የፍትሒብሓር ህግ ቁጥር 973 ስለ ኑዛዜ መነበብ እንዱሁም ኑዛዜው ሲነበብ የነበሩ ሰዎች ኑዛዜው እንዱፈርስ አቤቱታ የሚያቀርቡበትን ሥርዓት እና ጊዜውን በሚመለከት የሚደነግግ እንጂ ኑዛዜ ከውርስ ተነቅለናል በማለት ኑዛዜው እንዱፈርስ የሚቀርብን ወይም የቀረበን አቤቱታን የሚመለከት ስላለመሆኑ አንድ ኑዛዜ ከውርስ የመንቀል ውጤት ያለው በመሆኑ እንዱፈርስ የሚል የዲኝነት ጥያቄ ላታይ የሚገባው በፍትሒብሓር ህግ ቁጥር 1123 መሰረት እንጂ በፍትሐብሄር ህግ አንቀጽ 973 መሰረት ወ/ሮ ትግዔሥት ንጉሴ እና እነ አቶ አሰፊ ንጉሴ www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. VI
No summary available.
ህዲር 24 ቀን 2011 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውልስ ኦርሺሶ አመልካች፡- ወ/ሮ ትግዔሥት ንጉሴ- የቀረበ የለም ተጠሪዎች፡-
የነገሩ አመጣጥ የውርስ ንብረት ክርክርን የሚመለከት ነው። ጉዲዩ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። የአሁን አመልካች ከሥር 2ኛ አመልካች ሕፃን ኤልሻዲይ ንጉሴ ጋር በመሆን ግንቦት 15 ቀን 2008 ዓ/ም ጽፈው ባቀረቡት የክስ አቤቱታ የአመልካቾች ወላጅ አባት አቶ ንጉሴ ቱሩፋ አመልካቾችንና ተጠሪዎችን ጨምሮ ስድስት ልጆችን መውለዲቸውን፣ ጥር 26 ቀን 2007 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን፣ አባታቸው ከመሞታቸው በፉት ለረጅም ጊዜ የካንሰር ህመምተኛ እንደነበሩ፣ ራሳቸውን በማያውቁበት ሁኔታ ውስጥ እያለ 1ኛ ተጠሪ የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ከሆኑትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
አቶ መኩሪያ አይተንፍሱ ጋር በመሆን መስከረም 6 ቀን 2007 ዓ/ም አስገድደው ኑዛዜ እንዱፈጽሙ ማድረጋቸውን ፣ ኑዛዜውም ትክክል ያልሆነና የሁለንም ወራሾች መብት ያላከበረ መሆኑን፣ ተናዛዡም በተራ ቁጥር 5 እና 7 ላይ ጠቅሰው የተናዘዙት ንብረት በስማቸው የላለ መሆኑን፣ እንዱሁም ኑዛዜው አመልካቾችን የመንቀል ውጤት ያለው በመሆኑ ኑዛዜው እንዱፈርስልን በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
ተጠሪዎች ሰኔ 15 ቀን 2008 ዓ/ም በጻፈት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አመልካቾች ኑዛዜው መኖሩን ሟች ከሞተበት ቀን ጀምሮ ያውቃለ፣ ሟች ከሞተ 40 ቀን ሉሞላው ሳምንት ሲቀረው አመልካቾች በተገኙበት ኑዛዜው ተነቧል፣ በኑዛዜው መቃወሚያ ካላቸው በፍትሒብሓር ህግ ቁጥር 973 መሰረት ኑዛዜው አይፀናም በማለት መቃወሚያ ማቅረብ የሚችለት እስከ ሶስት ወር ድረስ ነበር ፣ ነገር ግን አመልካቾች መቃወሚውን ያቀረቡት ኑዛዜው ከተነበበ ከአንድ ዓመት በኃላ ውርስ ሲጣራ ውርስ አጣሪው ጋር ነው፣ መቃወሚያውም ማቅረብ ካለበት የሚቀርበው ህጉ ባስቀመጠው ጊዜ ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ነው። ስለዚህ መቃወሚያው በይርጋ ይታገዲል።
አመልካቾችም ኑዛዜ ስለመኖሩ ከውርስ አጣሪ መሾም በፉት ያውቃለ። በዚሁ ኑዛዜም ወራሽነታቸውን አስመስክረዋል። ኑዛዜውን የሚቃወሙ ከሆነ ይህንን ማቅረብ የሚችለት የኑዛዜ ወራሽነት ማስረጃ ለሰጠው ለአዱስ አበባ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እንጂ ለዚህ ፍርድ ቤት ባለመሆኑ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን የማየት ሥልጣን የለውም በማለት ተከራክረዋል።
