አንድ ንብረት የገዛ ሰው የገዛውን ንብረት በፈለገው መልኩ መጠቀም የማያስችል ሁኔታ መፈጠር ፤ ውለ ከመደረጉ በፉት ችግሩ/ጉድለቱ እንዲለ ቢያውቁ ኑሮ ውለን አይፈጽምም ነበር የሚያሰኝ በመሆኑ ጉድለት ያለበት ውለ ነው ተብል ተዋዋይ ወገኖች ወደ ነበሩበት መመለስ ያለባቸው ስለመሆኑ፡ፍ/ብ/ሕ/ቁ 1815፣ፍ/ብ/ሕ/ቁ/ 2289
No summary available.
የሰ/መ/ ታህሳስ 26 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች:- ዲኜ መላኩ ተኽሉት ይመሰል ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ፀሐይ መንክር አመልካች፡- አቶ ጉልላት ግዛው - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- አቶ ጥላሁን ኃይለ - አልቀረቡም።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ የጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሆኖ በስር ከሣሽ ተጠሪ ተከሣሽ ደግሞ አመልካች በመሆን በመኪና ሽያጭ ውል መነሻነት ተከራክረዋል።
በስር ቀርቦ የነበረው ክስ የሚያመለክተው ከሣሽ የሰ.ቁ. ዐ2-99421 አ.አ.
የሆነውን የተከሣሽን የጭነት ተሽከርካሪ ምንም ዓይነት ችግር የላለበት መሆኑን አረጋግጠው ታህሳስ ዐ6 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም. በተፈረመ የመኪና ሽያጭ ውል መግዛታቸውን እና ከቤት መኪናነት ወደ ግል ተሽከርካሪነት ለማዛወር ለሚመለከተው የትራንስፖርት ጽ/ቤት ሲጠይቁ መኪናው በባለሙያ ተመርምሮ የመኪናው ቁጥርና ሻንሲ የተመታ መሆኑ ስለተረጋገጠ የተጠቀሰው እንደማይሰጣቸው የተገለፀላቸው በመሆኑ መኪናው ጉድለት እንዲለበት እያወቀ ከሣሽ ወደ ስህተት በመምራት ውለን እንድንፈራረም ያደረጉት ያለአግባብ ስለሆነ ውለም ሉፈፀም በሚችል አቅም ያልተመሰረተ ስለሆነ የመኪና ሽያጭ ውለ እንዱፈርስ ፣ ተከሣሽ ከሽያጭ ጋርwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በተያያዘ ከከሣሽ ላይ የተቀበለውን የሽያጭ ገንዘብ ከሣሽ መኪናውን ከገዛው በኋላ ለማስተካከል ያወጡትን ወጭ በአጠቃላይ ከሕጋዊ ወለድ ከክርክር ወጪና ኪሣራ ጭምር እንዱከፍለ እንዱወሰንላቸው የጠየቁ መሆኑን ተመልክተናል።
ተከሣሽ በሰጡት መልስ መኪናውን መሸጣቸውን ማመናቸውን ነገር ግን ሉብሬ ወደ ገዢ ሳያዛውሩ የተባለው ችግር በመኪናው ላይ ያለ መሆኑን በፍፁም እንደማያውቀ፣ በባለሙያ ተመርምሮ የተላለፈ መሆኑን፣ ከሣሽ ከተረከበው ጀምሮ በእጃቸው ሆኖ ጋራዥ እንደነበረ፣ ጉድለቱ ሲሸጥ ያልነበረ መሆኑን ኃላፉነቱም ለገዢ የተላለፈ መሆኑን፣ በመግለጽ ውለ ሉፈርስ አይገባም በማለት አቅርበዋል። ወደ ነበርንበት ለመመለስም አንችልም ብለዋል።
ፍርድ ቤቱም ውለ ጉድለት ያለበት ነው ወይንስ አይደለም ? መኪናውን ከሣሽ ከገዛ በኋላ ወጪ አጥቷል ወይንስ አላወጣም የሚለ ጭብጦችን በመያዝ የግራ ቀኙን ምስክሮች ሰምቷል።
አጠቃላይ ክርክሩን ከተመለከተ በኋላም በግራ ቀኙ መሐከል የመኪና ሽያጭ ውል መኖሩ አለማከራከሩን፣ በሽያጭ ውለ ላይ ጉድለት አለ ወይንስ የለም የሚለው በቅድሚያ መለየት የሚገባ መሆኑን እና የተሸጠው መኪና ሻንሲ እና ቁጥር የተመታ በመሆኑ መሸጥ መለወጥ የማይቻል መሆኑ በመንገድ ትራንስፖርት ፅ/ቤትም ከኮድ 2 ወደ ኮድ 3 መለወጥ እንደማይቻል መከልከለን በመያዝ የተሰሙ ምስክሮችን ቃል ሲመረመርም መኪናው ከመሸጡ በፉት በባለሙያ/መካኒክ/ የተመረመረ ቢሆንም መካኒክ ሲመረምር ሻንሲው የተመታ መሆኑን መለየት ይችላል ብለው ተከሣሽም ያነሱት ክርክር የላለ እና የተረጋገጠም ባለመሆኑ ከቀረበው የማስረጃ ክብደት አንፃር የሰ.ቁ.
