ስጦታ የሚደረገው ስጦታው በተደረገበት ቀን የአስተላላፉው /የሰጭው/ የራሱ በሆነ ሀብት ላይ ብቻ ስለመሆኑ የፍትሒብሓር ህግ አንቀጽ 2427፤2451 /1/
No summary available.
ግንቦት 27 ቀን 2010 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጰውልስ ኦርሺሶ አመልካች፡- ወ/ሮ ውዳ ደሴ- ጠበቃ አቶ አለማየሁ የኔት ቀረበ።
ተጠሪዎች፡- 1.አወቀ ደሴ 2 አዱስ ደሴ የቀረበ የለም።
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
የነገሩ አመጣጥ የውርስ ንብረት ክርክርን የሚመለከት ነው። ጉዲዩ የተጀመረው በአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት በአዊ ብሓረሰብ ዞን የባንጃ ወረዲ ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁን ተጠሪዎች ከሳሾች ሲሆኑ አመልካች ደግሞ ተከሳሽ ነበሩ። ከሳሾች /የአሁን ተጠሪዎች/ በ14/07/2008 ዓ/ም ጽፈው ባቀረቡት ክስ ወላጅ አባታቸው አቶ ደሴ ካሰ እና እናታቸው ወ/ሮ እምየ በላይ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ገልጸው የውርስ ንብረቶችን 1ኛ/ 56 ዘንግ ቆርቆሮ ቤት ግምቱ ብር 6,000 /ስድስት ሺህ ብር/፣ ሳር ቤት ግምቱ ብር 3,000 /ሶስት ሺህ ብር/፣100 ባህርዛፍ ግምቱ ብር 3,000 /ሶስት ሺህ ብር/ 2ኛ/ አዋሳኙን ጠቅሰው በተለያዩ በአምስት ቦታዎች የሚገኝ የእርሻ መሬት ተከሳሽ /የአሁን አመልካች/ ይዘው ያለትን የውርስ ድርሻ እንዱሰጡዋቸው ፈቃደኛ ሆነው ስላልተገኙ ድርሻቸውን እንዱሰጡ ዲኝነት ጠይቀዋል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የአሁን አመልካች /የሥር ተከሳሽ/ በቀን 12/09/2009 ዓ/ም በተጻፈ መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረቡ ሲሆን ይኸውም የከሳሾች እናት በ1993 ዓ/ም ስለሞቱ የእናታቸውን ድርሻ ለመጠየቅ መብታቸው በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1000/1/ መሰረት በሶስት ዓመት ይርጋ ይታገዲል የሚል ነው። ለፍሬ ነገሩ በሰጡት መልስ ቆርቆሮ ቤቱን በተመለከተ ከሟች አባታቸው በቀን 18/6/2007 ዓ/ም በተደረገ የሥጦታ ውል መሰረት ተከሳሽ ከባለቤታቸው ጋር የሰሩት በመሆኑ ከሳሾችን አይመለከታቸውም፣ሳር ቤቱን ድርሻቸውን መካፈል ይችላለ፣ከሳሾች አዋሳኞችን ጠቅሰው ካቀረቡት የእርሻ መሬት መካከል በክሳቸው ተራ ቁጥር 3 ላይ የተጠቀሱትን አራት ቀዲ መሬት አባታቸው በሥጦታ ውል የሰጡ በመሆኑ ከሳሾችን አይመለከታቸውም የተቀረውን የእርሻ መሬት በተመለከተ የእናታቸው ድርሻ በይርጋ የሚታገድ ሆኖ የአባታቸውን ድርሻ ከተከሳሽ ጋር መካፈል ይችላለ፣ባህርዛፈንም በተመለከተ ድርሻቸውን መካፈል እንደሚችለ ገልጸው ተከራክረዋል።
