የኑዛዜ ወራሽነት ይረጋገጥልኝ በሚል አቤቱታ በተከፈተ መዝገብ ላይ ኑዛዜው ሕጋዊ አይደለም የሚል ተከራካሪ ወገን በሚቀርብበት ጊዜ ፍ/ቤቶች ወደ ኑዛዜው ይዘት እና ሕጋዊነት ሁኔታ ገብተው ተገቢውን ውሳኔ መስጠት ያለባቸው በመሆኑ በጉዲዩ ላይ ግራ ቀኙን በሕጉ አግባብ በመስማትና በሚገባ በማጣራት ተገቢውን ዲኝነት መስጠታቸው ስነ ስርዓታዊ እንጂ በንብረት ክርክር ጊዜ የሚታይ ነው ተብል የሚታለፍ ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 996 www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. VII
No summary available.
መ/ቁ/ 159474 ህዲር 10 ቀን 2011 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውልስ ኦርሺሶ አመልካች፡- አቶ እንደገና ተሾመ- የቀረበ የለም።
ተጠሪ፡- አቶ ረታ መልካ - ታልፎል።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ ለቀረበው የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ ኑዛዜን መሰረት በማድረግ የቀረበውን ክርክር የሚመለከት ነው።
ክርክሩ በተጀመረበት በአዲማ ወረዲ ፍ/ቤት የአሁኑ አመልካች ሟች እማሆይ ውቢቱ ኃ/ማሪያም በ3/09/2009 ዓ/ም አድርገውት ያለፈት ኑዛዜ መሰረት ተደርጏ የወራሽነት ማስረጃ ይሰጣቸው ዘንድ ዲኝነት ጠይቀው ሶስት ምስከሮችን አቅርበው አሰምተዋል።
ከዚህም በኋላ የአሁኑ ተጠሪ ወደ ክርክሩ ጣልቃ እንዱገቡ ጠይቀው ሟች ወላጅ እናታቸው መሆናቸውን፣ የሟች የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ መሆናቸውን በፍርድ ቤት ያረጋገጡ መሆኑን፣ አመልካች አለኝ የሚለት ኑዛዜም ሕጋዊ አይደለም የሚለበትን ምክንያት ጠቅሰው ተከራክረዋል። በዚህ ተጠሪ ጣልቃ ገብተው በአቀረቡት መከራከሪያም የአሁኑ አመልካች አለኝ የሚለትን መከራከሪያ ነጥብ አቅርበዋል። የስር ፍርድ ቤትም ጉዲዩን መርምሮ በፍትሃ ብሓር ሕጉ መሰረት ኑዛዜ ይመዝገብልኝ፣ ይሻርልኝ፣ እንዱሁም መጠኑ ይቀነስልኝ በማለት ዲኝነት ከሚጠየቅ በስተቀር ይረጋገጥልኝ መባለ የህግ ድጋፍ የለውም በሚል ምክንያት የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ አድርጎታል። በዚህ ላይ ከአሁኑ አመልካች ይግባኝ የቀረበለት የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በስር ፍርድ ቤት ብይን ላይ ጉድለት የለውም በማለት በትእዛዝ የአመልካችን ይግባኝ የሰረዘ ሲሆን የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር አጣሪ ችልትም በበታች ፍርድ ቤቶች ዲኝነት ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለም ሲል የአመልካችን የሰበር አቤቱታ ሳይቀበለው ቀርቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚህ ላይ ሲሆን የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም የስር ፍርድ ቤትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
አመልካች የኑዛዜ ወራሽነት እንዱረጋገጥላቸው ያቀረቡትን አቤቱታ ተቀብል ምስክሮችን ከሰማ በኋላ በተጠሪ ጣልቃ ገብነት መነሻ የኑዛዜ ወራሽነት ይረጋገጥልኝ ተብል ዲኝነት አይጠየቅም ሲል መዝገቡን መዝጋቱም ሆነ የክልለ የበላይ ፍርድ ቤቶችም ይህንኑ የስር ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሳያርሙ መቅረታቸው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህትት ያለበት ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታቸው ተመርምሮም በዚህ ችልት እንዱታይ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው መጥሪያ ደርሷቸው ባለመቅረባቸውም በጽሐፍ መልስ የመስጠት መብታቸው እንዱታለፍ ተደርጎአል።
የክርክሩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ዲኝነት እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምሮታል። እንደመረመረውም የበታች ፍርድ ቤቶች የአመልካች የኑዛዜ ወራሽነት ይረጋገጥልኝ ጥያቄ ፍርድ ቤት የሚቀርብ አይደለም በማለት የሰጡት ዲኝነት የሕግ መሰረት ያለው መሆን ያለመሆኑን የሚመለከተው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሁኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መረዲት የታቻለው አመልካች ክስ ሉመሰርቱ የቻለት ሟች አደረጉ በተባለው ኑዛዜ መሰረት በማድረግ የወራሽነት ማስረጃ (የምስክር ወረቀት ) ይሰጠኝ (የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 996(1) በማለት መሆኑን፣ ይኼው መነሻ ተደርጎም የአመልካች ምስክሮች ሁለ ተሰምተው የነበሩ መሆኑን፣ ከዚህ በኋላም የአሁኑ ተጠሪ ወደ ክርክሩ ጣልቃ ገብተው የአመልካችን የዲኝነት ጥያቄ ሕጋዊ አይደለም የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረው የተከራከሩ መሆኑን ነው።
በመሰረቱ በፍትሐብሕር ሕጉ በግልጽ እንደተመለከተው ኑዛዜ ፈራሽ ነው ይባል በሚል የሚቀርበው ክስ የወራሽነት የምስክር ወረቀት እንዱሰጥ ከሚቀርበው ጥያቄ (አቤቱታ) የተለየ መሆኑ ይታወቃል። ጥያቄዎቹ የተለያዩ በመሆናቸውም የተለያዩ ውጤት ነው ያላቸው። በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 996(1) እንደተደነገገው ወራሽ ነኝ የሚል ማንኛውም ሰው የወራሽነት ምስክር ወረቀት ይሰጠው ዘንድ ለፍ/ቤት ሉያመለክት ይችላል። ፍ/ቤቱም ጥያቄውን ከመቀበለ በፉት ጠያቂው ማስረጃዎቹን ሁለ እንዱያቀርብ በማድረግ እና አስፈላጊ መስል የታየውን ዋስትና እንዱሰጥ በማስገደድ ጭምር ዋስትናውን ካገኘ በኋላ የተጠየቀውን የምስክር ወረቀት ላሰጥ እንደሚችል በፍ/ብ/ሕግ ቁ. 996(2) ተመልክቷል። በልላ በኩል ደግሞ ፍ/ቤቱ የአመልካቹን ጥያቄwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
መሰረት በማድረግ ሰጥቶት የነበረው የወራሽነት የምስክር ወረቀት ሉሰረዝው እንደሚችል በፍ/ብ/ሕግ ቁ.998(1) የተቀመጠው ድንጋጌ ያመለክታል። ይህ ላሆን የሚችለው ደግሞ ማስረጃው ከተሰጠ በኋላ ማስረጃው የተሰጠው ከህግ ውጪ ነው የሚል ወገን ክርክሩን ከአቀረበ ነው። ከዚህ እንግዱህ መገንዘብ እንደሚቻለው የምስክር ወረቀቱ በጠያቂው አቤቱታ መነሻነት የሚሰጥ ቢሆንም የተሰጠው ያለአግባብ ነው የሚል መቃወሚያ ላቀርብ የሚችልበት ሁኔታ መኖሩንና መቃወሚያው ተገቢ ሆኖ ከተገኘም የምስክር ወረቀቱ የሚሰረዝ መሆኑን ነው።
ወደ ያዝነው ጉዲይ ስንመለስ የወራሽነት የምስክር ወረቀት እንዱሰጥ ጥያቄ የቀረበበት ፍ/ቤት ጥያቄውን ተቀብል የምስክር ወረቀቱን ከመስጠቱ በፉት ይኼው ማስረጃ እንዲይሰጥ ተጠሪ ተቃውሞ አቅርበዋል። በሕግ አግባብ የተደረገ ኑዛዜ በፍርድ ቤት እንዱረጋገጥ የፍርድ ቤትን ቡራኬ የማያስፈልገው መሆኑን ይህ ችልት በሰ/መ/ እና በላልች መዝገቦች አስገዲጅ የህግ ትርጉም መስጠቱን ይታወቃል። ይህ የሚሆነው ግን ኑዛዜው ሕጋዊ አይደለም የሚል ተከራካሪ ወገን በቀረበበት አግባብ አይደለም። ይህ ችልት በሰ/መ/ የሰጠው አስገዲጅ የህግ ትርጉም የኑዛዜውን ህጋዊነት የሚቃወም ወገን በንብረት ክርክር ጊዜ ክርክሩን ሉያነሳ የሚችል መሆኑን የሚያመላክት ነው። ይህም የተከራካሪ ወገኖችን የመሰማትና ፍትህ የማግኘት መብትን ሁለ ያገናዘበ ነው ልባል የሚችል ነው። በመሆኑን ለፍርድ ቤት የሚቀርብ ጥያቄ በፍርድ ቤት ስልጣን ስር የሚወድቅ እስከሆነ ድረስ የተከራካሪ ወገኖችን የመሰማት መብትን ባከበረና የሥነ ስርዓት ሕጉን መሰረታዊ አላማ ባገናዘበ መልኩ ሉስተናገድ ይገባል።
