በአንድ ውል ላይ የገደብ (የመቀጫ)ስምምነት በተደረገ ጊዜ ባለገንዘቡ ተቃራኒ ስምምነት ከላለ በቀር ውለ እንዱፈፀም እንዱሁም የመቀጮ ገንዘብ እንዱከፈል ለመጠየቅ አቶ ሰለሞን መርደኪዮስ እና www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. VIII ሲሆን ነገር ግን መቀጮ የሚከፈለው የውለ መዘግየት ወይም ተጨማሪ ግዳታዎች ካለ የእነሱ አለመፈፀም የመቀጮውን ክፍያ የሚያስከትል ሲሆን ስለመሆኑ ፍ/ብ/ህ/ቁ 1890(1)(2) አቶ ሲሳይ ለበኔ
No summary available.
ታህሳስ 26 ቀን 2011 ዓ.ም.
ዳኞች- ተኽሉት ይመስል ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነአ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራው ፀሐይ መንክር አመልካች- አቶ ሰለሞን መርደኪዮስ- ቀረቡ:: ተጠሪ- አቶ ሲሳይ ለበኔ- አልቀረቡም:: በዚህ መዝገብ የተያዘውን ጉዲይ ከሰ/መ/ ጋር በማጣመር መርምረን የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
ለሰበር አቤቱታዎቹ መቅረብ ምክንያት የሆነው ክርክር የተጀመረው ተጠሪ በአመልካች ላይ በደቡብ ክልል አርባ ምንጭ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ ነው።
ተጠሪ ባቀረቡት ክስ፡- ከገኔ ዩናይትድ የመኪና አስመጪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጋር በነበረን ውል መሰረት ቅድመ ክፍያ ብር 160,000.00 (መቶ ስድሳ ሺህ) በመክፈል ሚኒባስ መኪና ለመውሰድ ስጠባበቅ ድርጅቱ የኢኮኖሚ ችግር ገጥሞት ሉፈጽም ባለመቻለ የአሁኑ አመልካች ለድርጅቱ ከሚከፍለው ብር 254,000.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ አራት ሺህ) ውስጥ የእኔን ገንዘብ ሉከፍል የዔዲ ማስተላለፍ ውል አድርገናል።
ነገር ግን አመልካች ብር 4,000.00 (አራት ሺህ) ብቻ ከፍል ላላውን ስልላከፈለ ቀሪውን ብር 156,000.00 (መቶ ሃምሳ ስድስት ሺህ) ከህጋዊ ወለድ ጋር እንዱሁም በውለ ከተመለከተው ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) መቀጮና ክርክሩ ካስከተለው ወጪና ኪሳራ ጋር እንዱከፍል ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
አመልካች ለክሱ በሰጡት መልስ በውለ መሰረት የዔዲ መክፈያ ጊዜ ገና ወደፉት ነው፤ በየሳምንቱ ብር 2,000.00 (ሁለት ሺህ) ለመክፈል የተስማማን ሲሆን የሁለት ሳምንት ብር 4,000.00 (አራት ሺህ) እንደከፈልኩ ውለ እንደተቋረጠ አድርጎ መክሰሱwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ያላግባብ ነው፤ ዔዲው በአንድ ጊዜ የሚከፈል ሳይሆን በ80 ሳምንታት የሚከፈል ነው፤
መኪናዬ ላይ የደረሰው ብልሽት ለውለ አለመፈፀም ምክንያት መሆኑን እያወቀ ክስ መመስረቱም ያላግባብ ነው፤ ስለሆነም በየሳምንቱ ብር 2,000.00 (ሁለት ሺህ) እየከፈልኩ ዔዲውን እንድጨርስ ይወሰን በማለት ተከራክረዋል።
ጉዲዩ በዚህ መልኩ የቀረበለት የስር ፍርድ ቤት ክርክርና ማስረጃውን መርምሮ እንደውለ ግዳታውን ያልተወጣ ተከሳሽ ስለመሆኑ በማስረጃ ስለተረጋገጠና ተከሳሽ በመኪናው መበላሸት ምክንያት እንደውለ አለመፈጸሙን የገለፀ ቢሆንም ስለመኪናው መበላሸት በውለ ላይ ያልተገለፀ በመሆኑ መከላከያ ላሆን አይችልም፤ በልላ በኩል በውለ አንቀጽ 6 መሰረት መቀጮ ብር 50,000.00 ሉከፍል እንደሚገባ የተመለከተ ቢሆንም ይህ የመቀጮ ገንዘብ የተጋነነ እና ለህግና ለሞራል ተቃራኒ በመሆኑ ሉሻሻል ይገባል በማለት ተከሳሽ (የአሁን አመልካች) ያልከፈለትን ብር 156,000.00 ከ9% ወለድ ጋር እንዱከፍለ እንዱሁም ከሳሽ የወጪና ኪሳራ ዝርዝር እንዱያቀርቡ በማለት ወስኗል።
