16. አንድ የባንክ ሰራተኛ በሥራው አጋጣሚ ያገኘውን የደንበኛ ገንዘብ ከህግ ውጭ ቀንሶ በማስተላለፍና በማውጣት መውሰደ በተረጋገጠበት ሁኔታ ሰራተኛው የወሰደውን ገንዘብ ዋሶቹ ከእርሱ ጋር በአንድነትና በነጠላ ገንዘቡን የመክፈል ኃላፉነት ያለባቸው ስለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁ 1920፣1922 እና 1933
No summary available.
የሰ.መ.
ቀን 24/09/2010 ዓ.ም ዳኞች፡ ዲኜ መላኩ ተኸሉት ይመስል ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ አብዬ ካሳሁን አመልካች፡ …………… ብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ አክሲዮን ማሕበር ነገረ ፈጅ ቤተልሓም ማትዎስ -ቀረቡ።
ተጠሪዎች፡ ………….. 1ኛ. አቶ እዮብ ሙለጌታ ቱሳና 2ኛ. ወ/ሮ መድሃኒት ሙለጌታ ቱሳና የቀረበ የለም።
መዝገቡ መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ ዋስትናን መሰረት ያደረገ ክርክር ሲሆን የጀመረው በኦሮሚያ ክልል ምዔራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። በስር አመልካች ከሳሽ፣ ተጠሪዎች እና በዚህ መዝገብ የክርክሩ ተካፊይ ያልሆነውን አቶ ፈቃደ ሙለጌታ ተከሳሾች በመሆን ተከራክረዋል።
አመልካች በስር ፍርድ ቤት ባቀረበው ክስ የስር 1ኛ ተከሳሽ የነበረው አቶ ፈቃደ ሙለጌታ የአመልካች ሰራተኛ በመሆን በወላይታ ቅርንጫፍ ተመድቦ እየሰራ በነበረበት ጊዜ ከባንኩ አሰራር ውጭ የአቶ ጀመሬ መጃ ልጊሶን ከሆነው ሂሣብ ቁጥር የባለ ሂሣቡን ስምና ፊርማ በማስመሰል ፈርሞ ወደ አመልካችwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ባንክ ሻሸመኔ ቅርንጫፍ በማዛወር ብር 50,000 በህገወጥ መንገድ በመውሰደ ገንዘቡን እንዱከፍል፤ የአሁኑ ተጠሪዎች ዋስ በመሆናቸው ገንዘቡን በአንድነትና በነጠላ እንዱከፍለ ይወሰን ዘንድ ዲኝነት ጠይቋል።
የስር ተከሳሾች ባቀረቡት የመከላከያ መልስ በስር 1ኛ ተከሳሽ ስምና ፊርማ የተደረገ የገንዘብ ዝውውር የለም በማለት ተከራክረዋል።
በዚህ አግባብ ክርክሩ የቀረበለት የስር ፍርድ ቤትም በክሱ የተጠቀሰው ገንዘብ በስር 1ኛ ተከሳሽ ወጭ ተደርጏ መወሰደን ተረጋግጦ በወንጀል የተቀጣ መሆኑን፤ የአሁኑ ተጠሪዎችም ዋስ ስለመሆናቸው ያልተካደ መሆኑን በመግለጽ ብር 50,000 በአንድነትና በነጠላ ይክፈለ ሲል ፍርድ ሰጥቷል።
የአሁኑ ተጠሪዎች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኝ ቅሬታ አቅርበው ፍርድ ቤቱም ግራቀኙን ከአከራከረ በኃላ የስር 1ኛ ተከሳሽ ድርጊቱ የፈፀመው ለደንበኞች አገልግልት እየሰጠ ሳይሆን ለራሱ የአመልካች ደንበኛ በመሆን እንደሆነ፤ የሻሸመኔ ቅርንጫፍም ባለመብት ባለማጣራት የከፈለው በመሆኑ ዋሶቹ ተጠያቂነት የለባቸውም በማለት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ሽሯል። አመልካች በውሳኔው ቅር በመሰኘት ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኝ ቢያቀርብም ተቀባይነት አላገኘም።
አመልካች ሐምል 25 ቀን 2009 ዓ.ም ባቀረበው የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ተፈፀመ ያለውን የህግ ስሕተት በዝርዝር ያቀረበ ሲሆን መሰረታዊ ይዘቱ ሲታይም የአሁኑ ተጠሪዎች በስር ፍ/ቤት ያላነሱት ክርክር ይግባኝ ሰሚ ችልት ለውሳኔ መነሻ ማድረጉ ተገቢ አለመሆኑን፤ የስር 1ኛ ተከሳሽ ገንዘቡ የወሰደው ከሥራው ጋር በተያያዘ ሁኔታ መሆኑን በመግለጽ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሳኔና ትዕዛዝ እንዱሻር አመልክቷል። ጉዲዩን የመረመረው አጠሪ ችልትም የአሁን ተጠሪዎች ኃላፉነት የለባቸውም ተብል የተወነበት አግባብ ባለበት ማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለዚህ ችልት ያስቀርባል ተብሎል። የአሁኑ ተጠሪዎች 03/05/2010 ዓ/ም የተፃፈ መልስ አቅርበው የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ እንዱጸና ጠይቋል። የመልስ መልስም ቀርቧል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ከሥር የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ፍርድና ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት መሆን አለመሆኑን እንደሚከተለው መርምረናል።
