ከባልና ከሚስት ባንደ የተፈጸመውና ለፍቺው ምክንያት ሆኖ የተገኘው ጥፊት በልላው ተጋቢ ላይ ጉዲት አስከትል ከተገኘ በዲዩ ላደረሰው ጉዲት ከጋራ ንብረት በካሳ መልክ ያንደኛውን ተጋቢ ድርሻ አብዛኛውን ወይም ሙለውን ሲ/ር ሐምዚያ ሱለይማን እና አቶ አያላው በቀለ www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. IV ለተፈጸመበት ወገን እንዱከፈል ሉወሰን የሚችል ስለመሆኑ የኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 69/95 እንደተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 83/96 አንቀጽ 111፣117
No summary available.
መስከረም 21 ቀን 2011 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውልስ ኦርሺሶ አመልካች፡- ሲ/ር ሐምዚያ ሱለይማን -ቀረቡ:: ተጠሪ፡- አቶ አያላው በቀለ-ጠበቃ ኩራባቸው ጎሳ ቀረቡ:: መዝገቡን መርምረን የሚከተውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የኦሮሚያ ብ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በኦሮሚያ ብ/ክ/መ/ አዲማ ልዩ ዞን በአዲማ ወረዲ ፍርድ ቤት ነው። በሥር ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
የአሁን አመልካች በቀን 14/02/2009 ዓ.ም ባቀረቡት አቤቱታ ከተጠሪ ጋር በ1983 ዓ.ም ጀምሮ በባህል ተጋብተው ሲኖሩ አራት ልጆች ማፍራታቸው በመግለጽ አመልካች በቅርብ ጊዜ ውስጥ ባህሪያቸው ስለቀየረ በተለያዩ ጊዜያት የሚደበድቧቸው፤የሚሰድቧቸው እንዱሁም የማያከብሯቸው በመሆኑ ጋብቻው ፈርሶ በጋራ አብረው ያፈሩት ንብረት ድርሻቸው እንዱወስነላቸው ዲኝነት ጠይቀዋል። ተጠሪም ራሷ ባህሪዋን ለውጣ እኔ ያልፈጸምኩት ድርጊት ፈጽመሃል በማለት እኔን መክሰሷwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ትክክል አይደለም በማለት ትዲራችን በአመልካች ጥያቄ እና ፍላጎት በመሆኑ በእርሷ ምክንያት የሚፈርስ መሆኑ ተቆጥሮልኝ የሞራል ካሳ እንድትከፍለኝ በማለት ለአቤቱታው መልስ በመስጠት ተከራክረዋል። ነገር ግን አመልካች የፍቺ ውሳኔ ከመሰጠቱ በፉት መዝገቡ ለጊዜው እንዱዘጋ በማመልከታቸው ምክንያት የማንቀሳቀስ መብታቸው በመጠበቅ ተዘግቶ የነበረ ሲሆን አመልካች የተዘጋው መዝገብ እንዱንቀሳቀስ በቀን 24/08/2009 ዓ.ም በተፃፈ ስለአመለከቱ ፍርድ ቤቱም ተዘግቶ የነበረው መዝገብ እንዱቀሳቀስ በማድረግ የግራ ቀኙ ክርክር ከሰማና ማስረጃ ከመዘነ በኋላ በቀን 28/09/2009 ዓ.ም በዋለው ችልት በግራ ቀኙ የነበረው ጋብቻ በፍቺ እንዱፈርስ ካደረገ ለጋብቻው መፍረስም ተጠሪ ምክንያት በመሆኑ በጋራ አፍርተው ካላቸው ንብረት ውስጥ ከተጠሪ ድርሻ 20 በመቶ ለአመልካች እንዱያካፍል እንዱሁም የሁለት ልጆች ቀለብ በወር ብር 1,500.00/ አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር/ እንዱከፍል ሲል ወስኗል።
የአሁን ተጠሪ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ በመቃወም ለአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኝ ቢያቀርቡም ተቀባይነት ሳያገኝ በትእዛዝ ሰርዞታል።