በዚህ ውሳኔ ላይ የአሁን ተጠሪ በውል የተመለከተው የመቀጮ ገንዘብ እንዱከፈል አለመወሰኑን በመቃወም የይግባኝ ቅሬታቸውን ለጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዋል። ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተከሳሽ የውል ግዳታውን በአግባቡ አለመወጣቱ በማስረጃ ከተረጋገጠ በኋላ በውል የተመለከተው መቀጮ ሉከፈል አይገባም መባለ አላግባብ ነው በማለት የስር ፍርድ ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ አሻሽል በውላቸው የተቀመጠውን ብር 50,000.00 አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍል ወስኗል።
አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም ቅሬታቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበው ችልቱም ጉዲዩን መርምሮ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ በመሻር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔን አጽንቷል።
በዚህ ውሳኔ ላይ የአሁን ተጠሪ ቅሬታቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት አቅርበዋል። የሰበር ችልቱ የግራቀኙን ክርክር መርምሮ የሥር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ በማሻሻል አመልካች ዋናውን ገንዘብ ብር 156,000.00 እና በውላቸው የተስማሙበትን ብር 50,000.00 ለተጠሪ ሉከፍለ ይገባል፤ መቀጮ እንዱከፍለ የተወሰነ በመሆኑ ወለድ 9% ሉከፍለ አይገባም በማለት ወስኗል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የሰበር አቤቱታው ለዚህ ፍርድ ቤት የቀረበው ይህን በመቃወም ነው።
አመልካች ነሒሴ 18/2010 ዓ.ም ባቀረቡት አቤቱታ ገና ወደፉት ሰማንያ ሳምንት የክፍያ ጊዜ ላለው ዔዲ መቀጮ እንድከፍል መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ ተሽሮ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ እንዱፀና ይወሰንልኝ በማለት ጠይቀዋል።
ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብና ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት የተደረገ ሲሆን ተጠሪ ጥቅምት 29/2011 ዓ.ም በተፃፈ መልስ ውሳኔ የተሰጠው በመካከላችን የተደረገውን ውል እና የቀረበውን ማስረጃ መሰረት በማድረግ በመሆኑ እንዱሁም የሰበር ቅሬታው የተፈጸመውን የህግ ስህተት የሚያሳይ ባለመሆኑ ውድቅ ተደርጎ ውሳኔው እንዱፀና በማለት ተከራክረዋል። አመልካችም የመልስ መልስ አቅርበዋል።
በልላ በኩል በሰ/መ/ የተያዘው ጉዲይ የወጪና ኪሳራን የተመለከተ ነው። ተጠሪ በአርባ ምንጭ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የወጪ ዝርዝር አቅርበው ፍርድ ቤቱ ዝርዝሩን መርምሮ ውሳኔ ባገኘው አጠቃላይ ብር 206,000.00 ላይ የጠበቃ አበል 7% ብር 14,420.00፣ የዲኝነት ብር 4,850.00፣ የምስክር አበል ብር 100.00፣ የቴምብር ብር 52.00 በድምሩ ብር 19,422.00 (አስራ ዘጠኝ ሽህ አራት መቶ ሃያ ሁለት) የአሁን አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍለ ወስኗል። ይግባኙ የቀረበለት የጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጠበቃ አበል አሻሽል 5% ብር 10,300.00 ላሆን ይገባል በማለት ላላውን ዝርዝር ተቀብል በአጠቃላይ ብር 15,302.00 (አስራ አምስት ሽህ ሶስት መቶ ሁለት) ወጪ እንዱተካ ወስኗል። የክልለ ሰበር ችልትም ይህን ውሳኔ ተቀብልታል። በዚህ ውሳኔ ላይ አመልካች ነሃሴ 12/2010 ዓ.ም ለዚህ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ቅሬታ የሥር ፍርድ ቤቶች የመቀጮውን ብር 50,000.00 አካተው የጠበቃ አበል እንዱታሰብበት ማድረጋቸው ስህተት ስለሆነ የጠበቃ አበል መታሰብ ያለበት ከዋናው ዔዲ ብር 156,000.00 ላይ ብቻ መሆን አለበት ተብል እንዱታረም ጠይቀዋል።
