የፍርድ ማስፈጸሚያ ይሆናል የተባለን የፍርድ ባለዔዲ ንብረት ሲጠቀምበት መቆየቱ የተረጋገጠበት የፍርድ ባለገንዘብ ለዚሁ ጊዜ ዉስጥ ከዋናዉ ገንዘብ በተጨማሪ የፍርድ ባለዔዲ ለባለገንዘቡ ወለድ የመክፈል ኃላፉነት የላለበት ስለመሆኑ፤ የፍ/ብ/ህግ አንቀጽ1803፣1751 እና 2478
No summary available.
መ/ቁ/136653 ግንቦት 23 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች፡ ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንዲሻዉ አዲነ ሸምሱ ሲርጋጋ እትመት አሰፊ አመልካች፡ አቶ ገ/ሚካኤል በርሀ ተጠሪ፡ አቶ ገ/ዮሃንስ ወ/ጊዮርግስ መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ በመሆኑ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
በዚህ መዝገብ የቀረበዉ ጉዲይ የአፈጻጸም ክርክር ላይ ልዩ ልዩ ወጪና ወለድ ክፍያ የሚመለከት ነዉ። የክርክሩ አመጣጥ ባጭሩ ሲታይ አመልካች የፍርድ ባለእዲ ተጠሪና ላልች በዚህ መዝገብ ያልተጠሩ ሰዎች የኢት/ልማት ባንክን ጨምሮ ፍርድ ባለመብቶች ሆነዉ የአመልካች ንብረት የሆነዉን በመቀላ ከተማ የሚገኝ የእንጨትና የብረታ ብረት ስራ ድርጅት ከነቤቱ በሀራጅ ለማሸጥ ሲንቀሳቀሱ ተጠሪ የፍርድ ባለገንዘቦችን ብር ለመክፈል ተስማምቶ ንብረቱን ያለጨረታ ለማስቀረት እንዱችል ፍርድ ቤቱን ጠይቆ የመቐለ ማእከላዊ ፍርድ ቤት ፈቅድለት ንብረቱን በ27/10/1999 ዓ.ም በተሰጠ ትእዛዝ የተረከበ ሲሆን አመልካች ይህንን በመቃወም ለክልለ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት እና ሰበር ችልት ያቀረበዉ አቤቱታ ተቀባይነት በማጣቱ ለዚህ ሰበር ችልት አቤቱታ አቅርቦ ሰበር ችልቱም በመ/ቁ/45733 በ29/11/02 ዓ.ም በሰጠዉ ፍርድ ተጠሪ የፍርድ ባለእዲን ተክቶ ለባለመያዣ ባንክ ገንዘቡን ከፍል ንብረቱን ካስለቀቀ እና ለላልች ባለገንዘቦች ገንዘባቸዉን ከከፈለ በኋላ የፍርድ ባለእዲዉን ንብረትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ያለጨረታ እንዱረከብ ሳይሆን ጨረታ ተከናዉኖ ራሱም ከፈቀደ በጨረታዉ ተካፊይ ሆኖ ላሆን ይገባል በማለት የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ በመሻር ጨረታ እንዱከናወን በትእዛዝ መልሷል። ይህንንም ተከትል የአመልካች ንብረት በጨረታ ከተሸጠ በኋላ ተጠሪ ቀደም ሲል ለፍርድ ባለገንዘቦች የከፈለዉ ገንዘብ እስከነወለደ ከሽያጭ ገንዘብ ላይ እንዱከፈለዉ በመጠየቁ የመቐላ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ ዋናዉ ፍርድ ላይ ለባለገንዘቦቹ የተፈረደዉ ዋና ገንዘብ ተከፍል አለቀ ድረስ ወለድ እንደሚታሰብ ስለተወሰነ ተጠሪ በጊዜዉ ገንዘቡን ለባለገንዘቦች ከራሱ ወጪ አድርጎ ስለከፈለ ወለድ ሉያገኝ ይገባል ካላ በኋላ ወለደ ሉታሰብ የሚገባዉ ከመቼ ጀምሮ ነዉ ለሚለዉ ጥያቄ ላይ በአብላጫ ድምጽ ተጠሪ ድርጅቱን ከተረከበበት ከ27/10/99 ዓ.ም እስከ 13/03/08 ዓ.ም ማለትም አመልካች ዋናዉን ገንዘብ በሞዳል 85 እስከ አስያዘበት ጊዜ ድረስ ያለዉን ወለድ በባንክ ምጣኔ መሰረት ተሰልቶ ለተጠሪ እንዱከፈል ትእዛዝ ሰጥቷል።