸውን የነገሩን አጋጣሚ ሁኔታ ያላግባብ በመያዝ ውሳኔ ከሰጡ ወይም ሉገምቱ የሚገባቸውን ትክክለኛውን መንገድ ትተው ያላግባብ የሆነውን ያገማመት መንገድ ይዘው የተገኙ እንደሆነ በካሳ መጠን ውሳኔው ላይ ይግባኝ የሚፈቀድ መሆኑን መደንገጉ የካሳ መጠን አወሳሰን በዘፈቀደ ሉበዛ ወይም ሉያንስ የማይገባ መሆኑን የሚያስገነዝቡ ናቸው።
አመልካች ላይ የደረሰው አካል ጉዲት ሙለ ለሙለ የመስራትን ችልታቸውን ያሳጣ ነው ባይባልም በ40% የመስራት ችልታቸውን የቀነሰ ስለመሆኑ በሕክምናwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ተረጋግጧል። በእርግጥ ለዚህ ጉዲት ተመጣጣኝ የሆነ ካሳ ለመወሰን አስቸጋሪ ቢሆንም የካሳውን መጠን በትክክል ለመወሰን ያልተቻለ እንደሆነ የካሳው መጠን በርትእ ሉወሰን እንደሚችል የፍ/ሕ/ቁ. 2102/1/ ያመለክታል። የጉዲት ካሳ መጠን ሲወሰን መታየት ያለበት ተጏጂው ከጉዲቱ በፉት ያገኘው ገቢ ሳይሆን በጉዲቱ ምክንያት ወደፉት በመስራት ችልት ላይ ሉያስከትል የሚችለው አለታዊ ተጽእኖ መሆኑ ደግሞ የሚታወቅ ነው። ከዚህ አንጻር ጉዲዩን ስንመለከተው የጉዲት ካሳ መጠኑን በርትዔ ለመወሰን እግምት ውስጥ ሉወስደ ሰለሚገባቸው ፍሬ ነገሮች የፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 2102 በዝርዝር አላመላከተም። ይህ በሆነ ጊዜ ደግሞ የቀረቡት ማስረጃዎችና ፍሬ ነገሮች በአግባቡ በማመዛዘን ፍርድ ቤቱ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2091 ስር የካሳ መጠኑ ከደረሰው ጉዲት ጋር ተመጣጣኝ መሆን አለበት ተብል የተቀመጠው መርህ ግንዛቤ ውስጥ ገብቶ የካሳው ውሣኔ መሰጠት ያለበት መሆኑን ከውል ውጪ ሃላፉነትን በተመለከተ ከተቀመጡ አጠቃላይ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ እንዱሁም መሰረታዊ ዓላማና መረዲት የምንችለው ጉዲይ ነው።
በዚሁ መርህ መነሻ አመልካች ላይ የደረሰውን የአካል ጉዲት አስመልክቶ የተረጋገጠው ፍሬ ነገር ስንመለከት ከአመልካች አካላቸው ውስጥ 40% ጉዲት የደረሰባቸው ስለመሆኑ በሕክምና ማስረጃ ተረጋግጧል። አመልካች ጉዲቱ ሲደርስ የነበራቸው እድሜና ስራ ሰርተው ሲያገኙት የነበረው የገቢ መጠን ያልተረጋገጠ ቢሆንም አመልካች ወደፉት በተለያዩ አማራጮች የሥራ እድልች ሉኖሯቸው እንደሚችል ነባራዊ ሐቅ አመላካች ከመሆኑም በላይ የወደፉት ኑሮአቸውን ለማሸነፍም ከፍተኛ ውድድር ሉያጋጥማቸው እንደሚችል ይታመናል። ለዚህ ደግሞ ባለሙለ አካል የሆነ ሰውና ከሰውነት ክፍልች ውስጥ አስፈላጊውን አካል በአደጋ ምክንያት ያጣ ሰው እኩል ተወዲዲሪ ናቸው ብል መገመት አይቻልም። ስለሆነም ካሳ በርትዔ ሲወሰን አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታዎችንና እነዚህ ነባራዊ ሁኔታዎች በአመልካች የወደፉት ህይወት ላይ ሉያስከትለ ስለሚችለት አለታዊ ተእጽኖ ግምት ውስጥ ማስገባት የካሳ መጠን አወሳንን ፍትሐዊ ያደርገዋል፣ ሕግ አውጪው ሉያሳካ ያሰበውን ግብም ለማሳካት ያስችላል ተብል ይታመናል።
