ገንዘብን በአደራ የማስቀመጥ ዉል (deposit fund) መነሻነት አደራ ያስቀመጠ ባንክ የአደራ አስቀማጩን ገንዘብ የመጠበቅ፣ ሲጠይቁ ወጪ አድርጎ የመክፈል ያዲኒ ራባ እና የኢትዮጵያ ንግድ www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XIII ከአስቀማጩ ዉጪ ለላላ ሰዉ ያለመክፈል ከዉል የመነጨ ግዳታ ሲኖርበት ይህን ግዳታውን ባይወጣ አስቀማጩ ላይ ሉደርስ ለሚችል ጉዲት ከዉል የመነጨ ኃላፉነት ያለበት ሲሆን ባንኩ የሚቀርብለትን የክፍያ ጥያቄ ሲያስተናግድ፣ገንዘብ እንዱከፈለዉ ጥያቄዉን ያቀረበ ሰዉ በርግጥም አደራ አስቀማጩ መሆን አለመሆኑን በቅድሚያ የማረጋገጥ ግዳታ የሚኖርበት ስለመሆኑ የንግድ ህግ 896 እና 897 ባንክ አንዋር መስጊድ ቅርንጫፍ
No summary available.
ቀን - 25/01/2011 ዳኞች፡- ተኽሉት ይመሰል ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራዉ አብዬ ካሳሁን አመልካች፡- ያዲኒ ራባ -አልቀረቡም ከተባለ ተወካይ ሰመረ ገ/ህይወት ቀርበዋል ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንዋር መስጊድ ቅርንጫፍ -አልቀረቡም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል
**
ክርክሩ የተጀመረዉ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን፤ አመልካች በተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ በመጋቢት ወር 2007 ዓ.ም የባንክ ደብተራቸዉን ይዘዉ ባደሩበት አልጋ ላይ ረስተዉ መሄዲቸዉን ተከትል ተጠሪ በባንክ ደብተራቸዉ ላይ ያለዉን ገንዘብ ማንነቱ ላልታወቀ ሰዉ በመክፈል የገንዘብ እና የሞራል ጉዲት ያደረሰባቸዉ መሆኑን ጠቅሰዉ ተጠሪ ያላግባብ የከፈለዉን ብር 46,900.00 እንዱሁም የሞራል ካሳ ብር 20,000.00 እንዱከፍል ይወሰንላቸዉ ዘንድ የጠየቁትን ዲኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ። ተጠሪ በበኩለ ለክሱ በሰጠዉ መልስ፤ ገንዘቡ የተከፈለዉ አመልካች ከሞለት ፍርም እና ከፊርማቸዉ ናሙና ጋር በማመሳከር ተገቢዉ ጥንቃቄ ተደርጎ ለአመልካች ለእራሳቸዉ የተከፈለ መሆኑን፣ እንዱሁም ደብተሩ ጠፍቶ አራት ወር ሲቆይ አመልካች ደብተሩ ስለመጥፊቱ ለፖሉስ አመልክተዉ ሂሳቡ እንዱታገድላቸዉ አለማድረጓጋቸዉን በመጥቀስ ኃላፉነት የለብኝም ሲል ተከራክሯል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ጉዲዩ በመጀመሪያ የቀረበለት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ከግራ ቀኝ በዚህ መልኩ የቀረበዉን ክርክር ከሰማ በኋላ፤ አመልካች ደብተሩ የጠፊባቸዉ ስለመሆኑ ለተጠሪ የማሳወቅ ግዳታ እያለባቸዉ ይህን ባለማድረግ የሂሳብ ደብተሩ ሦስተኛ ወገን እጅ ገብቶ ገንዘቡን ላላ ሰዉ እንዱያወጣ ምክንያት በመሆናቸዉ ተጠሪ ገንዘቡን እንዱከፍል የሚገደድበት ምክንያት የለም በማለት የቀረበዉን ክስ ዉድቅ በማድረግ ወስኗል። አመልካች ይህን ዉሳኔ ባለመቀበል ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ይግባኝም ተቀባይነት አላገኘም።
