የዉክልና ሰነድችን ለማረጋገጥና ለመመዝገብ ስልጣን በተሰጠዉ አካል የተረጋገጠ ሰነድ ሙለ እምነት የሚጣልበት ማስረጃ ሆኖ ቅቡልነት ያለዉ ስለመሆኑና የሰነደን ቅቡልነት መቃወም የሚቻለዉም በበቂ ምክንያት ፍርድ ቤት ሲፈቅድ ብቻ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ/922/08 አንቀጽ 23/1/
No summary available.
ቀን-ግንቦት 16 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንዲሻዉ አዲነ ኃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች:- ወ/ሮ ዘቢባ ሙሳ ተጠሪ፡- አቶ አማን በሪሶ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ለዚህ ሰበር ክርክር መነሻ የሆነው የከተማ ቦታ ይዞታ ጉዲይ ሲሆን የተጀመረው በኦሮሚያ ክልል በአዲማ ወረዲ ፍርድ ቤት ነው። በዚሁ ፍ/ቤት የአሁኑ አመልካች በተጠሪ ላይ ያቀረቡት ክስ ይዘት፡- በአዲማ ከተማ 01 ቀበላ ዉስጥ የሚገኘዉን የካርታ /06 የሆነዉ 180 ካ.ሜ የመኖሪያ ቤት ቦታ በአዲማ ከተማ መስተዲድር ተሰጥቶ በስሜ ተመዝግቦ የሚገኘዉን ተጠሪ ምንም መብት ሳይኖረዉ ቦታዉ ላይ ቤት መስራቱን አይቼ ግንባታዉን እንዱያቆም ብጠይቀዉም ፈቃደኛ ስላልሆነ ግንባታዉን በራሱ ወጪ አፍርሶ ይዞታዉን ይልቀቅልኝ የሚል ነዉ።
ተጠሪ በበኩላቸዉ በሰጡት መልስ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ መሬት አስመልክቶ አመልካች መንግስት አካል ጋር በመቅረብ በዉክልና በቀን 01/02/2008 ዓ.ም ለአቶ ፊአድ ጀማል ሙሳ ይዞታዉንና ንብረቷን እንዱሸጥ፣ እንዱለዉጥ፣ ለ3ኛ ወገን በማንኛዉም ሁኔታ እንዱያስተላልፍ ዉክልና ሰጥታዉ፤ እሱም ዉክልና አቶwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
አህመድ ለሚባል አሳልፍ ሰጥቶ ዉክልናዉ ሕጋዊ መሆኑን አረጋግጬ በቀን 05/07/2008 ዓ.ም በተጻፈ የግዥ እና ሽያጭ ዉል በብር 250,000 ተስማምቼ ገዝቼ ዉለም ስልጣን ባለዉ አካል ጸድቆ የሉዝ ዉለ ወደ ስሜ ተዛዉሮ የይዞታ ማረጋገጫ ተሰጥቶኝ ባለይዞታ የሆንኩበትና አመልካች ሳይቃወሙ የገነባሁት ቤት ስለሆነ ክሱ ተቀባይነት የለዉም በማለት ተከራክረዋል።
የወረዲዉ ፍ/ቤት የግራቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ መርምሮ ተጠሪ ክርክር ያስነሳዉን ይዞታ አመልካች ስልጣን ባለዉ አካል ፉት ለመሸጥ ዉክልና ከተሰጠዉ ሰዉ ጋር ተዋዉል የገዛና በአመልካች ስም የነበረዉ ወደ ተጠሪ ተዘዋዉሮና ተመዝግቦ የሚታወቅ በመሆኑ እንዱሁም አመልካች ከኢሜግሬሽን እና የዜግነት ጉዲዮች ጽ/ቤት ያቀረቡት ማስረጃም ቢሆን ከአመልካች ጋር ሳይሆን ከአመልካች ተወካይ ጋር ዉለ የተደረገ በመሆኑና ተጠሪ አመልካች ከአገር መኖር አለመኖሯን