አባትነትን በሕግ ግምት ወይም በመቀበል መንገድች ለመወሰን ክርክር ሲነሳ የባህሪ ወሳኝ ቅንጣት (DNA) ውጤት እንደ መከላከያ ማስረጃ እንዱቀርብ በሕጉ በግልጽ የተቀመጠ ድንጋጌ የላለ በመሆኑ ፍርድ ቤቶች በሕጉ የተረዘረጋውን ስርዓት ተከትለውና ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ አስፈላጊ መሆኑን ሲያምኑበት ተግባራዊ ሉያደርጉት የሚችለ ስለመሆኑ የዘር የባህሪ ወሳኝ ቅጣት (DNA) ምርመራ ውጤት በሕጉ በተመለከተው አግባብ በሕጋዊ ምክንያቶች ለማስረጃነት የሚቀርብ እንጂ በሕግ የተቀመጠውን ግምት እናት ስለካደች ብቻ ለማስረጃነት የሚቀርብ ማስረጃ ነው ተብል ድምዲሜ የሚደረስበት ስላለመሆኑ የአማራ ክልል የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 79/95 148570 ወ/ሮ ጃኖ ተሰማ እና አቶ አሉ ሰይድ ግንቦት28 ቀን 2010 ዓ.ም 12www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. III አንቀፅ 181፣183(1) እና 155(1(ሀ)) 4. የባህሪ ወሳኝ ቅጣት ( DNA) ምርመራ አንድ ሰው የልጁ አባት ወይም እናት አይደለም ለማለት የሚቀርብ ማስተባባያ ማስረጃ ላሆን የሚችል ቢሆንም የሚከናወነው አባትነትን በሚመለከት የመካድ ክስ ለማቅረብ የሚያስችለ ቀዲሚ ሁኔታዎች ሲሟለ ስለመሆኑ እና እናትነትን በተመለከተም በቤተሰብ ህግ ከአንቀፅ 153 እስከ 166 ድረስ የተዘረጋው ስርዓት የሚፈቅድ ሁኖ በፍትሃ ብሓር ስነ ስርዓት ሕጉ የተመለከቱትን የማስረጃ አቀራረብ ስርዓቶችን መሰረት በማድረግ ሲቀርብ ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 213/1992 ከአንቀጽ 167-179
No summary available.
መስከረም 23 ቀን 2011 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውልስ ኦርሺሶ አመልካች፡- ወ/ሮ ብርቱካን ታደሰ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ የሺእመቤት ታደሰ ከጠበቃ አበበ ማስረሻ ጋር ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ ተጠሪ የአመልካችን የሻለቃ ታደሰ በላይነህ ልጅነትን በመቃወም ለፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ያቀረቡትን ክርክር መሰረት በማድረግ የተሰጠውን ውሳኔ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀረመው የአሁኗ አመልካች በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጥር 27 ቀን 2006 ዓ/ም ባቀረቡት ክስ ነው።
የአመልካች የክስ ይዘት ሲታይም፡- ወላጅ አባታቸው ሻለቃ ባሻ ታደሰ በላይነህ ከወላጅ እናታቸው ከወ/ሮ ሙለነሽ አበበ ጋር በጋብቻ ውስጥ ሁነው በ 1964 ዓ/ም የወለዶቸው መሆኑን፣ የልደት ምስክር ወረቀትም ያላቸው፣ ከቤተሰቦቻቸው አሳድገው፣ አስተምረው የዲሯቸው መሆኑን፣ በሰፈር፣ በቤተዘመድ እና በወረዲም ልጅ ለመሆናቸው የሚታወቁ መሆኑን፣ ወላጆቻቸው ሲሞቱም ወራሽነታቸውን ሲያረጋግጡ የአሁኗ ተጠሪ በመቃወማቸው የወራሽነት ማስረጃውን የሰጠው ፍርድ ቤት አመልካችን ልጅነታቸውን አረጋግጠው እንዱቀርቡ በማዘዙ ምክንያት ክሱን ለማቅረብ የተገደደ መሆኑን ጠቅሰውwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የሁለቱም ሟቾች ልጅ መሆናቸው በፍርድ ተረጋግጦ የልጅነት ውሳኔ እንዱሰጣቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