አመልካች በቀን 15/06/2010 ተዘጋጅቶ በተወካያቸዉ አማካይነት በቀረበ የሰበር አቤቱታ፤ ተጠሪ ተገቢዉን ማጣራት እና ጥንቃቄ ሳያደርግ ከአመልካች የሂሳብ ደብተር ወጪ አድርጎ ለላላ ሰዉ ከፍል እያለ እና ገንዘቡን የከፈለዉ የባንኩ ሰራተኛም በዚህ ጉዲይ ላይ በወንጀል ተከሶ ጥፊተኛ ሆኖ እያለ አመልካች ደብተሩ መጥፊቱን ሪፖርት የማድረግ ግዳታቸዉን አልተወጡም የሚል ምክንያት በመጥቀስ ተጠሪ ኃላፉነት የለበትም በሚል በፋዳራለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ፀንቶ የተወሰነዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ በማለት ታርሞ ይወሰንላቸዉ ዘንድ ዲኝነት ጠይቀዋል። አቤቱታዉ ተመርምሮ የስር ፍርድ ቤት የአመልካችን ክስ ዉድቅ ያደረገዉ በአግባቡ መሆን ያለመሆኑን ግራ ቀኝ በተገኙበት አጣርቶ ለመወሰን ሲባል ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ በተደረገለት ጥሪ መሰረት ቀርቦ ግራ ቀኝ ክርክራቸዉን በጽሐፍ ተለዋዉጠዋል።
ከስር ጀምሮ የክርክሩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ሲታይ ከፍ ሲል የተመለከተዉ ሲሆን፣ ይህ ችልትም አቤቱታዉን ለማስቀረብ የተያዘዉን ጭብጥ ከግራ ቀኝ ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል። ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለዉ አመልካች በተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ለጠየቁት ዲኝነት መሰረት ያደረጉት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ 5634159 ያስቀመጡትን ገንዘብ የያዘ የባንክ ደብተር መጥፊቱን እና ባንኩ በሂሳብ ደብተሩ ላይ የተመለከተዉን ገንዘብ ለ3ኛ ወገን መክፈለን ሲሆን፤ ተጠሪም የባንክ ደብተር ላይ የተመለከተዉን ገንዘብ ወጪ አድርጎ የከፈለ ስለመሆኑ ክድ አልተከራከረም። የተጠሪ ክርክር የነበረዉ ተገቢዉን ጥንቃቄ አድርጎ ለአመልካች እራሷwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
መክፈለን እና የሂሳብ ደብተሩ ስለመጥፊቱ አመልካች ለተጠሪ የማሳወቅ ግዳታቸዉን አለመወጣታቸዉን ሲሆን፤ የስር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም የአመልካችን የዲኝነት ጥያቄ ተቀባይነት የለዉም በሚል ድምዲሜ ላይ የደረሰዉ አመልካች ደብተሩ ስለመጥፊቱ ለተጠሪዉ ባንክ ሪፖርት የማድረግ ግዳታቸዉን አለመወጣታቸዉን ስለመሆኑ የዉሳኔዉ ይዘት ያስገነዝባል።
በመሰረቱ በግራ ቀኝ መካከል ተደርጎ ለዚህ ክርክር ምክንያት የሆነዉ ግንኙነት መሰረቱ በንግድ ህጉ አንቀጽ 896 እና 897 ስር የተመለከተዉ ገንዘብ በአደራ የማስቀመጥ ዉል (deposit fund) ነዉ። በዚህ ዉል መሰረትም ተጠሪ አደራ አስቀማጭ እንደመሆኑ የአመልካችን ገንዘብ የመጠበቅ፣ አመልካች ሲጠይቁ ወጪ አድርጎ የመክፈል እና ከአመልካች ዉጪ ለላላ ሰዉ ያለመክፈል ከዉል የመነጨ ግዳታ ይኖርበታል። ይህን የማድረግ ግዳታዉን ባለመወጣት በአመልካች ላይ ሉደርስ ለሚችል ጉዲት ከዉል የመነጨ ኃላፉነት እንደሚኖርበትም ይታወቃል። በመሆኑም ማንኛዉም ባንክ የሚቀርብለትን የክፍያ ጥያቄ ሲያስተናግድ፣ ገንዘብ እንዱከፈለዉ ጥያቄዉን ያቀረበ ሰዉ በርግጥም አደራ አስቀማጩ መሆን አለመሆኑን በቅድሚያ የማረጋገጥ ግዳታ ይኖርበታል።
