አንድ ጉዲይ ከውል መተካት አንፃር እንዱታይ ይተካል በተባለው እና ተተክቷል በሚባለ ውልች መካከል አቶ በትግለ ከበደ እና www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XI የውለታ ጉዲይም ሆነ የውለታው ምክንያት በይዘቱ አዱስ መሆን እንዲለበትና ይህንኑ በውለታውም አይነት ሆነ ከውለታው ምክንያት አንፃር ታይቶ አዱስ የሆነው ውል ቀደም ሲል ተደርጎ በነበረው ውል ላይ የተመለከቱትን ግዳታዎች በማያጣራጥር አኳኋን ሉያስቀር የሚችል ፈቃድ ከተዋዋይ ወገኖች እንዱኖር አስፈላጊ ስለመሆኑ እና ውልን ከማሻሻል ጉዲይ አንፃር ላታይ የማይገባ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1826 እና 1828 ሽሬ እንዲስላሴ ማረሚያ ቤት
No summary available.
ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ.ም.
ዳኞች- ዲኜ መላኩ ተኽሉት ይመስል ተፈሪ ገብሩ(ዶ/ር) ቀነአ ቂጣታ አብዬ ካሳሁን አመልካች- አቶ በትግለ ከበደ ተጠሪ- ሽሬ እንዲስላሴ ማረሚያ ቤት መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመ/ በ30/10/2009 ዓ.ም ያሳለፈውን ትዕዛዝ በመቃወም ሲሆን ክርክሩ የጀመረው በሽረ እንዲስላሴ ወረዲ ፍርድ ቤት የአሁን አመልካች በተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ነው።
አመልካች ያቀረቡት ክስ ይዘት፡- በተጠሪ ተቋም ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች መንግስት በመደበላቸው በጀት መሰረት ከቀን 15/05/2007 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ዓመት ምግብ አብስዬ ለማቅረብ ከተጠሪ ጋር ውል አድርገናል፤ በሂደት ደግሞ በቀን 23/07/2007 ዓ.ም በውለ መሰረት እየመገብኩ እንደነበር በማረጋገጥ ከቀን 24/07/2007 ዓ.ም ጀምሮ ከሽንኩርት አቅርቦት ተቀንሶ ወደ በርበሬ፣ ስኳር እና ስጋ እንዱሸጋሸግ፤
በዚህ መሰረት የስጋ አቅርቦት ከነበረበት በተጨማሪ አንድ ጊዜ በወር ከተሸጋሸገው ዋጋ ስጋ እንዲቀርብ፤ ውል ከመሻሻለ በፉት ሳይቀርቡ የቀሩ ውዝፍ አቅርቦት በማጣጣም በቀጣይ በስጋ መልክ እንዲቀርብ ተስማምተናል፤ ነገር ግን ተጠሪ ከተሻሻለው ስምምነት ውጪ ስጋ አላቀረብክም በማለት መክፈል የሚገባውን ብር 230,472.00 አላግባብ የቀነሰብኝ በመሆኑ እንዱሁም በትርፍ ያቀረብኩት የሥጋ ዋጋ ብር 152,712.55 ስላልከፈለኝ እንዱከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ተጠሪ ለክሱ በሰጠው መልስ ያላቀረቡት አስቤዛ እና ስጋ በስምምነቱ መሰረት በግራሙ ተለክቶ ባላቀረቡት ልክ ክፍያው የተቀነሰ እንጂ ከውል ውጭ ያስቀረሁት ገንዘብ የለም በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩ በዚህ መልኩ የቀረበለት የወረዲው ፍርድ ቤት የግራቀኙን ክርክርና የምስክሮቻቸውን ቃል እንዱሁም የሰነድ ማስረጃውን መርምሮ በግራቀኙ መካከል የተደረገው የተሻሻለ ውል በወር አንድ ጊዜ አምስተኛ ሆኖ የሚቀርብ ስጋ ለአንድ ታራሚ 700 ግራም ከሳሽ እንዱያቀርብ የሚያስገድድ ስለሆነ፤ ውለ ከመሻሸለ በፉት የነበሩ ውዝፍ አቅርቦቶች በስጋ መልክ እንዱቀርቡ ተስማምተው ውዝፍ የስጋ አቅርቦት በተሻሻለው ውል መሰረት ማቅረብ የነበረበትን አመልካች ስላላቀረበ፤ እንዱሁም ላልች ለክስ ምክንያት የሆኑ አቅርቦቶች አልቀረቡም ተብል በተጠሪ የተቆረጠው ገንዘብ ከሳሽ ግዳታውን ባለመፈፀሙ ምክንያት መሆኑ ተረጋግጧል፤ ስለሆነም አመልካች በውለ መሰረት መቅረብ የነበረባቸውን ስላላቀረበ ለክስ ምክንያት የሆነው ገንዘብ ተጠሪ ቆርጦ ማስቀረቱ ውለን መሰረት ያደረገና አግባብነት ያለው ነው በማለት የክሱን ገንዘብ ተጠሪ የመክፈል ግዳታ የለበትም በማለት ወስኗል።
አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም ቅሬታቸውን ለሰሜን ምዔራብ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። የሰበር አቤቱታው ለዚህ ፍርድ ቤት የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች መስከረም 21/2010 ዓ.ም ያቀረቡት ማመልከቻ በአጣሪ ችልቱ ተመርምሮ በግራ ቀኙ መካከል የተፈፀመው የመጀመሪያ ውል በልላ ውል ተሻሽል እያለ ክፍያው ግን በመጀመሪያው ውል መሰረት እንዱፈፀም በሥር ፍርድ ቤቶች የመወሰኑን አግባብነት ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1826 እና ተከታዮች አኳያ ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ እና ተጠሪ መልስ እንዱሰጥበት ተደርጓል። በዚህ መሰረት ግራ ቀኙ ክርክራቸውን በማጠናከር በፅሁፍ ተለዋውጠዋል።