ተጠሪም ወደ ክርክሩ ጣልቃ ገብተው እንዱከራከሩ እንዱፈቀድላቸው በ17/07/2006 ዓ/ም በተጻፈ ማመልከቻ ጠይቀው ከተፈቀደላቸው በኋላ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትእዛዝ መነሻ አሻሽለው ባቀረቡት ክርክር ሟቾች ባልና ሚስት ቢሆኑም መሃን መሆናቸውን፣ አመልካች የሟች ወ/ሮ ሙለነሽ አበበ የወንድም ልጅ መሆናቸውን፣ ሟቾች ለተጠሪ ኑዛዜ ትተውላቸው ተጠሪ በፍርድ ቤት እንዱፀድቅ ማድረጋቸውንና አመልካች የሟቾች ተወላጅ ባልሆኑበት ሁኔታ ተጠሪ በሟቾች ኑዛዜ ወራሽነት ተጠቃሚ የሆኑበትን የውርስ ንብረት የሚጠይቁበት የሕግ አግባብ የለም በማለት ተክራክረዋል። ለዚህ ክርክራቸው አለኝ የሚሎቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ ዘርዝረው ከማቅረባቸውም በተጨማሪ በ26/08/2008 ዓ/ም በተፃፈ ማመልከቻም የዱ.ኤን.ኤ ምርምራ እንዱደረግ ትዕዛዝ እንዱሰጣቸው አመልክተው ፍርድ ቤቱም በ25/1/2/2008 ዓ/ም በዋለው ችልት የተጠሪን የዱ.ኤን.ኤ ምርመራ ጥያቄ ስነ ስርዓታዊ አይደለም በሚል ምክንያት ውድቅ አድርጎ ብይን ሰጥቷል።
ከዚህም በኋላ ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከሰማና ተገቢ ነው ባለው መንገድ ሁለ ከአጣራ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ አመልካች የሟቾች ልጅ መሆናቸውን በሰውና በሰነድ ማስረጃ ሲያስረደ ተጠሪ ይህንኑ አላስተባበለም በሚል ምክንያት አመልካች የሟች ሻለቃ ባሻ ታደሰ በላይነህና የሟች ወ/ሮ ሙለነሽ አበበ ልጅ ናቸው በማለት ወስኗል።
በዚህ ውሳኔ የአሁኗ ተጠሪ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ የተጠሪ የዱ.ኤን.ኤ ምርመራ የታለፈው ሕጋዊ ባልሆነ ምክንያት ነው በማለት የስር ፍርድ ቤት በፍሬ ነገሩ ላይ የሰጠውን ውሳኔ ሙለ በሙለ ሽሮ የአሁኗ አመልካች ከአቶ ገዛኽኝ በቀለ ጋር የዘረመል /D.N.A/ ምርመራ እንዱያደርጉ የስር ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዱሰጥና የምርመራ ውጤቱ ሲቀርብለት የመሰለውን እንዱወስን በማለት ጉዲዩን መልሶለታል። በዚህ ውሳኔ የአሁኗ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ቢያቀርቡምwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ይግባኛቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- ተጠሪ የዱ.ኤን.ኤ ምርምራ ጥያቄ መጀመሪያ በሕጉ አግባብ ያላቀረቡና ጥያቄውን ከአቀረቡ በኋላም ምራመራው ከማን ጋር እንደሚከናውን የተለያዩ አቋም ይዘው ሲከራከሩ የቆዩ ከመሆናቸውም በላይ ከአመልካች ጋር ምርመራ እንዱያደርግ የታዘዘው ግለሰብም ፍርድ ቤቱ በምስክርነት የሰማውና የአመልካችን ተወላጅነት ያረጋገጠ ሁኖ እያለ ተገቢ ባልሆነ ስነ ስርዓትና ምክንያት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ መሻሩ ያላግባብ ነው የሚል ሲሆን