ኮድ 2-99421 አአ የሻንሲ ቁጥር YN 52-009146 የሞተር ቁጥር 3Y-02313681 በማስመሰል የተመታው ከሽያጭ ውለ በፉት በተከሣሽ እጅ ላይ እያለ የነበረ ጉድለት መሆኑን ፍ/ቤቱ ግንዛቤ መውሰደን ገልጿል።
ይህ ጉድለት ውል እንዱፈርስ ምክንያት ይሆናል ወይ የሚለውን በተመለከተ በፍ/ብ/ሕ/ቁ/ 2289 ሻጭ ዋቢ ላሆንባቸው የሚገባቸው ጉድለቶች የሸጠው ነገር ለደንበኛው አገልግልት ወይም ለንግድ ሥራ ጥራትነት የላለው ዔቃ ከሆኑ በማለትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የሚደነግግ በመሆኑ በተያዘው ጉዲይ ሻጭ ዋቢ ላሆንለት የሚችል ጉድለት የተገኘበት ስለሆነ ሉፈርስ የሚገባው ውል ነው በሚል ወስኗል። ወጪን በተመለከተ ግን ከሣሽ ወጪዎችን ያስረደልኛል ብለው ያቀረቧቸውን ደረሰኞች እያንዲንዲቸውን በመመልከት የቀረበውን ወጪ ያስረደም በማለት ውድቅ አድርጏ መኪናው የተሸጠበትን ገንዘብ ብር 11ዐዐዐዐ.ዐዐ/ አንድ መቶ አስር ሺ ብር/ እና ብር 5798.ዐዐ/ አምስት ሺ ሰባት መቶ ዘጠና ስምንት ብር/ በመጨመር ተከሣሽ ለከሣሽ እንዱመልስ፣ ከሣሽ ደግሞ የሰ.ቁ. 2- 99421 አ.አ. የሆነውን ተሽከርካሪ አሁን ባለበት ሁኔታ ለተከሣሽ እንዱያስረክቡ መሆኑን በመ/ቁ/ 39866 ግንቦት 21 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም. የሰጠው የውሣኔ ግልባጭ ያመለክታል።
አመልካች ይግባኝ ቢለም ይግባኝ ቅሬታውን የመረመረው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙን አስቀርቦ እና አከራክሮ በመ/ቁ/ 156835 ህዲር 16 ቀን 2ዐዐ8 በዋለው ችልት የስር ፍርድ ቤት ውሣኔ ጉድለት የለበትም በሚል ሙለ በሙለ አጽንቶታል።
አመልካች በስር ፍርድ ቤት ውሣኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምላቸው የካቲት 11 ቀን 2ዐዐ8 ዓ.ም. የተፃፈ የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል። ይዘቱም በአጭሩ፡- ክርክር ያስነሳውን ተሽከርካሪ እዲ እና እገዲ የላለበት መሆኑ ተረጋግጦ ከሣሽ በስማቸው አዛውረዋል፣የባለቤትነት ደብተርም ተጠሪ በስማቸው አውጥተዋል።
ተጠሪ መኪናውን ሲገዙ በተለመደው አሰራር የራሳቸውን ባለሙያ አምጥተው አስመርምረዋል። ውለ ከተደረገ ከ5 ወር በኋላ በ9/ዐ7/2ዐዐ5 ዓ.ም. የመኪናውን አገልግልት ከኮድ 2 ወደ ኮድ 3 ለመቀየር ጥያቄ በሚያቀርቡበት ጊዜ የመኪናው ሞተርና ሻንሲ የተመታ መሆኑን የተገለፀላቸው ቢሆንም አመልካች ይህ ጉድለት ስለመኖሩና መቼ እንደተከሰተም የሚያውቁት ነገር የለም። ከቅን ልቦና ውጭ ያቀረቡት ጥያቄ ውለ በመሳሳት የተደረገ ነው ልባል አይችልም። ሽያጩ የተደረገው በታህሳስ ዐ6 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም. ሲሆን ተጠሪ መኪናውን እስካሁን ድረስ እየተጠቀሙበት የሚገኙ ከመሆኑ አኳያ የመኪና ሽያጭ ውለ በመፍረስ ወደነበርንበት እንዱመለሱ ቢደረግwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
አፈፃፀሙ አዲጋች ነው በሚል የስር ፍርድ ቤቶች ውሣኔ ላይ የተፈፀመው ስህተት እንዱታረምላቸው ጠይቀዋል።
