አንድ ዉክልና በላዩ ተዘርዝረዉ የተመለከቱትን ጉዲዮችና የነዚሁ ተከታታይ እና ተመሳሳይ የሆነዉን እንደ ጉዲዩ አይነትና እንደ ልማድ አሰራር አስፈላጊ የሆነዉን ማከናወን የሚያስችል ሲሆን ወካዩ የፈጸመዉ ተግባር የወካይና ተወካይ ጥቅሞችን ግጭት የሚያስከትል በሆነ ጊዜ 3ኛዉ ወገን ይህን ሁኔታ ያወቀና ሉያዉቅ የሚገባ መሆኑ ካልተረጋገጠ በቀር ኃላፉነት የማይኖርበት ስለመሆኑ ፍ/ሕ/ቁ 2206፤2187
No summary available.
ጥር 21 ቀን 2010 ዓ.ም.
ዳኞች- ተኽሉት ይመስል ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነአ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራው ፀሃይ መንክር አመልካች- ጅማ ዩኒቨርሲቲ -ነ/ፈጅ ጌታቸው ነጋሽ ቀረቡ።
ተጠሪ- ቢሉሱማ ሚአ የዔፀዋት ዘር አቅራቢ ድርጅት -አቶ ቢሉሱት ሚአ ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ በመቃወም ሲሆን ክርክሩ የጀመረው የአሁን ተጠሪ በምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረበው ክስ ነው። በሥር ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሳሽ አቶ ካሳሁን መሰለ፤ 2ኛ ተከሳሽ ደግሞ የአሁን አመልካች ነበሩ።
ተጠሪ ያቀረበው ክስ ይዘት፡- የተለያዩ ችግኞችን ለማቅረብ ከ2ኛ ተከሳሽ ጋር ውል የፈፀምኩ ሲሆን ስራውን መስራት ስለበዛብኝ 1ኛ ተከሳሽ ይህን ሥራ እንዱሰራልኝ በተወሰኑ ጉዲዮች ላይ እነሱም የችግኝ ዘር መቅረብን አስመልክቶ ጨረታ ላይ እንዱሳተፍ፤ የጨረታ ሰነድ እንዱገዛ እንዱያስገባ፤ ገንዘብ ፈርሞ እንዱወስድ፤
የወሰደውንም ገንዘብ በድርጅቱ ሥም (በቢሉሱማ ሚአ በኢትጵያ ንግድ ባንክ አዲአ ቅርንጫፍ ሂሳብ 0736679) ገቢ እንዱያደርግ ውክልና ስልጣን ሰጥቸዋለሁ፤ ይሁን እንጂ 1ኛ ተከሳሽ የሰጠሁትን ውክልና ስልጣን በህገወጥነት በመጠቀም ከ2ኛ ተከሳሽ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጅማ ቅርንጫፍ ሂሳብ 22 ከሆነው ብር 420,763.00 (አራት መቶ ሃያ ሺህ ሰባት መቶ ስድሳ ሶስት) በቀን 30/12/2006 ዓ.ም ወጪ በማድረግ ወደራሴ ሂሳብ ገቢ ማድረግ ሲገባቸው 2ኛ ተከሳሽ በቀጥታ ወደ ግለ ሂሳብ ቁጥር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቢሾፍቱ ቅርንጫፍ ሂሳብ 041892 አዙሮ ወስዶል፤ 1ኛ ተከሳሽ ባለው ውክልና ስልጣን መሰረት ይህን ገንዘብ ወደራሴ ሂሳብ እንዱመልስ ብጠይቀውም ፍቃደኛ ስላልሆነwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ገንዘቡን ሉከፍለኝ ይገባል፤ ከ2ኛ ተከሳሽ ጋር ችግኞች ለማቅረብ ስንስማማ የገንዘብ ክፍያ ሉከፈለኝ የሚገባውን ገንዘብ በሂሳብ 0736679 ገቢ እንዱያደርጉ ተስማምተን እያለ ከውለ ውጪ ሆነ ብለው እኔን ለመጉዲት ገንዘቤን ወደ 1ኛ ተከሳሽ ሂሳብ በማስገባታቸው የአንድነት ተጠያቂነት አለባቸው፤ ስለሆነም ተከሳሾች ብር 420,763.00 (አራት መቶ ሃያ ሺህ ሰባት መቶ ስድሳ ሶስት) እንዱከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
የሥር 1ኛ ተከሳሽ በሰጡት መልስ ብዙ ወጪ አውጥቼ ከቢሸፍቱ ከተማ እስከ ጅማ ከተማ ተመላልሼ ጨረታውን አሸንፋ ውል ተዋዉዬ የተለያዩ እፅዋቶችን ከተለያየ ቦታ ገዝቼ አቅርቤያለሁ፤ ከሳሽ ገንዘብ ለመክፈልም ሆነ እፅዋቶችን ለማቅረብ ያደረገው አስተዋፅኦ የለም፤ ከጅማ ዩንቨርሲቲ የተከፈለውን የሽያጭ ዋጋ ከከሳሽ ጋር ተስማምተን ለተለያዩ የግዥ ዋጋዎች ክፍያ ውሎል፤ የጽሁፍ ደብዲቤ እኔ እየፈረምኩ የከሳሽ ባለቤት የድርጅቱን ማህተም መታልኝ 2ኛ ተከሳሽ ገንዘቡን በስሜ ባለው ሂሳብ እንዱያስገባ ጠይቄ ገንዘቡ እንዱገባ ተደርጎ ያለብን እዲ የተከፈለ ሲሆን የቀረው ትርፍ ጥቂት ስለሆነ ከከሳሽ ጋር ሂሳብ እንድንሰራ እና የሚከፈለኝን ክፍያ ከፍልኝ እንዱያጠናቅቅ ከሳሽን ስጠይቀው ፈቃደኛ አልሆነም፤ ስለሆነም በሂሳብ ባለሙያ ተጣርቶ ያወጣሁት ገንዘብ እንዱቻቻል በማለት ተከራክረዋል።
የአሁን አመልካች በበኩለ በሰጠው መልስ ከከሳሽ ጋር በተደረገው ውል መሰረት ለቀረበው ችግኝ በውለ የተገለፀውን ብር 420,763.00 ከፍያለሁ፤ ከሳሽ ስራውን የሚሰራው በተወካዩ 1ኛ ተከሳሽ በኩል ነው፤ 1ኛ ተከሳሽ ገንዘቡን መውሰድ እንደሚችል የውክልና ሰነደ ይገልፃል፤ ይህ በመሆኑ ገንዘቡን ለ1ኛ ተከሳሽ ለመክፈል የህግ መሰረት ያለኝ ሲሆን በተሰጠው ውክልና ላይ የተመሰረተ ነው፤ የሚከፈለው ገንዘብ ወደተወካዩ ሂሳብ እንዲይገባ በሚል በውክልና ሰነደ አልተገለፀም፤ በፋዳራል ገንዘብ ክፍያ መመሪያ ቁጥር 4/2003 አንቀፅ 6(5) መሰረት ከብር 50,000.00 የሚበልጥ ክፍያ ወደሚከፈለው ሰው ባንክ ሂሳብ ቁጥር በማሳለፍ ክፍያ መፈፀም እንዲለበት ይደነግጋል፤ በዚሁ መሰረት ተወካይ የሂሳብ 041892 አቅርበው ገንዘቡ ተላልፎል፤ የከሳሽ ተወካይ ክፍያ እንዱፈፀምለት የጠየቀበት ደብዲቤ በከሳሽ ማህተም ተደግፍ የቀረበ ነው፤ ስለሆነም ከሳሽ እኔን መክሰሱ ተገቢ አይደለም ብሎል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ክርክሩ በዚህ መልኩ የቀረበለት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ መርምሮ 1ኛ ተከሳሽ ሂሳብ እንዱሰራ እና እንዱቻቻለ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት የለውም፤ ከሳሽ የሰጠው ውክልና ገንዘብ ወደራሱ ሂሳብ ቁጥር እንዱያስገባ የሚል አይደለም ስለሆነም ወደራሱ ሂሳብ ገንዘቡ እንዱገባ ማዘዙ ከውክልና ስልጣኑ በላይ አልፍ ለራሱ ጥቅም እንደሰራበት የሚያረጋግጥ በመሆኑ የወሰደውን ገንዘብ ሉመልስ ይገባል፤ 2ኛ ተከሳሽን (አመልካችን) በተመለከተም ገንዘቡን ወደ 1ኛ ተከሳሽ ሂሳብ ያስተላለፈ መሆኑን ያልካደ በመሆኑ፤ ይህን ያደረኩት በተፃፈልኝ ደብዲቤ ተመስርቼ ነው ይበል እንጂ 1ኛ ተከሳሽ በውክልና ስራውን እየሰራ መሆኑን ከውክልናው መረዲት የሚቻል ሲሆን የተሰጠው ውክልና ደግሞ ከችግኝ ሽያጭ የሚገኝ ገንዘብ ወደ ከሳሽ ሂሳብ ቁጥር መግባት እንዲለበት ተገልጾ የሂሳብ ቁጥሩም በውክልናው ላይ የተጠቀሰ በመሆኑ፤ ውክልናው ገንዘብ መግባት ያለበትን የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1ኛ ተከሳሽ መቀየር የሚችል ስለመሆኑም የተገለፀ ነገር ባለመኖሩ፤ 1ኛ ተከሳሽ ገንዘቡን በራሴ ሂሳብ አስገባው በማለት ያቀረበው ደብዲቤ ላይ የተመታው ማህተም መጀመሪያ ከሳሽ ፕሮፍርማ ሲያስገባ በፕሮፍርማው ላይ ካለው ማህተም የተለየ መሆኑን መረዲት ሲችል ገንዘቡን ወደ 1ኛ ተከሳሽ ማስገባቱ ስህተት ነው ኃላፉነትም አለበት ብሎል።
በአጠቃላይ ሁለቱም ተከሳሾች ከችግኝ ሽያጭ የተገኘውን ገንዘብ በከሳሽ ባንክ ሂሳብ ማስገባት እያለባቸው ይህን ባለማድረጋቸው የአንድነትና ነጠላ ግዳታ አለባቸው በማለት ብር 420,763.00 ከ 13% የጠበቃ አበል እና ልዩ ልዩ ወጪዎች ጋር እንዱከፍለ በማለት ወስኗል።
ይግባኙ የቀረበለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክርክሩን ሰምቶ የአሁን አመልካች በተወካዩ ደብዲቤ ሲቀርብለት በደብዲቤው መሰል ትዕዛዝ ለመስጠት ሙለ ስልጣን እንዲለው ማየትና ለተጠሪ ደውል ማጣራት ነበረበት የሚል ምክንያት በመጨመር የሥር ፍርድ ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ አጽንቷል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ነው። አመልካች ህዲር 28/2009 ዓ.ም ያቀረበው የሰበር ማመልከቻ ተመርምሮ ተጠሪ ለስር 1ኛ ተከሳሽ አቶ ካሳሁን መለሰ ችግኝ እንዱያቀርብ፤ በጨረታ ላይ እንዱሳተፍ፤ የግዢ ትዕዛዝ እንዱቀበል፤ ገንዘብ እንዱቀበል እና የተቀበለውን ገንዘብ በተጠሪ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ገቢ እንዱያደርግ ውክልና በሰጡበት ሁኔታ ተወካዩ ለአሁን አመልካች ችግኝ አቅርቦ የተከፈለውን ብርwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
420,763.00 ወደ ተወካዩ የባንክ ሂሳብ ገቢ በማድረጉ አመልካች ከሥር 1ኛ ተከሳሽ ጋር ለክስ ምክንያት የሆነውን ገንዘብ በአንድነትና በነጠላ ክፈል የመባለን አግባብ ከግራ ቀኙ የውል ግንኙነት አንጻር ለማጣራት ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጓል። ግራ ቀኙም የሥር ክርክራቸውን በማጠናከር በጽሁፍ ተለዋውጠዋል።
