አንድ የግልግል ዲኝነት ጉባኤ መቀመጫ አዱስ አበባ ከተማ ኢትዮጵያ ከሆነ፤ጉዲዩም ታይቶ ዉሳኔ የተሰጠበት በኢትዮጵያ ሕግ መሰረት ከሆነ፤የዓለም አቀፍ ስምምነቶች እና የአገሮች ልምድ እንዱሁም የኢትዮጵያ ሕጎች እና የፋ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ከዚህ በፉት ከሰጣቸዉ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም አንጻር ተከራካሪ ወገኖች “የግልግል የኢትዮጵያና የጅቡቲ ምድር ባቡር ድርጅት እና ኮንስታ ጆይንት ቬንቸር www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XIV ጉባኤው ዉሳኔ የመጨረሻ ዉሳኔ ነዉ” ብለው ቢስማሙም ዉሳኔዉ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ከሆነ በሰበር ከመታየት የሚከለከልበት የሕግ መሰረት የላለ ስለመሆኑ፤ በተንኮል የተደረገ ዉል ፈራሽ የሚሆነዉ ከተዋዋዮቹ አንደኛዉ ወገን ዉለ እንዱደረግ ያደረገዉ በሁለተኛዉ ተዋዋይ ላይ ተንኮል ባይደርስበት ኖሮ ዉል የማያደርግ እንደነበረ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ፤ የፍ/ብ/ሕ/ቁ.1704(1)፤1808(1) የአንድ ዉል በፍ/ቤት ዉሳኔ የፈረሰ እንደሆነ የዉለ መፍረስ የሚያስከትለዉ ዉጤት ተጣርቶ መወሰን ያለበት ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.1704(1)፤ 1808(1)፤1815www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XV
No summary available.
ግንቦት 16 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች፡ ...1.ተኽሉትይመሰል 2. ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) 3. ቀነዓ ቂጣታ 4. ተሾመ ሽፈራዉ 5. አብዬ ካሳሁን አመልካች፡- ......የኢትዮጵያና የጅቡቲ ምድር ባቡር ድርጅት....ጠበቃ ዶ/ር ዘዉድነህ በየነ እና ነ/ፈጅ አቶ አስራት መኮንን ቀርበዋል።
ተጠሪ፡- ............ኮንስታ ጆይንት ቬንቸር.....ጠበቃ አቶ ወሰንየለህ ትጉህ ቀርበዋል።
ይህ መዝገብ የተቀጠረዉ ለምርመራ ሲሆን ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
2.የጉዲዩአመጣጥሲታይከሳሽ ኮንስታ ጆይንት ቬንቸር ባቀረበዉ ክስ ከተከሳሽ የኢትዮጵያና የጅቡቲ ምድር ባቡር ድርጅት ጋር የባቡር መስመር ጥገና ዉል ህዲር 20 ቀን 1999 ዓ.ም (November 29, 2006) ተስማምተን ነበር። ከሳሽ በዉለ መሰረት ስራዉን እየሰራ የነበረ ቢሆንም በተከሳሽ ጥፊት በጠቅላላ የዉል ሁኔታዎች አንቀጽ 65 መሰረት ዉለ ተቋርጧል። በዚህ ዉል መሰረት ከሳሽ ሰርቶ ክፍያ ያልተፈጸመባቸዉ ሥራዎች እና በተከሳሽ ጥፊት ፕሮጀክቱ በመዘግየቱ በከሳሽ ላይ ጉዲት የደረሰ በመሆኑ፣ ተከሳሽ ካሳ በአጠቃላይ 21,076,081.00 (ሀያ አንድ ሚሉዮን ሰባ ስድስት ሺህ ሰማኒያ አንድ) ዩሮ ከሕጋዊ ወለድ ጋር እንዱከፈለን እንዱሁም ተከሳሽ ክፍያዉን ላዘገየበት ተጠያቂ ነዉ እንዱባልልን በማለት ከሷል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በዚህ ክስ ላይ ተከሳሽ ባቀረበዉ መልስ ኮንስታ ከተከሳሽ ጋር ዉለን ያደረገዉ በተንኮል ወይም በማጭበርበር ተግባር ሲሆን፣ በተጨማሪም ኮንሰታ የእሽሙር ማህበር በዉለ መሰረት መፈጸም የነበረባቸዉን ግዳታዎች አንድም ያልፈጸሙ በመሆኑ እና በዚህ ምክንያት ተከሳሽ ላይ ጉዲት የደረሰ በመሆኑ ከሳሽ የጉዲት ካሳ ለተከሳሽ ሉከፍለን ይገባል በማለት ተከራክሯል።
በልላ በኩል የተከሳሽ ከሳሽ ባቀረበዉ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ የከሳሽ ተከሳሽ በግንባታ ዉል መሰረት ባለመፈጸሙ ብር 66,444,384 ዩሮ ከወለድ ጋር እንዱከፍለን በማለት ጠይቋል፤ በአማራጭ የከሳሽ ተከሳሽ ይህን ዉል ያደረገዉ በተንኮል ወይም በማጭበርበር በመሆኑ ዉለ እንዱሰረዝ (invalidate) ተደርጎ ወደ ነበርንበት እንዱንመለስ፣ በዚህም የከሳሽ ተከሳሽ በባቡር መስመር ጥገና ዉል መሰረት ሥራዉን በአግባቡ ያላጠናቀቀ ስለሆነ ለዚህ ሥራ ተብል የተከፈለዉን 27,674,384.00 (ሀያ ሰባት ሚሉዮን ስድስት መቶ ሰባ አራት ሺህ ሶስት መቶ ሰማኒያ አራት) ዩሮ ከወለድ ጋር እንዱከፍለን፣ ወጪና ኪሳራ እንዱከፍለን በማለት ከሷል። በዚህ ክስ ላይ የከሳሽ ተከሳሽ ባቀረበዉ መልስ የተከሳሽ ከሳሽ ያቀረበዉ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ተቀባይነት የለዉም በማለት በዝርዝር ተከራክሯል።
ከዚህ በኋላ የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ ግራ ቀኛቸዉን በማከራከር ምስክሮችን በመስማት የሰነድ ማስረጃዎችን በመመርመር በሰጠዉ ዉሳኔ ከሳሽ ዉለ በማጭበርበር የተደረገ ነዉ ለተባለዉ እና የጂሲኤፍ በኮንስታ ጂቪ የነበረዉ ተሳትፍና ለዉለ መቋረጥ ተጠያቂነት የለበትም፣ ተከሳሽ ግን ለባቡር መስመር ሥራ ዉል መቋረጥ ተጠያቂነት አለበት፣ እንዱሁም በእያንዲንደ ነጥቦች ላይ ዉሳኔ በማስጠት፣ ተከሳሽ 20,664,767 (ሀያ ሚሉዮን ስድስት መቶ ስልሳ አራት ሺህ ሰባት መቶ ስልሳ ሰባት) ዩሮ ዉሳኔ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ እስከሚከፈልበት ቀን ድረስ ከሚታሰብ ወለድ ጋር ለከሳሽ እንዱከፍለዉ፣ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ደግሞ ተቀባይነት የለዉም በማለት ዉድቅ በማድረግ በአብላጫ ድምጽ ወስኗል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ ይህን የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ የአብላጫዉ ድምጽ ዉሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካች ግንቦት 18 ቀን 2008 ዓ.ም የተጻፈ አስራ ሁለት ገጽ የሰበር አቤቱታ አቅርቧል። የአቤቱታዉ ይዘት በአጭሩ፡ በአዉሮፓ የልማት ፈንድ ሕግ መሰረት የግልግል ዲኝነት ጉባኤ የሰጠዉ ፍርድ በአገሪቱ በሚገኙ ፍ/ቤቶች እንደተሰጠwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የመጨረሻ ፍርድ እንደሚቆጠር ስለሚያመለክት እና ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በ