አቤቱታው ተመርምሮም በዚህ ችልት እንዱታይ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ ቀርበውም ግራ ቀኙ በፅሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለዚህ ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር እንዱሚከተለው መርምሮታል። ጉዲዩ ለዚህ ችልት ሲቀርብ የተያዘው ጭብጥም ተጠሪ ባቀረቡት የጣልቃ ገብ አቤቱታ ላይ የዘረ መል ምርመራ እንዱደረግ ባልጠየቁበት ሁኔታና እንዱሁም አመልካች የዘረ መል ምርመራ አብረው እንዱያደርጉ የተባለው ግለሰብ ከሟች ጋር ያለው የቅርብ ዝምድና ሳይጣራ የዘረመል መርምራ እንዱደረግ የመታዘዙን አግባብነት የሚመለከት ነው።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የአሁኑ አመልካች በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ከሟች ሻለቃ ባሻ ታደሰ በላይነህና ከወ/ሮ ሙለነሽ አበበ በጋብቻ ውስጥ ተወልጄአለሁ በሚል ይኼው በፍርድ እንዱረጋገጥላቸው መሆኑንና የአሁኗ ተጠሪ ወደ ክርክሩ ጣልቃ እንዱገቡ ተደርጎ ሟቾች ልጅ መውለድ የማይችለና አመልካችም ከሟቾቹ ያልተወለደ መሆኑን፣ ተጠሪ ከሟቾቹ የኑዛዜ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀው የሚከራከሩ መሆኑን፣ ግራ ቀኙ አለን የሚሎቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎቻቸውን ከማቅረባቸውም በተጨማሪ ፍርድ ቤቱ ፍሬ ነገሩን ተገቢ ነው ባለው መንገድ ያጣራ መሆኑን፣ የአመልካች የሰው ምስክሮችም ሆኑ በተጠሪ በፍርድ ቤት ማጣሪያነት ቀርቦ እንዱመሰክር የተጠየቀው ምስክርም በማጣሪያ ምስክርነት ቀርቦ አመልካች የሟቾች ልጅ መሆናቸውን እንደሚያውቁ የመሰከሩ ሲሆን አመልካች በሰነድwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ማስረጃነት በ15/04/2006 ዓ/ም የተሰጣቸውን የልደት ምስክር ወረቀት፣ ሟች ወ/ሮ ሙለነሽ አበበ አባል መሆናቸው ከተረጋገጠው ከምስራቅ በር እድር የቀረበው ሰነድም አመልካችን የእድርተኛ አብራክ ልጅ በሚል ተመዝገበው የሚገኙ መሆኑን እንደሚያሳይ፣ ከክፍለ ቀበላ የቀረበው የቤተሰብ ቅጽም አመልካች ልጅ ተብለው የተመዘገቡ መሆኑን እንደሚያሳይ፣ ከኮሪያ ዘማቾች የቀረበው ቅጽም አመልካችና ተጠሪ ልጅ ተብለው የተመዘገቡ መሆኑን እንደሚያሳዩ፣ በአመልካች በኩል የተሰሙት አራት የሰው ምስክሮች አመልካችን ሟቾች ያሳደጓቸው እንጂ ያልወለዶቸው መሆኑን፣ አመልካች አለኝ የምትላቸው የኑዛዜ ተጠቃሚነት ሰነድች ሲታይም ሻለቃ ባሻ ታደሰ በላይነህ በ13/03/94 ዓ/ም አደረጉ የተባለው ኑዛዜ በመ/ቁጥር 300/97 በ6/6/97 ዓ/ም በፍርድ ቤት የጸደቀ መሆኑን፣ ሟች ወ/ሮ ሙለነሽ አበበ በ13/1/95 ዓ/ም አደረጉ የተባለው ኑዛዜ ደግሞ በመ//05 በ1/12/05 ዓ/ም ፀድቆ የነበረ ቢሆንም በአመልካች ተቃዋሚነት በ17/11/06 ዓ/ም የተሻረ መሆኑን የሚያስገነዝቡ መሆኑን የስር ፍርድ ቤት በውሳኔው ላይ በግልጽ ማስፈሩን ነው። ተጠሪ የአመልካችን የሟቾች ልጅነት ተረጋግጦ ማስረጃ ይሰጠኝ ጥያቄን ጣልቃ ገብተው ሲቃወሙ የዱ.ኤን.