በመርህ ደረጃ ጋብቻ በፍቺ እንዱፈርስ መጠየቅ የሚገባው ከባልና ሚስቱ አንደኛው ተጋቢ ወይም ሁለቱም ቢሆንም በህግ አግባብ ተቀባይነት ያለው ውክልና ማስረጃ ጋር የሚቀርብ የፍቺ ጥያቄ ተቀባይነት ያለው ስለመሆኑ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.58፤ በፍ/ብ/ህ/ቁ.2199 www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. V
No summary available.
ግንቦት 29 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውልስ ኦርሺሶ አመልካች፡- ወ/ሮ አመለወርቅ ፍቅሬ - ጠበቃ ለገሰ ማሞ -ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ተስፊሁን ታፈሰ -የቀረበ የለም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የወላይታ ሰድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በወላይታ ሰድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። አመልካች በተጠሪ ላይ ያቀረቡት ክስ ከተጠሪ ጋር በቀን 3/6/2006 ዓ.ም በተፈጸመ ጋብቻ በቁጥር 240/270//2006 በቀን 12/06/2006 ዓ.ም በብሓራዊ የጋብቻ ስነስርዓት መሰረት ከሶድ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የጋብቻ ምስክር ወረቀት ወስደው ጋብቻ ከፈጸሙ በኋላ እንደማንኛውም ባለትዲር በአንድ ጣራ ስር መኖር ሳይጅምሩ ወደ አሜሪካን አገር መሄዲቸው በመግለጽ ለአለፈት አራት ዓመታት ከተጠሪው ጋር ምንምwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ዓይነት ግንኙነት ሳይኖር በተለያየ ቦታ የሚኖሩ መሆናቸውና ልጆች ሆነ የጋራ ሀብት ያላፈሩ በመሆኑ በመካከላቸው ያለው ጋብቻ ፈርሶ የፍቺ ውሳኔ እንዱወሰንላቸው ተጠሪው ላይ ክስ አቅርበዋል። ተጠሪም ለቀረበው ክስ የሰጡት መልስ በአመልካችና በተጠሪ መካከል በህግ የፀና ጋብቻ ስለመኖሩ ሳይክደ በጋብቻ ውስጥ መኖራችን ጥያቄ ማንሳት የሚችለት ተጋቢዎች ወይም አንዲቸው እንጂ ላላ ሰው የሚያነሳው ሀሳብ የህግ ድጋፍ የላለው በመሆኑ ስለተጋቢዋ ሆኖ ጠበቃ የፍቺ ጥያቄ ማቅረብ የማይችል ስለሆነ ክሱ ወድቅ እንዱደረግ ይህ መቃወሚያ የሚታለፍ ከሆነ በህጉ መሰረት የሞራል ካሳ ተወስኖ የወጪና ኪሳራ የመጠየቅ መብት ተጠብቆ እንዱወሰንላቸው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና አማራጭ መከላከያ መልሳቸው በማቅረብ ተከራክረዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው ፍርድ ቤትም በቀረበው መቃወሚያ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ በቀን 4/3/2010 ዓ.ም በዋለው ችልት የአመልካች ወንድም አስቀድሞ የተጻፈ ሕጋዊ ውክልና ሰነድ ሳይኖር አመልካችን ወክል የአመልካች ጋብቻ እንዱፈርስ ጠበቃን የመወከል መብት በህጉ አልተሰጠውም፤ ስለሆነም በተጠሪ የቀረበው መቃወሚያ ተገቢ ሁኖ ስለአገኘን በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 33/2/ እና 244/መ/ መሰረት የአመልካች ተወካይ ነኝ ባይ ክሱን ለማቅረብ መብት የለውም ሲል ብይን ሰጥቷል።
ይህንን ብይን በመቃወም የአመልካች ተወካይ ይግባኛቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያቀረቡ ቢሆንም ተቀባይነት ሳያገኝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.337 መሰረት ሰርዞታል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበውም ይህንኑ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። አመልካች ታህሳስ 4 ቀን 2010 ዓ.