ላይ በሰጠዉ አስገዲጅ የህግ ትርጉም መሰረት ችልቱ ይህን ጉዲይ ለማየት ስልጣን ስላለዉ የሰበር አቤቱታዉ ለዚህ ችልት ለማቅረብ ችለናል። የባቡር መስመር ጥገና ዉለ 114 ኪ.ሜ ለማስጠገን የተስማመን ሲሆን፣ ለፕሮጀክቱ ፊይናንስ የተገኘዉ ከአዉሮፓ ልማት ፈንድ ነዉ። ከዚህ ዉል የሚነሱ አለመግባባቶች በአዉሮፓ ልማት ፈንድ የሥነሥርዓት ሕግ የሚመራ ሲሆን፣ የዉል ስምምነቱን የሚገዛዉ የኢትዮጵያ ሕጎች እና የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ መቀመጫ አዱስ አበባ ኢትዮጵያ ስለሆነ አቤቱታዉ ለዚህ ችልት ላቀርብ ችሎል። በዚህ ምክንያት ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በኢ.ፋ.ዱ.ሪ.ሕገ መንግስት አንቀጽ 80 (3፣ ሀ) መሰረት የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉን ፍርድ ለማረም ስልጣን ይሰጠዋል። እንዱሁም በአዉሮፓ ልማት ፈንድ የስነስርዓት ሕግ (EDF Rules)፣ የአዉሮፓ የፍርድች አፈጻጻም ሰርዓት የኢክሲድ ኮንቬንሽን (ICSID Convention)፣ የኒዉዮርክ ኮንቬንሽን የሚባለት የዓለም አቀፍ ስምምነቶች በግልግል ዲኝነት ጉባኤ ፍርድ የተሰጠ እንደሆነ ፍርደ በተሰጠ አገር በሚገኝ አግባብነት ባለዉ ፍ/ቤት ፍርደን ማስመርመር እንደሚቻል ያስገነዝባለ።
ስለሆነም ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በ
በሰጠዉ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም መሰረት ይህን ጉዲይ የማየት ስልጣን አለዉ። እነዚህ የዓለም አቀፍ ስምምነቶች እንደሚያመለክቱት ፍርደን ከሰጠዉ አንድ ደረጃ ከፍ ባለ አካል ሳይመረመር የሚፈጸመዉ ፍርድ ፍትሒዊና ተቀባይነት ያለዉ የፍትሕ ሥርዓት ስለመኖሩ ዋስትና የማይሰጥ መሆኑን ነዉ። አመልካች ባቀረበዉ ቅሬታ የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ በሰጠዉ ዉሳኔ የፈጸመዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ናቸዉ ያላቸዉ የሚከተለት ናቸዉ።
6.1. በአመልካች እና በተጠሪ መካከል በተደረገዉ የግንባታ ዉል ጠቅላላ ክፍል አንቀጽ 12.7 መሰረት በኮንስታ ጄቪ የዉስጥ አወቃቀር (የአክስዮን ድርሻ ክፍፍልን ጨምሮ) የሚደረግ ማናቸዉም ለዉጥ አስቀድሞ ለአመልካች የማሳወቅ ግዳታ ይጥላል።
እንዱሁም የግንባታ ዉለ ጠቅላላ ክፍል አንቀጽ 64.2 (h) መሰረት ኮንትራክተሩ በዉለ ጠቅላላ ክፍል አንቀጽ 12.7 የተጣለበትን ግዳታ ካልተወጣ የተንኮል ተግባር መፈጸሙን ማረጋገጥ ሳያስፈልግ አመልካች ዉለን ማፍረስ እንደሚችል ይደነግጋል። አመልካች ለክርክሩ ምክንያት ለሆነዉ የግንባታ ዉል ባወጣዉ ጨረታ ተጠሪ በጨረታዉ ለመወዲደር ባቀረበዉ የመወዲደሪያ ሰነድ የእሽሙር ማህበሩ ስምምነት ላይ ተጫራቹwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ኮንስታ ጆይንት ቬንቸር የተመሰረተዉ 70% የአክስዮን ድርሻ በያዘዉ ኮንሶርዚዮ ኮንስታ እና 30% የአክስዮን ደርሻ በያዘዉ ጂሲኤፍ በሚባለት ኩባንያዎች ናቸዉ። አመልካች ከተጠሪ ጋር የግንባታ ዉለን የፈጸመዉ በቅንጂቱ ዉስጥ ሁለቱ ድርጅቶች ያቀናጁትን እዉቀትና ሀብት እንዱሁም በተናጠል ያላቸዉ የግንባታ ግዳታ ደርሻ የዉለ መሰረታዊ ጉዲይ ነዉ። አመልካች ይህን የተጠሪ የሁለቱ ድርጅቶች ቅንጂት ባይኖር ኖሮ ተጠሪዉ ከመነሻዉ የጨረታዉን መወዲደሪያ መስፈርትም አያሟላም፣ አመልካችም ከተጠሪ ጋር የግንባታ ዉል ሉፈራረም አይችልም ነበር። ነገር ግን ተጠሪ ይህን ቅንጅት በተመለከተ ሶስት ስምምነቶችን በማድረግ ይህን ቅንጅት ወደ ማፍረስ ደረጃ ደርሷል። በዚህ መሰረት ሐምል 27 ቀን 1998 ዓ.ም (እ.ኤ.አ. ኦገስት 3 ቀን 2006) በተፈረመዉ የሚስጥር ስምምነት ቁጥር 1 መሰረት የጂሲኤፍን የአክስዮን ድርሻ ወደ 0.1% ዝቅ ለማድረግ ተስማምቷል፣ ህዲር 15 ቀን 1999 ዓ.ም (እ.ኤ.አ. ኖቬምበር 24 ቀን 2006) በተደረገዉ የምስጥር ስምምነት ቁጥር 2 የጂሲኤፍ የአክስዮን ድርሻ ወደ 0.2% ዝቅ እንዱል አድርጓል፤ መጋቢት 11 ቀን 1999 ዓ.ም (እ.ኤ.አ. ማርች 20 ቀን 2007) በተፈረመዉ የምስጥር ስምምነት ቁጥር 3 መሰረት ጂሲኤፍ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) ዩሮ ክፍያን በመቀበል ተሳትፍዉን እስካሁን ድረስ በተፈጸመዉ ብቻ እንዱገደብ አድርጎታል።
ይህም ድርሻ ለይስሙላ የተቀመጠ ነዉ። ተጠሪ ጨረታዉን ማሸነፈ የተገለጸለት መስከረም 19 ቀን 1999 ዓ.ም (እ.ኤ.አ. ሴፕቴምበር 29 ቀን 2006 ዓ.ም) ሲሆን፣ የባቡር መስመር ግንባታ ዉል የተደረገዉ ህዲር 20 ቀን 1999 ዓ.ም ነበር። አመልካች የተጠሪ የቅንጂት ለዉጥ ያወቃዉ በ2006 ዓ.ም እና በ2007 ዓ.ም ነበር። ተጠሪ እነዚህን ምስጥራዊ ስምምነቶች ማድረጉን አልካደም። ተጠሪ በክፈ ልቦና የዉለ መሰረታዊ የሆነዉን የለዉጥ መረጃ ከአመልካች መደበቁን ያሳያል፣ ይህ ደግሞ ተጠሪ ከጨረታ በፉትና በኋላ ሆነ ተብል የማታለል፣ የማጭበርበርና የተንኮል ተግባር መፈጸሙን የሚያረጋግጥ በመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ.1696 እና 1704 የሚጥስ እና ዉለ እንዱፈርስ የሚያደርግ ምክንያት ነዉ። የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ የአብላጫዉ ድምጽ ተጠሪ የተንኮል ተግባር አልፈጸመም በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነዉ።
6.2. የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ የአብላጫዉ ድምጽ የናቪጋንት የአማካሪ ድርጅት ባለሙያዎች የኢትዮጵያ የፍትሒ ብሓር ሕግ ቁጥር 1799-1801 የተመለከተዉንwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የጉዲት ካሳ አሰላል ሳያዉቁ ያቀረቡትን ሪፖርት መሰረት በማድረግ፣ በኢትዮጵያ ሕግ የተመለከተዉን የጉዲት ካሳ አሰላል ታሳቢ ሳያደርግ የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ።
6.3. የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ የአብላጫዉ ድምጽ ከግራ ቀኛቸዉ የቀረቡትን ማስረጃዎች ከወገንተኝነት በጸዲ ሁኔታ በእኩልነት በመመዘን መዲኘት ሲገባዉ ቅን ልቦና በጎደለዉ አካሄድ የተጠሪን ማስረጃዎች ሙለ ለሙለ በመቀበል፣ የአመልካችን ማስረጃዎች ሳይመዝን መጣለ የማስረጃ አቀባበል፣ የማስረጃ ምዘና ደንቦችን የሚጥስ ዉሳኔ መስጠቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ።