አቤቱታውን የመረመረው የሰበር አጣሪ ችልት ሉጣራ የሚገባውን ጭብጥ በመያዝ መዝገቡ ለችልቱ እንዱቀርብ በማድረጉ ላቀርብ ችሎል። አቤቱታው ከማስቀረቢያ ነጥቡ ጋር ለተጠሪ ደርሶ መልስ እንዱያቀርቡ ከመጥሪያ ጋር የተላከላቸው በመሆኑ ጥር 24 ቀን 2ዐዐ9 ዓ.ም. የተፃፈ መልስ አቅርበዋል። ይዘቱም ከማስቀረቢያ ነጥቡ አኳያ ካቀረቡት በጥቂቱ፡- ውል እንዱፈርስ ክስ ያቀረብኩት ውለ ከተደረገ እና መኪናውን ከተረከብኩ ከ3 ቀን በኋላ ነው። በመሆኑም መኪና ከተረከብኩ ከ3 ዓመት በኋላ ውል እንዱፈርስ ክስ አላቀረብኩም፣ መኪናውን በትራንስፖርት ቅርንጫፍ ባለሙያ አስመርምረው አላስረከቡኝም፣ በመኪናው ላይ ጉድለት ያለበት መሆኑ የታወቀው ተጠሪ መኪናውን ከቤት አገልግልት ወደ ንግድ ተሽከርካሪነት ለመለወጥ አስቤ መኪናው በትራንስፖርት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ባለሙያ በተመረመረበት ጊዜ ነው።
በዚህ መሰረት የስር ፍርድ ቤቶች ውሣኔ አግባብ በመሆኑ የተፈፀመበት የህግ ስህተት የለውም ተብል አቤቱታው ውድቅ እንዱሆን ጠይቋል። አመልካችም የመልስ መልስ አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተውን የሚመስል ሲሆን እኛም አጠቃላይ የቀረበውን ጉዲይ አግባብነት ካለው የህግ ድንጋጌ ጋር በማገናዘብ መርምረናል።
እንደመረመርነውም ከላይ በስር የቀረበው ክስ ላይ ታህሳስ ዐ6 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም.
ክርክር ያስነሳውን ተሽከርካሪ ሽያጭ ውል ግራ ቀኙ በማድረግ የሽያጭ ገንዘቡንም ብር 11ዐዐዐዐ.ዐዐ ሻጭ መቀበላቸውን ገዢም መኪናውን መረከባቸውን የተካደ ባለመሆኑ አለማከራከሩን ተመልክተናል። ሆኖም መኪናው በተገቢው ርክክብ ከተደረገ በኋላ ስመ ሀብትም ከዞረ በኋላ የመኪናውን አገልግልት ለመቀየር ለትራንስፖርት ባለሥልጣን ጥያቄው ቀርቦ ሲፈተሽ ግን የሻንሲው ቁጥር የተመታ መሆኑ በመረጋገጡ በቀይ ሰላዲ ላይ የተመዘገበ በመሆኑ አገልግልቱን ማግኘት እንደማይቻል ለተጠሪ የተገለፀላቸው በመሆኑ ውለ ጉድለት ባለበት ንብረት ላይ የተፈፀመ በመሆኑ ውለ እንዱፈርስ ጠይቀዋል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
አሁን እያከራከረ ያለው ጭብጥ መኪናው ከሻጭ ወደ ገዢ ከመተላለፈ በፉት በመካኒክ ተፈትሾ የተላለፈ በመሆኑ ኃላፉነት ለገዢ ተላልፎል ልባል ይገባል ወይንስ አይገባም የሚለው ነጥብ ላይ ይሆናል።
በስር ፍርድ ቤት መኪናው በአግባቡ ተጠሪ ራሣቸው ባመጡት ሜካኒክ ተፈትሾ እና ተነድቶ ጉድለት የላለበት መሆኑ ተረጋግጦ ገዢ የተረከቡ መሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ ተረጋግጧል። ነገር ግን ይህ የመካኒክ ፍተሻ የሻንሲ እና የሞተር ቁጥር ኦርጅናልነት ጨምሮ የሚያረጋግጥ ነው ወይንስ አይደለም የሚለው በአመልካች በስር ክርክር የተደረገበት ባይሆንም በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ግን ተነስቶ የነበረ በመሆኑ በዚህ መልኩ አመልካች መኪናው ተፈትሾ ለገዢ መተላለፈን ስለማስረዲታቸው የተቀመጠ ነገር የለም።