ኤ ምርመራ ጥያቄ ያላቀረቡ መሆኑን፣ በ06/11/2007 ዓ/ም በስር ፍርድ ቤት ፅፈው ባቀረቡት አቤቱታም በሟች ሻለቃ በሻ ታደሰ በላይነህ እና በአመልካች መካከል የዘረ መል ምርመራ እንዱካሄድ የሚል ሲሆን በዚህ የተጠሪ ጥያቄ ላይ አመልካች አስተያየት እንዱሰጡበት ተደርጎ አመልካች በ15/10/2008 ዓ/ም በሰጡት አስተያየት ተጠሪ ጣልቃ ለመግባት በጠየቁበት ማመልከቻ ያልጠየቁትና ስነ ስርዓታዊ ያልሆነ ጥያቄ መሆኑን፣ ሐምል 06 ቀን 2007 ዓ/ም አቀረብኩ ላለት አቤቱታም አቶ ገዛኽኝ በቀለ በምስክርነት እንዱሰሙና ከአመልካች ጋር የዘረመል ምርምራ እንዱያደርጉ በማለት የጠየቁት ጥያቄም ግለሰቡ በማስረጃነት የተሰሙ በመሆኑና ግለሰቡ ከአመልካች ጋር የዘረመል ምርመራ ለማድረግ የሚያስችል ሕጋዊ ምክንያት ያለመኖሩን ገልጸው የተከራከሩ መሆኑን ከክርክሩ ሂደት ተገንዝበናል።
በመሰረቱ አንድ ሰው ከአንድ አባትና እናት መወለደን በሕግ አግባብ በፍርድ ቤት እንዱረጋገጥ የሚቀርበውን ክስ መቃወም የሚቻለው በሕጉ በተዘረጋው ስርዓት ነው።
በአባት በኩል ያለውን መቃወም የሚቻለው የመካድ ክስ ወይም ክርክር በሚቀርብበት አግባብ ስለመሆኑ ከተሸሻለው የፋዳራል የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/1992www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ከአንቀጽ 167 -179 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንረዲው ጉዲይ ነው። ከእነዚህ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ መረዲት የሚቻለው የመካድ ክሱ የሚቀርበው አባት ነህ የተባለ ሰው ራሱ መሆኑ የቤተሰብ ህጉ አንቀጽ 174 ያስቀመጠ ሲሆን እርሱ የሞተ ወይም ችልታ ያጣ ከሆነ ደግሞ በቤተሰብ ህጉ አንቀጽ 177 የተጠቀሱት ሰዎች እንደቅደም ተከተላቸው መሆኑን ነው። በሕጉ ከተመለከቱት ከእነዚህ ሰዎች ውጪ የመካድ ክስ ላላ ሰው ሉያቀርብ የማይችል መሆኑን፣ በሕጉ የተፈቀደላቸው ሰዎች የመካድ ክስ ለማቅረብ የሚችለትም የቤተሰብ ህጉ አንቀጽ 171 መሰረት የፍርድ ቤት ፍቃድ ሲያገኙ ነው። በመሆኑም ይህ በሕጉ የተመለከተው ፈቃድ የማግኘት ጉዲይ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ ነው። ህጉ በእናትና በልጁ ያለው ግንኙነት እናትነት ለማረጋገጥ በመወለድ ብቻ እንደሆነ፣ ነገር ግን ይህን ሉሰተባበል አይቻልም ለማለት እንደማይቻል በተሻሻለው የፋዳራለ የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 163 ይደንግጋል።
ፍርድ ቤቱም ይህን ለማስረዲት ተጨባጭነት ያለው ተግባር መኖሩን ካልረተጋገጠ በቀር ሉፈቅድ እንደማይቻል በተጠቃሹ ሕግ 164/2/ ስር በግልጽ ተመልክቷል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም አመልካች ሟች ሻለቃ ባሻ ታደሰ በላይነህ እና ሟች ወ/ሮ ሙለነሽ አበበ በጋብቻ ውስጥ እያለ የተወለደ መሆኑን አመልካች ገልፀው ተከራክረው በስር ፍርድ ቤት የቀረቡት ምስክሮቻቸው ይህንኑ የመሰከሩላቸው ከመሆኑም በላይ ላልች የሰነድ ማስረጃዎች የቀረቡ ሲሆን ይህንን የሚያስተባብል ማስረጃ ተጠሪ ያለማቅረባቸውን የክርክሩ ሂደት ያሳያል። በጋብቻ ውስጥ የተወለደ ልጅ አባት ባልየው ስለመሆናቸው የሕግ ግምት መኖሩን ከተሻሻለው የፋዳራለ የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 126 ድንጋጌ መረዲት