ጉዲዩን የተመለከተው የባንጃ ወረዲ ፍርድ ቤት በይርጋ መቃወሚያ ላይ ማስረጃዎችን ሰምቶ ግራ ቀኙ እናት ከሞቱ በኃላ ክርክር የተነሳባቸው ንብረቶች አባታቸው እስከ ሞቱበት 2007 ዓ/ም ድረስ በእጃቸው የቆየ በመሆኑ እና የሥር ከሳሽ ከአባታቸው ጋር አብረው ቢኖሩም ንብረቶቹን የያዙት ከእሳቸው ሞት በኃላ በመሆኑ ይርጋ ሉያገድ አይችልም ሲል ብይን ሰጥቷል። ፍሬ ነገሩንም በተመለከተ ግራ ቀኙን አከራክሮ፣ ምስክሮችን ቃል ሰምቶና ሰነድ ማስረጃዎችን መርምሮ የቆርቆሮ ቤት አባታቸው በውል በሰጡት ቦታ ላይ ተከሳሽ እና ባለቤታቸው የሰሩበት መሆኑ ስለተረጋገጠ ለከሳሾች አይገባም፣ ተከሳሽ አባቷ በሥጦታ ሰጥቶኛል ያለችውን 4 ቀዲ መሬት በተመለከተ ሟች ሥጦታ ቢሰጥም እንኳ የራሱን ድርሻ እንጂ የላልችን ልጆች በሚጎዲ መልኩ መስጠት የለበትም፣ ማለትም የእናታቸውንም ሆነ የራሱን ድርሻ ማለት ነው፡፤ የሳር ኪዲን ቤት፣የባህርዛፍ ተክል የሟቾቹን ተከሳሽ መያዟን እና ያለ መሆኑን ያመነች በመሆኑ ባመነችበት መሰረት በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 242 መሰረት በዓይነት ወይንም በግምት ድርሻቸውን ለከሳሾች ልትሰጥ ይገባል በማለት ወስኗል።
የአሁን አመልካች /የሥር ከሳሽ/ ውሳኔውን ቅር ተሰኝተው ለአዊ ብሓረሰብ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበዋል።የይግባኝ ቅሬታ ይዘትም፡- የእናታቸው ድርሻ በይርጋwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ቀሪ መሆን ሲገባው በብይን መታለፈ አግባብ አይደለም፤ አባቴ በሥጦታ የሰጠኝን አራት ቀዲ መሬት ከሳሾችም እንዱካፈለ መወሰኑ ተገቢ አይደለም የሚል ነው። የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ይግባኙን ተቀብል ክርክራቸውን ከሰማ በኃላ በይርጋ አይታገድም መባለ ተገቢ እንደሆነና ሟች ለአሁን አመልካች በሥጦታ የሰጡትን አራት ቀዲ የእርሻ መሬት አመልካች /ይግባኝ ባይ/ ለመልስ ሰጪዎች /ለአሁን ተጠሪዎች/ ታካፍል መባለ ተገቢ አይደለም በማለት የወረዲ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔን በማሻሻል ወስኗል።
የአሁን ተጠሪዎች ይህን ውሳኔ በመቃወም ለአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን ጠቅላይ ፍርድ ቤቱም ይግባኙን ተቀብል ክርክራቸውን ከሰማ በኃላ ለይግባኙ ምክንያት የሆነው አራት ቀዲ መሬት የግራ ቀኙ ተከራካሪ ወገኖች ወላጆች መሆኑን፣ እናታቸው በ1993 ዓ/ም መሞታቸውን፣ ወላጅ አባታቸው ደግሞ በ2007 ዓ/ም መሞታቸውን፣ መልስ ሰጭ /የአሁን አመልካች/ ደግሞ ሁለንም መሬቶች በሥጦታ አግኝቻለሁ በማለት መከራከሯን ተመልክተናል። በመርህ ደረጃ ማንም ሉያስተላልፍ የሚችለው ያለውንና የእርሱ የሆነን እንጂ የእርሱ ያልሆነን ለማስተላለፍ አይችልም። ስለሆነም የአመልካች አባት ከእሳቸው ድርሻ ውጪ ያለውን የባለቤታቸውን ድርሻ በሥጦታ ማስተላለፍ አይችለም። ስለሆነም የአሁን መልስ ሰጭ /የአሁን አመልካች/ በሥጦታ ሉተላለፍላት የሚገባው የወላጅ አባታቸው ድርሻ የሆነው ሁለት ቀዲ መሬት ብቻ እንጂ የወላጅ እናታቸው ድርሻ የሆነው ሁለት ቀዲ መሬት ግን ይግባኝ ባዮችና መልስ ሰጭ እንደየ ድርሻቸው መብት ያላቸው ስለሆነ በአዋጁ ከተመለከተው አንጻር መካፈል የሚችል ከሆነ እንዱከፊፈለት፣ ለመካፈል የማይችል ከሆነ ግን በሚስማሙት መንገድ እንዱጠቀሙ በማለት ወስኗል።