ከፍሲል ባጭሩ የተመለከትነው የጉዲዩን አመጣጥ ሲሆን ለሰበር ችልቱ የተያዘውን ጭብጥ ከግራ ቀኙ ክርክርና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በስር ፍርድ ቤቶች በተላለፈው ውሳኔ የተፈፀመ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን መርምረናል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ከክርክሩ መረዲት እንደሚቻለው የአሁን አመልካች ባቀረቡት ክስ ተጠሪ ከተሻሻለው ስምምነት ውጪ ስጋ አላቀረብክም በማለት መክፈል የሚገባውን ገንዘብ አላግባብ የቀነሰብኝ በመሆኑና በትርፍ ላቀረብኩት የሥጋ ዋጋም ስላልከፈለኝ እንዱከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት የጠየቁ ሲሆን ተጠሪ በበኩለ ያላቀረቡት አስቤዛ እና ስጋ በስምምነቱ መሰረት በግራሙ ተለክቶ ባላቀረቡት ልክ ክፍያው የተቀነሰ እንጂ ከውል ውጭ ያስቀረሁት ገንዘብ የለም በማለት ተከራክሯል።
ግራ ቀኙ በዚህ መልኩ የተካካደበትን ፍሬ ነገር በማስረጃ ያጣራው የወረዲው ፍርድ ቤት አመልካች ስምምነት ባደረጉባቸው ውልች መሰረት ማቅረብ የነበረባቸውን ስላላቀረቡ የክሱን ገንዘብ ተጠሪ ቆርጦ ማስቀረቱ ውለን መሰረት ያደረገና አግባብነት ያለው ነው በማለት ክሱን ውድቅ አድርጓል። ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ይህንኑ የፍሬ ነገር መደምደሚያ ተቀብልታል።
በልላ በኩል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ የተደረገው የመጀመሪያው ውል በልላ ውል ተሻሽል እያለ ክፍያው በመጀመሪያው ውል መሰረት እንዱፈፀም በሥር ፍርድ ቤቶች የመወሰኑን አግባብነት ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1826 እና ተከታዮች አኳያ ለመመርመር በሚል ሲሆን መዝገቡ እንደሚያሳየው የቀደመው ውል መሻሻል የተደረገበት በአቅርቦት እንጂ በዋጋ ጉዲይ አይደለም። በቀደመው ውል ከነበረው የቀይ ሽንኩርት፣ ቲማቲም እና አትክልት አቅርቦቶች ላይ በመቀነስ በምትኩ ወደ በርበሬ ስኳርና ስጋ አቅርቦት እንዱጨመር መስማማታቸውን የሚያሳይ ነው። የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ የሰጠውም አመልካች ማቅረብ የነበረባቸውን እንዲላቀረቡ ተረጋግጧል በሚል እንጂ ጉዲዩ ከክፍያ ልዩነት አንፃር ታይቶ አይደለም። ከዚህም ላላ ጉዲዩ ከውል መተካት አንፃር እንዱታይ ይተካል በተባለው እና ተተክቷል በሚባለት ውልች መካከል ያለው የውለታ ጉዲይም ሆነ የውለታው ምክንያት በይዘቱ አዱስ መሆን እንዲለበትና ይህንኑ በውለታውም አይነት ሆነ ከውለታው ምክንያት አንፃር ታይቶ አዱስ የሆነው ውል ከዚህ ቀደም ተደርጎ በነበረው ውል ላይ የተመለከቱትን ግዳታዎች በማያጣራጥር አኳኋን ሉያስቀር የሚችል ፈቃድ ከተዋዋይ ወገኖች እንዱኖር አስፈላጊ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1826 እና 1828 የተደነገገ ሲሆን ውልን የማሻሻል ጉዲይ ግን ከዚህ አንፃር ላታይ እንደማይገባ መገንዘብ ይቻላል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የሥር ፍርድ ቤት ከፍሲል እንደተገለፀው አመልካች በውልቹ መሰረት ማቅረብ የነበረባቸውን ስላላቀረቡና ግዳታቸውን አለመፈፀማቸው በማስረጃ ተረጋግጧል ለክስ ምክንያት የሆነውን ገንዘብ ተጠሪ የመክፈል ግዳታ የለበትም በማለት የወሰነው ፍሬ ነገሩን ለማጣራት እና ማስረጃ ለመመዘን ባለው ስልጣን መሰረት ነው። ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በተሰጠው ውሳኔ የተፈፀመ የህግ ስህተት ካለ ከሚመለከት በቀር መሰል የፍሬ ነገር ክርክርን መርምሮ እና ማስረጃ መዝኖ ውሳኔ የሚሰጥም አይደለም።
በአጠቃላይ አመልካች በገቡት ውል መሰረት አለማቅረባቸውና ባጎደለት አቅርቦት ልክ ተጠሪ ክፍያ መቀነሱ በፍሬ ነገር ደረጃ ተረጋግጦ የአመልካች የዲኝነት ጥያቄ ውድቅ መደረጉ ውለን እና ህጉን የተከተለ ነው ከሚባል በቀር ውሳኔው የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው የሚሰኝ ሆኖ አላገኘነውም። ስለሆነም ተከታዩን ወስነናል።
No topics extracted.