ተጠሪ ውሳኔው እንዱፀና በመከራከር መልስ ሰጥተዋል።
ጉዲዩ ለምርመራ የተቀጠረው በዚህ ሁኔታ ሲሆን በበኩላችን ቅሬታ በቀረበባቸው ውሳኔዎች የተፈፀመ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን መርምረናል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
እንደመረመርነው የዔዲ ማስተላለፍ ውል መደረጉና ስምምነት ከተደረገበት ገንዘብ ውስጥ አመልካች ብር 4,000.00 (አራት ሺህ) ብቻ ከፍለው ቀሪውን ብር 156,000.00 (መቶ ሃምሳ ስድስት ሺህ) ያልከፈለ መሆኑ ግራ ቀኙን አላከራከረም።
አመልካች በስር ፍርድ ቤት ለክሱ በሰጡት መልስ ዔዲው በአንድ ጊዜ የሚከፈል ሳይሆን በ80 ሳምንታት የሚከፈል መሆኑንና በየሳምንቱ ብር 2,000.00 (ሁለት ሺህ) እየከፈልኩ ዔዲውን እንዱያጠናቅቁ እንዱደረግ ተከራክረው የነበረ ቢሆንም የስር ፍርድ ቤት ማስረጃውን ተመልክቶ ዔዲውን በአንድ ጊዜ እንዱከፍለ ሲወስን የበኩላቸውን ይግባኝ ለበላይ ፍርድ ቤቶች አላቀረቡም። ለይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ቅሬታ ያቀረቡት የአሁን ተጠሪ ሲሆኑ ቅሬታቸውም በውል የተመለከተው የመቀጮ ገንዘብ እንዱከፈል አለመወሰኑን የተመለከተ ነበር። ስለሆነም የአሁን አመልካች ገና ወደፉት ሰማንያ ሳምንት የክፍያ ጊዜ ያለው ዔዲ ነው በማለት በዚህ ፍርድ ቤት ያቀረቡትን ክርክር የምንቀበለው አይሆንም።
ይልቁንም የዚህን ፍርድ ቤት ውሳኔ የሚጠይቀው ቀዲሚ ጭብጥ እንደውለ እንዱፈፀም እንዱሁም የመቀጮ ገንዘብ እንዱከፈል የተሰጠው ውሳኔ ህጉን የተከተለ መሆን አለመሆኑ ነው። ተጠሪ በሥር ፍርድ ቤት ባቀረቡት የዲኝነት ጥያቄ ያልተከፈላቸው ቀሪ ብር 156,000.00 (መቶ ሃምሳ ስድስት ሺህ) ከህጋዊ ወለድ ጋር እንዱሁም በውለ ከተመለከተው ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) መቀጮ እንዱከፈላቸው ጠይቀዋል። የሥር ፍርድ ቤቶች የተለያየ ውሳኔ የሰጡ ሲሆን ጉዲዩን በመጨረሻ የተመለከተው የክልለ ሰበር ችልት አመልካች ዋናውን ገንዘብ ብር 156,000.00 እና በውላቸው የተስማሙበትን ብር 50,000.00 መቀጮ ለተጠሪ ሉከፍለ ይገባል ነገር ግን መቀጮ እንዱከፍለ የተወሰነ በመሆኑ ወለድ 9% ሉከፍለ አይገባም ብሎል።
የገደብ (የመቀጫ) ስምምነት በተደረገ ጊዜ ባለገንዘቡ ተቃራኒ ስምምነት ከላለ በቀር ውለ እንዱፈፀም እንዱሁም የመቀጮ ገንዘብ እንዱከፈል ለመጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1890(1) ሥር የተደነገገ ሲሆን በዚህ ረገድ ባለገንዘቡ ያለው መብት ግን የተገደበ መሆኑን ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1890(2) መገንዘብ ይቻላል።
በፍ/ብ/ህ/ቁ 1890(2) እንደተመለከተው፡-www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
“ኪሳራው የተወሰነው ለሥራው አፈፃፀም መዘግየት ብቻ ወይም ለተጨማሪ ግዳታዎች አለመፈፀም ካልሆነ በቀር ባለገንዘቡ ውለ እንዱፈፀምና (ገደቡን) መቀጮውንም እንዱቀበል ሁለቱንም በአንድ ጊዜ ለመጠየቅ አይችልም” ።
የድንጋጌው የእንግሉዝኛ ቅጅም፡-- “He may not require both the enforcement of the contract and the penalty unless the penalty was provided in respect of delay or the non-performance of a collateral obligation” በማለት ይደነግጋል።
