በአደራ የተሰጠ ገንዘብ መኖርን ለማስረዲት ተቀባይነት የሚኖረዉ ማስረጃ በጽሐፍ የተደረገ የአደራ ዉል እንጂ በልላ የሰዉ ወይም የሰነድ ማስረጃ ስላለመሆኑ የፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 2782 እና 2472(1)
No summary available.
ቀን - 30/09/2010ዓ.ም ዳኞች፡- ተኽሉት ይመሰል ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራዉ አብዬ ካሳሁን አመልካች፡- አቶ ቶዉፉቅ ላለ - ቀርበዋል ።
ተጠሪ፡- አቶ ስራጅ ጀማል - ቀርበዋል ።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ክርክሩ የተጀመረዉ በስልጤ ወረዲ ፍርድ ቤት ሲሆን፣ አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል። የአመልካች ክስም በአጭሩ በ2004 ዓ.ም ወደ አረብ አገር ስሄድ ዋጋቸዉ በድምሩ ብር 19,000.00 የሚያወጣዉን አንድ በሬ፣ አንዱት ላም ከነጥጃዋ እና አንዱት ሴት አህያ ተከሳሽ እንዱጠብቅልኝ አደራ ሰጥቻቸዋለሁ፤
እንዱሁም መኖሪያ ቤት እና ንግድ ቤት እንዱገዙልኝ አረብ አገር ሆኜ ብር 320,000.00 የላኩላቸዉ ቢሆንም ተከሳሽ ብር 120,000.00 መልሰዉልኝ ቀሪዉን ገንዘብ ለመመለስ ፉቃደኛ አልሆኑም፤ በመሆኑም ከብቶቹን እንዱሁም ቀሪዉን ገንዘብ ብር 200,000.00 ተከሳሽ እንዱመልሱ ይወሰንልኝ የሚል ይዘት ያለዉ ነዉ።
ተጠሪ ለቀረበባቸዉ ክስ በሰጡት መልስ በክሱ የተጠቀሱትን ከብቶች ከከሳሽ በአደራ አልተቀበልኩም፤ ከሳሽ ቤት እንዱገዛላቸዉ ዉጭ አገር ሆነዉ የላኩልኝ ገንዘብ የለም፤
ተከሳሽ ተከፍልኛል ያለት ብር 120,000.00 ብድር የሰጠሁት ነዉ በማለት የቀረበባቸዉ ክስ ዉድቅ እንዱሆን በማለት ተከራክረዋል። በበኩላቸዉ ባቀረቡት የተከሳሽwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ከሳሽነት ክስ በብድር መልክ በባንክ ሂሳባቸዉ ገቢ ያደረግኩትን ገንዘብ ብር 120,000.00 ከሳሽ እንዱከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት የጠየቁ ሲሆን፤ አመልካች በበኩለ ከተጠሪ የተበደርኩት ገንዘብ የለም በማለት ተከራክረዋል።
ጉዲዩ በመጀመሪያ የቀረበለት የወረዲ ፍርድ ቤትም በዚህ መልኩ ከግራ ቀኝ የቀረበዉን ክርክር እንዱሁም ማስረጃ ከሰማ በኋላ አመልካች ከብቶቹን ለተጠሪ አደራ መስጠቱን ለማስረዲት ቀርበዉ የተሰሙት የሰዉ ምስክሮች ቃል የተለያየ እና እርስ በርሱ የሚጋጭ በመሆኑ በግራ ቀኝ መካከል በህግ አግባብ የተደረገ የአደራ ዉል ስለመኖሩ አለመረጋገጡን፤ እንዱሁም ከብር 500 በላይ የሆነ ጥሬ ገንዘብን በአደራ የመስጠት ዉል ስለመኖሩ ማስረዲት የሚቻለዉ በጽሐፍ በተደረገ ዉል መሆኑን እና አመልካች በዚህ መልኩ ያቀረቡት ማስረጃ አለመኖሩን (የፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 2782(1) እና 2472(1) በዋቢነት በመጥቀስ) የአመልካችን ክስ ዉድቅ ያደረገ ሲሆን፤ ተጠሪ ለአመልካች .00 አበድሬያለሁ ያለትንም በተመለከተ በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 2472(1) መሰረት ይህን የሚያስረዲ በጽሐፍ የተደረገ የብድር ዉል አለመኖሩን ጠቅሶ የተከሳሽ ከሳሽነት ክሱንም ዉድቅ በማድረግ ወስኗል። አመልካች ይህን ዉሳኔ ባለመቀበል ለስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረበ ቢሆንም፣ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤቱን ዉሳኔ በማጽናቱ አመልካች ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም የክልለ ሰበር አጣሪ ችልት የቀረበዉን የሰበር አቤቱታ ሰርዞታል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበዉም በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ሲሆን፣ አመልካች በቀን 20/03/2010 ዓ.ም ተዘጋጅቶ በቀረበ የሰበር አቤቱታ በስር በክልለ በየደረጃዉ ባለት ፍርድ ቤቶች የተሰጡት ዉሳኔዎች እና ትዕዛዝ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመባቸዉ ናቸዉ የሚለባቸዉን ምክንያቶች በመዘርዘር ታርሞ ይወሰንላቸዉ ዘንድ ዲኝነት ጠይቀዋል። አቤቱታዉ ተመርምሮ ያስቀርባል በመባለም ተጠሪ በተደረገላቸዉ ጥሪ መሰረት ቀርበዉ ግራ ቀኝ ክርክራቸዉን በጽሐፍ ተለዋዉጠዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸዉ ነዉ። እኛም የስር ፍርድ ቤቶች የአመልካችን ክስ ዉድቅ በማድረግ የሰጡትን ዉሳኔ አግባብነት ከግራ ቀኝ ክርክር እናwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምረናል። ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለዉ አመልካች በስር ፍርድ ቤት ላቀረቡት ክስ መሰረት ያደረጉት ተጠሪ የተለያዩ ከብቶችን ሉጠብቁላቸዉ በአደራ መቀበላቸዉን እንዱሁም ቤት እንዱሰሩላቸዉ አመልካች የላኩትን ገንዘብ ተቀብለዉ አለመመለሳቸዉን ነዉ። ተጠሪ በበኩላቸዉ ከብቶቹንም ሆነ ገንዘቡን ከአመልካች በአደራ አለመቀበላቸዉን ገልጸዉ የተከራከሩ መሆኑን የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ ግልባጭ ያሳያል። በመሆኑም አመልካች በክሱ የተመለከቱትን ከብቶችም ሆነ ገንዘቡን ለተጠሪ በአደራ መልክ የሰጣቸዉ ስለመሆኑ በቅድሚያ የማስረዲት ግዳታ ይኖርባቸዋል። ከብቶቹን በአደራ መስጠታቸዉን በተመለከተ አመልካች የሰዉ ምስክሮችን አቅርበዉ ያሰሙ ሲሆን፣ የወረዲዉ ፍርድ ቤትም አመልካች ያቀረቧቸዉን የሰዉ ምስክሮች ቃል በመመዘን፣ የቀረቡት የሰዉ ምስክሮች ቃል የተለያየ እና እርስ በእርሱ የሚጋጭ መሆኑን ጠቅሶ የአደራ ዉል በመካከላቸዉ ስለመደረጉ አላስረደም በሚል ድምዲሜ ላይ መድረሱን ተመልክተናል። በልላ በኩል በኢፋዱሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3-ለ) እንዱሁም በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 10 መሰረት የዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ስልጣን መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተትን በማረም ላይ የተገደበ በመሆኑ ከፍሬ ነገር ጋር በተያያዘ በስር ፍርድ ቤቶች የቀረቡትን ማስረጃዎች ድጋሚ ሉመዝን የሚችልበት ህጋዊ ምክንያት አይኖርም። ስለሆነም አመልካች በክሱ የተመለከቱትን ከብቶች ለተጠሪ በአደራ ስለመስጠቱ አልተረጋገጠም በሚል የስር ፍርድ ቤት የደረሰበት ድምዲሜ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ለማለት የማይቻል በመሆኑ አመልካች በዚህ ረገድ ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት ያለዉ አይደለም።
ከዉጭ አገር የተላከ ገንዘብን በተመለከተ አመልካች የሚከራከሩት ተጠሪ የንግድ እና የመኖሪያ ቤት እንዱሰሩላቸዉ ገንዘቡን መላካቸዉን ነዉ። ከላይ እንደተመለከተዉ ተጠሪ የተላከላቸዉ የአደራ ገንዘብ አለመኖሩን ገልጸዉ ተከራክረዋል። የስር የወረዲዉ ፍርድ ቤት በዉሳኔዉ እንዲመለከተዉም፣ በአደራ የተሰጠ ገንዘብ መኖሩን ለማስረዲት ተቀባይነት የሚኖረዉ ማስረጃ በጽሐፍ የተደረገ የአደራ ዉል ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 2782 እና 2472(1) ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ መረዲት ይቻላል። ይሁንና አመልካች በዚህ መልኩ ያቀረቡት ማስረጃ የለም። በልላ የሰዉ ወይም የሰነድ ማስረጃ ደግሞ ይህን ማረጋገጥ አይቻልም።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በአጠቃላይ የስልጤ ወረዲ ፍርድ ቤት የአመልካችን ክስ ዉድቅ በማድረግ የሰጠዉ ዉሳኔ እንዱሁም የስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የክልለ ሰበር ችልት የወረዲዉን ፍርድ ቤት ዉሳኔ በማጽናት፣ በቅደም ተከተል፣ የሰጡት ፍርድ እና ትዕዛዝ በህግ አግባብ ነዉ ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አላገኘንም። በመሆኑም ተከታዩ ተወስኗል።
የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/ 08453 በቀን 20/12/09 ዓ.ም በዋለዉ ችልት፣ የስልጤ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/11642 በቀን 19/06/09 ዓ.ም በዋለዉ ችልት እንዱሁም የስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/13236 በቀን 25/09/09 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉን ዉሳኔ በማጽናት፣ የሰጠዉ ትዕዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት በተደረገ ክርክር ምክንያት የወጣዉን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ።
በዚህ ችልት በቀን 30/05/2010 ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረዉ ዔግድ ተነስቷል፤
ይፃፍ።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።
No topics extracted.