6.4. የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ የተሟላ ዱዛይን ሰርቶ ግንባታዉን የማጠናቀቅ ኃላፉነት የተጠሪ መሆኑን በግንባታ ዉለ ጠቅላላ ክፍል አንቀጽ 12.1 እና 17.1 የተመለከተዉን በኢትዮጵያ ሕግ ስለዉልች አተረጓጎም የተደነገገዉን ወደ ጎን በመተዉ ተጠሪ ኃላፉነት የለበትም በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ።
6.5. የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ የአብላጫዉ ድምጽ ወገንተኛነትና የጥቅም ግጭት እያለበት ተጠሪ በዉለ መሰረት 27 ሚሉዮን ዩሮ ከወሰደ በኋላ አንድ ሜትር እንኳን ተቀባይነት ያለዉ የባቡር መስመር ጥገና ሥራ ሳይሰራ ፕሮጀክቱ ለዘገየበት ተብል ተጨማሪ 20 ሚሉዮን ዩሮ ይከፈለዉ መባለ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነዉ። ስለሆነም አመልካች የሚጠይቀዉ ዲኝነት ከፍ ሲል በተጠቀሱት በእነዚህ ምክንያቶች ሁለ የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ የአብላጫዉ ድምጽ የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱሻርልን፣ በዚህ ክርክር ምክንያት አመልካች ያወጣዉን ወጪዎች ተጠሪ እንዱከፍለን እንዱወሰንልን በማለት ተከራክሯል።
አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዱሰጥ ባዘዘዉ መሰረት አስራ ዘጠኝ ገጽ መልስ አቅርቧል።
የመልሱም ይዘት በአጭሩ፡ 7.1. ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በ
ላይ የሰጠዉ ዉሳኔ በዚህ ጉዲይ ላይ ተፈጻሚነት የለዉም።
7.2. በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80 (3፣ ሀ) እና በአዋጅ ቁጥር 25/1988 መሰረት ይህ ችልት በመደበኛ ፍ/ቤቶች የተሰጡትን ዉሳኔ እንጂ የግልግል ዉሳኔዎችን እንደማይመለከት በግልጽ ያስቀመጠ ስለሆነ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት ይህን ጉዲይ ለማየት አይችልም።
7.3. የአዉሮፓ የልማት ፈንድ የስነስርዓት ሕግ አንቀጽ 33 እና 34 ድንጋጌዎች መሰረት የተሰጠዉ ዉሳኔ በተዋዋይ ወገኖች ላይ አስገዲጅነት ያለዉ እና የመጨረሻ መሆኑን እና በአባል አገሩ የአፈጻጸም ሕግ መሰረት ሉፈጸም የሚገባዉ መሆኑን እንጂ በኢትዮጵያ ዉስጥ እንደተሰጠ የመጨረሻ ዉሳኔ በዚህ ሰበር ላታይ የሚችል አይደለም።
እንዱሁም የኢክሲድ እና የኒዉዮርክ ኮንቬንሽኖች ይህ ሰበር ሰሚ ችልት ይህን ጉዲይ እንዱያይ ስልጣን የሚሰጡት አይደለም። የኢክሲዱ ኮንቬንሽን እና የኢዱኤፍ ስነስርዓት በሽምግልና የተሰጡ ፍርድች በአገራዊ ፍ/ቤቶች እንዲይከለሱና ሉፈጸም የሚገባ መጨረሻ ፍርድ መሆኑን ያስገነዝባለ። በግራ ቀኛቸዉ መካከል በሽምግልና ዲኝነት የተሰጠዉ ዉሳኔ የመጨረሻ በመሆኑ አመልካች ዉሳኔዉ በዚህ ችልት እንዱታይለት ያቀረበዉ አቤቱታ በሽምግልና ዲኝነት አለምአቀፍ ደረጃ አዉቅና ያገኘ መርህ እና ተሞክሮ የሚጻረር ስለሆነ ተቀባይነት የለዉም። አመልካች እንደሚለዉ የግልግል ዲኝነት መቀመጫዉ አዱስ አበባ ነዉ በሚለዉ መነሻ ብቻ ፍርደን እና ይዘቱን ወደ መመርመር ማለፍ ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸዉን የሁለትዮሽ የኢንቨስትመንት ስምምነትን ጭምር የሚጥስ ነዉ። ስለዚህ በዚህ ረገድ የሽምግልና ዲኝነት ፍርድ የሕግ ስህተት ያለዉ መሆኑን አመልካች ያላስረዲ ስለሆነ ጥያቄዉ ዉድቅ እንዱደረግልን።
7.4. የግንባታ ዉለ በተንኮል የተደረገ ነዉ ለተባለዉ የተጠሪ የህብረቱ ጥንክርና አቋም አንጻር የግንባታ ዉለ ጠቅላላ ክፍል አንቀጽ 12 (7) እና 64 (2፣h) አንጻር ሲታይ ተጠሪ ያደረገዉ የሕግ ሰዉነት ለዉጥ ስለላለ፣ በተፈጥሮዉም ላይ ሆነ በቁጥጥር ላይ ያደረገዉ ለዉጥ የለዉም፣ የድርሻዉ መጠን ቢለዋወጥም ቁጥጥር የተጠሪ ሆኖ ስለቆየwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የቁጥጥር ለዉጥ አልተደረገም። አመልካች ለእነዚህ የዉለ ድንጋጌዎች የሰጠዉ ትርጉም የተሳሳተ ነዉ። ተጠሪ እነዚህን የዉለን አንቀጽ ተላልፎል ቢባል እንኳን ግዳታዉን መተላለፈ ብቻ ዉለን እንደጣሰ ከማስረዲት ባለፈ እነዚህ የዉል ግዳታዎች በመጣስ የማታለልና የማጭበርበር ወይም የተንኮልን ተግባር ፈጽሟል ብል ለመደምደም የሚያስችል አይደለም። አመልካች ይህ የዉል ድንጋጌ አለመከበሩም ከአምስት አመት በፉት እራሱ ለተጠሪ በጻፈዉ ደብዲቤዎች አዉቆ እና የዉለ አፈጻጸም እያስቀጠለ ቆይቶ አሁን የዉለ መጣስ ማጭበርበር ነዉ ዉለ ይፍረስልን በማለት ያቀረበዉ ጥያቄ ተቀባይነት የለዉም።
7.5. በተጠሪ እና በጂሲኤፍ መካከል የተደረገዉ የእሽሙር ማህበር ስምምነት እና የተደረጉት ለዉጦች የአክስዮን ደርሻ መቀነስ ጉዲይ በተጨባጭ ምክንያት እንጂ አመልካችን ለመጉዲት በተንኮል የተደረገ ድርጊት አልነበረም። በኮንስታ እና በጂሲኤፍ መካከል የተደረገዉ ስለሥራ ተግባራት፣ እና ስለትርፍና ኪሳራ ክፍፍል የሚደረግ የዉስጥ ስምምነት ባለድርሻዎቹ ለአመልካች ባላቸዉ የአንድነትና የነጠላ ኃላፉነት ላይ ዉጤት የሚኖረዉ አይደለም። ይህን የዉስጥ ስምምነት ለማድረግ ደግሞ የአመልካችን የቅድሚያ ስምምነት የሚጠይቅ አይደለም። አመልካች የጂሲኤፍን የተቀነሰ ሚና እያወቀ የተቃወመዉ ነገር በላለበት አሁን ያቀረበዉ ጥያቄ ዉድቅ ነዉ። ኮንስታ ፕሮጀክቱን በዉጤታማነት ለማከናወን የሚያስችለዉን ልምድና ያፈጻጸም ሪከርድ ያለዉ ነዉ።
7.6. የኦላፍ ሪፖርት የተዘጋጀዉ ዉለ ከተቋረጠ ከዓመታት በኋላ እና የግልግል ዲኝነቱ በሂደት ላይ እያለ ሲሆን ሪፖርቱም በመጨረሻ ጸድቆ በደይሬክተር ጄኔራል እንዱዘጋ የተደረገ አይደለም። ይህ ሪፖርት የዉለ ድንጋጌ መጣሱን ከማመልከትና በሂደቱ ዉስጥ የተለያዩ ወገኖች የአሰራር ግድፈት መፈጸማቸዉን ከማመልከት ዉጪ የተንኮል ተግባር መኖሩን የሚጠቅስ ነገር የለም።
7.7. ተጠሪ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.1704 መሰረት የፈጸመዉ የተንኮል ተግባር ስለላላ አመልካች ያቀረበዉ ክርክር ተቀባይነት የለዉም። ተጠሪ የትርፍና የሥራ ድርሻ ክፍፍልን አስመልክቶ በባለድርሻዎች መካከል የተደረገዉን ስምምነት ሳይገልጽ ቢቀር እንኳን በፍ/ብ/ሕ/ቁ.1705 መሰረት በግራ ቀኛቸዉ መካከል ልዩ ግንኙነት ስለላለ ዉለ ፈራሽ የሚሆንበት ሁኔታ የለም። አመልካች በፕሮጀክቱ ላይ የጂሲኤፍን አለመኖር እያወቀwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ዉለ እንዱቀጥል አድርጎ እያለ አሁን ያቀረበዉ ክርክር ከክፍያ ግዳታ ለማምለጥ ነዉ።
አመልካች በዚህ ምክንያት የዉል ይፍረስልን ጥያቄ በግልግል ጉባኤዉ ተቀባይነት ማጣቱ በሕጉ አግባብ ስለሆነ አመልካች በዚህ ረገድ ያቀረበዉ የመከራከሪያ ነጥብ የሕግ መሰረት የላለዉ ስለሆነ ዉድቅ እንዱደረግልን።