ም በፃፈት አቤቱታ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶችን ዘርዝረው አቅርበዋል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በዚህ ጉዲይ አመልካች ለወንድማቸው የሰጡት ውክልና በውጭ ጉዲይ ሚኒስቴር ተረጋግጦ ቀርቦ ባለበት የተሟላ ውክልና አልቀረበም በሚል ውድቅ መደረጉ ያላግባብ ነው በማለት በአመልካች የቀረበው አቤቱታ ከውክልና አንፃር ለመጣራት ለሰበር ችልት እንዱቀርብ በመደረጉ ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት በታዘዙት መሰረት የካቲት 21 ቀን 2010 ዓ.ም የተፃፈwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
መልስ አቅርበዋል። አመልካች ጠበቃ በተጠሪ የቀረበው መልስ ላይ የመልስ መልስ መስጠት የማይፈልጉ መሆኑን በመግለጻቸው ምክንያት የቀረበ የመልስ መልስ የለም።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለክርክሩ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር መርምረናል። በመሰረቱ በመርህ ደረጃ የግራ ቀኙ ጋብቻ በፍቺ እንዱፈርስ መጠየቅ የሚገባው ከባልና ሚስቱ አንደኛው ተጋቢ ወይም ሁለቱም ቢሆንም በህግ አግባብ ተቀባይነት ያለው ውክልና ማስረጃ ጋር የሚቀርብ የፍቺ ጥያቄ በህግ የተከለከለ አይደለም። ከባልና ሚስት አንዲቸው የፍቺ ጥያቄ እስካቀረቡ ድረስ ፍቺው ሉከለከል እንደማይቻልና ፍቺ ሉወሰን አይገባም የሚለውን ነጥብ መሰረት በማድረግ ብቻ የይግባኝ አቤቱታ ማቅረብ እንደማይቻል በተሻሻለው ፋዳራል ቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 112 ሆነ በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 75/1996 አንቀጽ 127 ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል። በልላ በኩል ፍርድ ቤት የባልና ሚስትን ክርክር በሚያይበት ጊዜ እንደነገሩ ሁኔታ አስፈላጊ ሁኖ ካገኘው ባልና ሚስቱን በአንድነት ወይም በተናጠል ሲያነጋግር ወይም ጉዲዩን ሲመረምርና ምስክር ሲሰማ በዝግ ችልት ያስችላል የሚለውን የቤተሰብ ህጉ ድንጋጌ/አንቀጽ 110/ በመጥቀስ ጋብቻና ጋብቻ ፍቺ በውክልና ላቀርብ አይችልም በማለት በተጠሪ የሚቀርበው ክርክር ተቀባይነት የለውም። ምክንያቱም ፍርድ ቤቱ ተጋቢዎችን የሚያነጋግራቸው አስፈላጊ ሁኖ ሲገኝ እንጂ የግድ ማናጋገር እንዲለበት የሚደነግግ ባለመሆኑ፤ጋብቻ በእንደራሴ መፈጸም በመርህ ደረጃ የማይቻል ቢሆንም ከተጋቢዎች አንደኛው ጋብቻው ለመፈጸም ፈቃደን በማያሻማ ሁኔታ በመግለጽ በግንባር ለመገኘት የማያስችለው ከባድ ምክንያት ሲያጋጥመው ጉዲዩ ለፍትህ ሚኒስትሩ ቀርቦ ሲረጋገጥ ጋብቻውን በእንደራሴ አማካኝነት መፈጸም እንደሚቻል በግልጽ በተሻሻለው ፋዳራል ቤተሰብ ህግ አንቀጽ 12 ተደንግጓል።
ጋብቻ ለመፈጸም በልዩ ሁኔታ በውክልና እንደሚቻል ህጉ እየፈቀደ የፍቺ ጥያቄ በውክልና ላቀርብ አይችልም በማለት በተጠሪ በኩል የሚቀርበው ክርክር ተቀባይነት ያለው ሁኖ አልተገኘም። እዚህ ላታይ የሚገባው ነጥብ የውክልናው ማስረጃ ህጋዊነት ነው። ጉዲይ በስር ፍርድ ቤት የአመልካቹ ወኪል ሆነው የቀረቡት ሰው በፍርድ ቤት በሚደረግ ክርክር በተሟጋችነት ሉቆሙ ስለሚችለ ሰዎች በሕጉ የተመለከተውን መስፈርት የሚያሟለ ናቸው ወይስ አይደለም? የሚለው ጥያቄ ነው።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በመሰረቱ በማናቸውም ፍርድ ቤት አቤቱታ ለማቅረብ ወይም ለመከራከር ባለጉዲዩ ራሱ እንዱቀርብ የሚያስገድድ ሕግ ወይም በፍርድ ቤቱ የተሰጠ የተለየ ትዕዛዝ የላለ በሆነ ጊዜ ባለጉዲዩ ራሱ ለመቅረብ የማይችል ወይም የማይፈቅድ ሲሆን ነገሩን ለማስረዲት፣ ለመከራከር፣ለሚጠየቀው ሁለ በቂ መልስ ለመስጠት የሚችል ሰው በዋናው ባለጉዲይ ተተክቶ በነገረ ፈጅነት፣በወኪልነት፣በጠበቃነት እንዱከራከር ለማድረግ እንደሚችል በፍ.ስ.ስ.ሕ.