አናሳዉ ድምጽ ወለድ ለተጠሪ ሉታሰብ እንደሚገባ ተስማምቶ ጊዜዉን በተመለከተ ግን በከፍተኛ ፍርድ ቤት በ27/10/99 ዓ.ም በተሰጠ ትእዛዝ ተጠሪ ድርጅቱን እንዱረከብ ተደርጎ በእጁ መግባቱ ተረጋግጦ የአፈጻጸም መዝገብ ከተዘጋበት ቀን ጀምሮ ፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልት ጨረታ ሉካሄድ ይገባል በሚል ይህንን ትእዛዝ እስከሻረበት 29/11/02 ዓ.ም ድረስ ላለዉ ጊዜ ተጠሪ ድርጅቱን በእጁ አድርጎ ሲጠቀም ስለነበር ወለድ ሉታሰብ አይገባም ይልቁንም ወለድ ሉታሰብለት የሚገባዉ በ29/11/02 ዓ.ም ጀምሮ አመልካች ገንዘቡን በሞዳል 85 እስከአስያዘበት ጊዜ ድረስ መሆን አለበት የሚል ሀሳብ አስፍሯል።
አመልካች በዚህም ትእዛዝ ቅር በመሰኘት ለክልለ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኝ ቅሬታ የቀረበ ቢሆንም ተቀባይነት አላገኘም።ለዚህ ሰበር ችልት አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ላይ ሲሆን የአመልካች ሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በግራቀኙ መካከል በነበረዉ የገንዘብ ክርክር የትግራይ ክልል ጠ/ፍ/ቤት በመ/ቁ/01885 በ17/10/08 ዓ.ም በዋለዉ ችልት አመልካች በባንክ እዲ ዋስትና ተይዞ የነበረዉን አከራካሪ ቤት የተረከቡት በ13/03/08 ዓ.ም ቢሆንም የባንኩን ወለድ ከ27/10/99 እስከ 13/03/08 ዓ.ም ታስቦ ይክፈለ መባለ በአግባቡ መሆን አለመሆኑን ለመመርመር እንዱቻል በሚል ሰበር አጣሪ ጭብጥ ይዞ ተጠሪ መልስ እንዱሰጥ ተደርጓል። ለተጠሪ መጥሪያ ደርሶ ተለዋጭwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ቀጠሮም ጠይቀዉ በተሰጠዉ ተለዋጭ ቀጠሮ መልስ ባለማቅረቡ መልስ የመስጠት መብቱ ታልፍ መዝገቡ ተመርምሯል።
መዝገቡን መርምረን እንደተገነዘብነዉ ተጠሪ ቀደም ሲል በመቐላ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/01885 በ27/10/99 ዓ.ም በሰጠዉ ትእዛዝ መሰረት አከራካሪዉን ቤትና ድርጅት እንዱረከብ የተደረገዉ ከአመልካች የሚፈለግ የኢት/ልማት ባንክ ብድር ብር 740,963.00 ፣የወ/ሮ ስላስ በርሄ እዲ ብር 80,688.00፣የአቶ ስዩም ተሰማ እዲ ብር 125,568.00 እና የተጠሪዉ ገንዘብ ብር 177,561.00 በድምሩ ብር 1,134,780.00 በመክፈለ ስለመሆኑ ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ ተችሎል።በዚሁ አግባብ ተጠሪ የፍርድ ባለእዲን/የአመልካቹን /ንብረት ተረክቦ ስመ ሀብቱም በስሙ ተመዝግቦለት ንብረቱን እየተጠቀመ የቆየ ሲሆን አመልካች ለዚህ ሰበር ችልት ያቀረበዉ አቤቱታ ተቀባይነት አግኝቶ ተጠሪ የአመልካችን ንብረት ያለጨረታ መረከቡ ተገቢ አይደለም ተብል በሰበር መ/ቁ/45733 ዉሳኔ ተሰጥቶ በንብረቱ ላይ ጨረታ እንዱደረግ ወደ ስር ፍርድ ቤት መመለሱም ተረጋግጧል።