በኑሮ ልማድ እውቀት እንደሚታወቀው መካኒክ የሚፈትሸው ጉድለት ከመኪናው ጤነኝነት ማለትም አገልግልት መስጠት እና አለመስጠት ጋር በተያያዘ እንጂ የሻንሲን እና የሞተርን ቁጥር ኦርጅናልነትን የሚጨምር አይደለም። ይህ ማለት አመልካች መኪናውን ሲሸጡ ይህ ጉድለት መኖሩን ያውቁ ነበር ለማለትም አስቸጋሪ ነው። ምክንያቱም አመልካችም በአቤቱታቸው እንደገለፁት መኪናው የተላለፈላቸው ከላላ ሰው መሆኑን የገለፁ በመሆኑ ይህን ምርመራ የመካኒክ ምርመራ የሚያካትት ቢሆን ኑሮ ቀድመው የሚያውቁበት እድል ይኖራቸው ነበር።
ሆኖም አመልካች ጉድለቱ መኖሩን በፍፁም አላውቅም በማለት ይከራከሩ እንጂ ጉድለቱ የለም አላለም፣ እያነሱ ያለት ርክክብ ከተፈፀመ በኋላ ከእጄ ወጥቶ በተጠሪ እጅ ገብቷል ስለሆነም ኃላፉነት ተላልፎል የሚል ሆኖ ተገኝቷል። ኃላፉነት ተላልፎል ጉድለቱ አይመለከተኝም ለማለት ደግሞ ቀድሞ ጉድለቱ ያለመኖሩን በእርግጠኝነት ማረጋገጥ የሚገባው ኃላፉነቱ ከተላለፈ በኋላ ነው ጉድለቱ የደረሰው የሚለው ወገን መሆን ይኖርበታል።
እንዱህ ከሆነ ጉድለቱ መኖሩ የተረጋገጠ በመሆኑ ይህ ጉድለት ደግሞ ገዢን አንድ የንብረት ባለቤት ሉያገኝ የሚችለውን መብት የሚቀንስ ወይም ጨርሶ የሚያሳጣ ከሆነ ውለ የተፈፀመው በመሳሳት በመሆኑ የማይፈርስበት ምክንያት አይኖርም። ይህንwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ተሽከርካሪ ተጠሪ የአገልግልት ዘርፍ በመቀየር ሥራ ላይ ለማዋል የማይችለ እና በትራንስፖርት ባለሥልጣን አባባል ቀይ ሰላዲ ላይ የተመዘገበ በመሆኑ የገዙትን ንብረት ስም ብቻ ማዛወራቸው ንብረቱን ህግ በሚፈቅደው መልክ በመቀየር ሉጠቀሙ የማያስችላቸው አዲጋች ነገር ተፈጥሮባቸዋል። ስለሆነም የገዙትን ንብረት በፈለጉት መልኩ መጠቀም የማያስችል ሁኔታ መፈጠር ደግሞ ውለ ከመደረጉ በፉት ችግሩ/ጉድለቱ እንዲለ ቢያውቁ ኑሮ ውለን አይፈጽሙም ነበር የሚያሰኝ በመሆኑ ጉድለት ያለበት ውለ ነው ተብል በስር ፍርድ ቤት እንዱፈርስ መወሰኑ እና በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1815 መሰረት ተዋዋይ ወገኖች ወደ ነበሩበት እንዱመለሱ በሚል የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ሉያስብል የሚችል ምክንያት አልተገኘም። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤትን ውሣኔ በማጽናት አቤቱታውን አልተቀበልነውም ስለሆነም ተከታዩ ውሣኔ ተሰጥቷል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ/ 156835 ህዲር 16 ቀን 2ዐዐ8 ዓ.ም. በዋለው ችልት የስር ፍርድ ቤትን ውሣኔ በማጽናት የሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ባለመገኘቱ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙ ያወጡት ወጪ ካለ የየራሣቸውን ይቻለ።
የውሣኔው ትክክል ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤት ይድረስ።
መዝገቡ ውሣኔ ስላገኘ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.