7.8. የአሁን አመልካች የግልግል ጉባኤዉ ስለዉልች አተረጓጎም፣ ስለጉዲት ካሳ ስላት እና የማስረጃ አቀባበልና ምዘና በተመለከተ የኢትዮጵያ ሕግ ወደ ጎን ትቷል በማለት ያቀረበዉ አቤቱታ የሕግ መሰረት የለዉም። እንዱሁም የግልግል ጉባኤዉ ወገንተኝነትና የጥቅም ግጭት የሚታይበት ነዉ በማለት አመልካት ያቀረበዉ ቅሬታ ተቀባይነት የለዉም። ስለዚህ ይህ ችልት ጉዲዩን የማየት ስልጣን የለዉም ተብል አቤቱታዉ ዉድቅ እንዱደረግልን፣ ይህ ካልሆነ ተጠሪ ያቀረባቸዉን ክርክሮች በመቀበል የሽምግልና ጉባኤዉ አብላጫዉ ድምጽ የሰጠዉ ዉሳኔ እንዱጸናልን፣ የጠበቃን አበል ጨምሮ ወጪና ኪሳራ እንዱወሰንልን በማለት በዝርዝር ተከራክሯል።
የአሁን አመልካች በበኩለ የሰበር አቤቱታዉን በማጠናከር የካቲት 21 ቀን 2009 ዓ.ም የተጻፈ አስራ ስምንት ገጽ የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኛቸዉን ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንዱሁም አቤቱታዉ ያስቀርባል ሲባል ከተያዘዉ ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመርነዉ በዚህ ጉዲይ ምላሽ ማግኘት የሚገባቸዉ ጉዲዮች በመጀመሪያ ደረጃ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ የሰጠዉን ዉሳኔ በሰበር የማየት ስልጣን አለዉ ወይስ የለዉም? በሁለተኛ ደረጃ ግራ ቀኛቸዉ መካከል የተደረገዉ የባቡር መስመር ሥራ ዉል ሉፈርስ ይገባል ወይስ አይገባም? ዉጤቱስ ምን ይሆናል? የሚለት ነጥቦች መሆናቸዉን ተገንዝበናል።
የመጀመሪያዉን ጭብጥ በተመለከተ ይህ ችልት ይህን ጉዲይ የማየት ስልጣን አለዉ ወይስ የለዉም? የሚለዉን የሚመለከት ነዉ። በዚህ ረገድ አመልካች ባቀረበዉ ክርክር ይህን ሰበር ሰሚ ችልት ይህን ጉዲይ በማየት የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ የፈጸመዉን መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የማረም ስልጣን አለዉ የሚል ነዉ። ተጠሪ በበኩለ ባቀረበዉ ክርክር የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ ዉሳኔ የመጨረሻ ዉሳኔ እና በአባልwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
አገር የሚፈጸም እንጂ በፍ/ቤት ለክለሳ የሚቀርብ ስላልሆነ ይህ ችልት ጉዲዩን የማየት ስልጣን የለዉም በማለት ተከራክሯል።
እንዱሁም በፋዳራል ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 ሥር እንደተመለከተዉ በዚህ ድንጋጌ በተመለከተዉ አግባብ የተሰጠዉን የመጨረሻ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት እንደሆነ በሰበር የማየት ስልጣን እንዲለዉ ያሳያል።
ከፍ ሲል እንደተመለከተዉ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በመደበኛ ፍ/ቤት፣ በሕግ ከፉል የዲኝነት ስልጣን የተሰጣቸዉ አካል እና በሕግ አግባብ በተቋቋመ የግልግል ዲኝነት ጉባኤ ታይቶ የመጨረሻ ዉሳኔ የተሰጠባቸዉን ማናቸዉንም ጉዲዮች መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመባቸዉ እንደሆነ በሰበር አይቶ የማረም ስልጣን እንዲለዉ መገንዘብ ያስፈልጋል። ከዚህ አንጻር ይህ ችልት የፍሬ ነገር ስህተት፣ የማስረጃ ምዘና ጉዲይ እና በዉሳኔዉ ላይ ምንም ተጽህኖ የላለዉን ቀላል የሕግ ስህተት በሰበር የማየት ስልጣን እንደላለዉ መገንዘብ ይቻላል።
ይህ በእንዱህ እንዲለ የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ የሰጠዉን ዉሳኔ በፍርድ ቤት የማሳረሙ ጉዲይ ከዓለም አቀፍ ስምምነቶች እና ከአገሮች ልምድ አንጻር ማየቱ አስፈላጊ ነዉ። እንደሚታወቀዉ የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ ፍርድ እንደተሰጠ ሶስት ዉጤቶችን ያስከትላል፡
ተሸናፉዉ ወገን በፈቃደኝነት እንደፍርደ መፈጸም።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
አሸናፉዉ ወገን በዓለም አቀፍ የግልግል ዲኝነት የተሸናፉዉ ወገን ንብረት ባለበት አገር ፍርደ እንዱጸድቅ፣ እዉቅና እንዱያገኝ ወይም እንዱፈጸምለት ይፈልጋል።
በአለም አቀፍ የግልግል ዲኝነት ተሸናፉዉ ወገን ፍርደ በተሰጠበት አገር ፍርደ እንዱሰረዝ ማድረግ ናቸዉ።
በዚህ መሰረት ከዓለም አቀፍ ስምምነቶች አንጻር ሲታይ የኒዉዮርክ ስምምነት አንቀጽ 5 (New York Convention Art 5) መሰረት የግልግል ጉባኤ ብይን እዉቅና እና ተፈጻሚነት የሚነፈግበትን ሁኔታዎች ወይም ምክንያቶች ተዘርዝረዉ እናገኛለን።
ኢትዮጵያ ይህን ስምምነት ያልፈረመች ብትሆንም ስምምነቱ የግልግል ዲኝነት ጉባኤ የሰጠዉን ብይን እዉቅና ሉከለከል እና ለመፈጸም እምቢ የሚባልባቸዉን ምክንያቶች ያስቀምጣል።
የዩኒስትራል ሞዳል ሕግም (UNCITRAL MODEL LAW) የግልግል ጉባኤ ብይን ወይም ዉሳኔ ሉሰረዝ የሚችልበትን ምክንያቶች ያመለክታል። ይህን ብይን ወይም ዉሳኔ ለማሰረዝ የሚቀርብ አቤቱታ መቅረብ የሚገባዉ የግልግል ዲኝነት መቀመጫ በሆነዉ ፍርድ ቤት እንደሆነ የዚህ አንቀጽ 34 ይደነግጋል። የግልግል ዲኝነት ሲታይ በነበረዉ ቦታ ያለዉ ፍርድ ቤት በሂደቱ ላይ የተቆጣጣሪነት ስልጣን ስለሚኖረዉ ሂደቱ ፍትሒዊ እና ከሙስና የጸዲ መሆኑን የመቆጣጠር ኃላፉነት አለበት። ይህን ሕግ ተከትል አገሮች የየራሳቸዉ ሕጎች ያወጡ ሲሆን፣ የግልግል ብይን የሚታረምበት ዓይነት እና ደረጃ ከአገር አገር እንደሚለያይ መገንዘብ ያስፈልግል። በዚህ መሰረት የዩኒስትራል ሞዳል ሕግ አንቀጽ 34 የግልግል ብይን ዉድቅ የሚደረግበትን ምክንያቶች ያስቀምጣል።
በአዉሮፓ ልማት ፈንድ ስነስርዓት ሕግ (EDF Rules) የአዉሮፓ የልማት ፈንድ የስነስርዓት ሕግ አንቀጽ 33 (1፣ 3) መሰረት የሽምግልና ዲኝነቱ በጽሐፍ የሚደረግ ሆኖ በተዋዋይ ወገኖች ላይ የመጨረሻና ገዢ እንደሚሆን ያመለክታል። የዚህ ሕግ አንቀጽ 34 ማየቱም አስፈላጊ ነዉ። ተዋዋይ ወገኖች ሳይዘገዩ ፍርደን ተግባራዊ ማድረግ ያለባቸዉ መሆኑን ያስገነዝባል። እያንዲንደ የኤሲፒ አገር ወይም አባል አገር አኢዳፍ የስነስርዓት ሕጎች መሰረት የተሰጠ ፍርድን እዉቅና ሰጥቶ ልክ በግዛቱ ዉስጥ የሚገኙ ፍ/ቤቶች ወይም ፍትህ አካላት እንደሰጡት ፍርድ በመቁጠር በግዛቱ ዉስጥ ተፈጻሚ እንዱሆን ማድረግ አለባቸዉ።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የኒፍርም አርብትሬሽን አክት ክፍል 23 (Uniform Arbitration Act section 23) መሰረት የግልግል ብይን በማመልከት ለፍ/ቤት ብይኑን ለማሰረዝ የሚቻልባቸዉን ምክንያቶችን ያሳያል።