የማወቅ ግዳታ የላለዉ በመሆኑ አመልካች ተጠሪ ይዞታዬን በሕገ-ወጥ መንገድ ይዟል በማለት ያቀረቡት ክስ ተቀባይነት የለዉም በማለት ወስኗል። በዚህ ዉሳኔ ቅር ተሰኝተዉ አመልካች ባቀረቡት ይግባኝ መነሻ ጉዲዩን የተመለከተዉ የአዲማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ግራ ቀኙን ካከራከረ በኃላ የስር ፍ/ቤትን ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል። በመቀጠል አመልካች የሰበር አቤቱታ ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ቢያቀርቡም አቤቱታዉ ተቀባይነት አላገኘም። ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚሁ ውሳኔ ላይ አመልካች ቅር በመሰኘታቸዉ ዉሳኔዉን ለማስለወጥ ነው።
አመልካች ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ይዘት፡- ለክርክሩ ምክንያት የሆነዉ የመኖሪያ ቤት ቦታዬ እንዱሸጥም ሆነ እንዱለወጥ የሰጠሁት ሕጋዊ ዉክልና እንደላለ እየተከራከርኩ እና ዉክልናዉ ተሰጥቶኛል በተባለበት ወቅትም ሀገር ዉስጥ ያልነበርኩ መሆኔን በመግለጽ የኢሚግሬሽን እና የዜግነት ጉዲዮች ቢሮ በቀን 22/03/09 ዓ.ም ለአዲማ ወረዲ ፍ/ቤት በመግለጽ ተጽፍ እያለ ጉዲዩ በሚገባ ሳይጣራ ሀሰተኛ በሆነ ዉክልና ስሙ ከአመልካች ጋር የሚመሳሰል በመሆኑ ብቻ ተጠሪ በዚህ ዉክልና መሰረት በግዢ ዉል የያዘዉ ነዉ በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ። የምስራቅ ሸዋ ዞን ፍትህ ቢሮ በቀን 15/02/2009 ዓ.ም ለወረዲዉ ፍ/ቤት በጻፈዉ ደብዲቤ አመልካች በአካል ቀርባ የዉክልና የሆነ በቀን 01/02/2008 ዓ.ም ዉክልና ሰጥታለች በማለት ስለገለጸ ብቻ የወረዲዉ ፍ/ቤት ዉሳኔ መስጠቱ ተገቢ አይደለም። ምክንያቱም ዉክልና ሰጥታለች በተባለበት ቀን በአገርwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ያልነበርኩ መሆኔን ስልጣን ከተሰጠዉ አካል በተጻፈ ደብዲቤ ተረጋግጧል። ስለሆነም ዉሳኔዉ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይሻርልኝ የሚል ነዉ።
የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች ዉክልናዉ ተሰጠ በተባለበት ጊዜ በሀገር ዉስጥ አልነበርኩም በማለት ከኢሚግሬሽን የተጻፈ መግለጫ ያቀረበችዉና በዉክልናዉ ላይ ያለዉ ፊርማ በፍረንሲክ እንዱመረመር የጠየቀችዉ በስር ፍ/ቤት የታለፈበትና ዉድቅ የተደረገበትን አግባብነት ለማጣራት ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል የተባለ ሲሆን ግራቀኙ መልስ እና የመልስ መልስ በጽሁፍ በማቅረብ ተከራክረዋል።