እንደመረመረነውም የአሁኑ ተጠሪዎች በስር 1ኛ ተከሳሽ ለነበሩት አቶ ፈቃደ ሙለጌታ ዋስ ስለመሆናቸው፤ የገንዘብ መጠኑም እስከ ብር 50,000 ስለመሆኑ ያከራከረ ጉዲይ አይደለም። ከስር ፍ/ቤት መዝገብ መረዲት የተቻለው ተጠሪዎች ከባንክ ገንዘብ አልወጣም የሚል ክርክር ሳያቀረቡ ነገር ግን ገንዘቡ ሥርዓቱን ጠብቆ ያልወጣ በመሆኑ ልንጠየቅ አይገባም በማለት ተከራክረዋል።
በስር ፍርድ ቤት በፍሬ ነገር የተረጋገጠው የስር 1ኛ ተከሳሽ የአቶ ጀመሬ መጃን ፊርማ ለማስመሰል ብር 50,000 በህገወጥ መንገድ ማውጣቱን ገንዘቡም ከሻሽመኔ ቅርንጫፍ ወጭ አደረጎ መውሰደን ነው። የስር የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ተጠሪዎች ተጠያቂ ሉሆኑ አይገባም ለማለት እንደምክንያት የጠቀሰው ድርጊቱ የተፈፀመው አገልግልት እየሰጠ ሳይሆን እንደደንበኛ ቀርቦ ገንዘብ ሲያወጣ ተገቢ ማጣራት አልተደረገም በሚል ነው።
ከመዝገቡ እንደተረዲነው የስር 1ኛ ተከሳሽ በአመልካች ባንክ የወላይታ ቅርንጫፍ ሰራተኛ በመሆን ሲሰራ እንደነበር፤ ከዚህ ቅርንጫፍ ባንክ ደንበኛ ገንዘብ በሕገወጥ መንገድ ወጭ አድርጎ ወደ ሻሸመኔ ቅርንጫፍ በማስተላለፍ ወጭ አድርጎ መወሰደን ነው። ከዚህ የምንረዲው የስር 1ኛ ተከሳሽ ከሚሰራበት ቅርንጫፍ ባንክ ያለው የደንበኛ ሂሣብ ቁጥር በሕገወጥ መንገድ ገንዘብ በመወሰድ ወደ ላላ ቅርንጫፍ በማስተላለፍ ገንዘቡን ለግል ጥቅሙ ማዋለን ነው። የስር 1ኛ ተከሳሽ ድርጊት ከሻሸመኔ ቅርንጫፍ ገንዘብ ማውጣት ብቻ ተነጥል የሚታይ ሳይሆን የወላይታ ቅርንጫፍ ሰራተኛ በመሆን ከህግ ውጭ ከደንበኛ ሂሣብ ገንዘብ ቀንሶ ማስተላለፍንና ወጪ አድርጎ መወሰደን አብሮ መታየት ያለበት ጉዲይ ነው። የአሁኑ ተጠሪዎች የስር 1ኛ ተከሳሽ ዋሶች መሆናቸው አልተካደም። ይህ ከሆነ ደግሞ ተጠሪዎች የስር 1ኛ ተከሳሽ በሥራው አጋጣሚ ያገኘው የደንበኛ ገንዘብ ከህግ ውጭ ቀንሶ በማስተላለፍና በማውጣት መውሰደ በተረጋገጠበት ሁኔታ ከኃላፉነት ነፃ የሚያደርጋቸው ሆኖ አልተገኘም። የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት እና የፋዳራልwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሳኔና ትዕዛዝ የስር 1ኛ ተከሳሽ ድርጊት ህጋዊ ውጤት እና የተጠሪዎች የግዳታ አድማስ መሰረት ያላደረገ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው። የአሁኑ ተጠሪዎች የስር 1ኛ ተከሳሽ የወሰደው ብር 50,000 በአንድነትና በነጠላ ሉከፍለ ይገባል።
በመሆኑም የስር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ተጠሪዎች ከስር 1ኛ ተከሳሽ ጋር በአንድነትና በነጠላ ገንዘቡን የመክፈል ግዳታ እያለባቸው ከኃላፉነት ነፃ ማድረጋቸው የፍ/ሕ/ቁ 1920፣1922 እና 1933 ድንጋጌዎች መሰረታዊ ይዘትና መንፈስ ያላገናዘበ ነው ብለናል። በዚሕም ተከታዩን ወስነናል።
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የደቡብ ችልት በመ/ 03/06/2009 ዓ/ም የክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በ23/01/2009 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በመሻር የተሰጠው ፍርድ እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በፍ/ብ/ይ/መ/ በ03/09/2009 ዓ/ም የሰጠው ትዕዛዝ ተሽሯል።
ተጠሪዎች ከስር 1ኛ ተከሳሽ አቶ ፈቃደ ሙለጌታ ጋር በአንድነትና በነጠላ በዋስትና ውለ የተመለከተውን ብር 50,000 የመክፈል ግዳታ አለባቸው በማለት ወስነናል።
የምዔራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በ23/01/2009 ዓ/ም የሰጠው ፍርድ ጸንቷል።
ወጭና ኪሳራ ግራቀኙ የየራሳቸው ይቻለ ብለናል።
የዚህ ፍ/ቤት ውሳኔ ግልባጭ ለስር ፍ/ቤቶች ይተላለፍ ብለናል።
No topics extracted.