የፓነማ ስምምነት (Inter-American Convention On International Commercial Arbitration (B-35) (Panama Convention) የሚባለዉ በአንቀጽ 5 እና 6 ሥር እንደተመለከተዉ የግልግል ብይን የታየበት ሕግ አገር፣ ይህን ብይን እዉቅና ለመንፈግና ተፈጻሚነቱን እምቢ ማለት የሚልባቸዉን ምክንያቶች አስቀምጧል።
የአሜሪካ የፋዳራል የግልግል ሕግ (The Federal Arbitration Act (USA) ) የግልግል ዲኝነት ብይን የሚታረምበትን በጠባብ ምክንያቶች መሆኑን ያመለክታል።
በሕጉ ክፍል 10 (ሀ) ሥር የግልግል ብይን የሚሰረዝበትን ምክንያቶች ይዘረዝራል።
በዚህ ድንጋጌ ሥር የሕግ ስህተት አልተመለከተም። የአሜሪካ ፍ/ቤቶች እና ተከራካሪ ወገኖች በፋዳራል የግልግል ሕግ ከተመለከተዉ በላይ ሰፊ ያለ የግልግል ብይን የሚታረምበትን ምክንያቶች ያስቀምጣለ። እንዱሁም የክልል ሕግ አዉጪዎች የግልግል ብይኑ ሥራ ነገር የሚታረምበትን ማሻሻያዎች እንዱካተቱ አድርጓል። ሕግ አዉጭዉ ፍ/ቤት በምን ምክንያቶች የግልግል ብይን መሰረዝ እንዲለበት መወሰን እንደሚገባዉ በዚህ ዘርፍ የዲበረው የህግ ልምድ ያስገነዝበናል።(የሕግ ምሁራን ይገልጻለ።) የፋዳራል ፍ/ቤቶች የግልግል ዲኛ በሰጠዉ ብይን ግልጽ የሆነ ሕግ የመተዉ ሁኔታ የሚታይበት እንደሆነ (manifest disregard of the law) ብይኑን የሚሰርዙበትን ምክንያት አግባብ ተግባራዊ አድርጓል። የግልግል ዲኛዉ ሕግን በግልጽ ወደ ጎን ትቷል የሚባለዉ፡ ሀ) ጉዲዩ ግልጽ በሆነ አግባብነት ባለዉ የህግ መርህ የሚገዛ እንደሆነ እና ለ) የግልግል ዲኛዉ አስቦ/አዉቆ በጥንቃቄ ትኩረት ሳይሰጠዉ የቀረበ እንደሆነ ነዉ።
የግልግል ብይን በሕግ ስህተት ምክንያት የሚታረምበት ምክንያት አንደ ሕጋዊነት ሲሆን ብይኑ በሕግ ስህተት ምክንያት እንዱታረም በሕግ ስልጣን የተሰጠ ወይም አስገዲጅ የሆነ የህግ ትርጉም የተሰጠበት እንደሆነ ነዉ። የአሜሪካ የፋዳራል የግልግል ሕግ አንቀጽ 10 (ሀ) ሥር የተዘረዘሩት ምክንያቶች የሕግ ስህተት የሚያካትት አይደለም። የኒዉ ጄርሲ የግልግል ሕግ የግልግል ዲኛ ሕግን ተፈጻሚ በሚያደርግበት ጊዜ ጉልህ የሆነ ስህተት የፈጸመ እንደሆነ ፍርድ ቤት ይህን የግልግል ብይን እንደሚሰርዝ ተመልክቷል። በዚህ መሰረት ፍ/ቤት የግልግል ብይን ግልጽ የሆነ የሕግwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ስህተት ያለበት እንደሆነ በጠባቡም ቢሆን ብይኑን ከማረም የሚከለክለዉ ሕግ እንደላለ መገንዘብ ያስፈልጋል።
እ.ኤ.አ. 1996 የወጣዉ የእንግሉዝ የግልግል ሕግ አንቀጽ 69 (England Arbitration Act 0f 1996) ተከራካሪ ወገኖች የሕግ ስህተት በማንሳት ለፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረብ የግልግል ብይን እንዱታረም መጠየቅ እንደሚችለ ያመለክታል።
በሲዊዘርላንድ ኢንተርካንቶናል የግልግል ሕግ አንቀጽ 36 ደግሞ የግልግል ብይን የተሰጠዉ በተሳሳታ የፍሬ ነገር ድምዲሜ መሰረት በማድረግ የሆነ እንደሆነ ወይም ግልጽ የሆነ የሕግ ወይም ርትዔ ጥሰት የተፈጸመበት እንደሆነ ፍ/ቤት ብይኑን እንዱሰርዝ የሚፈቀድ መሆኑን ማየት ይቻላል።
ከኢትዮጵያ አንጻር ሲታይ ከክርክር አፈታት ዘዳዎች መካከል አንደ የግልግል ዲኝነት ጉባኤ እንደሆነ የኢትዮጵያ የፍትሒ ብሓር ሕግ፣ የፍትሒ ብሓር ስነስርዓት ሕግ እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ዉሳኔዎችን ማየት ይቻላል።
ከዚህ አንጻር የፍትሒ ብሓር ሕግ አንቀጽ 3325-3346 እንዱሁም የፍትሒ ብሓር ስነስርዓት ሕግ ቁጥር 315-319 እና አንቀጽ 350-357 ድንጋጌዎችን ያስገነዝባለ።
የግልግል ዲኝነት የሚታየዉ በኢትዮጵያ ሕግ እስከሆነ ድረስ እነዚህ ድንጋጌዎች ተፈጻሚነት ያላቸዉ መሆኑ አከራካሪ አይሆንም። የፍትሒ ብሓር ሕጉ መሰረታዊ መብት የሚደነግግ ሲሆን የፍትሒ ብሓር ስነስርዓት ሕጉ ደግሞ ይህን መሰረታዊ መብት ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል የስነስርዓት ደንቦችን የሚደነግግ እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል። የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ በሕግ አግባብ ተቋቁሞ የተከራካሪ ወገኖችን ክርክር ሰምተዉ አጣርተዉ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.318 ሥር በተመለከተዉ መሰረት ብይን ወይም ዉሳኔ መስጠት እንደሚችል ተደግጓል። ይህ ብይን ወይም ዉሳኔ ልክ በፍርድ ቤት እንደሚሰጥ ብይን ወይም ዉሳኔ ዓይነት መወሰን እንዲለበት ያስገነዝባል። የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ በሰጠዉ ብይን ወይም ዉሳኔ ላይ ይግባኝ የሚቀርብበት ወይም እንዱሰረዝ አቤቱታ የሚቀርበዉ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.350-357 ሥር በተመለከተዉ አግባብ እንደሆነ የዚህ ሕግ አንቀጽ 319 (1) ድንጋጌ ያመለክታል። ከዚህ ድንጋጌ መገንዘብ እንደሚቻለዉ የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ በኢትዮጵያ አገር እና በዚህ አገር ሕግ አግባብ የተከራካሪ ወገኖችን ክርክር አይቶ ዉሳኔ የሰጠ እንደሆነ፣ በዚህ ብይን ወይም ዉሳኔ ያልተስማማ ወይም ቅሬታ ያለዉ ወገን ይግባኝ የሚልበት ወይምwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ዉሳኔ እንዱሰረዝለት የሚጠይቅበት ስርዓት የተዘረጋ መሆኑን እና የግልግል ብይን ወይም ዉሳኔ ከሕግ የሚቃረን ወይም ኢ-ፍትሒዊ ቢሆንም እንኳን ዝም ተብል የሚፈጸም ነዉ ለማለት የሚቻል አይደለም። ከእነዚህ የሕጉ ድንጋጌዎች መረዲት እንደሚቻለዉ የግልግል ብይን ወይም ዉሳኔ በሕጉ በተመለከተዉ አግባብ እና ምክንያቶች በፍ/ቤት ታይቶ ሉታረም እንደሚችል ነዉ እንጂ በምንም መልኩ ሉታረም የማይችል የመጨረሻ ዉሳኔ ነዉ ለማለት የሚቻልበት ሁኔታ የለም። ከዚህ አንጻር ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በአመልካች በናሽናል ሞተርስ ኮርፖሬሽን እና በተጠሪ ጄኔራል ቢዝነስ ዱቨልፕመንት መካከል በነበረዉ ክርክር በ
ላይ ህዲር 12 ቀን 2000 ዓ.ም በሰጠዉ ዉሳኔ ተዋዋይ ወገኖች (ተከራካሪ ወገኖች) በግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ ታይቶ የተሰጠዉ ዉሳኔ የመጨረሻ ነዉ በማለት የተስማሙ በመሆኑ፣ የግልግል ዉሳኔዉ እንደዉለ በእራሱ የመጨረሻ ዉሳኔ በመሆኑ በሰበር ቀርቦ ላታይ የሚችል አይደለም በማለት መወሰኑን ማየት ይቻላል። ነገር ግን ይሄው ችልት በአመልካች ብሓራዊ ማዔድን ኮርፖሬሽን ኃ/የግ/ማህበር እና በተጠሪ ዲኒ ድሪሉንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር መካከል በነበረዉ ክርክር በ