ይቻላል። በሕግ የልጁ አባት ነው የተባለው ሰው የልጁ አባት ላሆን እንደማይችል በማያጠራጥር አኳኋን በማስረዲት ለመካድ እንደሚችልና በዚህ መሰረት የሚቀርበው የመካድ ክስ ግን ፍ/ቤት ካልፈቀደና ላቀርብ እንደማይችል ከተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 170 እና 171/1/ ድንጋጌ በግልጽ መረዲት ይቻላል። የተሻሻለው የፋዳራለ የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 176/1/ የእኔ ልጅ አይደለም የሚል የመካድ ክስ የልጁን መወለድ ካወቀበት ወይም ማወቅ ከሚገባው 180 ቀናት ውስጥ መቅረብ አለበት የሚል ይዘት ያለው ሲሆን በድንጋጌው "…በተለይ ማወቅ ከሚገባው…." የሚለው የድንጋጌው አገላለጽ የልጁን መወለድ ማወቅ ከሚገባው ቀን ጀምሮ ተብል የሚተረጏም መሆኑንwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የድንጋጌው ይዘትና መንፈስ የሚያስገነዝበው ጉዲይ ነው። በመሆኑም ልጁ በሕጉ ግምት መሰረት አባት የተባለው ሰው ልጅ ያለመሆኑን በማናቸውም ጊዜ ወሬ ከሰማበት ወይም ጥርጣሬ ከተፈጠረበት ቀን ጀምሮ በሚል የተቀመጠ ባለመሆኑ የመካድ ክስ በማናቸውም ጊዜ የሚቀርብ ነው ተብል የማይወሰድ መሆኑን ሕጉ ያሳያል። በጋብቻ ውስጥ የተወለደን ልጅ ባልየው አባት ነው ብል የተወሰደው የሕግ ግምት ጥብቅ ድንጋጌ በመሆኑ አባት አይደለም የሚል ጥያቄ ሲነሣ ይህንን በሚያጠራጥር አኳኋን ማስረዲት እንደሚጠበቅበትና የመካድ ክስ ለማቅረብ እንኳ የፍ/ቤት ፈቃድ እንደሚያስፈልግ መደንገጉ ሲታይ ሕጉ በጋብቻ ውስጥ የተወለደን ልጅ በማናቸውም ጊዜ ማንኛውንም ምክንያት በማቅረቡ መካድ እንዲይኖር ከፍተኛ ጥበቃ ያደረገ መሆኑን መረዲት ይቻላል። ይህ የሕጉ ጥብቅ ድንጋጌ እና ጥበቃ ያስፈለገበት ዋና ምክንያት ልጆች በወላጆቻቸው ተገቢ ባልሆነ ምክንያት ተክደው ወላጅ አልባ ሆነው እንዲይቀሩ፣ ለተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እንዲይዲረጉ፣ በቤተሰብ መካከል የሚፈጠረውም ያለመተማመን ማህበራዊ ምስቅልቅልች እንዲይፈጥር በወላጆችና በተወላጆች መካከል ለሚፈጠሩ መብቶችና ግዳታዎችን በአግባቡ ለማስተናገድ ሥርዓት ለማስያዝ ጭምር ነው ተብል ይታሰባል።
ከዚህ አንጻር ጉዲይ በዔጃችን የተያዘው ጉዲይ ሲታይም የአሁኑ ተጠሪ አመልካች የሻለቃ ታደሰ በላይነህ ልጅ አይደለም በማለት ተቃውሞአቸውን ለስር ፍርድ ቤት ሲያቀርቡ ከላይ በተጠቀሰው ህግ መሰረት አስቀድሞ የፍርድ ቤት ፍቃድ አላገኙም፤
በተጨማሪም ተጠሪ የኑዛዜ ተጠቃሚ ከመሆናቸው ውጪ በቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 174 እና 177(3) ውስጥ ከተዘረዘሩት የመካድ ክስ ለማቅረብ ከተፈቀደላቸው ሰዎች ውስጥ የሚካቱ አይደለም።
አመልካች የሟች ወ/ሮ ሙለነሽ አበበ ልጅ ነኝ በማለት ያቀረቡትን ክርክር ተጠሪ የሚቃወሙበትን አግባብ ስንመለከተውም እናትነትን ለማስረዲት በተጠቃሹ አዋጅ ውስጥ ከአንቀጽ 163-166 ስር ስርዓቱ ተዘርግቷል። ይዘታቸውም በሚከተለው መልኩ የተቀመጠው ነው። በእናት በኩል ያለው ተወላጅነት በማንኛውም ባለጉዲይ በማንኛውም ጊዜ ሁለ ክርክር ላደረግበት እንደሚችል ህጉ በግልጽ የሚያሳይ ሲሆን የተጠቃሹ ህግ አንቀጽ 164 ድንጋጌ በተለይ ሲታይም በተወላጅነት ላይ ስለሚደረገው ክርክር የሚቀርበውwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ክስ ፍርድ ቤት ካልፈቀደ በስተቀር ላቀርብ የማይችል መሆኑን በንዐስ ቁጥር አንድ ድንጋጌ ስር ሲያስቀምጥ በንዐስ ቁጥር ሁለት ድንጋጌ ስር ደግሞ በተወላጅነት ላይ ክርክር ለማድረግ ለሚቀርበው ክስ ፈቃድ የሚሰጠው ፍርድ ቤቱ ክሱን እንዱቀበል የሚያደርጉት ተጨባጭነት ካላቸው የሚመነጩ ግምቶች ወይም ምልክቶች ሲኖሩ ብቻ ነው በሚል አስገዲጅነት ባለው መልኩ አስቀምጦ ይገኛል። የአዋጁ አንቀጽ 165 ድንጋጌም ልጁ ተወላጅነቱን የሚያረጋግጥ የልደት ምስክር ወረቀትና ከዚህ ጋር የሚስማማ የልጅነት ሁኔታ ያለው እንደሆነ በተወላጅነቱ ላይ ለመከራከር ፈቃድ አይሰጥም በሚል በኃይለ ቃል ደንግጓል። እንዱሁም የአዋጁ አንቀጽ 166 ንዐስ ቁጥር አንድ በተወላጅነት ምክንያት የሚቀርበው ክስ በተወላጅነቱ ላይ ክርክር በተነሳበት ሰው ላይ ወይም በወራሾቹ ላይ ሉመሰረት እንደሚችል ያሳያል።
ከእነዚህ ድንጋጌዎች አቀራረፅ፣ ይዘት እና መንፈስ መገንዘብ የሚቻለው የአንድ ልጅ እናት እገሉት አይደለችም ወይም እኔ ነኝ የሚለው ክርክር የሚነሳው የመወለድ የምስክር ወረቀት ከላለ ወይም የልጅነት ሁኔታ በላለ ወይም ይህ ሁኔታ ክርክር የቀረበበት እንደሆነ ስለመሆኑ ነው። እንግዱህ ከላይ የተጠቀሱት የሕጉ ድንጋጌዎች ተወላጅነት ላይ የሚነሳን ክርክር የሚገዙ ሲሆን በተሻሻለው የቤተሰብ ሕጉ አንቀፅ 154 እስከ 162 ድረስ ያለት ድንጋጌዎች ስለልጅነት ማስረጃ /Proof of Filiation/ የሚገዙ እና ተወላጅነት ላይ ስለሚነሳ ክርክር አግባብነት ካላቸው ከላይ ከተጠቀሱት ድንጋጌዎች የተለዩ ስለመሆኑ መገንዘብ የሚቻል ነው።
በመሰረቱ ስለልጅነት ቀዲሚ ማስረጃ የልደት ምስክር ወረቀት ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 154 የሚያስገነዝብ ሲሆን የልደት ምስክር ወረቀት በላለ ጊዜ የልጅነት ሁኔታ በመኖሩ ልጅነት እንደሚረጋገጥ በተጠቀሰው አዋጅ በአንቀጽ 155 ስር የተመለከተ ሲሆን የልጅነት ሁኔታ መኖር የሚለው ትርጉም ደግሞ አንድ ሰው በማህበረሰቡ ዘንድ የእርሱ ወይም የእርሷ ልጅ ነው እየተባለ የሚገመት ሲሆን ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 156 ስር በግልጽ ተቀምጧል። በዚህ አኳኋን የልጅነት ሁኔታ መኖሩን ለማስረዲት የተቻለ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ልጅ ነው ሲል የሕግ ግምት እንደሚወስድ፣ የሕግ ግምቱ ልጁ የተባለው ሰው ልጅ ላሆን እንደማይችል ሉፈርስwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
እንደሚችል በአዋጅ አንቀፅ 157 ንዐስ ቁጥር አንድና ንዐስ ሁለት ስር እንደቅደም ተከተለ ተመልክቷል።
የደም ምርመራ ( DNA) አንድ ሰው የልጁ አባት ወይም እናት አይደለም ለማለት የሚቀርብ ማስተባባያ ማስረጃ ላሆን የሚችል ቢሆንም ይህ የሚከናወነው ደግሞ አባትነትን በሚመለከት የመካድ ክስ ለማቅረብ የሚያስችለ ቀዲሚ ሁኔታዎች ሲሟለ ነው፣ እናትነትን በተመለከተም በተጠቃሹ ህግ ከአንቀፅ 153 እስከ 166 ድረስ የተዘረጋው ስርዓት የሚፈቅድ ሁኖ በፍትሃ ብሓር ስነ ስርዓት ሕጉ የተመለከቱትን የማስረጃ አቀራረብ ስርዓቶችን መሰረት በማድረግ ላቀርብ የሚገባ ነው።