ተጠሪዎች ላቀረቡት መቃወሚያ አመልካቾች በሰጡት መልስ ኑዛዜው መኖሩን ያወቅነው ውርስ አጣሪ ዘንድ ነው፤ ኑዛዜው ተነበበ በተባለበት ቦታ አልነበርንም። ስለዚህ ይርጋው መቆጠር የሚጀምረው ካወቅንበት ጊዜ ጀምሮ ሲሆን በህፃን ኤልሻዲይ ንጉሴ ላይ መቆጠር የሚጀምረው አካለ መጠን ከደረሰችበት ጊዜ አንስቶ ላሆን ይገባል፤ የአዱስ አባባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካቾችን የኑዛዜ ወራሽ ያደረገው በወቅቱ ለፍርድ ቤቱ ቀርበው የነበሩት ጠበቃ ከአመልካቾች ባልተሰጣቸው ውክልና ያወጡትን ማስረጃ መሰረትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በማድረግ ነው። የአዱስ አበባ ፍርድ ቤቶች የኑዛዜ ይፍረስልኝ ጥያቄን የማየት ሥልጣን የላቸውም በማለት ተከራክረዋል።
ጉዲዩን የተመለከተው የፈዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር እንዱሁም ማስረጃዎችን መርምሮ በመዝገብ በሆነው በቀን 19/05/2009 ዓ/ም በዋለው ችልት ህፃን ኤልሻዲይ ንጉሴ ኑዛዜው ሲነበብ ክስ ለመመስረት የሚያስችል የእድሜ ደረጃ ላይ ባትደርስም ሞግዚትና አስተዲዲሪው የሆኑት ወ/ሮ ትግዔሥት ንጉሴ በቦታው የነበሩ መሆኑን የተጠሪዎች ምስክሮች በተሻለ ሁኔታ ስላስረደ የሁለቱም አመልካቾች መብት በፍትሒብሓር ህግ ቁጥር 973 መሰረት በይርጋ ይታገዲል ሲል ብይን ሰጥቷል።
ይህን ብይን ቅር በመሰኘት የአሁን አመልካች እና የሥር 2ኛ ይግባኝ ባይ ኤልሻዲይ ንጉሴ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበዋል። የይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ይግባኙን ተቀብል ክርክራቸውን ከዲመጠ በኃላ በኮ/መ/ቁ. 193480 ጥቅምት 14 ቀን 2010 ዓ/ም በዋለው ችልት 1ኛ ይግባኝ ባይ /የአሁን አመልካች/ ያቀረቡት የኑዛዜ ይፍረስልኝ ጥያቄ በይርጋ ይታገዲል በማለት የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔን አጽንቷል። በልላ በኩል የህፃን ኤልሻዲይ ንጉሴን ይግባኝ በተመለከተ ክስ ሲመሰረት ዘጠኝ ዓመቷ የነበረ መሆኑ በመልስ ሰጪዎች /በአሁን ተጠሪዎች/ የተካደ አይደለም። የ2ኛ ይግባኝ ባይ እድሜ ይህ ከነበረ ደግሞ በፍትሒብሓር ህግ ቁጥር 1846 እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር መዝገብ በሰጠው አስገዲጅ የህግ ትርጉም መሰረት ይርጋው መቆጠር የሚጀምረው አካለ መጠን ከደረሰች በኃላ ነው። ህጉ ሞግዚት ካለ መደበኛው የይርጋ ጊዜ አቆጣጠር ይፈጸምባቸዋል በማለት አልደነገገም። በሞግዚቶች ቸልተኝነትና ተገቢ ያልሆነ ሥራ መብታቸው እንዲይጎዲ በሚል እሳቤ ነው።
በመሆኑም የሥር ፍርድ ቤት የሁለተኛ ይግባኝ ባይ ጥያቄም በይርጋ ይታገዲል በማለት የሰጠው ብይን ተገቢ ስላልሆነ 2ኛ ይግባኝ ባይና መልስ ሰጪዎችን ያለዋቸውን ላልች ክርክሮች እና ማስረጃዎች ሰምቶ የመሰለውንwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