የተጠሪ መልስ ይዘት በአጭሩ፡- ከኢሚግሬሽን የመጣ ደብዲቤ እና የፍረንሲክ ምርመራን ከፍትሕ ቢሮ ከመጣዉ ደብዲቤ ጋር አመዛዝኖ ዉሳኔ መስጠት የስር ፍ/ቤት ማስረጃን የመመዘን ስልጣን እንጂ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስላልሆነ አቤቱታዉ ዉድቅ ይደረግልኝ። አመልካች በስር ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ በሕገ-ወጥ መንገድ ያለእኔ ፈቃድ የተደረገ የሽያጭ ዉል ይፍረስልኝ የሚል እስካልሆነ ድረስ የሚያዘዉ ጭብጥ ከቀረበዉ ክስ አንጻር ተጠሪ ንብረቱን የያዘዉ በሕገ-ወጥ መንገድ ነዉ ወይስ በሕጋዊ መንገድ የሚለዉ ነዉ። ለዚህ በማስረጃነት ያቀረብኩት አመልካች እራሷ ለወንድሟ የሰጠችዉን ዉክልና፣ ወንድሟ ለአቶ አህመድ የሰጠዉን ዉክልና፣ በእኔና በ2ኛ ተወካይ መካከል የተደረገ ሕጋዊ የሽያጭ ዉል እንዱሁም የሉዝ ዉል፣ በስሜ የተሰጠኝ ካርታና ፕላን እና የግንባታ ፈቃድ ነዉ። ዉክልናዉ ሕጋዊ ስለመሆኑ የፍትህ ቢሮ እና ማዘጋጃ ቤቱ ተጠይቆ በስር ፍ/ቤት ተረጋግጧል። ይህ መሰረት ተደርጎ ማስረጃ ተመዝኖ የተሰጠ ዉሳኔ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህትት ተፈጽሞበታል የሚባል አይደለም።
ኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት በ01/03/2009 ዓ.ም በጻፈዉ ደብዲቤ ላይ በግልጽ እንዲመለከተዉ አመልካች በአካል ቀርባ አገር ዉስጥ ስለመኖሯ አረጋግጦ ሳይሆን ካላቸዉ ዲታ ዉስጥ ባደረገዉ ማጣራት መሆኑን ገልጽዋል። ይህ ማስረጃ በአካል ቀርባ ከሰጠችዉ ዉክልና ጋር ተመዝኖ የተሰጠዉ ዉሳኔ ተገቢ ነዉ። በ01/03/2009 ዓ.ም በተጻፈዉ ደብዲቤ አመልካች በ5/03/2014 ወደ ሮም መሄዶን የገለጸ ሲሆን በ22/03/2009 ዓ.ም በጻፈዉ ደብዲቤ ላይ ደግሞ አመልካቿ በ09/02/2014 ወደ አገር ዉስጥ ገብታ በ05/06/2014 ከአገር መዉጣቷን ወይም ካናዲ መሄዶንና አገር ዉስጥ ተመልሳ ያልገባች መሆኑን ይገልጻል። ይህም እርስ በርሱ የሚጋጭ ነዉ። በፍረንሲክ ፊርማዉ መጣራት ነበረበት የሚለዉም ቢሆን ዉክልናዉ የመንደር ዉል ሳይሆንwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ስልጣን ከተሰጠዉ የመንግስት አካል ተረጋግጦ የቀረበ በመሆኑ ክርክሩ ተገቢነት የለዉም። ስለሆነም የስር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ባለመሆኑ ይጽናልኝ የሚል ነዉ። አመልካች በሰጡት የመልስ መልስ የሰበር አቤቱታቸዉን በሚያጠናክር መልኩ ተከራክረዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር በአጭሩ ከላይ የተመለከተዉን የሚመስል ሲሆን ከስር ፍ/ቤት ዉሳኔ እና ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል ተብል ከተያዘዉ ጭብጥ ጋር በማገናዘብ መርምረናል። መርምረን