እንግዱህ በሕጉ የተዘረጋውን ስርዓት ይዘን ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስም ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች የተነሳ የስር ፍ/ቤት አመልካች ሕግ ጥበቃ በሚያደረገው ጋብቻ ውስጥ የተወለደ መሆኑንና ሟች ሻለቃ ባሻ ታደሰ በላይነህና ሟች ወ/ሮ ሙለነሽ አበበ በጋብቻ ውስጥ ሁነው አመልካችን መወለዲቸውን በአረጋገጠበት ሁኔታና በዚህ ግንኙነት ውስጥ የሚወለድ ልጅ አባት ተብል በሕጉ ግምት የሚወሰድበት ከልጁ እናት ጋር የተቀመጠው ወንድ መሆኑ፣ ይህ የህግ ግምት የሚፈርስበት አግባብም የመካድ ክስን በማቅረብ ሁኖ ክሱን ወይም መቃወሚያውን ለማቅረብ የሚችለ ወገኖች ማንነትና ማቅረቢያ ጊዜውም በህጉ ተለይቶ ከመቀመጡም በላይ የመካድ ክስ እንዱቀርብ የሚፈቀደው በማያጠራጥር ሁኔታ ልጁ ከተወለደበት ወደኋላ ሲቆጠር በ300 እና 180 ቀናት ዉስጥ ከልጁ እናት ጋር ሩካቤ ሥጋ ግኙኝነት ያለመፈጸሙን ሲረጋገጥ ወይም በልላ ማስረጃ የልጅ አባት መሆን አለመቻለም ሲያሰረዲ አባት መሆኑ በሕጉ ጥብቅ በሆነ አግባብ ተመልክቶ እያለ፣ እንዱሁም ሟች ወ/ሮ ሙለነሽ አበበም በሕጉ ከአንቀፅ 163 እስከ 166 አግባብ ተጠሪ መቃወሚያ ለማቅረብ የሚያስችለ ሁኔታዎች ተገኝተው ፍርድ ቤቱ ፈቃደን ባልሰጠበት ሁኔታ ከማስረጃ አቀራረብ ስርዓት ውጪ፣ አመልካች ምርመራ እንዱያደርጉ የታዘዘው ግለሰብም በፍርድ ቤት ቀርቦ የአመልካችን ተወላጅነት ባረጋገጠበትና የዚህ ግለሰብ ዝምድናም ከሁለቱም ሟቾች ጋር ስለመሆኑ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ፤ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ያለምንም መነሻ የባህሪ ወሳኝ ቅጣት (DNA) ምርመራ እንዱደረግ ተጠሪ ጥያቄ በሕጉ አግባብ አቅርበዋል ወደሚል ድምዲሜ ደርሶ የደም ምርመራ እንዱረግ ማዘዙ ከመነሻውም በሕጉ የተመለከተውን ስርዓት ያልተከተለ በመሆኑ በሕጉ ከተዘረጋውwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ስርዓት ውጪ እንዱከናውን ተደርጎ የነበረው ምርመራ ታልፍ በጉዲዩ ላይ በቀረቡት የሰውና የሰነድ ማስረጃ የአመልካች የሟቾች መሆናቸው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መወሰኑ ከውጤት አንጻር የሚነቀፍበትን አግባብ አላገኘንም። ከዚህ አንጻር ሲታይ የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት፣ የስር ፍርድ ቤት ግን በጉዲዩ ላይ የቀረቡትን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን መዝኖ አመልካች የሟቾች ልጅ ናቸው በማለት የሰጠው ውሳኔ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የላለበት ሁኖ ስለተገኘ ተከታዩን ወስነናል።
150307 በ9/5/2010 ዓ/ም የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ በ25/12/2008 ዓ/ም የሰጠው ብይንና ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ቁጥር 348(1) መሰረት ጸንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
ትእዛዝ 11/07/2010 ዓ/ም ተሰጥቶ የነበረው እግድ ተነስቷል። ይጻፍ።
No topics extracted.