እንዱወስን በማለት በፍትሒብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 343 /1/ መሰረት መልሶታል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ውሳኔውን ለማስለወጥ ሲሆን የአመልካች አቤቱታ ይዘትም በአጭሩ፡- ኑዛዜው ከሩብ በላይ ጉዲት አድርሶብኛል ሉፈርስ ይገባል በሚል ለቀረበ ክስ የፍትሒብሓር ህግ ቁጥር 973 መሰረት አድርገው የሥር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ብይን እና ውሳኔ ተገቢ አይደለም ፣ የፍትሒብሓር ህግ አንቀጽ 973 ተፈጻሚ የሚሆነው ውርስ ተከፍቶ ውርስ አጣሪ ከተሾመ በኃላ የሚፈጸም ድንጋጌ ሆኖ እያለ ኑዛዜ በማን እና መቼ ተነቧል የሚለውን ነጥብ የሥር ፍርድ ቤቶች በፍትሒብሄር ህግ ቁጥር 946፣ 965 አንጻር ሳይመረምሩ ብይን እና ውሳኔ መስጠታቸው አግባብነት የለውም፣ በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በከፉል የተሻሻለው ውሳኔ ከአመልካች ውጪ ክርክሩ እንዱቀጥል ማድረጉ የፍትሒብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 40 ድንጋጌን ያላገናዘበ ነው፣ ከኑዛዜው ተጠቃሚ የሆነ ሰው ኑዛዜው እንዲይፈርስ የተንኮል ሥራ የሰራ መሆኑን፣ ከጠበቃ ጋር ተመሳጥሮ የላልች ወራሾች መብት ሲያሳጣ የነበረ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ በቀረበበት ሁኔታ፣ በዚሁ ተግባሩ በወንጀል ተከሶ እንዱከላከል ብይን በተሰጠበት ሁኔታ እሱ /1ኛ ተጠሪ/ ቀጥሮ የሚያሰራቸው ሰራተኞች እና ባለቤቱ የሰጡትን የምስክርነት ቃል ብቻ መሰረት ተደርጎ የተሰጠ ፍርድ መሰረታዊ ማስረጃ ምዘና ግደፈት ያለበት ስለሆነ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ውሳኔው እንዱሻር እና በኑዛዜ ላይ ተገቢውን ህጋዊ ክርክር እንዱያቀርብ እንዱደረግልኝ እንዱሁም በዚህ የሰበር ቅሬታ ምክንያት ያወጣሁትን ወጪና ኪሳራ እንዱተኩልኝ እንዱወሰንልኝ እጠይቃለሁ የሚል ነው።
የሰበር አቤቱታውን አጣሪው መርምሮ አመልካች ተደረገ ስለተባለው ኑዛዜ አላውቅም እያለ ኑዛዜውን በወቅቱ ስላልተቃወሙ ይርጋ ያግዲቸዋል የመባለ እና ኑዛዜው አመልካችን ከውርስ የሚነቅል ነው የሚለው አቤቱታም ከፍትሒብሓር ህግ ቁጥር 1123 (1) አንጻር ሳይታይ የመታለፈ አግባብነትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
መጣራት ያለበት መሆኑ ስለታመነበት ጉዲዩ ለሰበር ችልት ይቅረብ ሲል ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎላቸው 1ኛ ፣ 3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች በጠበቃቸው በኩል በቀን 20/7/2010 ዓ/ም የተጻፈ ዝርዝር መልስ አቅርበው የተከራከሩ ሲሆን አመልካችም ሚያዚያ 16 ቀን 2010 ዓ/ም የተጸፈ የመልስ መልስ አቅርበዋል። 2ኛ ተጠሪን በተመለከተ መጥሪያ ደርሶዋቸው ቀርበው ለመከራከር ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሚያዚያ 17 ቀን 2010 ዓ/ም በተሰጠው ትዕዛዝ መልስ የመስጠት መብታቸው ታልፎል።
የነገሩ አመጣጥና የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተመለከተውን የሚመስል ሲሆን የአመልካች ዲኝነት ጥያቄ በፍትሒብሓር ህግ ቁጥር 973 መሰረት በይርጋ ይታገዲል ተብል በተሰጠው ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል ወይስ አልተፈጸመበትም? የሚል ጭብጥ ተይዞ ጉዲዩ እንደሚከተለው ተመርምሯል። ለክርክሩ ምክንያት የሆነውንና መስከረም 6 ቀን 2007 ዓ/ም ከሟች ተሰጠ የተባለውን ኑዛዜ በተመለከተ አመልካች ያወቁት ውርስ እንዱጣራ ሲደርግ ውርስ አጣሪ ዘንድ እንደሆነ፣ ኑዛዜውን ሟች ያልሰጡትና ሀሰተኛ መሆኑን፣ ከአመልካችና ከህፃን ኤልሻዲይ ንጉሴ ለጠበቃ ውክልና ሳይሰጥ ውክልና እንደተሰጠ በማድረግ ለአዱስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቅርበው ኑዛዜውን መሰረት በማድረግ ወራሽነትን ተጠሪዎች ማስወሰናቸውን፣ ይህን ሀሰተኛ ተግባር የፈጸሙ ጠበቃም ለጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቤቱታ ቀርቦባቸው በጉባኤ ከታየ በኃላ በአዋጅ ቁጥር 199/92 አንቀጽ 24/3/ለ/2 መሰረት 2 ዓመት ከ6 ወር ከጥብቅና አገልግልትና የማማከር ተግባር እንዱታገደ የተደረገ መሆኑን፣ ጠበቃዋ ያስወሰኑት የወራሽነት ማስረጃን በተመለከተ ውሳኔውን ለሰጠው ለአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካቾች /ህፃን ኤልሻዲይ ንጉሴን ጨምሮ/ አቤቱታ አቅርበው በአሁን አመልካች እና በህፃን ኤልሻዲይ ላይ የተሰጠውን የውሳኔ ክፍል የከተማው ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 2940/07 በቀን 9/2/2009 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰረዘ መሆኑን፣ እንዱሁም የአሁን 1ኛ ተጠሪ እና ጠበቃዋwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በፈጸሙት የወንጀል ድርጊት ተከሰው እንዱከላከለ ብይን የተሰጠ መሆኑን አመልካች አጥብቀው ይከራከራለ። ጠበቃዋ በፈጸሙት ድርጊት ጉባኤው ቅጣት የወሰነባቸው መሆኑን እንዱሁም ከአሁን አመልካች እና ከህጻን አልሻዲይ ንጉሴ ውክልና ሳይሰጣቸው እንደተሰጠ በማድረግ ጠበቃዋ ለአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኑዛዜውን መሰረት በማድረግ አቤቱታ አቅርበው ያስወሰኑት ውሳኔ አመልካችን እና ህጻን አልሻዲይ ንጉሴን በሚመለከት የተሰረዘ መሆኑን ይህ ችልት ተመልክቷል።
በመሰረቱ የአሁን አመልካች እና የሥር 2ኛ አመልካች ህፃን ኤልሻዲይ አቤቱታ ኑዛዜው በማስገደድ የተደረገ እንዱሁም ከውርስ የነቀለ በመሆኑ እንዱፈርስ የሚል ዲኝነት የጠየቁ ሲሆን የተጠሪዎች ክርክር አመልካቾች ኑዛዜው ሲነበብ በቦታው ላይ ስለነበሩ በፍትሒብሓር ህግ ቁጥር 973 መሰረት በ3 ወር ውስጥ ኑዛዜው እንዱፈርስ ጥያቄ ስላልቀረበ በይርጋ ይታገዲል የሚል ነው።
ከዚህ ክርክር ተነስተን የአሁን አመልካችም ሆነ የህፃን አልሻዲይ አቤቱታ በፍትሒብሓር ህግ ቁጥር 973 መሰረት የሚታይ ነው ወይ? የሚለውን ጥያቄ ያስነሳል። የፍትሒብሓር ህግ ቁጥር 973 ስለ ኑዛዜ መነበብ እንዱሁም ኑዛዜው ሲነበብ የነበሩ ሰዎች ኑዛዜው እንዱፈርስ አቤቱታ የሚያቀርቡበትን ሥርዓት እና ጊዜውን በሚመለከት የሚደነግግ ነው። ይህ ድንጋጌ ኑዛዜው ከውርስ ነቅልኛል /ነቅልናል/ በማለት ኑዛዜው እንዱፈርስ የሚቀርብን ወይም የቀረበን አቤቱታን የሚመለከት አይደለም። በተያዘው ጉዲይ አመልካችም ሆኑ ይርጋው አያግድም ተብል በከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ የተሰጣት ህፃን ኤልሻዲይ ንጉሴ መሰረታዊ አቤቱታ ይዘት ኑዛዜው ከውርስ የመንቀል ውጤት ያለው በመሆኑ እንዱፈርስ የሚል ነው። ይህ የዲኝነት ጥያቄ ላታይ የሚገባው በፍትሒብሓር ህግ ቁጥር 1123 መሰረት ነው እንጂ በተጠቀሰው ህግ አንቀጽ 973 መሰረት አይደለም። የክርክሩ ይዘት እንደሚያመለክተው የአመልካቾች አባት ኑዛዜ ሰጡ የተባለው በ6/7/2007 ዓ/ም ሲሆን የሞቱት ደግሞ በ26/1/2007 ዓ/ም ነው። ኑዛዜው እንዱፈርስ ዲኝነት የተጠየቀው ግንቦት 15 ቀን 2008 ዓ/ም ነው። ይህም በፍትሒብሓር ህግ ቁጥር 1123 /3/ መሰረት ጊዜው ያላለፈበት መሆኑን በግልጽ የሚያመለክት ነው።