ይህን ውሰኔ ለማስለወጥ የአሁን አመልካች ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ አቅርበው ተዘግቶባቸዋል።
የአሁን አመልካች የሰበር አቤቱታም ውሳኔውን በመቃወም ሲሆን በጠበቃቸው በኩል የቀረበ የሰበር አቤቱታ ይዘቱም በአጭሩ፡- ሟች ወላጅ እናታችን የሞተችው ነሐሴ 16 ቀን 1993 ዓ/ም ሆኖ እያለ ከ15 ዓመት በላይ ቆይተው ያቀረቡትን ክስ በይርጋ ይታገዲል በማለት እየተቃወምኩ እያለ በብይን መታለፈ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ሉታረም ይገባል፣ሟች ደሴ ካሰ ለአመልካች አራት ቀዲ ይዞታwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
መሬት በሥጦታ ሲያስተላልፍ ተጠሪዎች የሟች እናታችን እማሆይ እምየ በላይ ድርሻ ጭምር በሥጦታ ማስተላለፍ ተገቢ ባለመሆኑ የሥጦታ ውል እንዱፈርስ በማለት በሥር ወረዲ ፍርድ ቤት ዲኝነት አልጠየቁም። አመልካች በቀን 16/03/2005 ዓ/ም የተሰጠ እና በሚመለከተው አካል የፀደቀ የሥጦታ ውል አቅርባ ይህም ውል በፍርድ ፈራሽ ሳይሆን ባልተጠየቀ ዲኝነት ሟች ደሴ ካሰ የሟች ባለቤቱን ድርሻ ጭምር ይዞታ ማስተላለፍ አይችልም በማለት ለአመልካች በሥጦታ የተላለፈልኝን አራት ቀዲ ይዞታ ጭምር ለተጠሪዎች ልታካፍል ይገባል በሚል የተሰጠው ውሳኔ ተጠሪዎች በሥር ፍርድ ቤት ያልጠየቁት ዲኝነት ላይ የተሰጠው ውሳኔ በመሆኑ የህግ ስህተት አለበት እንዱባልልኝ የሚል ነው፡ የሰበር አቤቱታውን አጣሪው መርምሮ በተጠሪዎች በኩል በክስ ቁጥር 2 እና 3 ላይ የተጠቀሰው የይዞታ መሬት ለአመልካች በሥጦታ የተላለፈና ሥጦታም መመዝገብ ያለበት አካል ተመዝግቦና ለአመልካች በተላለፈበት ሁኔታ የሥጦታ ውለ ሳይፈርስ የውርስ ንብረት ነው የተባለበት አግባብነት መጣራት ያለበት መሆኑ ስለታመነበት ጉዲዩ ለሰበር ችልት ይቅረብ ሲል ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርገጎላቸው በጠበቃቸው በኩል በ23/4/2010 ዓ/ም ጽፈው ባቀረቡት መልስ አካራካሪውን መሬትና ሀብት ሟች አባታችን አስከሞቱበት 2007 ዓ/ም ድረስ በእሳቸው እጅ የነበረ መሆኑን፣ እሳቸውም የእናታችንን ድርሻ ጭምር በሥጦታ ማስተላለፊቸውን ግራ ቀኙ ሳንካካድ፣ ሥጦታ ውለም በህግ መሰረት ሉጸና የማይችል በመሆኑ ሉፈጸም አይገባም በሚል በቂ መቃወሚያ ቀርቦበት ይህ ስለመሆኑም ተረጋግጦ የይዞታ መሬቱን ጨምሮ ላልች ሀብቶች የውርስ ሀብት ተብል በድርሻችን ልክ እንድንከፊፈል መወሰኑ ስህተት የላለበት ስለሆነ በቂ ወጪና ኪሳራም ታስቦልን በነፃ እንድንሰናበት በማለት ተከራክረዋል።