ስለሆነም አመልካች ለቋሚ የአካል ጉዲት መዲረጋቸው ለካሣ ገንዘብ መጠን አወሳሰን እግምት ውስጥ ሉገባ የሚገባ ከመሆኑም በላይ ላላው መሰረታዊ ጉዲይ ዛሬ ያለንበትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ እድገት እና ተጨባጭ የገንዘብ /ብር/ የመግዛት አቅም በየጊዜው እየቀነሰ መሄደ ወደፉት ሉታጣ የሚችለው ገቢ ሲወሰን ግንዛቤ ውስጥ የማይገባበት ህጋዊ ምክንያትም የለም። ስለሆነም ካሳ በርትዔ ሲወሰን ከእነዚህ ተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር ተገናዝቦ መታየት ያለበት መሆኑ ይታመናል።
ባአጠቃላይ አመልካች ላይ የደረሰው ጉዲት ቋሚ የአካል ጉዲት እንደመሆኑ እና የአካል ጉዲት በተፈጥሮ እንደ ንብረት በገበያ ዋጋ ሉተመን የማይችል በመሆኑ የካሣ ገንዘብ ሉሰላ የሚገባው ባጠቃላይ የመስራት አቅሙ ላይ የደረሰውን የጉዲት መጠን መነሻ በማድረግ እና ከላይ በዝርዝር የተመለከትናቸው የሕጉ መንፈስና ዓላማ ግብ ለማድረስ በሚያስችል አግባብ ላሆን ይገባል።
ስለዚህም አመልካች ላይ የደረሰ ዘላቂ ጉዲት 40% /አርባ በመቶ/ የመስራት ኃይል ማጣታቸውን በዝርዝር ከተመለከቱት የሕጉ ሕሣቤዎች እና የተጎጂዋን ግለሁኔታ በአግባቡ ሳያመዛዝኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2153(ሀ) ድንጋጌ ጋር የሚቃረን ምክንያት በመያዝ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ብር 40,ዐዐዐ.00 (አርባ ሺህ) ብቻ ለአመልካች ለአካል ጉዲት እንዱከፈል የወሰነው የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2091 እና 2102 እና 2153(ሀ)) ድንጋጌዎችን በጣሰና ከውል ውጪ ኃላፉነትን በተመለከተ የተቀመጠውን ሕግ አጠቃላይ ዓላማ ባላገናዘበ መልኩ ሆኖ አግኝተናል። ስለሆነም በዚህ ረገድ የተፈፀመው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ሉታረም የሚገባው ነው ብለናል። ከላይ የተመለከቱትን ምክንያቶችን እግምት ውስጥ ስናስገባ በአመልካች ላይ ለደረሰው የአካል ጉዲት በርትዔ ሉወሰን የሚገባው የካሳ መጠን ብር 200,000.00(ሁለት መቶ ሺህ ብር) ሁኖ ስለአገኝን ተከታዩን ውሣኔ ሰጥተናል።
በሰሜን ሸዋ መስተዲደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፊ/መ/5 ጥቅምት 17 ቀን 2010 ዓ/ም ተሰጥቶ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር አጣሪ ችልት በመ/ቁጥር 030-9010 ታህሳስ 24 ቀን 2010 ዓ/ም በትዕዛዝ የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348 (1) ተሻሽሎል።
በአመልካች ላይ ለደረሰው የአካል ጉዲት በርትዔ ሉወሰን የሚገባው የካሳ መጠን ብር 200,000.00(ሁለት መቶ ሺህ ብር) ነው በማለት ተጠሪ ይህንኑ ገንዘብwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ይህ ችልት ውሳኔ ከሰጠበት ጊዜ ጀምሮ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ(9%) ጋር ሉከፍለ ይገባል ብለናል።
ሰ/አ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.