ከፍሲል ከተጠቀሰው ድንጋጌ መረዲት እንደሚቻለው በፍ/ብ/ህ/ቁ 1890(1) የተመለከተው ድንጋጌ ተጠቃሚ ለመሆን መቀጮ የሚከፈለው የውለ መዘግየት ወይም ተጨማሪ ግዳታዎች ካለ የእነዚህ አለመፈፀም የመቀጮውን ክፍያ የሚያስከትል ሲሆን ነው። በተያዘው ጉዲይ ግራቀኙ ባደረጉት ስምምነት የውል ግዳታውን ያልተወጣ ወገን ውለን ላከበረው ወገን መቀጮ ብር 50,000.00 ለመክፈል የተስማሙ መሆናቸውን ከስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መገንዘብ የሚቻል ሲሆን ይህ በመዘግየት የሚከፈል ኪሳራ ስለመሆኑና ከተጨማሪ ግዳታዎች አለመፈፀም ጋር የሚያያዝ ስለመሆኑ በማረጋገጥ የተሰጠ ውሳኔ የለም። ይህ በሆነበት ሁኔታ ዋናው ዔዲ ተከፍል እንደውለ እንዱፈፀም እና መቀጫ (ገደብ) ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) እንዱከፈል መወሰኑ የፍብ/ህ/ቁ 1890(2) ድንጋጌን እና የውለን ይዘት እንዱሁም የግራቀኙን ክርክር መሰረት ያደረገ ባለመሆኑ መቀጮ እንዱከፈል የተሰጠው የውሳኔ ክፍል የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል።
በልላ በኩል ክርክሩ ያስከተለውን ወጪ በተመለከተ የሥር ፍርድ ቤቶች የመቀጮውን ብር 50,000.00 አካተው የጠበቃ አበል እንዱታሰብበት ማድረጋቸው ተገቢ ስለማይሆን የጠበቃ አበል 5% መታሰብ ያለበት በዋናው ዔዲ ብር 156,000.00 ላይ መሆን አለበት ብለናል። ስለሆነም ተከታዩንም ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በደቡብ ብ/ብ/ህ/ክልል መንግስት የአርባ ምንጭ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ በ29/01/2009 ዓ.ም፤ የጋሞ አካ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በ27/04/2010 ዓ.ም፤ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ በ18/07/2010 ዓ.ም እንዱሁም የክልለ ሰበር ችልት በሰ/መ/ በ20/11/2010 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሻሽሎል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
አመልካች ዋናውን ዔዲ .00 (መቶ ሃምሳ ስድስት ሺህ) የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ከሰጠበት ከ29/01/2009 ዓ.ም ጀምሮ ዔዲው ተከፍል እስካለቀበት ድረስ ከሚታሰብ 9% ወለድ ጋር እንዱከፍለ በማለት ወስነናል።
ክርክሩ ያስከተለውን ወጪ በተመለከተ የአርባ ምንጭ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ በ06/07/2010 ዓ.ም፤ የጋሞ አካ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በ26/08/2010 ዓ.ም፤ እንዱሁም የክልለ ሰበር ችልት በሰ/መ/ በ30/11/2010 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔ ተሻሽሎል። ውሳኔ ባገኘው ብር 156,000.00 (መቶ ሃምሳ ስድስት ሺህ) ላይ የጠበቃ አበል 5% ብር 7800.00፣ የዲኝነት ብር 4,850.00፣ የምስክር አበል ብር 100.00፣ የቴምብር ብር 52.00 በአጠቃላይ የአሁን አመልካች ብር 12,802.00 (አስራ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ሁለት) ወጪ ለተጠሪ እንዱተኩ ወስነናል።
ላላውን ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ።
በዚህ መዝገብ የተሰጠው ውሳኔ ተገልብጦ ከሰ/መ/ ጋር ይያያዝ።
No topics extracted.