ከፍ ሲል ባጭሩ የገለጽነው የጉዲዩን አመጣጥ ሲሆን በበኩላችን ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረናል። እንደመረመርነው ተጠሪ በአመልካች ላይ ክስ የመሰረቱት ችግኝ የማቅረብ ስራውን መስራት ስለበዛብኝ የሥር 1ኛ ተከሳሽ ይህን ሥራ እንዱሰራልኝ የችግኝ ዘር መቅረብን አስመልክቶ ጨረታ ላይ እንዱሳተፍ፤ የጨረታ ሰነድ እንዱገዛ እንዱያስገባ፤ ገንዘብ ፈርሞ እንዱወስድ፤ የወሰደውንም ገንዘብ በድርጅቱ ሥም ገቢ እንዱያደርግ ውክልና ስልጣን ሰጥቸዋለሁ፤ ይሁን እንጂ ከአመልካች ጋር ችግኞች ለማቅረብ ስንስማማ የገንዘብ ክፍያ በሂሳብ ቁጥሬ ገቢ እንዱያደርጉ ተስማምተን እያለ ከውለ ውጪ ገንዘቤን ወደ 1ኛ ተከሳሽ ሂሳብ በማስገባታቸው ተጠያቂነት አለባቸው፤ ገንዘቡን ብር 420,763.00 (አራት መቶ ሃያ ሺህ ሰባት መቶ ስድሳ ሶስት) እንዱከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ነው። አመልካች በበኩለ ከተጠሪ ጋር በተደረገው ውል መሰረት ለቀረበው ችግኝ በውለ የተገለፀውን ብር 420,763.00 ከፍያለሁ፤ ተጠሪ ስራውን የሚሰራው በተወካዩ በኩል ነው፤ ተወካዩ ገንዘቡን መውሰድ እንደሚችል በውክልና ሰነደ ተገልጿል፤ በዚሁ መሰረት ተወካይ የሂሳብ 041892 አቅርበው ገንዘቡ ተላልፎል፤ ተወካይ ክፍያ እንዱፈፀም የጠየቁበት ደብዲቤ በተጠሪ ማህተም ተደግፍ የቀረበ ነው በማለት ተከራክሯል። የሥር ፍርድ ቤቶች በተጠየቀው ዲኝነት መሰረት አመልካች ገንዘቡን ለመክፈል ከተወካዩ ጋር የአንድነትና የነጠላ ኃላፉነት አለበት በማለት የወሰኑት የአመልካች መከራከሪያ ተቀባይነት የለውም በማለት ነው።
ከፍሲል እንደተገለፀው በአመልካች እና በተጠሪ መካከል በተደረገው ውል መሰረት ለቀረበው ችግኝ በውለ የተመለከተው የብር 420,763.00 ክፍያ አመልካች ለተጠሪ ተወካይ መክፈለ ፤ ተጠሪ ስራውን የሚሰራው በተወካዩ በኩል መሆኑ፤ እንዱሁም ተወካዩ ገንዘቡን መውሰድ እንደሚችል በውክልና ሰነደ ስልጣን የተሰጠው መሆኑ ግራ ቀኙን አላከራከረም። ተጠሪ በውለ ላይ የገንዘብ ክፍያ በሂሳብ ቁጥሬ ገቢ እንዱያደርጉ ተስማምተን እያለ ከውለ ውጪ አመልካች ገንዘቤን ወደ ተወካይ ሂሳብ በማስገባቱwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ተጠያቂነት አለበት በማለት የተከራከሩ ቢሆንም ከውለ በኋላ ነሃሴ 12/2006 ዓ.ም ለተወካዩ በሰጡት ውክልና ገንዘቡን እንዱቀበል እና የተቀበለውን ገንዘብ በድርጅቱ የባንክ ሂሳብ ገቢ እንዱያደርግ ውክልና መስጠታቸውን አላስተባበለም። የውክልና ሰነደም ይህን የሚያሳይ ነው። ይልቁንም የሥር 1ኛ ተከሳሽ (ተወካይ) በተሰጠው ውክልና መሰረት ገንዘቡን መውሰደን ሳይክድ ከአሁን ተጠሪ ጋር የመቻቻል እና የሂሳብ እናድርግ ጥያቄ ማቅረቡ ለክሱ መነሻ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። ይህ ደግሞ ለውክልናው 3ኛ ወገን የሆነውን የአሁን አመልካችን ሳይሆን በወካይ እና ተወካይ መካከል የተፈጠረን የጥቅም ግጭት የሚመለከት ነው።