የተያዘዉን ጉዲይ በተመለከተ ተጠሪ በአመልካች የባንክ ሂሳብ ላይ የሚገኘዉን ለክርክሩ ምክንያት የሆነዉን ገንዘብ ወጪ አድርጎ ክፍያ የፈጸመ ስለመሆኑ ክድ እስካልተከራከረ ድረስ፣ ከኃላፉነት ሉድን የሚችለዉ ገንዘቡን የከፈለዉ በባንኩ በተዘረጋዉ ደንብና አሰራር መሰረት አስፈላጊዉን ጥንቃቄ ሁለ አድርጎ ተከፊይ አመልካች መሆኑን በማረጋገጥ ክፍያዉን የፈጸመ ስለመሆኑ ማረጋገጥ ሲችል ብቻ ነዉ። በርግጥ አመልካች ደብተሩ ስለመጥፊቱ ለተጠሪ ባንክ የማሳወቅ ግዳታ እንዲለባቸዉ ይታወቃል። ይሁንና፣ ተጠሪ የአመልካችን ገንዘብ በአደራ የመጠበቅ ባለበት ግዳታ መሰረት ተገቢዉን ጥንቃቄ ባለማድረግ ገንዘቡን ለላላ ሰዉ በመክፈለ ምክንያት በአመልካች ጉዲት መድረሱ ከተረጋገጠ፣ አመልካች ደብተሩ ስለመጥፊቱ ለተጠሪ አለማሳወቃቸዉ የተጠሪን ኃላፉነት ሉያስቀር የሚችል አይሆንም። በመሆኑም በስር ፍርድ ቤት በፍ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 246(1) መሰረት ተይዞ በማስረጃ ተጣርቶ እልባት ሉሰጠዉ የሚገባዉ ትክክለኛ ጭብጥ፣ ተጠሪ ለክርክሩ ምክንያት የሆነዉን ገንዘብ የከፈለዉ አስፈላጊዉን ጥንቃቁwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በማድረግ ተከፊዩ አመልካች መሆኑን በማረጋገጥ መሆን አለመሆኑ ነዉ። ከዚህ አንፃር ሲታይ፣ የስር የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች ደብተራቸዉ ስለመጥፊቱ ለተጠሪ የማሳወቅ ግዳታቸዉን አልተወጡም በሚል የፍ/ሕጉን አንቀጽ 1752 ድንጋጌ ያለቦታዉ በመጥቀስ የቀረበዉን ክስ ዉድቅ በማድረግ የሰጠዉ ዉሳኔ፣ እንዱሁም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ይህኑን በማጽናት የሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተናል። በመሆኑም ተከታዩ ተወስኗል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ በቀን 20/04/09 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ፤ እንዱሁም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 25/03/2010 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ትዕዛዝ በፍ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ተሽረዋል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተዘግቶ የነበረዉን መዝገብ በማንቀሳቀስ ተጠሪ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ገንዘብ ከአመልካች የባንክ ሂሳብ ወጪ አድርጎ ሲከፍል በባንኩ በተዘረጋዉ ደንብና ስርዓት መሰረት ክፍያዉ ለአመልካች የተከፈለ መሆኑን ማረጋገጥ በሚያስችል ደረጃ አስፈላጊዉን ጥንቃቄ በማድረግ መሆን አለመሆኑን በተመለከተ የግራ ቀኝን ማስረጃ እንዱሁም፣ እንዲስፈላጊነቱ፣ ላልች ተጨማሪ ማስረጃዎችን ጭምር አስቀርቦ በመመርመር ባንኩ አደራ አስቀማጭ ከመሆኑ አንፃር ክፍያን በመፈጸም ረገድ እንዱያደርግ ከሚጠበቅበት ጥንቃቄ አንፃር በማገናዘብ ተገቢዉን ዉሳኔ እንዱሰጥበት መዝገቡ በፍ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 343(1) መሰረት ተመልሶለታል።
በዚህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.