በጋብቻ ውስጥ የተደረገ የብድር ውል ከአንደኛው ተጋቢ እውቅና ውጪ የተደረገና የጋራ እዲ መሆኑ ፍሬነገር የማጥራትና ማስረጃን የመመዘን መርህን በተከተለ መንገድ ተረጋግጦ መወሰን ያለበት ስለመሆኑ ፍ/ብ/ህግ ቁጥር 2472
No summary available.
የሰ/መ/ ቀን 28/9/2010 ዓ/ም ዳኞች:- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውልስ ኦርሺሶ አመልካች:- ወ/ሮ ሰብለ ታምራት - ከጠበቃ ቤተልሄም አያላው - ቀርበዋል ተጠሪ:- አቶ ግሩም ግዛቸው - የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ለዚህ ሰበር መዝገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዲይ የቀረበው አመልካች መስከረም 29 ቀን 2010 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ሐምል 5 ቀን 2009 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ትእዛዝ እና የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ ህዲር 21 ቀን 2009 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ቅሬታዋን በማቅረቧ ነው። ቅሬታዋም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካች የምትቃወምባቸውን ምክንያቶች የሚዘረዝርና በሰበር ሰሚው ችልት በኩል ላታይልኝ ይገባል የምትለውን ዲኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣ የስር ፍ/ቤቶች በጋብቻ ውስጥ ስለተፈራው መኪና ገቢ በተመለከተ በማስረጃ አረጋግጬ እያለ መታለፈ ተገቢ አይደለም። በጋብቻ ውስጥ የተደረገ የብድር ውል ከአሁን አመልካች እውቅና ውጪwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የተደረገ በመሆኑ ውድቅ መደረግ ሲገባው የጋራ እዲ መባለ ስህተት በመሆኑ ይታረምልኝ የሚል ነው።
በስር ፍ/ቤት የነበረው ክርክር የጀመረው ከፋደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን ከሳሽ የአሁን አመልካች ባቀረበችው ክስ ከተከሳሽ (የአሁን ተጠሪ) ጋር ያለን ጋብቻ ፈርሷል። በጋራ ያፈራነው ንብረት 1. መኪና የሰ/ቁጥር 3-26589 ኦሮ 2. የመኪና ገቢ በቀን 600 የሾፋር ተቀንሶ ከ17/5/2006 ዓ/ም ጀምሮ ያለው 3. 20/80 የቤቶች ፕሮግራም በንግድ ባንክ የተቆጠበ ገንዘብ 4. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተቆጠበ 5. 61000 የእቁብ ገንዘብ ያካፍለኝ ስትል ጠይቃለች። ተከሳሽም መኪና የሰ/ቁጥር 3-26589 ኦሮ. የሆነ በብድር ገንዘብ የተገዛ በመሆኑ ብድሩ የጋራ እዲ ይሁን። የተበደርነውን እዲ ያልከፈልን ስለሆነ የጋራ እዲ ነው ይባልልኝ።
የቤት ቁሳቁስ ጠቅሶ የየግላቸው የሆነውን ለይቶ መካፈል እንደላለበት መልስ ሰጥተዋል። የስር የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ ህዲር 21 ቀን 2009 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ መኪና የሰላዲ ቁጥር 3-26589 ኦሮ.