ጥቅምት 29 ቀን 2003 ዓ.ም በሰጠዉ ዉሳኔ ተከራካሪ ወገኖቹ የግልግል ዉሳኔ የመጨረሻ ዉሳኔ ብለዉ ቢስማሙም፣ በግልግል ዉሳኔዉ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት እንደሆነ ለዚህ ችልት ቀርቦ የማይታይበት የህግ ምክንያት የለም በማለት በ
የሰጠዉን አስገዲጅ የህግ ትርጉም በመለወጥ ወስኗል።
የግልግል ዲኝነት ጉባኤ ብይን ላይ ቅሬታ ያለዉ ተከራከሪ ወገን መቃወሚያዉን የሚያቀርብባቸዉ መንገድች በፍ/ብ/ሕ/ቁ.350-357 ሥር ተመልክቷል። እነዚህም፡
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.351 ሥር በተዘረዘሩት የይግባኝ ምክንያቶች ለመደበኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ማቅረብ ይችላል፣ ነገር ግን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.350 (2) መሰረት ማንኛዉም ተከራካሪ ወገን አዉቆ፣ ገብቶት ወይም ተረድቶ ይህን የይግባኝ መብቱን መተዉ እንደሚችል ይደነግጋል።
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.355 መሰረት የግልግል ብይን እንዱሻርልኝ በማለት ለፍ/ቤት አቤቱታ ማቅረብ እንደሚቻል ያመለክታል። ይህ ድንጋጌ ለፍ/ቤት የሚቀርብ አቤቱታ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.356 ሥር የተዘዘሩትን ምክንያቶች የያዘ መሆን እንዲለበትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ያመለክታል። ፍ/ቤቱም በድንጋጌው ስር የተዘረዘሩት ሁኔታዎች መከሰታቸዉን ያረጋገጠ እንደሆነ የግልግል ብይኑን መሰረዝ እንደሚችል ያሳያል።
ከእነዚህ የሕጉ ድንጋጌዎች መገንዘብ እንደሚቻለዉ ከግልግል ብይን ላይ ይግባኝ የሚባልበት እና ብይኑ እንዱሻር ወይም እንዱሰረዝ በመጠየቅ መካከል ልዩነት መኖሩን ነዉ። ፍ/ቤት የግልግል ብይን የሚሰረዝበት ወይም የሚያነሳበት አግባብ የሥነሥርዓት እና የስልጣን ትክክለኛነት የሚቆጣጠርበት መንገድ ነዉ። የግልግል ብይን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.356 መሰረት ለመሻር ወይም ለማንሳት ምክንያት የሆኑት ሁኔታዎች ለይግባኝ ምክንያቶች ሉሆኑ እንደማይችለ መገንዘብ አስፈላጊ ነዉ።የይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት የግልግል ብይን ያጸናል ወይም በሶስት ወር ጊዜ ዉስጥ ድጋሚ አይቶ እንዱወስን ለግልግል ዲኝነት ጉባኤ ይመልሳል።
ጥቅምት 29 ቀን 2003 ዓ.ም በሰጠዉ ዉሳኔ የግልግል ብይን በተመለከተ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት እንደሆነ ተመሳሳይ የሕግ አፈጻጸም እና ትርጉም እንዱኖር ከማድረግ አንጻር ቅሬታዉ ለዚህ ችልት መቅረብ የለበትም አይባልም። ይህ ደግሞ ለዚህ ችልቱ በኢ.ፋ.ዳ.ሪ.ሕገ መንግስት እና በአዋጅ ቁጥር 454/1997 ከተሰጠዉ ስልጣን አንጻር ማየት ያስፈልጋል።
የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ በሰጠዉ ዉሳኔ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.351 እና 356 ሥር በተመለከቱት ምክንያቶች ዉሳኔዉ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት እንደሆነwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ለዚህ ችልት ቀርቦ የማይታይበት እና የማይታረምበት የሕግ አግባብ የለም፣ ችልቱ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን እንዲለዉ በማለት አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል። ይህ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ደግሞ የፋዳራል ፍ/ቤቶች እንደገና ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀጽ 2 (4) መሰረት ሕግ በመሆኑ አስገዲጅነት ያለዉ ነዉ። ስለሆነም ተከራካሪ ወገኖች የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ የሚሰጠዉ ዉሳኔ የመጨረሻ ነዉ ብል ቢስማሙም፣ ከዉሳኔዉ ቅሬታ ያለዉ ተከራካሪ ወገን ጉዲዩን ለሰበር ከማቅረብ የሚያግደዉ እንዲልሆነ እና ይህ ሰበር ሰሚ ችልትም መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት እንደሆነ ከማረም የሚከለክለዉ እንዲልሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል።
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.461 ለብይኑ እዉቅና ላለመስጠት እና ተፈጻሚ ላለማድረግ ሥር ስድስት ምክንያቶች መዘርዘሩን ማየት ይቻላል።
ነገር ግን በፍ/ቤት የግልግል ብይን የማሳረም ወይም የማሰረዙ ጉዲይ ተዋዋይ ወገኖች የግልግል ዲኝነት ጉባኤን የሚያቋቁሙበት ዓላማ ሙለ ለሙለ ዋጋ በሚያሳጣ መልኩwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
መሆን እንደላለበት መገንዘብ ያስፈልጋል። ተከራካሪ ወገኖች ክርክራቸዉ በግልግል ዲኝነት ጉባኤ እንዱታይላቸዉ ከሚፈልጉባቸዉ ምክንያቶች መካከል የተሰወኑትን ለመጥቀስ በመረጡት ገላጋይ ዳኞች ለመዲኘት ካላቸዉ ፍላጎት፣ የተከራካሪ ወገኖች ነጻነት፣ ጊዜያቸዉን ለመቆጠብ እና ወጪን ለመነቀስ የሚለት ናቸዉ። ከዚህም በላይ የግልግል ብይን በፍ/ቤት ሉታረም ይገባል ሲባል በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለዉን የንግደን ማህበረሰብ ዝንባላ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢንቨስትመንት ከመሳብ አንጻር ያለዉን ተጽኖ ከግምት ያስገባ መሆን እንዲለበት ግልጽ ነዉ። የግልግል ዲኝነት ጉባኤ በፍ/ቤት ከመታየት የማይድን ቢሆንም እነዚህን ሁኔታዎች ታሳቢ በማድረግ በሕጉ በተመለከቱት ሁኔታዎች መሰረት በጠባቡ መሆን እንዲለበት መረዲት ያስፈልጋል።