በመቀጠል ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን አስቀርቦ ካከራከረ በኋላ የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ በማሻሻል በተከራካሪዎች መካከል የነበረው ጋብቻ በተጠሪው ጥፊት በመፍረሱ በጋብቻ ውስጥ 20 በመቶ ለአመልካች እንዱያካፍል በማለት የተሰጠው ወሳኔ ውድቅ በማድረግ የልጆች ቀለብ በማጽናት ወስኗል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበውም ይህንኑ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። አመልካች ጥር 23 ቀን 2010 ዓ.ም በፃፈው አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶችን ዘርዝረው አቅርበዋል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ በመደረጉ ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት በታዘዘው መሰረት ሚያዚያ 26 ቀን 2010 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርበዋል። አመልካችም አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ እንደተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው የሕግwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን ለሰበር ችልቱ ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የአመልካች ጥያቄ ልጆችን ለማሳደግ ደፊ ቀና ብዬ እንዱሁም በአሁኑ ወቅት አካል ጉዲተኛ ልጅ በሰው እርዲታ የሚኖር አሸብር አያላው የሚባለውን ለማሳደግ በጥረት ላይ እያለሁ እና አቅመ አዲም ያልደረሱ አዲን እና ኢለያላ አያላው የሚባለትን ለማሳደግ እና ለማስተማር በጥረት ላይ እያለሁ ይህ ተጠሪ በየጊዜው ረብሻ እየፈጠረ አፀያፉ ቃላት እየተናገረ ለዚህ ሁለ ለትዲር መበተን ዋና ተዋናይ እራሱ ሆኖ እያለ፤እንዱሁም ከእኔ ከአመልካች ጋር በጋብቻ ተሳስረን ወይም ተጋብተን እየኖርን እያለን ከትዲር ውጭ ከላላ ሴት ጋር በፈጸመው የግብረ ስጋ ግንኙነት አንድ ልጅ የወለደ ለመሆኑ በስር ፍርድ ቤት በማያሻማ ተመስክሮበት መከላከል ያልቻለ ስለሆነ በገንዘብ መቀጮ ተቀጥቶ እያለ ምንም አይነት ጥፊት እንዲልፈጸመ ሰው ንብረቱን እኩል እንድንካፈል የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ሉታረም ይገባል የሚል ሲሆን ተጠሪ በበኩላቸው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የስር ፍርድ ቤት የተካሄደውን ክርክር እና ያቀረብኩትን አቤቱታ መርምሮ ከተጠሪ ድርሻ 20% /ሃያ በመቶ/ ለአመልካች ሉከፍል ይገባል የተወሰነው የህግ መሰረት የላለው በመሆኑ ውድቅ መደረጉ ምንም አይነት መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት በመሆኑ ሉፀና ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
የኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 69/95 እንደተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 83/96 የፍቺው ምክንያት ለፍቺው አስፈላጊ ባይሆንም ለውጤቱ በተለይም ለጋራ ንብረት ክፍፍለ ግን ግምት ውስጥ ሉገባ ይችላል። ለምሳላ ለፍቺው የተጠየቀው አንደኛው ወገን በፈፀመው ዝሙት ወይም ድብደባ ምክንያት ከሆነ ፍቺው ተወስኖ በሚደረገው የንብረት ክፍፍል ወቅት ንብረቱ በእኩል መከፊፈለ ቀርቶ ይህንኑ ጥፊት ግምት ውስጥ ያስገባ ክፍፍል ማድረግ ይቻላል። ምክንያቱም በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 69/95 እንደተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 83/96 አንቀጽ 111 ከባልና ከሚስት ባንደ የተፈጸመውና ለፍቺው ምክንያት ሆኖ የተገኘው ጥፊት በልላው ተጋቢ ላይ ጉዲት አስከትል ከተገኘ በዲዩ ላደረሰው ጉዲት