በትዲር ውስጥ የተገዛና ከእዲም ነጻ መሆኗን በምስክሮች በሚገባ የተረጋገጠ በመሆኑ የጋራ ንብረት ነው። የመኪና ገቢ አመልካች ለግል ጥቅሙ ያዋለው መሆኑን ከሳሽ ያላስረዲች በመሆኑ ታልፎል። ለኮንድሚንየም ቤት የተጠራቀመ ገንዘብ የጋራ መሆኑን በተማመኑት መሰረት ይካፈለ። የእቁብ .37 መኖሩ ተረጋግጧል እኩል ይካፈለ። ተከሳሽ የብድር እዲ የጋራ ይባልልኝ ያለው በተመለከተ በሰው ምስክሮች ብድሩ መኖሩ በመረጋገጡ የጋራ እዲ ነው። የቤት ቁሳቁስ ተዘርዝሮ የጋራ የሆኑትን የጋራ የግል ናቸው ያለውን የግል ነው ሲል ወስኗል። ከሳሽ የአሁን አመልካች ለፋደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የይግባኝ ቅሬታ አቅርባ በመ/ ሐምል 5 ቀን 2009 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 337 መሰረት አያስቀርብም ሲል መዝገቡን ዘግቶታል።
የአሁን አመልካችም ይህን ውሳኔ በመቃወም ቀርበዋል። መዝገቡም ተመርምሮ በስር ፍ/ቤት በዚህ ጉዲይ የብድር ውለ በአበዲሪው ብቻ ምስክር አመልካች ስለ ብድሩ ያውቁ ነበር መባለ የብድሩ ድንጋጌዎች መስፈርት ያሟለ መሆን አለመሆኑን እና የመኪናው ገቢም ሙለ በሙለ መኪናው ካልተሸጠ አይከፈልም ተብል የመወሰኑን አግባብነትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ለመመርመር ሲባል ቀርቧል። መልስና የመልስ መልስም ተሰጥቶበታል። ተጠሪ ታህሳስ 20 ቀን 2010 ዓ/ም በተጻፈ መልስ የመኪና ገቢ በተመለከተ መኪናው የተሸጠው በ14/6/2006 ዓ/ም ሲሆን የሽያጭ ውለ የፈረሰው በ26/2/2007 ዓ/ም መሆኑን አመልካች ገልጻ እያለ ከ17/5/2006 ዓ/ም ጀምሮ የመኪና ገቢ ያካፍለኝ ብላ መጠይቋ ተገቢ አይደለም። በጋብቻ ውስጥ የተበደርነው ብድር ለትዲር ጥቅም የዋለ መሆኑ የቤተሰብ ህጉ ግምት የሚያስቀምጥ ሆኖ እያለ እና አመልካች ለትዲር ጥቅም ያልዋለ መሆኑን ባለማስረዲቷ የተሰጠው ውሳኔ ስህተት የተፈጸመበት ባለመሆኑ ይጽናልኝ ሲል ተከራክሯል። አመልካችም ጥር 9 ቀን 2010 ዓ/ም በተጻፈ የመልስ መልስ አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል፣ እኛም የቀረበውን አቤቱታ፣ መልስ እና የመልስ መልሱን እንዱሁም የስር ፍርድ ቤት ውሣኔዎችን እና ከጉዲዩ ጋር አግባብነት ያላቸውን የሕግ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን ከተያዘው ጭብጥ አንጻር መርምረናል።
እንደመረመርነውም 1ኛ. የሰላዲ ቁጥር 3-26589 ኦሮ. የመኪና ገቢ በተመለከተ በስር ፍ/ቤት በማስረጃ የተረጋገጠው መኪናዋ ተሸጣ እንደነበረና የተሸጠችውም በ14/6/2006 ዓ/ም መሆኑን የዚች መኪና የሽያጭ ውለ ደግሞ በ26/2/2007 ዓ/ም የፈረሰ መሆኑን ነው። የአሁን አመልካች የዚች መኪና ገቢ ግማሹ እንዱከፈለኝ ሲለ የጠየቁት ከ17/5/2006 ዓ/ም ጀምሮ ያለውን በቀን 600 ብር ትከራያለች በሚል ሲሆን መኪናውን የተከራየው ራማ ኮንስትራክሽን ከ23/7/2006 ዓ/ም ጀምሮ 600 ብር ከአቶ ዲንኤል ቱፊ ላይ የተከራየ መሆኑን አሳውቋል። በመሆኑም የአሁን አመልካች የመኪናዋ ገቢ ይከፈለኝ ስትል በጠየቀችበት ቀን በፉት በ14/6/2006 ዓ/ም ጀምሮ መኪናዋ የተሸጠችና የሽያጩም ውል በ26/2/2007 ዓ/ም ከፈረሰ በኋላ አመልካችና ተጠሪ መኪናዋን ያስመለሱ ስለመሆኑ የተረጋገጠ ነገር አለመኖሩና የአሁን ተጠሪ የመኪናዋን ገቢ መሰብሰቡ ባለመረጋገጡ የመኪናዋ ገዥ የነበረው ገቢዋን ሰብስቦ ከሆነም ከውለ ጋር በተያያዘ የሚታይ ከሚሆን በቀር የስር ፍ/ቤት የአሁን አመልካችን ጥያቄ ሳይቀበለው ማለፈ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አልተገኘም። 2ኛ. በስር ፍ/ ብር የብድርwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