የተጠሪዎችን መልስ ለመቀበል በተቀጠረ ቀን አመልካች ባለመቅረባቸው ከፈለጉ የመልስ መልስ ከምርመራ ቀጠሮ ቀን በፉት እንዱያቀርቡና ለተጠሪዎች እንዱያደርሱ ታህሳስ 25 ቀን 2010 ዓ/ም ታዞ የመልስ መልስ አላቀረቡም።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የነገሩ አመጣጥና የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸውን የሚመስል ሲሆን ሟች ለአመልካች በሥጦታ ከሰጡት አራት ቀዲ መሬት የግራ ቀኙን የእናታቸውን ድርሻ ሟች አባታቸው ለአሁን አመልካች በሥጦታ ሉሰጡ አይችለም ተብል የተሰጠው ውሳኔ ህጋዊ መሰረት አለው ወይስ የለውም? የሚል ጭብጥ ተይዞ ጉዲዩ እንደሚከተለው ተመርምሯል። ለዚህ የሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነውን አራት ቀዲ የእርሻ መሬት በተመለከተ ይዞታው የወላጆቻቸው ስለ መሆኑ ግራ ቀኙን አላከራከረም። ነገር ግን ከዚህ ጋር በተያያዘ የአሁን አመልካች ሁለት መከራከሪያዎችን ያነሳለ። የመጀመሪያው የአመልካችና የተጠሪዎች እናት በ1993 ዓ/ም ስለሞቱ የአሁን ተጠሪዎች እናታቸው ከሞቱ ከ15 ዓመት በኃላ ያቀረቡ ክስ በመሆኑ በይርጋ ይታገዲል የሚል ነው። ለዚህ መቃወሚያ የአሁን ተጠሪዎች ለሥር ፍርድ ቤት በሰጡት መልስ የእናታቸው ድርሻ እስከ አባታቸው ሞት ማለትም እስከ 2007 ዓ/ም ድረስ በአባታቸው እጅ የቆየ በመሆኑና የሥር ተከሳሽ /የአሁን አመልካች/ እጅ ተይዞ ያልቆየ በመሆኑ በይርጋ አይቋረጥም በማለት ተከራክረዋል። ይህንን በተመለከተ የሥር ወረዲ ፍርድ ቤት የሟች እናታቸው ድርሻ አባት እስከሞቱበት እስከ 2007 ዓ/ም ድረስ በአባታቸው እጅ የቆየ እንጂ የአሁን አመልካች ይዘው የቆዩበት ባለመሆኑ በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1000/1/ መሰረት በሶስት ዓመት ይርጋ ሉቋረጥ አይችልም በማለት ብይን ሰጥተዋል። አመልካች ዋናው ጉዲይ ውሳኔ ሲያገኝ ይህን ብይን የመጀመሪያ የይግባኝ ቅሬታ አድርገው ቢያቀርቡም ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የአዊ ብሓረሰብ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አጽንቶበታል። የአሁን አመልካች በዚህ ቅር ተሰኝተው ይግባኝ አላቀረቡም። በከፍተኛ ፍርድ ቤት ለዚህ የሰበር ምክንያት የሆነው መሬት ለአሁን አመልካች በሥጦታ የተሰጣቸው በመሆኑ ለተጠሪዎች አይገባም ተብል ስለተወሰነ የይርጋውን ክርክር አመልካች ትተውታል። የአሁን ተጠሪዎች አራት ቀዲ መሬት ለአሁን አመልካች ይገባል ተብል መወሰኑን በመቃወም ይግባኝ ለአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው የእናታቸውን ድርሻ አባታቸው ለአሁን አመልካች በሥጦታ ሉሰጡ አይችለም ተብል ተወስኗል። የአሁን አመልካች ይህን ውሳኔ ለማስለወጥ ለክልለ ሰበር ችልት አቤቱታ አቅርበው ተዘግቶባቸዋል። አመልካች ለዚህ ችልት ባቀረቡት አቤቱታ ላይ አንደ የቅሬታ ነጥብ ይርጋን የተመለከተ ነው። ይህ ቅሬታ ነጥብ /ጥያቄ/ ሥነ ሥርዓታዊ ነው ወይ? የሚለውን ጥያቄ ያስነሳል። ይኸውም ከላይwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
