በአንድ ውል ምክንያት ለደረሰ የጉዲት ኪሣራ ምክንያት ግራቀኙ ተዋዋይ ወገኖች መሆናቸው ከተረጋገጠ ቻን ቹን ያን ኃላፉነቱ የተ/የግ/ማህበር www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. X የጉዲት ኪሣራ ሁለቱም ሃላፉነቱን መሸከም ያለባቸው ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ህ/ቁ. 1799(1) ፣1802 (1)፣2090፣2091 እና ወ/ሪት ሞሚና ሁሴን
No summary available.
ሐምል 16 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውልስ ኦርሺሶ አመልካች፡- ቻን ቹን ያን ኃላፉነቱ የተ/የግ/ማህበር ተጠሪ፡- ወ/ሪት ሞሚና ሁሴን -ጠበቃ ፈለቀ ዋጎ ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመ/ደ/ ፍርድ ቤት ነው። በፋ/መ/ደ/ ፍርድ ቤት የአሁን አመልካች ተከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ከሳሽ ነበሩ። የአሁን ተጠሪ ያቀረቡት የክስ አቤቱታ በአመልካችና ተጠሪ መከካል የመጋዝን ኪራይ መኖሩን በመግለጽ አመልካች የተከራየውን መጋዝን ከውለ ጊዜ መጠናቀቅ በኋላ መጋዘኑን ሳይለቅልኝ ማሽኑን በማስቀመጡ መጋዘኑን በወር ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ ላከራየው እችል የነበረ ሲሆን በዚሁ ስላት እስኪያስረክበኝ ድረስ ታስቦ እንዱከፍለኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል። የአሁን አመልካች ለቀረበበት ክስ መልስ የሰጠ ሲሆን በበኩለ የብር 1,537,322.00/አንድ ሚሉዮን አምስት መቶ ሰላሳ ሰባት ሺህ ሶስት መቶ ሃያ ሁለት ብር/የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ አቅርበዋል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙ ክርክር ከሰማና ማስረጃ ከመዘነ በኋላ ተጠሪ ከሰኔ 20 ቀን 2004 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 2005 ዓ.ም ድረስ አመልካች ማሽኑን እንዲያወጣ የከለከለ በመሆኑ የጠየቁት የዚህ ወቅት ኪራይ ሉከፈል አይገባቸውም፤ሆኖም ከመስከረም 2006 ዓ.ም ጀምሮ አመልካች ማውጣት እየቻለ ስላላወጣ ከዚሁ ጊዜ ጀምሮ እስከ የካቲት 30 ቀን 2009 ዓ.ም ላለው ጊዜ በወር ብር 10,000.00/አስር ሺህ ብር/ሑሳብ የሶስት ዓመት ከአምስት ወር ብር 410,000.00/አራት መቶ አስር ሺህ ብር/ ሉከፍል ይገባል እንዱሁም ተጠሪ የወጪና ኪሳራ ዝርዝር እንዱያቀርቡ፤በአመልካች በኩል የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ በተመለከተ ተጠሪ የባትሪ ድንጋይ ማምረቻ ማሽኑን ለአመልካች ሉያስረክቡ ይገባል ቀሪዎቹ የአመልካች ጥያቄ ውድቅ በማድረግ የሰጠው ውሳኔ አመልካች በመቃወም ይግባኛቸውን ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ይግባኝ ሰሚ ችልት ቢያቀርቡም ተቀባይነት ሳያገኝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.337 መሰረት በትእዛዝ ሰርዞታል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበውም ይህንኑ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። አመልካች ሰኔ 22 ቀን 2009 ዓ.ም በፃፈው አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶችን ዘርዝረው አቅርበዋል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች እስከ ሚያዚያ 2009 ዓ.ም ድረስ ከመጋዝኑ ዔቃውን ሉያወጣ ያልቻለው በተጠሪ ጥፊት ስለመሆኑ በክርክር ሂደት የስር ፍርድ ቤት በፍሬ ነገር ደረጃ ያረጋገጠው ጉዲይ መሆኑ ከታወቀ የአሁን አመልካች ክስ ከቀረበበትን የኪራይ ገንዘብ የመክፈል ኃላፉነት አለበት ወይስ የለበትም እንዱሁም የአሁን ተጠሪ ከዚሁ መጋዝን ኪራይ ጋር በተያያዘ በአመልካች ላይ የኪራይ ገንዘብ ይከፈለኝ ክስ አቅርበው ብር 240,000.00 በመ/ቁ.196134 ማስወሰናቸውን እራሳቸው በክሳቸው ላይ ያረጋገጡት ጉዲይ በመሆኑ ከሳሽ በዚህ የሰበር ጉዲይ መነሻ የሆነ ክስ ማስቀረት ይቻል ዘንድ ከኪራይ ገንዘቡ ክስ ጋር በመጋዝን ያለውን ዔቃ አውጥቶ መጋዝኑን እንዱያስረክብኝ ይወሰንልኝ በማለት የተጠቃለለ ክስ በማቅረብ ጉዲቱን የመቀነስ ግዳታውን አልተወጣም በማለት አመልካች በቀረበው ክርክር ላይ ዲኝነት ሳይሰጥበት በዝምታ የመታለፈን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልት እንዱቀርብ በመደረጉ ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት በታዘዘው መሰረት ህዲር 20www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ቀን 2010 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርበዋል። አመልካችም አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ እንደተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን ለሰበር ችልቱ ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