ከፍ/ብ/ህ/ቁ 2206 ፣ 2187 እና ተያያዥ ድንጋጌዎች መገንዘብ እንደሚቻለው ውክልናው በላዩ ተዘርዝረው የተመለከቱትን ጉዲዩችና የነዚሁ ተከታታይ እና ተመሳሳይ የሆነውን እንደ ጉዲዩ አይነትና እንደ ልማድ አሰራር አስፈላጊ የሆነውን ማከናወን የሚያስችል ሲሆን ተወካዩ የፈፀመው ተግባር የወካይና ተወካይ ጥቅሞችን ግጭት የሚያስከትል በሆነ ጊዜ 3ኛው ወገን ይህን ሁኔታ ያወቀና ሉያውቅ የሚገባ መሆኑ ካልተረጋገጠ በቀር ኃላፉነት የሚኖርበት አይሆንም።
በተያዘው ጉዲይ ተጠሪ ከአመልካች ጋር ውል ካደረገ በኋላ ለወኪለ የሰጠው ውክልና ችግኝ እንዱያቀርብ፤ በጨረታ ላይ እንዱሳተፍና የግዢ ትዕዛዝ እንዱቀበል የሚል ብቻ ሳይሆን ገንዘብ እንዱቀበል እና የተቀበለውን ገንዘብ በተጠሪ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ገቢ እንዱያደርግ ስልጣን የሚሰጥ ነው። አመልካች በውል ግዳታው መሰረት ብር 420,763.00 ብር ለተጠሪ ተወካይ ከፍሎል። ስለሆነም አመልካች ገንዘቡን ለተጠሪ ተወካይ መክፈለ (በባንክ ሂሳቡ ማስገባቱ) ውለን እና የውክልና ሰነደን መሰረት ያደረገ አይደለም የሚባልበት ምክንያት የለም። ከዚህ በቀር አመልካች ውክልናውን ተከትል ክፍያ ለተወካይ የፈፀመው በወካይ እና ተወካይ መካከል ያለውን የጥቅም ተቃርኖ እያወቀ ወይም ማወቅ እየተገባው ነው የሚሰኝ ስለመሆኑ ክርክር እና ማስረጃ አልቀረበም።
በአጠቃላይ የስር ፍርድ ቤቶች አመልካች የውለን ገንዘብ ለተጠሪ ተወካይ በመክፈለ ከተወካዩ ጋር የአንድነትና የነጠላ ኃላፉነት አለበት በማለት የደረሱበት መደምደሚያ በክርክሩ የተረጋገጠውን ፍሬነገር እና ከፍ ሲል የተጠቀሱትን የህጉንwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ድንጋጌዎች ይዘት መሰረት ያደረገ ባለመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለን በአብላጫ ድምጽ ተከታዩንም ወስነናል።
የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ሰኔ 28/2008 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እንዱሁም የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ህዲር 20/2009 ዓ.ም ያሳለፈው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት በአብላጫ ድምፅ ተሻሽሎል።