እንደተገለጸው የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ አመልካች ያቀረቡትን የይርጋ ቅሬታን በተመለከተ የወረዲ ፍርድ ቤት የሰጠውን ብይን ተገቢ ነው ብል ሲያፀና የአሁን አመልካች ይግባኝ አላለበትም። ይልቁንም በዋናው ጉዲይ ላይ የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ አይደለም በማለት ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያለት የአሁን ተጠሪዎች ናቸው። በመሆኑም ይርጋን በተመለከተ የአሁን አመልካች ከከፍተኛ ፍርድ ቤት ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ባላለበት ሁኔታ አሁን ለዚህ ችልት ይህን በተመለከተ በቅሬታነት ማንሳታቸው የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ስለ ይግባኝ አቀራረብ ሥርዓት የደነገገውን አንቀጽ 320 እና ተከታዮቹን ድንጋጌዎችን የተከተለ ባለመሆኑ ቅሬታው ተቀባይነት ያለው አይደለም።
አመልካች ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረቡት የሁለተኛ ቅሬታ ነጥብ አባታቸውም በህግ አግባብ ከሰጡት አራት ቀዲ መሬት ላይ ሁለቱ ቀዲ የእናታቸው ስለሆነ ግራ ቀኙ እኩል ይካፈለ ተብል የተሰጠው ውሳኔ ተጠሪዎች የሥጦታ ውል ይፍረስልን ብለው ባልጠየቁት ዲኝነት ላይ የተሰጠ ውሳኔ ስለሆነ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው የሚል ነው። ለዚህ የቅሬታ ነጥብ የአሁን ተጠሪዎች ለዚህ ችልት በሰጡት መልስ አካራካሪውን መሬትና ሀብት ሟች አባታችን እስከሞቱበት 2007 ዓ/ም ድረስ በእሳቸው እጅ የነበረ ሲሆን እሳቸውም የእናታችንን ድርሻ ጭምር በሥጦታ ማስተላለፈቸውን ግራ ቀኙ ሳንካካድ፣ ሥጦታ ውለም በህግ መሰረት ሉጸና የማይችል በመሆኑ ሉፈጸም አይገባም በሚል በቂ መቃወሚያ ቀርቦበት ይህ ስለመሆኑም ተረጋግጦ የይዞታ መሬቱን ጨምሮ ላልች ሀብቶች የውርስ ሀብት ተብል በድርሻችን ልክ እንድንከፊፈል ተወስኗል በማለት ተከራክረዋል። አመልካችና ተጠሪዎች በሥር ፍርድ ቤት ከተከራከሩባቸው ንብረቶች መካከል የአሁን አራት ቀዲ መሬት አንደ ሲሆን የአሁን ተጠሪዎች ይህ መሬት የአባታቸው ብቻ ሳይሆን የሟች እናታቸው ድርሻ ጭምር ያለበት ስለሆነ ለአሁን አመልካች በሥጦታ መሰጠቱ ህጋዊ አይደለም በማለት መከራከራቸውን የሥር ፍርድ ቤት የውሳኔ ግልባጭ ያስረዲል። ሥጦታው መብታችንን የሚጎዲ ስለሆነ በህግ ይሁንታ ሉሰጠው አይገባም የሚል ክርክር እስከ ቀረበ ድረስ ሥጦታው እንዱፈርስ የተለየ የዲኝነት ጥያቄ ላቀርብ ይገባል የሚለው የአመልካች ክርክር ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ግራ ቀኙ አባት አራት ቀዲ መሬት ለአሁን አመልካች ሲሰጡ የግራ ቀኙ እናት ድርሻ እንዲለ የአሁን አመልካችም አይክደም። ነገር ግን ይህን በተመለከተ አመልካች ይርጋን አንስተው ቢከራከሩም ጥያቄኣቸው ወድቅ ሆኖባቸዋል።