እንደተረዲነዉ በስር ፍ/ቤት አመልካች ክስ ያቀረቡት ተጠሪ በሕገ-ወጥ መንገድ ይዞታዬን በመያዝ የገነባዉን ግንባታ በራሱ ወጪ እንዱያፈርስ የሚጠይቅ ሲሆን ተጠሪ በበኩለ ይዞታዉ አስቀድሞ የአመልካች የነበረ ቢሆንም በሕጋዊ መንገድ የዉክልና ስልጣን ካለዉ ሰዉ ጋር ተዋዉል መግዛቱንና ሕጋዊ ባለይዞታ መሆኑን በመግለጽ ክሱ ዉድቅ እንዱደረግለት በመጠየቅ ተከራክሯል። የስር ፍ/ቤትም አመልካች ስልጣን ባለዉ የመንግስት አካል ጋር ቀርባ የዉክልና በሆነ ጥቅምት 01 ቀን 2008 ዓ.ም ለአቶ ፈአድ ጀማል ሙሳ ይዞታዉንና ንብረቱን እንዱሸጥ፣ እንዱለዉጥና ለ3ኛ ወገን በማንኛዉም መንገድ እንዱያስተላልፍ ዉክልና መስጠቷን፤ ተወካይዋ ደግሞ በተሰጠዉ ዉክልና መሰረት ለአቶ አህመድ በሪሶ በቀን 06/03/2008 ዓ.ም ምስራቅ ሸዋ ፍትሕ መምሪያ ቀርቦ ዉክልና መስጠቱን እንዱሁም አቶ አህመድ በሪሶ ደግሞ መጋቢት 05 ቀን 2009 ዓ.ም ከተጠሪ ጋር ባደረገዉ የሽያጭ ዉል ይዞታዉን ለተጠሪ ሸጦለት ቅድመ ሁኔታዎቹ ተሟልቶ የሉዝ ዉለ ወደ ተጠሪ ስም መዛወሩንና የይዞታ ማረጋገጫና የግንባታ ፈቃድ የተሰጠዉ መሆኑ አረጋግጧል። ዉክልናዎቹ ትክክለኛ መሆናቸዉ እና በአግባቡ ሽያጭና የስም ዝዉዉር ተደርጎ ይዞታዉ ለተጠሪ መተላለፈን የምስራቅ ሸዋ ፍትሕ መምሪያና በአዲማ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት ተጠይቀዉ አረጋግጠዋል።
አመልካች አጥብቃ የምትከራከረዉ ዉክልና ሰጥታለች በተባለችበት ወቅት አገር ዉስጥ ያልነበረች መሆኑን ኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዲዮች መስሪያ ቤት አረጋግጦልኛል እንዱሁም በዉክልናዉ ላይ ያለዉ ፊርማ የእኔ አይደለም፤ በፍረንሲክ ይመርመርልኝ በሚል ነዉ።
በመሰረቱ አንድ የዉክልና ሰነድ ሰነድችን ለማረጋገጥና ለመመዝገብ ስልጣን በተሰጠዉ አካል ፉት እንዱሰጥና እንዱመዘገብ ያስፈለገበት ዋናዉ ምክንያት ዉክልናዉwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ትክክለኛ እና በወካዩ አማካይነት የተሰጠ መሆኑን በማረጋገጥ ዉክልናን መሰረት ተደርገዉ የሚፈጸሙ ሕጋዊ ተግባራት የተሳለጡ እንዱሆኑ ለማስቻልና ዉክልናዉ በወካይ አልተሰጠም የሚል አላስፈላጊ ክርክርና ጥርጣሬዎችን ለማስወገድ ነዉ። በዚህ ረገድ በአዋጅ ቁ/922/08 አንቀጽ 23/1/ ላይ እንደተደነገገዉ በሰነድ መዝጋቢዉ አካል የተረጋገጠዉ ሰነድ ሙለ እምነት የሚጣልበት ማስረጃ ሆኖ ቅቡልነት ያለዉ ነዉ።