ይህንን ተከትል አመልካች በተጠሪ እጅ ያለዉ ቤትና ድርጅት በጨረታ እንዱሸጥ ትእዛዝ እንዱሰጥ ለከፍተኛዉ ፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርቦ በክርክር ላይ እያለ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ክርክር የተነሳበትን ቤትና ድርጅት በተጠሪ ስም በመያዣ ይዞ ብር 1,700,000 መስከረም 29 ቀን 2003 ዓ.ም በተደረገ ዉል ያበደረዉ መሆኑን ገልጾ የቅድሚያ መብት ያለዉ በመሆኑ በጨረታ እንዲይሸጥ በጣልቃ ገብነት ስለመከራከሩና እስከ ፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ደርሶ ባንኩ ንብረቱ እግድ ያለበትንና ሰበር መ/ቁ/45733 ዉሳኔ የተሰጠበትን በሚጻረር ሁኔታ በመያዣነት መያዙ ከቅን ልቦና ዉጪ ነዉ ተብል ስለመወሰኑ ሰበር መ/ቁ/80258 ላይ በ07/09/05 ዓ.ም የተሰጠዉ ዉሳኔ ይዘት ያስረዲል። ከዚህም ባሻገር ተጠሪና ባለቤቱ የሆነችዉ ወ/ሮ/ ኪሮስ ሲባጋድስ እግድ ያለበትን ንብረት እግድ እንደላለበት አስመስለዉ ለባንክ መያዣ አስይዘዉ ብድር ወስደዋል ተብለዉ በማታለል ወንጀል ተከሰዉ የጥፊተኝነትና የቅጣት ዉሳኔ የተላለፈባቸዉ ስለመሆኑም የፍርድ ቤት ዉሳኔ ግልባጭ ከዚህ መዝገብ ጋር ተያይዟል።ከዚህ በኋላ አመልካች ቤቱ ከተጠሪ እጅ ወጥቶ በጨረታ እንዱሸጥ ሲጠይቁ ተጠሪ ለፍርድ ባለገንዘቦች የከፈለዉን ገንዘብ በሞዳል 85 እንዱያስይዙ የከፍተኛዉ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/01885 ላይ ትእዛዝ መስጠቱንና አመልካችም ገንዘቡን በ13/03/08 ዓ.ም በሞዳል 85 ማስያዙ በስር ፍርድ ቤት የተረጋገጠ ፍሬነገር ነዉ።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
እንግዱህ አከራካሪዉ ጉዲይ አመልካች ለተጠሪ ወለድ ሉከፍል ይገባል ወይስ አይገባም? ወለድ ሉከፍል ይገባል ከተባለስ ከመቼ ጀምሮ ይታሰብለታል? የሚለዉ ነዉ ።በመሰረቱ ባለእዲ ወለድ ሉከፍል የሚገደደዉ በዉል ሲገለጽ ወይም በፍርድ ሲወሰን አሉያም በህግ በግልጽ የተደነገገ ሲሆን እንደሆነ ከፍ/ብ/ህግ አንቀጽ1803፣1751 እና 2478 ድንጋጌዎች ይዘት መገንዘብ ይቻላል።በመሆኑም አመልካች የፍርድ ባለእዲ መሆኑና የፍርድ ባለመብቶች ገንዘብ ተከፍል አለቀ ድረስ ወለድ እንዱታሰብ በዋናዉ ክርክር መዝገብ ፍርድ መሰጠቱ እና ተጠሪ አመልካችን ተክቶ ለፍርድ ባለገንዘቦች ገንዘቡን መክፈለ እስከተረጋገጠ ድረስ ተጠሪ ዋናዉ ገንዘብ ተጠቃል እስከ ከፈለዉ ድረስ ዋናዉን ገንዘብ ብቻ ሳይሆን ወለደንም ጭምር ማግኘት እንዲለበት በፍርድ የተላለፈለት መብት ከመሆኑ አኳያ በመርህ ደረጃ ተቀባይነት ያለዉ ነዉ። ነገር ግን ተጠሪ የአመልካችን ንብረት ከ27/10/99 ዓ .ም ጀምሮ በእጁ አድርጎ እስከ 13/03/08 ዓ.ም ድረስ ላለፈት 9 ዓመታት ንብረቱን በእጁ አድርጎ እየተጠቀመበት መሆኑን በመግለጽ ወለድ ሉታሰብ እንደማይገባ አመልካች አጥብቆ መከራከሩን መዝገቡ ያስረዲል።ስለሆነም በእርግጥም ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት በ27/10/99ዓ.ም በተሰጠዉ ትእዛዝ መሰረት የአመልካችን ንብረት በእጁ አድርጎ ሲጠቀም በቆየበት ጊዜ ከዋና ገንዘብ በተጨማሪ ለገንዘቡ ወለድ እንዱታሰብ ማድረግ ተጠሪ ያለአግባብ እንዱበለጽግ አመልካች ደግሞ ያለአግባብ እንዱጎዲ የሚያደርግ እንደሆነ መረዲት አዲጋች አይደለም።
