በአንድ የብድር ዉል ላይ ያለ ፊርማ የኔ አይደለም የሚል ክርክር በመነሳቱ በብድር ዉለ ላይ ያለዉን ፊርማ ተበዲሪው በመካደ በፍረንሲክ ምርመራ የእሱ ፊርማ አለመሆኑ የተረጋገጠ ሰነድ ላይ ፊርማው የተበዲሪው ስለመሆኑ አበዲሪው በሰዉ ምስክሮች ላስረዲ በማለት የሚያቀርበው አቤቱታ ተቀባይነት አቶ አክልለ ጌታሁን እና ወ/ሮ ፍሪህይወት አሰፊ www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XII ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 2006 እና 2472(1)
No summary available.
ቀን፡- 24/1/2011ዓ.ም ዳኞች፡ ..1. ተኽሉት ይመሰል 2. ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) 3. ቀነዓ ቂጣታ 4. ተሾመ ሽፈራው 5. አብዬ ካሳሁን አመልካች፡ .፡- አቶ አክሉለ ጌታሁን ጠበቃ ክፍለ ታደሰ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ፍሬህይወት አሰፊ ጠበቃ ቸርነት ተገኝ ቀረቡ መዝገቡ መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
አመልካች በመዝገብ ሚያዝያ 12 ቀን 2007ዓ.ም ባቀረቡት ክስ የአሁን ተጠሪ በብድር የወሰደት ብር 200,000 እንዱመለስላቸዉ ዲኝነት ጠይቋል። ተጠሪ በ23/2/2008ዓ.ም በሰጡት መልስ ከአመልካች የወሰደት ብድር አለመኖሩን፣ ለተጠሪ እናት የተላከዉ ብር 60,000 ፈርመዉ የተቀበለት ብድር አለመሆኑን በመግለጽ ክሱ ዉድቅ እንዱሆን አመልክቷል።
የለም፣ ተከፈለ የተባለዉ ብር 60,000 ከብድር ዉለ ጋር ግንኙነት የለዉም በማለት የስር ፍ/ቤት ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል።
የአመልካች አቤቱታ የመረመረዉ አጣሪ ችልትም የብድር ዉል ሲፈረም የነበሩ ምስክሮች ሳይሰሙ ተጠሪ ሉጠይቁ አይገባም በማለት በስር ፍ/ቤቶች የተሰጠዉ ዉሳኔ ከ
አንፃር እንዱመረመር በድምጽ ብልጫ ለዚህ ችልት አስቀርቦታል። ተጠሪ ሰኔ 7 ቀን 2010ዓ.ም በሰጡት መልስ በስር ፍ/ቤት የብድር ዉል የላለ መሆኑን ተረጋግጦ የተሰጠዉ ዉሳኔ እንዱጸና አመልክቷል። አመልካች አቤቱታቸዉን የሚደግፍ የመልስ መልስ ሰኔ 22 ቀን 2010ዓ.ም አቅርቧል።
ከስር የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸዉ ሲሆን እኛም የሥር ፍ/ቤቶች በሰጡት ፍርድ ላይ ሉታረም የሚችል መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት መሆን አለመሆኑን እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነዉም የአመልካች መሰረታዊ የዲኝነት ጥያቄ በብድር የተወሰደዉ ብር 200,000 እንዱመለስላቸዉ የሚያመለክት ነዉ። ተጠሪ ብድር አለመዉሰዲቸዉን በመግለጽ ተከራክሯል። የስር ፍ/ቤቶች በህጉ አግባብ የተቋቋመ የብድር ዉል ከሚል መደምደሚያ ላይ የደረሱ መሆኑን መዝገቡ ያሳያል። አመልካች እና ተጠሪ እያከራከረ ያለዉ ብድር ዉል ነዉ። አመልካች /ከሳሽ/ የብድር ዉል መኖሩን ለማስረዲት ተጠሪም የተበደሩ መሆኑን ከተረጋገጠ ክፍያ መፈፀማቸዉን ለማስተባበል መቅረብ ያለበት የማስረጃ ዓይነት ምን መሆን እንዲለበት በፍ/ብ/ህ/ቁ. 2472 ላይ በግልጽ ተመልክቷል።
በብድር የተሰጠዉ ገንዘብ ከብር 500,00 በላይ ከሆነ ብድሩን ለማስረዲት የብድር ዉል መቅረብ ያለበት ሲሆን የብድር ዉለ ካልቀረበ ደግሞ ተበዲሪዉwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በፍ/ቤት ካላመነ ወይም በቃለ መሀላ ስር ሆኖ ቃለን ካልሰጠ በስተቀር በልላ አግባብ ማስረዲት እንደማይቻል ድንጋጌዉ ያመለክታል። አመላለሱ በተመለከተም ተመሳሳይ የማስረጃ መርህ የሚከተል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ.