የአሁን አመልካች ከተጠሪ ጋር ያደረገውን ውል እና ተጠሪ ለተወካያቸው የሰጡትን የውክልና ስልጣን መሰረት በማድረግ የውለን ገንዘብ ለተወካይ የከፈለ በመሆኑ ኃላፉነት የለበትም ብለናል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻቻለ።
የሐሳብ ልዩነት እኛ ስማችን በአራተኛ እና በአምስተኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሰው ዳኞች አመልካች በተጠሪ ተወካይ ሂሳብ ቁጥር ገቢ በማድረጉ ከተወካዩ ጋር በአንድነት እና በነጠላ ለተጠሪ ሃላፉነት የለበትም በሚለው በአብላጫው ድምጽ ድምዲሜ ስለማንስማማ በሃሳብ ተለይተናል።
አቶ ካሳሁን መሰለ የተጠሪ ተወካይ በመሆን ከአመልካች ጋር ያደረገው የችግኝ ሽያጭ ውል በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 2189/1/ እና 2199 መሰረት አመልካች እና ተጠሪ መካከል እንደተደረገ ስለሚቆጠር፣ አመልካች ችግኙን ስረከብ ተጠሪ ገንዘቡን የማግኘት መብት ያለው ሲሆን አመልካችም ገንዘቡን ለተጠሪ የመክፈል ተነጻጻሪ ግዳታ እንደሚኖርበት ይታወቃል። ተጠሪ ለተወካዩ በሰጠው የውክልና ስልጣን ተወካዩ ገንዘብ ፈርሞ እንዱወስድ ጭምር ስልጣን የሚሰጥ ቢሆንም፣ በአመልካች እና በተጠሪ መካከልwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በተደረገ የችግኝ አቅርቦት ውል አመልካች ገንዘቡን በተጠሪ የባንክ ሂሳብ ገቢ ማድረግ እንዲለበት ተስማምቶ የተጠሪ የባንክ ሂሳብ ቁጥር የተሰጠው ሲሆን፣ አመልካች ይህ ስለመሆኑ ክድ አልተከራከረም። አመልካች በዚህ መልኩ መስማማቱን ሳይክድ ገንዘቡን በተወካዩ ሂሳብ ቁጥር ገቢ ለማድረግ የቻለው ተወካዩ ይህን እንዱያደርግ በደብዲቤ የገለጸለት መሆኑን በመጥቀስ መሆኑን ተገንዝበናል። በልላ በኩል ገንዘቡ በተጠሪ የባንክ ሂሳብ ገቢ እንዱሆን ግራቀኝ ሲስማሙ በምክንያት ነው ተብል ስለሚታመን አመልካች ይህን ስምምነት የማክበር ግዳታ አለበት። ተጠሪ ለተወካዩ የሰጠው ውክልና ገንዘብ እንዱቀበል ጭምር የሚያካትት ቢሆንም፣ ገንዘቡ በተወካዩ ሂሳብ ገቢ እንዱደረግ ግራቀኝ በተለየ ሁኔታ ያደረጉት ግልጽ ስምምነት በውክልና ሰነድ ላይ ከተመለተው የውክልና ስልጣን በልዩ ሁኔታ መታየት ያለበት በመሆኑ የማይፈጽምበት ምክንያት የለም። በመሆኑም አመልካች ገንዘቡን በተጠሪ የሂሳብ ቁጥር ገቢ ለማድረግ ከተጠሪ ጋር ባደረገው ስምምነት ግዳታ ገብቶ እያለ ከስምምነቱ ውጪ በሆነ ሁኔታ በተጠሪ ሂሳብ ገቢ ማድረግ ያለበትን ገንዘብ በተወካዩ የባንክ ሂሳብ ገቢ በማድረጉ ገንዘቡን ከተጠሪ ተወካይ ጋር በአንድነት እና በነጠላ ለተጠሪ የማይከፍልበት ምክንያት የለም።
በዚህም ምክንያት ከባልደረቦቻችን በሃሳብ ተለይተናል።
No topics extracted.