ሲጠቃለል ይህ ሰበር ሰሚ ችልት፣ የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ መቀመጫ አዱስ አበባ ከተማ ኢትዮጵያ እስከሆነ ድረስ እና ጉዲዩም ታይቶ ዉሳኔ የተሰጠበት በኢትዮጵያ ሕግ መሰረት በመሆኑ፣ ከፍ ሲል ከተጠቀሱት የዓለም አቀፍ ስምምነቶች እና የአገሮች ልምድ እንዱሁም የኢትዮጵያ ሕጎች እና ይህ ችልት በበርካታ መዛግብት ከሰጣቸዉ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም አንጻር፣ ተከራካሪ ወገኖቹ የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ ዉሳኔ የመጨረሻ ዉሳኔ ነዉ ብል ቢስማሙም ዉሳኔዉ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት እንደሆነ በሰበር ከማየት የሚከለክለዉ የሕግ መሰረት የለም። በመሆኑም ተጠሪ ይህ ችልት ይህን ጉዲይ የማየት ስልጣን የለዉም በማለት ያቀረበዉ ቅሬታ ተቀባይነት የለዉም ብለናል።
ሁለተኛዉን ጭብጥ በተመለከተ ግራ ቀኛቸዉ መካከል የተደረገዉ የባቡር መስመር ሥራ ዉል ሉፈርስ ይገባል ወይስ አይገባም? ዉጤቱስ ምን ይሆናል? የሚለዉ ነጥብ እንደሚከተለዉ የሚታይ ይሆናል።
በአዉሮፓ ልማት ፈንድ ስነስርዓት (EDF Rules) አንቀጽ 14.1 መሰረት የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ የኢትዮጵያ ሕግን ተግባራዊ ማድረግ እና የኢትዮጵያ ሕግ እስከፈቀደ ድረስ የንግድ ልማድ ከግምት ዉስጥ መግባት እንደሚገባ ተመልክቷል። ስለሆነም ለተያዘዉ ጭብጥ ምላሽ ለመስጠት በዚህ ጉዲይ የኢትዮጵያ የዉል ሕግን መፈተሽ ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል።
እንደሚታወቀዉ በሕግ ፉት የሚጸና ዉል አለ ለማለት ማሟላት ካለባቸዉ ሁኔታዎች መካከል አንደ ተዋዋይ ወገኖች ጉደለት የላለበትን ስምምነት ማድረግwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.1678 /ሀ/ ሥር ተመልክቷል። ተዋዋይ ወገኖች የሚገቧቸዉን ግዳታዎች ፈቅደዉ እና አዉቀዉ መሆን እንዲለበትም የፍ/ብ/ሕ/ቁ.1679 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ያስገነዝባለ። በሕጉ አግባብ የተቋቋሙ ዉልች ደግሞ በተዋዋይ ወገኖች ላይ ሕግ እንደሚሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ.1731 /1/ ድንጋጌ የሚያስገነዝበዉ ጉዲይ ነዉ።
ተዋዋይ ወገኖች ዉልን ሲዋዋለ የፈቃድ ጉድለት መኖር እንደላለበት የፍ/ብ/ሕ/ቁ.1696 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ያመለክታለ። በዚህ መሰረት የፍ/ብ/ሕ/ቁ.1696 ሥር እንደተመለከተዉ ዉል የሚያፈርሰዉ ከተዋዋዮቹ ወገኖች የአንደኛዉ መፍቀድ በስህተት፣ በድንገተኛ ተንኮል ወይም በኀይል የተገኘ ሲሆን ነዉ በማለት ይደነግጋል።
ዉል ሲደረግ የተዋዋይ ወገን የፈቃድ ጉድለት ከሚያስከትለት ምክንያቶች መካከል የተንኮል ተግባር አንደ ነዉ። በፍ/ብ/ሕ/ቁ.1704 (1) መሰረት በተንኮል የተደረገ ዉል ፈራሽ የሚሆነዉ ከተዋዋዮቹ አንደኛዉ ወገን ዉለ እንዱደረግ ያደረገዉ በሁለተኛዉ ተዋዋይ ላይ ተንኮል ባይደርስበት ኖሮ ዉል የማያደርግ እንደነበረ ሲገለጽ ነዉ በማለት ይደነግጋል።
በዚህ መሰረት አሁን ወደ የተያዘዉ ጉዲይ ስንመለስ በግራ ቀኛቸዉ መካከል የተደረገዉ የባቡር መስመር ሥራ ዉል ተጠሪ በፈጸመዉ የተንኮል ተግባር የተደረገ ነዉ ወይስ አይደለም? የሚለዉ ነጥብ በቅድሚያ መታየት ያለበት ጉዲይ ነዉ። በዚህ መሰረት ይህን የባቡር መንገድ ጥገና ሥራ ለመሥራት ጨረታዉን ተወዲድረዉ ያሸፈት የእሽሙር ማህበር የተቋቋመዉ በኮንስታ ኮንሶርዞ እና ጂሲኤፍ (GCF) ሆነዉ የኮንስታ ጄቪ (consta JV) በሚል የእሽሙር ማህበር ነዉ። በዚህ የእሽሙር ማህበር ኮንሶርዚዮ ኮንስታ 70% የአክስዮን ድርሻ እና ጂሲኤፍ ደግሞ 30% የአክስዮን ደርሻ መያዛቸዉ ተገልጾ መሆኑ ተረጋግጧል። ይህን ጨረታ ተክትል ህዲር 19 ቀን 1999 ዓ.ም (እ.ኤ.አ. ህዲር 29 ቀን 2006) በተደረገዉ የባቡር መስመር ሥራ በአጠቃላይ በብር 40,433,056.70 ዩሮ ተስማምቷል። በዚህ የዉል ስምምነቱ የሚሰሩ በርካታ ሥራዎች ተዘርዝሮ እናገኛለን።
ይህ በእንዱህ እንዲለ ኮንሰታ እና ጂሲኤፍ መካከል ይህን ቅንጅት በተመለከተ ሶስት ምስጥራዊ ስምምነቶች መደረጋቸዉ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ። በዚህ መሰረት ሐምል 27 ቀን 1998 ዓ.ም (እ.ኤ.አ. ኦገስት 3 ቀን 2006) በተፈረመዉ የሚስጥር ስምምነት ቁጥር 1 መሰረት የጂሲኤፍን የአክስዮን ድርሻ ወደ 0.1% ዝቅ ለማድረግ ተስማምቷል፣www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ህዲር 15 ቀን 1999 ዓ.ም (እ.ኤ.አ. ኖቬምበር 24 ቀን 2006) በተደረገዉ የሚስጥር ስምምነት ቁጥር 2 የጂሲኤፍ የአክስዮን ድርሻ ወደ 0.2% ዝቅ እንዱል አድርጓል፤
መጋቢት 11 ቀን 1999 ዓ.ም (እ.ኤ.አ. ማርች 20 ቀን 2007) በተፈረመዉ የሚስጥር ስምምነት ቁጥር 3 መሰረት ጂሲኤፍ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) ዩሮ ክፍያን በመቀበል ተሳትፍዉን እስካሁን ድረስ በተፈጸመዉ ብቻ እንዱገደብ ማድረጉ የተረጋገጠ ጉዲይ ነዉ። የአሁን ተጠሪም ቢሆንም እነዚህ ስምምነቶች መደረጋቸዉን የካደ ነገር የለዉም። ከዚህም በላይ የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ በሰጠዉ ዉሳኔ እነዚህ ምስጥራዊ ስምምነቶች መደረጋቸዉን በዉሳኔዉ አረጋግጧል። በዚህ ረገድ የአዉሮፓ አንቲፍራዉድ ቢሮ (OLAF) ባዘጋጀዉ የመጨረሻ ሪፖርት ይህ ዉል ከመፈረሙ አምስት ቀን ቀደም ብል ጂሲኤፍ በኮንስታ ጂቪ ያለዉን ተሳትፍ ከ30% ወደ 0.2% ዝቅ ማድረጉን እና በዚህም ተጠሪዉ የጠቅላላ ዉል ክፍል አንቀጽ 12.7 መጣሱን አረጋግጧል። የአሁን ተጠሪ እነዚህን ስምምነቶች ለአመልካች የማሳወቅ ግዳታ ቢኖርበትም የአዉሮፓ አንቲ-ፍራዉድ ቢሮ (OLAF) ባደረገዉ ምርመራ ባይደርስበት እና ይፊ ባያደርጋቸዉ ኖሮ ተደብቀዉ እንደሚቀሩ ተረጋግጧል።
አመልካች ስለእሽሙር ማህበሩ ያልሆነ አቋም እንዱይዝ በማድረግ፣ ተጠሪዉ ለሥራዉwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ብቃት እንዲለዉ በመቁጠር ጨረታዉን አሸንፍ ዉል እንዱያድርግ ያደረገዉ መሆኑን ያስገነዝባል። የአሁን ተጠሪ በፈጸመዉ የተንኮል ተግባር አመልካች የባቡር መስመር ሥራ ዉል ከተጠሪ ጋር እንዱያደርግ ያደረገዉ መሆኑን ያመለክታል። ስለሆነም የአሁን ተጠሪ በአመልካች ላይ በፈጸመዉ የተንኮል ወይም የማጭበርበር ተግባር አመልካች ከተጠሪ ጋር ይህን ዉል ሉያደርግ የቻለ በመሆኑ፣ በአመልካች በኩል ዉለን ሲያደርግ የፈቃድ ጉድለት መኖሩን የሚያረጋግጥ ነዉ። በመሆኑም ይህ ችልት የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ የአሁን ተጠሪ ተግባር የተንኮል ወይም የማጭበርበር ተግባር አይደለም በማለት የደረሰበት ድምዲሜ እና የአሁን ተጠሪ የተንኮል ተግባር የለም በማለት ያቀረበዉ ክርክር ተቀባይነት የለዉም ብለናል።