2472(3) ደንግጓአል። በተያዘዉ ጉዲይ አመልካች ብር 200,000 ማበደራቸዉ በመግለጽ ክስ ቢያቀርቡም የብድር ዉለ በተጠሪ አልታመነም። የብድር ዉል የተባለዉ ሰነድ በፍረንሲክ ምርመራ የተደረገለት ሲሆን በሰነድ ላይ ያረፈዉ ፊርማ የተጠሪ አለመሆኑን ተረጋግጧል። እንዱሁም ተጠሪ ወሰደት የተባለዉ ብር 60,000 ብድር ክርክሩ የተያያዘ አለመሆኑን የስር ፍ/ቤት ማረጋገጡን መዝገቡ ያሳያል። አመልካች አጥብቀዉ የሚከራከሩት በሰነድ ላይ የተመለከቱ ምስክሮች ሳይሰሙ ዉሳኔ መስጠቱ ተገቢ አይደለም በሚል ነዉ። በመሰረቱ ዉለ በጽኁፍ እንዱሆን በህጉ በተመለከተበት ሁኔታ ሰነድ ራሱ አስረጂ መሆኑን ነገር ግን ሰነድ የተቀደደ፣ የተሰረቀ፣ የጠፊ ስለመሆኑ ከተረጋገጠ ዉለ በምስክሮች ማስረዲት የሚቻልበት ስርዓት ተመልክቷል። በተያዘዉ ጉዲይ ሰነድ ቀርቧል። በሰነደ ላይ ያረፈዉ ፊርማ ግን የተጠሪ አለመሆኑን ተረጋግጧል። በመሆኑም አመልካች በተጠሪ ተክድ በፍረንዚክ ምርመራ ተጠሪ ፊርማ አለመሆኑን የተረጋገጠዉ ሰነድ ላይ ያለዉ ፊርማ የተጠሪ ስለመሆኑ በሰዉ ምስክሮች ለማስረዲት ያቀረቡት አቤቱታ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 2006 እና 2472(1) ድንጋጌዎች መሰረታዊ ይዘት ያላገናዘበ ነዉ ብለናል።
አስቀርበን እንደመረመርነዉም በብድር ዉለ ላይ ያለዉ ፊርማ የኔ አይደለም የሚል ክርክር በመነሳቱ በብድር ዉለ ላይ ያለዉ ፊርማ ተመርምሮ የተበዲሪ ስለመሆኑ የተረጋገጠ መሆኑን መነሻ በማድረግ እንዱሁም ተጨማሪ ማጣራት በማድረግ ዉሳኔ መስጠቱን የሚያሳይ እንጂ የተካደዉ ፊርማ የተበዲሪ ስለመሆኑ ሳይንሳዊ በሆነ የምርመራ ዘዳ ሳይረጋገጥ የሰዉ ምስክሮች ብቻ በማዲመጥ ዉሳኔ አለመስጠቱን የሚያሳይ ነዉ። እንዱህ ከሆነ ደግሞ አመልካች ያቀረቡት ቅሬታ መሰረት የላለዉ መሆኑን ከሚያሳይ በቀር የሰበርwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ዉሳኔዉ በጭብጥ ከተያዘዉ ጉዲይ አንድና ተመሳሳይ ነዉ ተብል የሚወስድበት የህግ አግባብ አይኖርም። አመልካች በሰበር ቅሬታቸዉ ብር 60,000 መከፈለን ክርክር ያልቀረበበት ነዉ። ያለ ቢሆንም ተጠሪ በስር ፍ/ቤት ባቀረቡት መልስ ብር 60,000 ለተጠሪ እናት የተላከ እንጂ በብድር ወሰደት የተባለዉ ብር 200,000 ከፉል ክፍያ ስለመሆኑ አልተረጋገጠም። አመልካች በስር ፍ/ቤት ክሱን ለማስረዲት የብድር ዉል የተባለዉን ከማቅረብ ዉጭ በቃለ መሀላ ስር ሆነዉ ተጠሪ እንዱያረጋግጡ ያቀረቡት ክርክር ስለመኖሩ መዝገቡ አያሳይም።
በዚህ ሁለም ምክንያት የሥር ፍ/ቤቶች በግራ ቀኙ መካከል በህጉ አግባብ የተቋቋመ የብድር ዉል የለም በማለት የደረሱበት መደምደሚያ ህግን ያገናዘበ ነዉ ከሚባል በቀር መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነዉ ለማለት አልተቻለም።
በዚህም ተከታዩን ወስነናል።
የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ. 226304 በ18/2/2010 የሰጠዉ ፍርድ፣ የፋ/ከ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ. በመ/ቁ. 186042 በ 14/6/2010ዓ.ም የሰጠዉ ፍርድ ጸንቷል።
የዚህ ፍ/ቤት ክርክር ያስከተለዉ ወጪና ኪሳራ ካለ ግራ ቀኙ የየራሳቸዉ ይቻለ ብለናል።
መዝገቡ ተዘጋ ወደ መዝገብ ቤት ተመለሰ።
No topics extracted.