ስለሆነም ለተጠሪ ወለድ መታሰብ አለበት ቢባል እንኳን ወለድ ከመቼ ጀምሮ ሉታሰብ ይገባል የሚለዉን ለመወሰን ተጠሪ የአመልካችን ንብረት በሰበር ችልት በመ/ቁ/45733 በተሰጠ ፍርድ መሰረት መልሶ ለአመልካች ያስረከበበት ወይም ከተጠሪ እጅ ወጥቶ በሃራጅ የተሸጠበት ቀን በግልጽ ሉታወቅ ይገባል።በዚህ ረገድ ደግሞ አመልካች ቤቱና ድርጅቱ በሃራጅ እንዱሸጥ ገንዘቡን በሞዳል እንዱያስዝ የስር ፍርድ ቤት ትእዛዝ መስጠቱን እና ቤቱና ድርጅቱ ከተጠሪ እጅ ወጥቶ ወደ ሐራጅ ስርዓት እንዱገባ የተደረገዉ በ13/03/08 ዓ.ም ስለመሆኑ በስር ፍርድ ቤት ትእዛዝ መሰጠቱን ገልጾ አመልካች ያቀረበዉን ክርክር የስር ፍርድ ቤት ትእዛዝ የሚያስለዉጥ ክርክርና ማስረጃ በተጠሪ በኩል አልቀረበበትም።ከዚህም ባሻገር ቀደም ሲል ተጠሪ ለክልለ ጠ/ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና ሰበር ሰሚ ችልት እንደቅደም ተከተለ በመ/ቁ/ 81191 በ05/05/08 እና በመ/ቁ/52053 በ04/06/08 ዓ.ም በተሰጠ ትእዛዝ የተጠሪwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የወለድ ጥያቄ ዉድቅ ተደርጎ ያደረዉን ንብረቱ በጨረታ ከተሸጠ በኋላ በሂሳብ መተሳሰብ ሰበብ የወለድን ጉዲይ እንደአዱስ በተጠሪ በኩል ጥያቄ ሲቀርብለት ከፍተኛዉ ፍርድ ቤት ተቀብል በ17/10/08 ዓ.ም በአብላጫ ድምጽ ወለድ ከ27/10/99 ዓ.ም እስከ 13/03/08 ዓ.ም ድረስ ይታሰብለት ማለቱ ፍርድ ቤቱ ራሱ በ05/05/08 ዓ.ም ከሰጠዉ ትእዛዝ ጋር የሚቃረን በመሆኑ ስነስርዓታዊ አይደለም።
ሲጠቃለል የፍርድ ማስፈጸሚያ ይሆናል የተባለዉን የአመልካችን ንብረት ተጠሪ ከ27/10/1999 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 13/03/08 ዓ.ም ማለትም ለፍርድ ባለገንዘቦች የከፈለዉ ዋና ገንዘብ በሞዳል እስከተያዘበት እለት ድረስ ንብረቱን በእጁ አድርጎ ሲጠቀምበት የነበረ ከመሆኑም በተጨማሪ በባንክ በመያዣ አስይዞ ገንዘብ ብድር የወሰደበት መሆኑ ጭምር በክርክሩ ሂደት የተረጋገጠ ነዉ። በመሆኑም ተጠሪ በአመልካች ንብረት ሲጠቀም መቆየቱ ተረጋግጦ እያለ ለዚሁ ጊዜ ዉስጥ ከዋናዉ ገንዘብ በተጨማሪ አመልካች ለተጠሪ ወለድ እንዱከፍል በስር ፍርድ ቤት በአብላጫ ድምጽ የተሰጠዉ ዉሳኔ እና በክልለ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የጸናዉ ፍትሃዊና ምክንያታዊ ባለመሆኑ ሉታረም ይገባል ብለናል።በዚሁ አግባብ ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል።
1ኛ/የመቐላ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/01885 ላይ በ17/10/08 ዓ.ም የሰጠዉ ብይን እና ይህንኑ በማጽናት የክልለ ጠ/ፍ/ቤት በመ/ቁ/87641 በ09/03/09 ዓ.ም የሰጠዉ ትእዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁ/348/1/ መሰረት ተሽሯል።
2ኛ/ተጠሪ በአመልካች ንብረት ሲጠቀም መቆየቱ ስለተረጋገጠ አመልካች ወለድ የመክፈል ሃላፉነት የለበትም ብለናል።ይጻፍ
No topics extracted.