የሚለዉ ነጥብ ነዉ። ከዚህ አንጻር ጠቅላላ የዉል ሁኔታዎች አንቀጽ 12.7 እና 64.2 (h) ድንጋጌዎች መታየት እንዲለባቸዉ ተገንዝበናል። ጠቅላላ የዉል ሁኔታዎች አንቀጽ 12.7 እንደሚያመለክተዉ የሥራ ተቋራጩ የእሽሙር ማህበር ወይም ከሁለት እና ከዛ በላይ የሆኑ ሰዎች ማህበር እንደሆነ፣ እነዚህ ሰዎች ሁለም በተዋዋይ ባለስልጣን አገር ሕግ መሰረት በዉለ መሰረት ለመፈጸም የአንድነትና የነጠላ ግዳታ አለባቸዉ እና በተዋዋይ ባለስልጣን ጥያቄ ከእነዚህ ሰዎች መካከል አንደን እንደማህበሩ መሪ ሆኖ ከባለስልጣኑ ጋር በመስራት የእሽሙር ማህበሩን ወይም ማህበሩን ለማስገደድ ነዉ።
የእሽሙር ማህበሩ ወይም የማህበሩ አወቃቀር ወይም አደረጃጀት ያለ ተዋዋይ ባለስልጣኑ ቅድሚያ ፈቃድ ሉለወጥ አይችልም። ይህ ድንጋጌ እንደሚያስገነዝበዉ የእሽሙር ማህበር አባላት በማህበሩ ባላቸዉ የአክስዮን ድርሻ መጠን በዉለ የሚመለከታቸዉን ግዳታዎቻቸዉን መወጣት እንዲለባቸዉ ነዉ። ከእነዚህ አባላት መካከል አንደ የላለዉን ወገን ግዳታ ሸፍኖ ሉወጣ እንደሚችል የሚያመለክት ነገር የለዉም። የማህበሩ አባላት ደርሻቸዉን እና ተሳትፍአቸዉን ለመቀየር ከፈለጉ መጀመሪያ የአመልካች ፈቃድ ማግኘት እንደሚገባቸዉ ያስገድዲል። ይህ ማለት የዚህ የእሽሙር ማህበር አባላት የአክስዮን ድርሻ ወይም የስራ ተሳትፍ መጠን ካለ አመልካችwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
እዉቅና ሉለወጥ እንደማይችል ያመለክታል። ይህ የሚያመለክተዉ የአሁን አመልካች ከተጠሪ ጋር ዉል ሲያድርግ የእሽሙር ማህበር አባላት አደረጃጀታቸዉን እና አወቃቀራቸዉን ኮንስታ 70% የአክስዮን ድርሻ እና ጂሲኤፍ 30% የአክስዮን ድርሻ ጠብቀዉ እያንዲንዲቸዉ በዉለ የገቡትን ግዳታ እንደሚፈጽሙ በማመን መሆኑ ግልጽ ነዉ። የአሁን ተጠሪ ጨረታዉን ሲወዲደር እና አሸንፍም ዉል ከአመልካች ጋር ሲያደርግ በዚህ የድርሻ መጠን እና በዚህ መሰረት በዉለ የተመለከተዉን ግዳታዎቻቸዉን በሥራዉ ቦታ በመገኘት ለመወጣት እንደሆነ ግልጽ ነዉ። አመልካች የዚህ ማህበር አባላት ድርሻ ጨረታዉን ሲወዲደሩና ዉል ሲያደርጉ የተገለጸዉን አለመሆኑን ቢያዉቅ ይህ ዉል ያደርጋል ተብል አይታሰብም። በዚህ ረገድ የአዉሮፓ አንቲ-ፍራዉድ ቢሮ (OLAF) ባዘጋጀዉ የመጨረሻ ሪፖርት በዉለ የተመለከተዉን ሥራ ለመስራት ኮንስታ ብቻዉን የቴክኒካል ችልታ ወይም ብቃት ስለላለዉ ዉለ እንደማይሰጠዉ እና በፏርሰንት የተመለከተዉ የተሳትፍ መጠን እያንዲንደ አባል የሚፈጽመዉን ሥራ ድርሻ መሆኑን እና የኮንስታ አባላት የጠቅላላ የዉል ክፍል አንቀጽ 12.7 መጣሳቸዉን አረጋግጧል። ከዚህም በላይ የጂሲኤፍ ሥራ አስኪያጅ የሆነዉ ሚ/ር ሮሲ የተባለዉ የተጠሪ ምስክር በሰጠዉ የምስክርነት ቃል የጂሲኤፍ ድርሻ ወደ 0.2% መቀነሱን የአሁን አመልካች እና የአዉሮፓ ህብረት ቢያዉቁ ኖሮ ዉለ ለተጠሪ እንደማይሰጥ መመስከሩን የሥር ዉሳኔ ግልባጭ ያሳያል። የአሁን ተጠሪ ሆነ የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ ይህ ድርጊት ጠቅላላ የዉል ሁኔታዎች አንቀጽ 12.7 እንደሚጥስ መሆኑን ቢያምኑም የተንኮል ወይም የማጭበርበር ተግባር እንዲልሆነ መግለጻቸዉን መዝገቡ ያሳያል።
መሰረታዊ የሆነ ነገር (essential or material) መሆኑን ያስገነዝባል። ስለሆነም የአሁን ተጠሪ ባቀረበዉ ክርክር ጂሲኤፍ በማህበሩ ዉስጥ የነበረዉ ድርሻ መቀነሱ እና የዉለ አንቀጽ 12.7 የሚጥስ ቢሆንም ለዉለ መሰረታዊ የሆነ ነገር አይደለም፣ ኮንስታ ብቻዉን ይህን ሥራ ለመስራት ሙለ አቅም አለዉ በማለት ያቀረበዉ ክርክር እና የግልግል ጉባኤዉ በሰጠዉ ዉሳኔ ይህ ድርጊት የሚያደርሰዉ ጉዲት የለም በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ ከፍ ሲል የተጠቀሱትን ጠቅላላ የዉል ሁኔታዎችን ድንጋጌዎች የሚጥስ ስለሆነ ተቀባይነት የለዉም ብለናል።
ባቀረበዉ ክርክር ጂሲኤፍ አምስት አመት በኢትዮጵያ በስራ ቦታ እንደላለ እያወቀ ሥራዉ እንዱቀጥል አድርጓል በማለት ተከራክሯል። በዚህ ረገድ የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ ጂሲኤፍ በሥራ ቦታ መገኘት አለመገኘቱን ለአመልካች ማሳወቅ የሚገባዉ ተጠሪ መሆኑን አረጋግጧል። ስለሆነም የአሁን ተጠሪ ይህ የሚስጥር ስምምነት መደረጉን እና ጂሲኤፍ በሥራዉ ቦታ ያልነበረ መሆኑን ከአመልካች ሸሽጎ እንደቆየ መገንዘብ ይቻላል። ይህ የሚያሳያዉ ተጠሪ ዉለ ከተደረገ በኋላም የተንኮል ተግባሩን የገፊበት መሆኑን የሚያስገነዝብ ጉዲይ ነዉ።
ነገር ግን አሁን የተያዘዉ ጉዲይ ሲታይ በግራ ቀኛቸዉ መካከል የተደረገዉ የባቡር መስመር ሥራ ዉል እንዱፈርስ እስከተወሰነ ድረስ ዉጤቱ ምን ይሆናል? የሚለዉ ነጥብ ሲታይ የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ ከዚህ አንጻር ጭብጥ በመያዝ የዉለ መፍረስ የሚያስከትለዉን ዉጤት አጣርቶ ዉሳኔ ያልሰጠበት በመሆኑ፣ በዚህ ረገድ ይህ ችልት የዉለ መፍረስ የሚያስከትለዉ ዉጤት በተመለከተ ዉሳኔ ለመስጠት የሚያስችለዉ ነገር ካለመኖሩም በላይ በዚህ አግባብ ተጣርቶ የቀረበ ግልጽ የሆነ ነገር ስለላለ ጉባኤዉ ድጋሚ አይቶ ዉሳኔ እንዱሰጥበት መመለስም የሚቻል ሆኖ አልተገኘም። ስለሆነም የዚህ ዉል መፍረስ የሚያስከትለዉን ዉጤት በተመለከተ መብት አለኝ የሚል ወገን ካለ በሕጉ አግባብ ከሚጠይቅ በስተቀር በዚህ መዝገብ ላይ ዉሳኔ ለመስጠት የሚያስችል ሁኔታ አልተገኘም ብለናል።
(እ.ኤ.አ. ግንቦት 6 ቀን 2016) የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 (1) መሰረት ተሽሯል።
በግራ ቀኛቸዉ መካከል ህዲር 20 ቀን 1999 ዓ.ም (November 29, 2006) የተደረገዉ የባቡር መስመር ሥራ ዉል የአሁን ተጠሪ በአመልካች ላይ በፈጸመዉ የተንኮል ተግባር የተደረገ ስለሆነ ዉለ ፈራሽ ነዉ ብለናል።
የዉል መፍረስ የሚያስከትለዉን ዉጤት በተመለከተ መብት አለኝ የሚለዉ ወገን በሕግ አግባብ መብቱን ከመጠየቅ ይህ ዉሳኔ አያግደዉም ብለናል።
የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር የግልግል ዲኝነት ጉባኤ ይድረስ።
ግራ ቀኛቸዉ በዚህ ችልት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።
በ22/9/2008 ዓ.ም የተሰጠዉ የአፈጻጸም እግድ ትዕዛዝ በዚህ ዉሳኔ ተነስቷል። ይጻፍ።
No topics extracted.