የማይንቀሳቀስ ንብረት ካለዉ ልዩ ባህርይ አንፃር ንብረቱን ከአንድ ወደ ላላ ሰዉ በሽያጭ ለማስተላለፍ የሚደረግ ዉል በሦስተኛ ወገን ላይ ህጋዊ ዉጤት ያስከትል ዘንድ ወ/ሮ አሻ ፊራህ እና እነ አብደራህማን www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. IX በህግ አግባብ በሚመለከተዉ አካል ዘንድ ካልተመዘገበ ውለ ፈራሽ የሚሆን ሲሆን ሻጩም በዉለ ምክንያት የተቀበለዉን ገንዘብ የመመለስ ግዳታ ያለበት ሲሆን፣ ይህን እንዱያደርግ ላላ ክስ ማቅረብ ሳያስፈልግ በዚያው መዝገብ ላይ መወሰን የሚቻል ስለመሆኑ በፍ/ሕ/ቁ አንቀጽ 2878 ጣሂር (ሰዎች
No summary available.
ቀን - 29/01/2011 ዳኞች፡ ተኽሉት ይመሰል ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራዉ አብዬ ካሳሁን አመልካች፡- ወ/ሮ አሻ ፊራህ -ጠበቃ ጣሂር ሼህ አብደላህ ተጠሪዎች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ክርክሩ የተጀመረዉ በኢትዮጵያ ሶማላ ክልል መንግስት በፊፈን ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን፤ ተጠሪዎች ከሳሽ፣ አመልካች እና በዚህ ችልት የክርክሩ ተካፊይ ያልሆነዉ አቶ ሰኢድ አሉ፣ በቅደም ተከተል፣ 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች በመሆን ተከራክረዋል። የተጠሪዎች ክስ ይዘትም በአጭሩ፤ እናቶቻችን ከአያታችን የወረሱት እና በዉርስ ሉተላለፍልን የሚገባ ቦታ 2ኛ ተከሳሽ በህገ ወጥ መንገድ ለ1ኛ ተከሳሽ በሽያጭ በማስተላለፈ ዉለ ፈርሶ ቦታዉ ይመለስልን የሚል ነዉ። ተከሳሾች ለፍርድ ቤቱ ቀርበዉ በሰጡት መልስ፤ ቦታዉ ለ2ኛ ተከሳሽ በተለይ ከእናቱ የተሰጠዉ መሆኑን፣www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ከሳሾች ከቦታዉ የዉርስ ድርሻ የላላቸዉ መሆኑን፣ ቦታዉን 2ኛ ተከሳሽ ቆርቆሮ ቤት ሰርቶበት በህጋዊ መንገድ ለ1ኛ ተከሳሽ የሸጠ በመሆኑ ዉለ ሉፈርስ አይገባም በማለት ተከራክረዋል።
ጉዲዩ በመጀመሪያ የቀረበለት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ከግራ ቀኝ በዚህ መልኩ የቀረበዉን ክርክር እና ማስረጃ ከሰማ በኋላ ለክርክሩ ምክንያት የሆነዉ እና ቆርቆሮ የተሰራበት ቦታ ከስር 2ኛ ተከሳሽ ጋር ባደረጉት የሽያጭ ዉል መሰረት በአመልካች እጅ እንደሚገኝ በማስረጃ መረጋገጡን ገልፆ ቤትና ቦታዉ የአመልካች ነዉ በማለት የተጠሪዎችን ክስ ዉድቅ በማድረግ ወስኗል። ተጠሪዎች በዚህ ዉሳኔ ባለመስማማት ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን፣ ይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት በበኩለ ለክስ ምክንያት የሆነዉ ዉል በሚመለከተዉ አካል ዘንድ የተመዘገበ እና የተፈረመም አለመሆኑን፣ ተጠሪዎች ወራሾች መሆናቸዉን እና ለስር 2ኛ ተከሳሽ ለብቻዉ የተሰጠ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ባለመቅረቡ ንብረቱ ለተጠሪዎች ሉመለስላቸዉ ይገባል፤ አመልካች በቦታዉ ላይ ቤት ለሰራችዉ ቤት ግምቱን ተጠሪዎች ለአመልካች እንዱከፍለ፤ አመልካች በዉለ ምክንያት ያጣችዉ መብት ካለ በስር 2ኛ ተከሳሽ ላይ ክስ የማቅረብ መብት አላት በማለት የስር ፍርድ ቤትን ዉሳኔ በመሻር ወስኗል። አመልካች ይህን ዉሳኔ ባለመቀበል ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር አቤቱታ ያቀረበች ሲሆን፣ ሰበር ሰሚዉ ችልት የስር 2ኛ ተከሳሽ በሽያጭ ዉለ መሰረት የወሰደዉን ገንዘብ ለአመልካች ሉመለስ ይገባል በሚል ይግባኝ ሰሚዉ ችልት በዚህ ረገድ የሰጠዉን የዉሳኔ ክፍል ብቻ በመሻር ቀሪዉን በማጽናት ወስኗል።
አመልካች በቀን 05/06/2010 ዓ. ም ተዘጋጅቶ በጠበቃዋ አማካይነት በቀረበ አምስት ገጽ የሰበር አቤቱታ፤ ተጠሪዎች ወራሾች መሆናቸዉ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ፣ እንዱሁም በግራ ቀኝ መካከል የተደረገዉ ዉል ተገቢዉን ፍርም ያሟላ መሆን አለመሆኑን በተመለከተ የቀረበዉ ክርክር በላለበት ሁኔታ የስር የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ሰሚ ችልቶች በፊፈን ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ የነበረዉን ዉሳኔ በመሻር የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ በማለት ተከራክራለች። አቤቱታዉ ተመርምሮ ያስቀርባል በመባለም ተጠሪዎች በተደረገላቸዉ ጥሪ መሰረት ቀርበዉ ግራ ቀኝ ክርክራቸዉን በጽሐፍ ተለዋዉጠዋል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተመለከተዉ ሲሆን፣ ይህ ችልትም ለአቤቱታዉ ምክንያት የሆነዉን ዉሳኔ ከግራ ቀኝ ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል። ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለዉ ለክርክሩ ምክንያት የሆነዉ ቤት እና ቦታ በአመልካች እጅ ሉገባ የቻለዉ ከስር 2ኛ ተከሳሽ ጋር ባደረጉት የሽያጭ ዉል መሰረት ስለመሆኑ ግራ ቀኝን ያከራከረ ጉዲይ አይደለም። ተጠሪዎች የሚከራከሩት ቤትና ቦታዉ ከአያታቸዉ በዉርስ ሉተላለፍላቸዉ የሚገባ መሆኑን ሲሆን፣ አመልካች እና የስር 2ኛ ተከሳሽ በበኩላቸዉ ቤትና ቦታዉ ለስር 2ኛ ተከሳሽ (ሽያጭ) በግል የተሰጠዉ እንጂ የዉርስ ሀብት አለመሆኑን ገልጸዉ የተከራከሩ መሆኑን መዝገቡ ያስረዲል። ይሁንና ቤትና ቦታዉ ቀደም ሲል የተጠሪዎች አያት የነበረ ሆኖ ለተጠሪዎች በዉርስ የተላለፈላቸዉ እንጂ ለስር 2ኛ ተከሳሽ በግል የተሰጠዉ ያለመሆኑን ማስረጃን መዝኖ ፍሬ ነገርን የማጣራት ስልጣን በተሰጣቸዉ በስር ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል። በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠዉ ይህ ከሆነ፣ በአመልካች እና በስር 2ኛ ተከሳሽ መካከል የተደረገዉ እና ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ዉል ህጋዊ ዉጤት የሚያስከትል መሆን ያለመሆኑን ስለ ጉዲዩ ከሚደነግገዉ የፍትሐብሕር ህጉ ድንጋጌ ጋር አገናዝቦ ማየቱ ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል።