በልላ በኩል የኑዛዜ ወራሽነት እንዱረጋገጥለት አቤቱታ አቅርቦ ማስረጃ ያሰማ ወገን ማስረጃውን ከማግኘቱ በፉት ማስረጃው እንዲይሰጥ የሚል ተከራካሪ ወገን ከቀረበ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር በሕጉ አግባብ ተመልክቶ ተገቢውን ዲኝነት ላሰጥበት የሚገባው እንጂ ከመነሻውም የኑዛዜ ወራሽነት ይረጋገጥልኝ የሚል አቤቱታ መቅረብ አልነበረበትም በማለት መዝገቡን ሉዘጋው የሚገባው አይደለም። ምክንያቱም ማስረጃው እንዲይሰጥ የሚል ወገን ቀርቦ ስለኑዛዜው ፍርማሉቲ ሳይሆን ስለኑዛዜው ሕጋዊነት (ኑዛዜው የሚሻርባቸውን ወይም ውድቅ የሚሆንባቸውን ምክንያቶች በሚመለከት) ክርክር ከአነሳ በዚህ ረገድ ጭብጦችን ይዞ ተገቢውን ዲኝነት መስጠትን የሚጠይቅwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ነውና። ስለሆነም የኑዛዜ ወራሽነት ይረጋገጥልኝ የሚለው ጥያቄ በፍርድ ቤት እንዱቀርብ ሕጉ የግድ አይልም ሲባል ከኑዛዜ ፍርማሉቲ ጋር ተያይዞ የሚታይ እንጂ ስለኑዛዜው ሕጋዊነት ጭምር ነው ልባል የሚችል አይደለም። የኑዛዜ ወራሽነት ይረጋገጥልኝ በሚል አቤቱታ በተከፈተ መዝገብ ላይ ኑዛዜው ሕጋዊ አይደለም የሚል ተከራካሪ ወገን ከቀረበ ደግሞ ፍ/ቤቱ ወደ ኑዛዜው ይዘት እና ሕጋዊነት ሁኔታ ገብቶ ውሳኔ መስጠትን የግድ የሚል በመሆኑ በጉዲዩ ላይ ግራ ቀኙን በሕጉ አግባብ በመስማትና በሚገባ በማጣራት ተገቢውን ዲኝነት መስጠት ስነ ስርዓታዊ እንጂ በንብረት ክርክር ጊዜ የሚታይ ነው ተብል የሚታለፍ አይደለም። ክርክሩ በንብረት ክርክር ጊዜ የሚታይ ነው ብል መዝገቡን መዝጋትም ክርክሮች በአነስተኛ ወጪ፣ በተፊጠነ ጊዜና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ መሰጠት አለባቸው ከሚለው የስነ ስርዓት ሕጉ መሰረታዊ ዓላማ ጋርም አብሮ የማይሄድ በመሆኑ ተገቢነት የለውም።
ሲጠቃለል የስር ፍ/ቤቶች በጉዲዩ ላይ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ ስለአገኘን ተከታዩን ወስነናል።
በአዲማ ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ በ3/05/2010 ዓ/ም ተሰጥቶ በአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በ22/05/2010 ዓ/ም፣ በኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር አጣሪ ችልት በመ/ በ25/08/2010 ዓ/ም በትእዛዝ የፀናው ብይን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የአዲማ ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤት ክርክሩን በመ/ ቀጥል የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ በመስማት እንዱሁም አስፈላጊ ሁኖ ሲያገኘው ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸውን ማስረጃዎች በማስቀረብና ክርክሩን ስነ ስርዓቱ በሚፈቅደው አግባብ ጭምር በመመራት በጉዲዩ ላይ ተገቢውን ዲኝነት እንዱሰጥበት ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 343(1) መሰረት መልሰን ልከንለታል። ይጻፍ።
ወጪና ኪሣራ በተመለከተ ግራ ቀኙ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.