ይህንን ሰነድ ቅቡልነት መቃወም የሚቻለዉም በበቂ ምክንያት ፍርድ ቤት ሲፈቅድ ብቻ እንደሆነ በዚሁ አንቀጽ ንኡስ ሁለት ስር ተመልክቷል። ስለሆነም አመልካች ሰነደን የሚቃወሙበት በቂና ህጋዊ ምክንያት ካላቸዉ ሰነደ እንዱሰረዝ በህግ አግባብ ከሚጠይቁ በስተቀር በሚመለከተዉ አካል የተረጋገጠ የዉክልና ሰነድ ቅቡልነት ሉኖረዉ አይገባም የሚለዉ ክርክር ስለሰነድች ምዝገባ የወጣዉን አዋጅ ይዘትና ዓላማ ያላገናዘበ እንደሆነ መረዲት ይቻላል። ከዚህ አንጻር ከተወካይ ጋር ዉል የሚገባ ሰዉ ዉክልናዉ በተወካይ የተሰጠና ተመዝግቦ የሚገኝ መሆኑን ከማረጋገጥ ባለፈ ወካይ ውክልናዉ በተሰጠበት ወቅት በአገር ዉስጥ መኖር አለመኖራቸዉንና ፊርማዉ የወካይ መሆን አለመሆኑን የሚያጣራበት አግባብ የለም።
በተያዘዉ ጉዲይ አመልካች ተጠሪ ይዞታዉ በሽያጭ ዉል ተላልፍልኛል ያለበት ዉክልና በአመልካች ያልተሰጠና የሀሰት ነዉ በማለት የሚከራከሩት የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዲዩች መስሪያ ቤት አመልካች ከአገር የወጣችበትና ወደ አገር የገባችበትን ቀን የገለጸ በመሆኑ ዉክልና በተሰጠበት ጊዜ በአገር ያልነበርኩ በመሆኔ ዉክልናዉን ልሰጥ አልችልም ፊርማዉ የእኔ ባለመሆኑ በፍረንሲክ ይመርመርልኝ የሚል ነዉ። ዉክልናዉ ሰነድችን ለማረጋገጥና ለመመዝገብ ስልጣን በተሰጠዉ አካል ፉት ተሰጥቶ ተመዝግቦ የሚገኝ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ አመልካች ከአገር የወጡበትና ወደ አገር የገቡበትን ጊዜ በማረጋገጥ እንዱሁም በዉክልናዉ ላይ ያለዉ ፊርማ በፍረንሲክ ቢመረመርና ልዩነት አለዉ ቢባል እንኳ ዉክልናዉ በአመልካች አልተሰጠም የሚል ድምዲሜ ላይ የሚያደርስ አይሆንም። ስለሆነም አመልካች ከአገር የወጡበትን እና ወደ አገር የገቡበትን ጊዜ በማስረዲት እንዱሁም በዉክልና ሰነደ ላይ ያለዉ ፊርማ ከአመልካች ከተለመደዉ ፊርማ ጋር ልዩነት ያለዉ መሆን ያለመሆኑን በማስመርመር ዉክልናዉ በአመልካች አልተሰጠም የሚል ድምዲሜ ላይ መድረስ የሚቻል ባለመሆኑ፤ የስር ፍ/ቤት ዉክልናዉ በአመልካች የተሰጠና ተመዝግቦ የሚገኝ መሆኑን ሰነድችን ለመመዝገብና ለማረጋገጥwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ስልጣን ተሰጥቶት ዉክልናዉን የመዘገበዉን አካል በመጠየቅና በማረጋገጥ እንዱሁም በዉክልናዉ መሰረት የሽያጭ ዉል ተፈጽሞ ይዞታዉ ወደ ተጠሪ ስም በሕግ አግባብ ተላልፍ ተጠሪ ባለይዞታ የሆነበት መሆኑን በማረጋገጥ የአመልካችን ክስ ዉድቅ ማድረጉ የሚነቀፍ ሆኖ አልተገኘም።
ሲጠቃለል ተጠሪ ክርክር ያስነሳዉ ይዞታ በሕግ አግባብ ተላልፍለት የባለይዞታነት መብት መፍጠሩን በማረጋገጥ፤ አመልካች ተጠሪ በሕገ-ወጥ መንገድ የያዘብኝን ይዞታ ይልቀቅልኝ በማለት ያቀረቡትን ክስ ዉድቅ በማድረግ የወረዲዉ ፍ/ቤት የሰጠዉም ዉሳኔ ሆነ በየደረጃዉ ጉዲዩን የተመለከቱት የስር ፍ/ቤቶች ዉሳኔዉን ማጽናታቸዉ የሚነቀፍበት በቂ ምክንያት ባለመኖሩ ዉሳኔዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል ለማለት አልተቻለም። በመሆኑም የሚከተለዉ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
No topics extracted.