ቁ.57 ተደንግጎ የሚገኝ ሲሆን በዚሁ ሕግ በቁጥር 60፣61 እና 62 ስር የተመለከቱት ልዩ ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሆነው አበል ሳይሰጣቸው ስለላላ ሰው ሆኖ በወኪልነት ወይም በነገረ ፈጅነት አቤቱታ ለማቅረብ፣ ለመከራከር፣ ለመሟገት እና ነገሩን ለመከታተል የሚችለት የዋናው ባለጉዲይ ባለቤት፣ወንድም፣እህት፣ልጅ፣አባት ወይም አያት ስለመሆናቸው በቁጥር 58(1) ስር ተመልክቷል። በተያዘው ጉዲይ ስለአመልካቹ በመሆን ውክልና የተሰጣቸው የአመልካች ወንድም በመሆናቸው ከዋናው ባለጉዲይ ጋር በቁጥር 58(1) ከተመለከተው የዝምድና ግንኙነት መካከል አንደን የሚያሟለ ስለመሆኑ አከራካሪ ጉዲይ አይደለም። ነገር ግን የውክልና ሰነድ ከውጭ ሀገር ተዘጋጅቶ የተሰጠ በመሆኑ ከሰነድች ማረጋገጥና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 922/2008 አንጻር መመርመሩ ተገቢ ሁኖ አግኝተነዋል። ከኢትዮጵያ ውጭ የተዘጋጁ ሰነድች ትክክለኝነታቸው በሰነድች ማረጋገጥና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 922/2008 አንቀጽ 1፤6፤23 እና 24 ድንጋጌዎች መሰረት በኢፋዳሪ ውጭ ጉዲይ ሚንስትር እና በኢፋዳሪ የፍትህ ሚንስተር የሰነድች ማረጋገጥና ምዝገባ ጽ/ቤት መረጋገጥ እንዲለበት ተደንግጓል።
አመልካች ለወንድሟቸው የሰጡት ውክልና ስልጣን በኢፋዳሪ ኢምባሲ ዋሽንግተን /09 በቀን 14/07/2009 ዓ.ም የፊርማና ማህተም ትክክለኛነት ተረጋግጦ የተሰጣቸውን ውክልና የኢፋዳሪ ውጭ ጉዲይ ሚንስተር /10 በቀን 22/01/2010 ዓ.ም የፊርማ ማህተሙ ህጋዊነት ከተረጋገጠ በኋላ የኢፋዳሪ የሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት በቁጥር ቅጽ/2330/10/2010 በቀን 22/01/2010 ዓ.ም ትክክለኛነቱ የተረጋገጠና የተመዘገበ የውክልና ማስረጃ መሆኑን በተጠሪ በኩል ማስተባበያ ያልቀረበበት መሆኑ ከክርክሩ ሂደት ተገንዝበናል። የተሰጠው ውክልና ማስረጃ ይዘትም በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.58 እና በፍ/ብ/ህ/ቁ.2199 አመልካችን ፍቺን ጨምሮ በማናቸውም ጉዲዮች ወክል ለመከራከርም ሆነ ላላ የህግ ባለሙያ ለመወከል እንደሚችለ በውክልና ሰነድ ላይ በግልጽ የተመለከተ መሆኑን ተገንዝበናል። በመሆኑምwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ተጠሪ የውክልና ማስረጃው ፍትህ ሚንስተርና ውጭ ጉዲይ ሚንስተር ቀርቦ ማህተም ተደርጎ በባለስልጣን ፊርማ ተረጋግጦ የቀረበ ባለመሆኑ ሕጋዊነት የጎደለው ነው በማለት ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት ያለው ሁኖ አልተገኘም። በአጠቃላይ ከላይ በዝርዝር እንደተገለጸው የቤተሰብ ህጉ የጋብቻ ፍቺ ክስ በወኪል ማቅረብ የማይከልክል ሁኖ እያለ እንዱሁም አመልካች ለወንድሟቸው የሰጡት ውክልና ማስረጃ የህጉን መስፈርት የሚያሟላ ሁኖ ተወካዩ በራሰቸው ወይም ጠበቃ በመወከል ክስ ለማቅረብና ለመከራከር የሚያስችላቸው ህጋዊ ውክልና በመያዝ ያቀረቡት ክስ ውድቅ በማድረግ የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ብይንና ትእዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሁኖ ስለተገኘ ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
21387 ህዲር 19 ቀን 2010 ዓ.ም በትእዛዝ ያጸናው ብይን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የወላይታ ሶድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተዘጋውን መዝገብ በማንቀሳቀስ ጉዲዩን ተመልክቶ ተገቢውን እንዱወስን ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 341(1) መሰረት መልሰናል። ይፃፍ።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
ቅ/ሀ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት።
No topics extracted.