ይህ ከሆነ አባት ከራሳቸው ድርሻ አልፈው ሟች ባላቤታቸውን ድርሻ ጭምር ለአሁን አመልካች ሉሰጡ ይችላለ ወይ? የሚለው ጥያቄ ምላሽ ሉያገኝ የሚገባው ነው።
የአመልካች አባት ድርሻቸውን በሥጦታ ለአመልካች መስጠት ይችላለ እንጂ የባለቤታቸውን ማለትም የግራ ቀኙን እናት ድርሻ ሉሰጡ የሚችለበት የህግ አግባብ አይኖርም። በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 2427 “ ከንብረቶቹ አንደን የሚለቅበት” በማለት የተደነገገውም ይህንኑ የሚያሳይ ነው። እንዱሁም የፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 2451 /1/ የተመለከተው ጽንሰ ሀሳብም አስተላላፉው /ሰጭ/ የራሱ የሆነን ሀብት ብቻ ሉያስተላልፍ እንደሚገባ የሚያስገነዝብ ነው። በያዝነው ጉዲይ ሟች ደሴ ካሳ ለአሁን አመልካች ሥጦታ ያደረጉት የአሁን ተጠሪዎችን ወላጅ እናት ድርሻ መሬት ነው። ይህም ደግሞ ከፍ ሲል ከተመለከተው የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 2451 /1/ አንጻር ሲታይ አግባብነት ያለው አይደለም። ፡ በመጨረሻም ለአሁን አመልካች በሥጦታ ሉተላለፍላቸው የሚገባው የወላጅ አባታቸው ድርሻ የሆነው ሁለት ቀዲ መሬት ብቻ እንጂ የወላጅ እናታቸው ድርሻ የሆነው ሁለት ቀዲ መሬት ላሆን ስለማይችል ግራ ቀኙ እንደየድርሻቸው ሉካፈለት ይገባል በማለት የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔም ሆነ ይህ ውሳኔ በአቤቱታ የቀረበለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በትዕዛዝ መዝጋቱ ሲታይ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አልተገኘም። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 45274 በቀን 13/11/2009 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ እንዱሁም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/አ/መ/ቁ. 70347 በቀን 20/2/2010 ዓ/ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 348 /1/ መሰረት ፀንቷል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የአመልካች አባት ከድርሻቸው ውጪ ያለውን የእርሻ መሬት ለአሁን አመልካች በሥጦታ ሉሰጡ አይችለም፤የሟች እናታቸውን ድርሻ የሆነው ሁለት ቀዲ የእርሻ መሬት ለግራ ቀኙ ላሆን ይገባል ተብል በተሰጠው ውሳኔ ላይ የተፈጸመ መሥረታዊ የህግ ስህተት የለም ተብል ተወስኗል።
የዚህን ችልት ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
የውሳኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይድረሳቸው።
መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
ቅ/ሀ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት።
No topics extracted.