ተመጣጣኝ የሆነ ካሳ እንዱከፍል ፍርድ ቤቱ ይወስናል። ፍርድ ቤቱ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ/1/ መሰረት ከጋራ ንብረት በካሳ መልክ ያንደኛውን ተጋቢ ድርሻ አብዛኛውንwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ወይም ሙለውን በደል ለተፈጸመበት ወገን እንዱከፈል ሉወሰን ይችላል በማለት ተደንግጎ ይገኛል። በርግጥ በፍቺ ወቅት የሚኖረው የጋራ ሀብት ክፍፍል በአንጽ 117 እንደተመለከተው የጋራ ሀብቱ ለሁለቱም እኩል የሚከፊፈል ነው። ከዚህ አንፃር ሲታይ አንቀጽ 111 የአንቀጽ 117 ልዩ ሁኔታ መሆኑ ግንዛቤ ሉወሰድበት ይገባል። ወደያዝነው ጉዲይ ስንመለስ የአሁን አመልካች የፍቺ ውሳኔ እንዱሰጥ አቤቱታ ሲያቀርቡ እንደምክንያት ያቀረቡት ተጠሪ ባህሪያቸው በመቀየር በተለያዩ ጊዜያት የሚደበድቧቸው፤
የሚሰድቧቸው እና የማያከብሯቸው ከመሆናቸውም በላይ ከትዲር ውጭ ከላላ ሴት ጋር በፈጸሙት የግብረ ስጋ ግንኙነት አንድ ልጅ የወለደ መሆናቸው በዚህ ተግባራቸውም በአፊር ክልል ልጊያ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.392/2009 በቀን 12/07/2009 ዓ.ም በዋለው ችልት ጥፊተኛ በማለት በገንዘብ መቀጮ የቅጣት ውሳኔ የተወሰነባቸው መሆኑን በተጠሪ ከመታመኑም በላይ ፍሬ ነገሩን የማጣራትና የመመዘን ስልጣን የተሰጣቸው የስር ፍርድ ቤቶችም ያረጋገጡት ጉዲይ ነው። ስለሆነም ከላይ በዝርዝር እንደተመለከትነው በአመልካችና ተጠሪ መካከል የነበረው ጋብቻ መፍረስ በተጠሪ ጥፊት መሆኑና በአመልካች ጉዲት ስለመድረሱ ተረጋግጦ እያለ ተጠሪ ለአመልካች ካሳ የማይከፍለበት ህጋዊ ምክንያት የለም። ሲጠቃለል የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የስር ፍርድ ቤቶች በማሻሻል የሰጠው ውሳኔ በከፉል መሰረታዊ የሕግ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ ስለተገኘ ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የኦሮሚያ ብ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ.269768 መጋቢት 7 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.348/1/ መሰረት ተሻሽሎል።
በአመልካችና ተጠሪ የነበረው ጋብቻ በፍቺ እንዱፈርስ እና ተጠሪ ለልጆች ቀለብ በወር ብር 1,500.00/አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር/እንዱከፍል የተሰጠ ውሳኔ ክፍል ፀንቷል።
ተጠሪ ለአመልካች ካሳ ሉከፍል አይገባም ሲል የሰጠው ውሳኔ ክፍል ተሽሯል።
በአዲማ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.101604 ግንቦት 28 ቀን 2009 ዓ.ም በዋለው ችልት በሰጠው ውሳኔ ውስጥ በተከራካሪዎቹ መካከል የነበረው ጋብቻ በተጠሪ ጥፊት በመፍረሱ በጋብቻ ውስጥ በጋራ ከተፈራው ንብረት ውስጥ ተጠሪwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ከድርሻው ውስጥ 20 በመቶ ለአመልካች እንዱከፍል በማለት የተሰጠው ውሳኔ በአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.26872 ሰኔ 21 ቀን 2009 ዓ.ም በትእዛዝ ያጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ወጭ እና ኪሳራ የግራ ቀኙን ተከራካሪ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻለ።
በቀን 17/08/2010 ዓ.ም የተሰጠው እግድ ተነስቷል፣ ይፃፍ፡ መዘገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.