የውርስ ንብረት ክፍያ ከተደረገ በኋላ በክፍያ ውስጥ ያልገቡ በውርሱ ንብረት ውስጥ ገብተው የሚቆጠሩ አዱስ ሀብቶች የተገኙ እንደሆነ አዱስ የክፍያ ስርዓት መፈፀም የሚቻል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1103፣1104
No summary available.
መስከረም 25 ቀን 2011 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውልስ ኦርሺሶ አመልካቾች፡-
ጉዲዩ የቀረበው አመልካቾች የኦሮሚያ ብ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየውwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልል መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን ወጫላ ወረዲ ፍርድ ቤት ነው።
በስር ፍርድ ቤት የአሁን አመልካቾች ከሳሾች ሲሆኑ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ ነበሩ።
የአመልካቾች ክስ ይዘትም ሟች አቶ ደበላ ሄዪ በቀን 13/12/2003 ዓ.ም በሞት ከዚህ አለም የተለዩ መሆናቸው በመግለጽ ተጠሪ ከዚህ በፉት የተወሰነልን መልሶ በመያዝ የባለይዞታነት ማስረጃ ወስድበት ድርሻችንን ስለከለከለን እንዱሁም የአባታችን ይዞታ ረስተን ውሳኔ ሳይሰጥበት ሳናውቅ የአባታችን የመሬት ይዞታ በእጁ ይዞ ስለሚገኝ ድርሻቸውን ተከፍል እንዱሰጠን ሲለ ዲኝነት ጠይቀዋል። በመጀመሪያ ጉዲዩን የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙ ክርክር ከሰማና ማስረጃ ከመዘነ በኋላ የሰጠው ውሳኔ እና በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ውሳኔ በመቃወም የአሁን ተጠሪ ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙ ክርክር ከሰማ በኋላ በኋላ በቀን 28/02/2009 ዓ.ም በዋለው ችልት የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በመሻር በሽማግላዎች አማካኝነት ከዚህ በፉት ተከፊፍልላቸው የነበረውን ተጠሪ መልሶ ይዞባቸዋል? ወይስ አልያዘም? ተደብቆ ያለው ይዞታ አለ? ወይስ የለም? ይዞታው አመልካቾች ሳያውቁ ከውርስ ክፍፍል የቀረ ነው ? ወይስ እያወቁ ነው የተውት?
ይዞታው የሚገኝበት መደበቅ የሚችልበት ቦታ ነው? የሚለ ነጥቦች በግራ ቀኙ ማስረጃ ከተጣሩ በኋላ ውሳኔ እንዱሰጥበት በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.343/1/ መሰረት ለወረዲ ፍርድ ቤት መልሶታል።
ፍርድ ቤቱም የተዘጋው መዝገብ አንቀሳቅሶ በተመለሱት ነጥቦች ላይ የግራ ቀኙ ክርክር ከሰማና ማስረጃ ከመዘነ በኋላ ተጠሪ ያለ አመልካቾች ፈቃድ እነሱ ሳያውቁ በይዞታቸው ላይ በሀይል ቤት የሰራ ስለሆነ በተጠሪ ወጪ በክሱ ተራ ቁጥር 1ኛ ላይ የሚገኝበት ቦታ እና አዋሳኙ በተገለጸው ይዞታ ላይ የተሰራውን ቤት በማፍረስ ለከሳሾች/አመልካቾች/ ይዞታውን እንዱለቅ፤በክሱ ከ2ኛ እስከ 6ኛ እና 8ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱት ይዞታዎች የወላጅ አባታቸው መሆናቸውና፤ ከሳሾች የይዞታዎቹ አዋሳኝ የማያውቁ መሆናቸውና እናታቸው ጋር በመሁክ ጡሪ ከተማ ያደጉ ስለሆነ ማወቅ አለመቻላቸውን እና የተደበቀ መሆኑን ስለተረጋገጠ የፍ/ብ/ህ/ቁ.1103 በመጠቀስ ወራሾች እኩል እንዱካፈለ ሲል ወስኗል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የአሁን ተጠሪ በዚሁ ውሳኔ ቅር በመሰኘት አቤቱታቸው ለሰሜን ሽዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙ ክርክር ከሰማ በኋላ የስር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ስህተት ያለበት ሁኖ አልተገኘም በማለት በውሳኔ አጽንቶታል።
በመቀጠል ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታቸው አቅርበዋል።
ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን አስቀርቦ ካከራከረ በኋላ የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ በማሻሻል በክሱ ተራ ቁጥር 1ኛ እና 7ኛ የተጠቀሱት ይዞታዎች በተመለከተ የተሰጠ ውሳኔ በማጽናት በክሱ ተራ ቁጥር 2-6 እና 8ኛ የተመለከቱት ይዞታዎች ላይ የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ በመሻር ተጠሪ ለአመልካቾች ሉያካፍል አይገባም ሲል ወስኗል።
አመልካቾች ያቀረቡት አቤቱታ ተመርምሮ የስር ፍርድ ቤት የጉዲዩ አከራካሪ የሆነው የውርስ ይዞታ ተረስተው የታለፈና በድጋሚ መጠየቁ አግባብነት ያለው ነው ብለው የወሰነውን የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት መሬት የማይረሳ ነው ልጠይቁ አይገባም ያለበት አግባብነት ተጠሪው ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል። የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለክርክሩ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር መርምረናል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካቾችና ተጠሪ የሟች ወላጅ አባታቸው አቶ ደበላ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሾች መሆናቸው፤አመልካቾች በተጠሪ እጅ የሚገኙትን የውርስ ንብረትና ይዞታዎች ክፍፍል እንዱደረግ ዲኝነት በመጠየቃቸው ምክንያት ግራ ቀኙ በስምምነት ክፍፍል ማድረጋቸው በመግለጽ ነገር ግን ከውሳኔ በኋላ ለአመልካቾች በደረሳቸው ይዞታ ላይ ተጠሪ በሀይል ቤት በመስራቱ እንዱሁም የተረሱ ይዞታዎች ድርሻቸው እንዱያካፍላቸው ዲኝነት በመጠየቃቸው ምክንያት የግራ ቀኙ ክርክር ከተደረገ በኋላ ተጠሪ በአመልካቾች ድርሻ ላይ ቤት መስራቱን በማረጋገጥ የሰራውን ቤት በራሱ ወጪ አፍርሶ ይዞታው ለአመልካቾች እንዱለቅ መስጠቱን ተገንዝበናል በዚህ ረገድ የቀረበ አቤቱታ የለም። አከራካሪ የሆነው አመልካቾች በክሳቸው ከ1ኛ እስከ 6ኛ እንዱሁም 8ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱትን ይዞታዎችን በሚመለከት ነው። አመልካቾች ከውሳኔ በኋላ ክስwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ለማቅረብ በምክንያትነት የጠቀሱት የውርስ ይዞታዎች የሆኑትን መኖራቸው ባለማወቅቸው መሆኑን የተረሱ የውርስ ሀብት መጠየቅ እንደሚቻል የፍ/ብ/ህ/ቁ.1103፤1104 ስለሚፈቅድ በዚሁ አግባብ የቀረበ ክስ መሆኑን በመግለጽ የተከራከሩ ሲሆን ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም በተጠሪ እጅ የሚገኙትን ክፍፍል ሳይደረግባቸው የቀሩትን እኩል እንዱከፊፈለ የሰጠው ውሳኔ በመቃወም ጉዲዩ እስከ ክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ደርሶ ተጠሪ ጉዲዩ ውሳኔ ካገኘ በኋላ በድጋሚ የቀረበ ነው በማለት ያቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በመሻር በፍሬ ነገር ዲግም ተጣርቶ ውሳኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩን በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.343/1/ መሰረት ለስር ፍርድ መልሶታል። የተመለሰለት ፍርድ ቤትም የተዘጋው መዝገብ አንቀሳቅሶ የግራ ቀኙ ክርክርና ማስረጃ ከመዘነ በኋላ ለክርክር ምክንያት የሆኑት ይዞታዎች ግራ ቀኙ እኩል እንዱካፈለ ሲል የሰጠው ውሳኔ በይግባኝ ሰሚ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፀና ቢሆንም የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩን ከፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 216/3/ አንጻር ተመልክቶ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በመሻር በክሱ ከ1ኛ እስከ 6ኛ እና 8ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱት ይዞታዎች ተጠሪ ለአመልካቾች ሉያካፍል አይገባም ሲል ወስኗል። የአመልካች አቤቱታ መሰረት ያደረገው በስር ፍርድ በተጠሪ ያልተነሳ ጉዲይ በማንሳት የተሰጠ ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ ሉታረም ይገባል የሚል ሲሆን በተጠሪ በኩል ደግሞ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩን በአግባቡ አጣርቶ የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት በመሆኑ ሉፀና ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
በመሰረቱ አንድ ተከራካሪ ወገን ከአንድ የክስ ምክንያት የመነጨ የመብት ጥያቄ ካለው እና በአንድ ክስ የሚጠቃለል የክስ ምክንያት ሆን ብል በመቀነስ ያስቀረ ከሆነ በድጋሚ በተመሳሳይ ጉዲይ አዱስ ክስ ማቅረብ እንደማይችል ከፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ/ 216 /3/ ድንጋጌ መሰረታዊ ይዘት የምንገነዘበው ነው። የአንድ ክስ ምክንያት መከፊፈል ባለጉዲዮች ጊዜ፤
ወጪና ጉልበት አላስፈላጊ ጫና እና የማጉላላት ውጤት እንዲለው መረዲት ይቻላል።
የፍ/ብ/ስ/ስ/ስ/ህግ/ዓይነተኛ ዓላማ /main purpose / ጉዲዮችን በህግ አግባብ በመምራት በተቻለ አጭር ጊዜ ውጤታማ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፍትሃዊ ውሳኔ መስጠት ስለመሆኑ ከአጠቃላይ የህጉ ድንጋጌዎች የምንረዲው ነው። ከአንድ ጉዲይ የመነጨ የመብት ጥያቄ የሚያቀርቡ ተከራካሪ ወገኖች ክሱን ለመመስረት መነሻ የሆነባቸው ጉዲይ አጠቃልለውwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የማቅረብ ግዳታ አለባቸው። ተከራካሪ ወገኖች ከአንድ የክስ ምክንያት የሚመነጭ ክርክር ከፊፍለው ከቀረቡ /spilting of claim/ በድጋሚ በተመሳሳይ ጉዲይ ላላ ክስ የማቅረብ መብት የሚሰጣቸው አይደለም።
ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩን የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.216 መሰረት በማድረግ የሰጠው ውሳኔ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ መመርመሩ ተገቢ ሁኖ አግኝተነዋል። የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔ በሁለት ምክንያት ተገቢ ሁኖ አልተገኘም። አንደኛው ይህ ጉዲይ ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የቀረበው ሁለት ጊዜ መሆኑን ከክርክሩ ሂደትና ከውሳኔ ግልባጭ ተገንዝበናል። በስር ፍርድ ቤት አመልካቾች ያቀረቡት ክስ ላይ በተጠሪ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 216 መሰረት በማድረግ ያቀረቡት ክርክር ካለመኖሩም በላይ ጉዲዩ ክልል ሰበር ሰሚ ችልት ደርሶ ጉዲዩ እንደገና ወደ ፍሬ ነገር ገብቶ እንዱጣራ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.343/1/ መሰረት ሲመልስ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.216 ጥያቄ አልነበረም። አንድ ተከሳሽ ለቀረበለት ክስ በዝርዝርና በግልፅ መቃወምና መካድ እንደለበት በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.83 ተመልክቷል። በይግባኝ ደረጃም ፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.329/1/ በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያልተነሳወን ክርክርና ያልቀረበውን አዱስ ነገር ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት መቀበል እንደማይችል ተደንግጓል። እንዱሁም ፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.182/2/ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተከራካሪዎቹ በዝርዝር ባላቀረቡት ወይም በግልፅ ባላመለከቱት ጉዲይ ላይ ፍርድ መስጠት እንደማይቻል ይደነግጋል። ስለሆነም በዚህ ረገድ የክልለ ሰበር ውሳኔ ተገቢ ሆኖ አልተገኘም፤ በልላ በኩልም የውርስ ንብረት ክፍያው ከተደረገ በኋላ በክፍያ ውስጥ ያልገቡ በውርሱ ንብረት ውስጥ ገብተው የሚቆጠሩ አዱስ ሀብቶች የተገኙ እንደሆነ አዱስ የክፍያ ስርዓት መፈጠም እንደሚቻል ከፍ/ብ/ህ/ቁ.1103 እና 1104 ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል። ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ በከፉል መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
በወጫላ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 24658 ሚያዚያ 17 ቀን 2009 ዓ.ም እና በሰሜን ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 55692 ግንቦት 24 ቀን 2009 ዓ.ም ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በኦሮሚያ ብ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 268679 ህዲር 4 ቀን 2010 ዓ.ም በውሳኔ የተሻሻለው ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.348 (1) መሰረት ተሻሽሎል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በክሱ በ1ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሰውን የይዞታ መሬት ተጠሪ ለአመልካቾች እንዱለቅ የተሰጠ ውሳኔ ክፍል ፀንቷል።
በክሱ ከ2ኛ እስከ 6ኛ እንዱሁም 8ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱት ይዞታዎች የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ በመሻር የወረዲ ፍርድ ቤትና ከፍተኛ ፍርድ ቤት በክሱ ከ2ኛ እስክ 6ኛ እንዱሁም 8ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱት ይዞታዎች አመልካችና ተጠሪ እኩል እንዱካፈለ በማለት የሰጡት ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.348 (1) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.