እንደመረመርነው አመልካች የ3 ዓመት ከ5 ወር የኪራይ ገንዘብ ሉከፍል ይገባል ወይስ አይገባም? የሚለው ነጥብ ምላሽ የሚያስፈልገው ሆኖ አግኝቶታል። ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው በአመልካችና ተጠሪ መካከል የመጋዝን ኪራይ ውል የተደረገው ለተወሰነ ጊዜ ከሐምል 20 ቀን 2001 ዓ.ም እስከ ሰኔ 20 ቀን 2004 ዓ.ም ድረስ ለሶስት ዓመት መሆኑ፤ተጠሪ የውለ ጊዜ ከማብቃቱ በፉት ሰኔ 5 ቀን 2004 ዓ.ም ያልተከፈላቸው የኪራይ ገንዘብ እንዱከፈላቸው ክስ መሰርተው አመልካች ብር 240,000.00 /ሁለት መቶ አርባ ሺህ ብር/ለተጠሪ እንዱከፍል የተወሰነ መሆኑ፤በዚሁ ክስ መጋዝኑን እንዱያስረክባቸው ዲኝነት ያልጠየቁ መሆናቸው፤ይህ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ ለዚህ ክርክር መነሻ የሆነው ሚያዚያ 10 ቀን 2005 ዓ.ም ክስ ማቅረባቸው፤ተጠሪ የኪራይ ገንዘብ ካልተከፈለኝ በሚል ምክንያት አመልካች ተከራይቶ ከነበረው መጋዝን ውስጥ ያለውን ዔቃ እንዲያወጣ የከለከለ ስለመሆናቸው በስር ፍርድ ቤቶች የተረጋገጡ ጉዲዮች ናቸው። ተጠሪ የመጋዝኑ የኪራይ ዋጋ ይታሰብልኛል በሚል ብቻ መጠበቅ ሳይኖርባቸው መጋዘኑ እንዱለቀቅላቸው ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ መጠየቅ ነበረባቸው።
በፍ/ብ/ህ/ቁ 1802 እንደሚደነግገው ተጠሪ የጉዲት ኪሣራ የመቀነስ ግዳታ ነበረባቸው።
አመልካችም ዔቃዎቹ ከመጋዝኑ እንዱያወጣ በህግ አለመጠየቁ ለደረሰው የጉዲት ኪሣራ አስተዋጾ አላቸው። በመሆኑም ለደረሰው የጉዲት ኪሣራ ሃላፉነት የአመልካች ብቻ አለመሆኑን መገንዘብ ይቻላል። የጉዲት ኪሣራ አመልካች ብቻ እንዱከፍል መወሰኑ ከፍ/ብ/ህ/ቁ. 1799(1) እና 1802 (1) እንዱሁም ተበዲዩ የሚካሰው ለጉዲቱ ተመዛዛኝ የሆነ ኪሣራ መሆን ስለሚገባው ለደረሰው ጉዲት ሃላፉነት ያለበት ሰው ታውቆ የተጎዲው ወገን ከደረሰበት ጉዲት ጋራ ተመጣጣኝ የሆነ ካሳ መከፈል ሲለሚገባው ከፍ/ብ/ህ/ቁ 2090 እና 2091 መሰረት ሲመዘን ህጋዊ ውሳኔ ነው ለማለት የሚቻልwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
አይደለም። ለደረሰው የጉዲት ኪሣራ ምክንያቶቹ ከላይ እንደተገለጸው አመልካችም ተጠሪም በመሆናቸው ለደረሰው የጉዲት ኪሣራ ሁለቱም ሃላፉነቱን መሸከም አለባቸው።
በመሆኑም በስር ፍ/ቤት በተጣራው የኪራይ ዋጋ በብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ታስቦ የስድስት ወር አመልካች ለተጠሪ ሉከፍል ይገባል። የስር ፍ/ቤት በዚህ መሰረት አመዛዝኖ መወሰን ሲገባው የተጠሪ ጉዲት የመቀነስ ሃላፉነት ግምት ውስጥ ሳይገባ አመልካች ብቻ ሙለውን የጉዲት ኪሣራ እንዱከፍለ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.134483 መጋቢት 5 ቀን 2009 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ.140438 ግንቦት 9 ቀን 2009 ዓ.ም በትእዛዝ ያፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.348/1/ መሰረት ተሻሻሎል።
አመልካች ከመስከረም 2006 ዓ.ም እስከ የካቲት 30 ቀን 2009 ዓ.ም ድረስ ያለውን የ3 ዓመት ከ5 ወር የኪራይ ሂሳብ በድምሩ ብር 410,000.00 /አራት መቶ አስር ሺህ ብር/ ለተጠሪ እንዱከፍል በማለት የተሰጠ ውሳኔ ክፍል ተሽሯል።
የስድስት ወር ብር 60,000.00 /ስልሳ ሺህ ብር/ አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍል ተብል ተወስኗል።
የተቀሩት የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔዎች አልተነኩም።
በዚህ ችልት ለተደረገው ወጭ እና ኪሳራ የግራ ቀኙን ተከራካሪ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻለ።
መዘገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.