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በመሆኑም የአመልካች ጥያቄ ይህን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ መታየት ሲገባው የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 973 ድንጋጌ ተወስድ አቤቱታው በይርጋ ይታገዲል ተብል የተሰጠው ብይንም ሆነ ውሳኔ የሚነቀፍ ሆኖ ተገኝቷል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር መዝገብ ላይ አስገዲጅ የህግ ትርጉም የሰጠ ሲሆን ይህም ትርጉም በየትኛውም ደረጃ በሚገኙት ፍርድ ቤቶች ላይ አስገዲጅነት ያለው ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 494/97 አንቀጽ 2(1) በግልጽ ተደንግጓል።
በመሆኑም የሥር ፍርድ ቤቶች የአመልካች ዲኝነት ጥያቄ በፍትሒብሓር ህግ ቁጥር 973 መሰረት በይርጋ ይታገዲል በማለት የሰጡት ብይንም ሆነ ውሳኔ የአቤቱታውን ይዘት ያላገናዘበ በመሆኑ አመልካችን ኑዛዜው ከውርስ የነቀለ ነው ወይስ አይደለም? የነቀለ ነው የሚባል ከሆነ ውጤቱ ምን ላሆን ይገባል? የሚለው ጭብጥ ተይዞ ጉዲይ ተጣርቶ ሉወሰን የሚገባ ሆኖ ተገኝቷል።
በመጨረሻም የሥር ፍርድ ቤቶች ከላይ የተመለከቱትን መሰረታዊ ነገሮችን በአግባቡ ሳያጤኑ የሰጡት ብይንም ሆነ ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
1.የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ቁ. 193480 ጥቅምት 14 ቀን 2010 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ በፍትሒብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 348 (1) መሰረት ተሻሽሎል።
2.የህፃን ኤልሻዲይ ንጉሴ አቤቱታ በይርጋ አይታገድም ተብል የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ፀንቷል።
3.የአሁን አመልካች አቤቱታ በፍትሒብሓር ህግ ቁጥር 973 መሰረት በይርጋ ይታገዲል ተብል የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ተሽሯል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
4.የአመልካች አቤቱታ በይርጋ ሉታገድ የሚችልበት ህጋዊ መሰረት ስለላለው አመልካችን ኑዛዜው ከፍ/ህ/ቁ 1123 አንፃር ሲታይ አመልካችን ከ1/4ኛ በላይ የጏዲ ውርስ ነው ወይስ አይደለም? የጏዲ ነው የሚባል ከሆነ ውጤቱ ምን ላሆን ይገባል?
የሚለውን የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አጣርቶ እንዱወስን በፍትሒብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 343/1/ መሰረት መልሰንለታል።
የዚህን ችልት ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
የውሳኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይድረሳቸው።
ጉዲዩ ውሳኔ ስላገኘ መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
ፊ/ዘ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት።
No topics extracted.