እዲ የጋራ እዲ ነው የተባለበትን ውሳኔ በተመለከተ ከ500 የኢትዮጵያ ብር በላይ የብድር ውል በጽሁፍ ወይም በፍርድ ቤት በተደረገ የእምነት ቃል ወይም በመሐላ ካልሆነ በስተቀር ማስረዲት እንደማይቻል በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 2472 ላይ ተደንግጎ ይገኛል።
የአሁን ብር ብድር የአሁን አመልካችና ተጠሪ አብረን ተበድረናል ሲል ለማስረዲት ያቀረበው የሰነድ ማስረጃ በብድሩ ውል ላይ ያለው ፊርማ የአሁን አመልካች ፊርማ እንዲልሆነ በፍረንሲክ ምርመራ ተረጋግጧል። በብድር ውለ ላይ ያለት ሁለት ምስክሮችም ስለመመስከራቸው አያመለክትም። እንዱሁም የአሁን ተጠሪ መጀመሪያ ባቀረበው ክስ ጋር ያላቀረበውን ማስረጃ ባሻሻለው ክስ ጋር አያይዞ ማቅረቡም የብድር ውል ሰነደን ህጋዊነት የማያሳይ ነው። ላላው የአሁን ተጠሪ ከአቶ ገናናው ተናገር ተበደርኩ የሚለው በ4/5/2006 ዓ/ም ሲሆን የአሁን አመልካች ከቤት የወጣችው በ17/5/2006 ዓ/ም መሆኑና በ18/11/2006 ዓ/ም በመሀላቸው ጋብቻ በፍቺ መፍረሱ አላከራከረም። ተጠሪ ገንዘቡን ተበድሬያለሁ ከሚልበት ከ4/5/2006 ዓ/ም ጀምሮ አመልካች ከ12 ቀን በኋላ በ17/5/2006 ዓ/ም ከቤት ወጥታለች። ተጠሪ ገንዘቡን የተበደረው ለመኪና ማስጠገኛ መሆኑን ገልጾ ለመኪናዋ ማስጠገኛ ስለማዋለ ግን ያቀረበው ማስረጃ የለም። በመሆኑም በአመልካችና በተጠሪ መሀከል አለመግባባት በተፈጠረበት ጊዜ ውስጥ የአሁን ተጠሪ የተበደረው የ180000 ብር ብድር ለትዲር ጥቅም ስለመዋለ መረጋገጥ አለበት። በዚሁ መሰረት የስር ፍ/ቤት ብድሩ ስለመኖሩ የአሁን ተጠሪን ማስረጃ አበዲሪውን የሰው ምስክር ብቻ ሰምቶ የአሁን አመልካችና ተጠሪ ብድሩን ስለመበደራቸው አረጋግጫለሁ ሲል የጋራ እዲ ነው በማለት የሰጠው ውሳኔ ፍሬነገር የማጥራትና ማስረጃን የመመዘን መርህ ባለመከተል የተሰጠው ውሳኔ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ብለናል።
የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ሐምል 5 ቀን 2009 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ትእዛዝ እና የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ ህዲር 21 ቀን 2009 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ብድር እዲ የባልና ሚስት የጋራ እዲ መሆኑ ባለመረጋገጡ የአሁን አመልካችን የሚመለከታት አይደለም ብለናል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።
የዚህ ውሳኔ ትክክለኛ ግልባጭ ለስር ፍ/ቤት ይድረሳቸው ብለናል።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።
No topics extracted.