እንደሚታወቀዉ የማይንቀሳቀስ ንብረት ካለዉ ልዩ ባህርይ አንፃር፣ ንብረቶቹን ከአንድ ወደ ላላ ሰዉ ለማስተላለፍ የሚደረጉ አሰራሮች እና ስርዓቶች ጥብቅ መሆን እንዲለባቸዉ ይታወቃል። የማይንቀሳቀስ ንብረትን ከአንደ ወደ ላላ ሰዉ ማስተላለፍ ስለሚቻልበት ሁኔታ በተመለከተ በፍትሐብሕር ህጋችን የተለያዩ አንቀፆች የተደነገጉ ድንጋጌዎችም ይህኑን የሚያሳዩ ናቸዉ። ከእነዚህም ድንጋጌዎች ዉስጥ አንደ በህጉ አንቀጽ 2878 ስር የተመለከተዉ ድንጋጌ ነዉ። በዚህ ድንጋጌ መሰረት የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሽያጭ ለላላ ሰዉ ለማስተላለፍ የሚደረግ ዉል በሦስተኛ ወገን ላይ ህጋዊ ዉጤት ያስከትል ዘንድ ንብረቱ በተመዘገበበት መዝገብ ላይ መመዝገብ አለበት።
የተያዘዉን ጉዲይ በተመለከተም፣ ተጠሪዎች ከቤቱ ላይ መብት ያላቸዉ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ አመልካች ከስር 2ኛ ተከሳሽ ጋር ያደረገችዉ ዉል ህጋዊ ዉጤት ያስከትል ዘንድ የሽያጭ ዉለ በህግ አግባብ የተመዘገበ መሆኑን የማስረዲት ግዳታ አለባት። ሆኖም ለክርክሩ ምክንያት የሆነዉ ዉል በሚመለከተዉ አካል ዘንድ ያልተመዘገበ መሆኑ በስር ፍርድ ቤት ተረጋግጧል። ስለሆነም ለክርክሩ ምክንያትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የሆነዉ ዉል የሚጸናበት የህግ ምክንያት የላለ በመሆኑ ዉለ ሉፈርስ ይገባል በማለት የስር የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ሰሚ ችልቶች የደረሱበት ድምዲሜ የሚነቀፍበት ምክንያት የለም። ሽያጩ ሉፈርስ ይገባል የሚባል ከሆነ ደግሞ የስር 2ኛ ተከሳሽ (ሻጭ) ሰዑድ አሉ ዩሱፍ በዉለ ምክንያት የተቀበለዉን ገንዘብ የመመለስ ግዳታ ያለበት ሲሆን፣ ይህን እንዱያደርግ ላላ ክስ ማቅረብ ሳያስፈልግ በዚሁ መዝገብ ላይ መወሰን የሚቻል በመሆኑ፣ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዚህ ረገድ የሰጠዉን የዉሳኔ ክፍል በመሻር የደረሰበት ድምዲሜም በአግባቡ ሆኖ ተገኝቷል።
በአጠቃላይ ለክርክሩ ምክንያት የሆነዉ ቤትና ቦታ የተጠሪዎች የዉርስ ድርሻ ያለበት መሆኑ እስከተረጋገጠ እና አመልካች ቤትና ቦታዉን ለመግዛት ያደረጉት ዉልም በህግ አግባብ በሚመለከተዉ አካል ዘንድ ያልተመዘገበ በመሆኑ ዉለ ሉፈርስ ይገባል በማለት የስር 2ኛ ተከሳሽ የሽያጩን ገንዘብ ለአመልካች እንዱመልስ በሚል የተሰጠ ዉሳኔ በአግባቡ ነዉ ከሚባል በስተቀር በዚህ ችልት ሉታረም የሚችል መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ስላልተገኘ ተከታዩ ተወስኗል።
የኢትዮጵያ ሶማላ ክልል መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/ 05-1-101/09 በቀን 04/03/2010 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ጸንቷል።
በዚህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ።
አመልካች ቦታዉን ከተረከቡ በኋላ ላካሄደት ተጨማሪ ግንባታ ያወጡትን ወጪ በተመለከተ ወጪዉ እንዱመለስላቸዉ ሉያቀርቡ የሚችለትን ክስ ይህ ዉሳኔ አይከለክልም።
No topics extracted.