የዉክልና ሰነድችን ለማረጋገጥና ለመመዝገብ ስልጣን በተሰጠዉ አካል የተረጋገጠ ሰነድ ሙለ እምነት የሚጣልበት ማስረጃ ሆኖ ቅቡልነት ያለዉ ስለመሆኑና የሰነደን ቅቡልነት መቃወም የሚቻለዉም በበቂ ምክንያት ፍርድ ቤት ሲፈቅድ ብቻ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ/922/08 አንቀጽ 23/1/
No summary available.
መ/ ግንቦት 28 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውልስ ኦርሺሶ አመልካች፡- ወ/ሮ ጃኖ ተሰማ -ቀረቡ።
ተጠሪ፡- አቶ አሉ ሰይድ -ቀረቡ።
መዝገቡ መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የአባትነትና የሞግዚትነት ጥያቄን የሚመለከት ክርክር ሲሆን ጉዲዩ የተጀመረው የአሁን ተጠሪ በአሁኗ አመልካች ላይ በመ/69 በአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት በሃብሩ ወረዲ ፍርድ ቤት ጥር 08 ቀን 2009 ዓ/ም ባቀረቡት ክስ መነሻነት ነው። የተጠሪ ክስ ይዘትም ባጭሩ፡- አመልካች በሀብሩ ወረዲ ፍርድ ቤት በፍ/መ/ቁጥር 427/2000 በ17/03/2000 ዓ/ም በዋለው ችልት የወራሽነትና የሞግዚነት እንዱሁም የሚስት ማስረጃ ያገኙ መሆኑን፣ ይሁን እንጂ ኢብራሂም መሐመድ በሚል ወራሽነት ያሳወጁለት ከአሁኗ አመልካች ጋር በጸና ጋብቻ ውስጥ ሆነው የወለደትና እያሳደጉ የነበሩ መሆኑን፣ ይህ ሁኖ እያለ አመልካች ህጻኑ ከመሐመድ ሁሴን እንደተወለደና ወራሽ መሆኑን፣ የላላ ሰው ሚስት መሆናቸውን የህጻኑ ሞግዚት መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ የሚይዙበት አግባብ የላለ መሆኑንና አመልካች እነዚህን ሁኔታዎችን የሚያሳይ ውሳኔ ያገኙ መሆኑን በልላ ክርክር ጊዜ ማወቅ የቻለ መሆኑን ጠቅሰው በመ/ቁጥር 427/2000 በ17/03/2000 ዓ/ም የተሰጠው ውሳኔ ውድቅ እንዱሆንላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኗ አመልካች ለክሱ በሰጡት መልስም ጉዲዩ ቀድሞ ታይቶ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ችልት ጭምር የመጨረሻ ፍርድ የተሰጠበት መሆኑን፣ በጉዲዩ ላይ ተጠሪ መብትና ጥቅምም የላላቸው መሆኑንና ሕጻኑ የሐጂ መሀመድ ሐሰን ልጅ መሆኑን ጠቅሰው ተከራክረዋል። የሥር ፍርድ ቤትም የአመልካችን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ነጥቦችን ውድቅ አድርጎ ከአለፈ በኋላ ክርክሩን መርቶ ተጠሪ ማስረጃዎቻቸውን ያሰሙ ሲሆን የአሁኗ አመልካች ግን በተደጋጋሚ ጊዜ ማስረጃዎቻቸውን እንዱያቀርቡ እድለ ተሰጥቶአቸው ማስረጃዎቻቸውን በራሳቸው ጉድለት ሉያቀርቡ ባለመቻላቸው ይህንኑ መብታቸውን በማለፍ ጉዲዩን መርምሮ የአሁኗ አመልካች ህጻኑን ከሟች አቶ መሐመድ ሀሰን የወለደት ሳይሆን ከአሁኑ ተጠሪ ጋር በጋብቻ ተሳስረው በነበሩበት ጊዜ የወለደት መሆኑ ተረጋግጦአል፣ በጋብቻ ውስጥ ለተወለደ ህጻን ደግሞ የደም ምርመራ የሚደረግበት የሕግ አግባብ የለም ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። አመልካች የሰበር አቤቱታቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበውም በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለም ተብል ተሰርዞባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ሲሆን የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ጉዲዩ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ በሆነ የመጨረሻ ፍርድ ያገኘ መሆኑን፣ የአመልካች የማስረጃ ማሰማት መብት የታለፈውም ያላግባብ መሆኑ የሚዘረዝርና ህፃኑ የሟች ሀጂ መሐመድ ሀሰን ልጅ እንጂ ከተጠሪ የወለደት ያለመሆኑን ጠቅሰው የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ተሽሮ በመ/ቁጥር 427/2000 በ17/03/20000 ዓ/ም የተሰጠው ውሳኔ እንዱፀናላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም ግራ ቀኙ የሚከራከሩበት ጉዲይ አመልካች ልጃቸው ኢብራሂም መሀመድ ወይም አቡበከር መሀመድ የሟች ሼህ መሀመድ ሀሰን ልጅ ነው፣ ልጁ የማን እንደሆነ የማውቀው እኔ እናቱ ነኝ ሲለ ተጠሪ ደግሞ ልጁ የእኔ ነው ፣ ከአመልካች ጋር በነበረን ጋብቻ ውስጥ የተወለደ ነው የሚል ሲሆን ይህንን ለመለየት የዱ.ኤን.ኤ ምርመራ ሳይደረግ በጋብቻ ውስጥ በመወለደ ብቻ የሕግ ግምት ወስድ ልጁ የተጠሪ ነው የመባለን አግባብነት ለመመርመር ተብል ጉዲዩ በዚህ ችልት እንዱታይ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ ቀርበውም ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን ለዚህ ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለው መርምሮታል።
ከክርክሩ መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ በአመልካች ላይ ክሱን ሉመሰርቱ የቻለት ከአመልካች ጋር ሕዲር 10 ቀን 1995 ዓ.ም ተጋብተው በመርሳ ከተማ 01 ቀበላ ይኖሩ እንደነበር፣ በጋብቻ ወቅት ስሙ አቡበከር አሉ /ኢብራሑም አሉ/ የተባለ ወንድ ልጅ ነሃሴ 25 ቀን 1996 ዓ.ም እንደወለደ፣ ይህ ሁኖ እያለ አመልካች ህጻኑ የሟች ሼህ መሀመድ ሀሰን ልጅ ነው በማለት የወራሽነትና የሚስትነት ማስረጃ መውሰዲቸው አግባብ ያለመሆኑን ጠቅሰው በዚህ ረገድ በመ/ቁጥር 427/2000 በቀን 17/03/2000 ዓ/ም በወረዲው ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ እንዱሻርላቸው መሆኑን፣ ይህን ክስ ሲያቀርቡና ዲኝነት ሲጠየቁም አለኝ የሚለትን ማስረጃ ከመቁጠራቸውም በላይ የዱ.ኤን.ኤ ምርመራም ተደርጎ የልጁ አባትነታቸው እንዱረጋግጥላቸው መከራከራቸውን፣ አመልካች ህፃኑን ከተጠሪ እንዲልወለደት፣ የሕፃኑ ትክክለኛ አባትም ተጠሪ ሳይሆኑ ሟች መሐመድ ሀሰን መሆናቸውን ጠቅሰው የሚከራከሩ መሆኑን ነው።
እንዱሁም በሰ/መ/ በሆነው ይህ ሰበር ሰሚ ችልት ሚያዚያ 11 ቀን 2008 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ ይዘቱም አመልካች ከተጠሪ ጋር የእስልምና ሃይማኖት በሚያዘው አግባብ በኒካ መጋባታችን አልተረጋገጠም በማለት ያቀረቡት ክርክር የስር ፍርድ ቤቶች በሐይማኖቱ ስርዓት በፍሬ ነገር ደረጃ አጣርተው ውድቅ ያደረጉት በሐይማኖት ስርዓት ላይ የተመሰረተ በመሆኑ በሰበር ችልቱ ተቀባይነት እንዲላገኘ፣የሕፃን አቡበከር /ኢብራሑም/ አባትነት በተመለከተ የሟች ሃጅ መሐመድ ሀሰን ልጅና ወራሽ መሆኑን የሚያረጋግጥ አስቀድሞ የተሰጠው ማስረጃ በሕጉ አግባብ መቃወሚያ ቀርቦበት ሳይሰረዝ የተጠሪ ልጅ ነው በማለት መወሰኑ ስነ ስርዓታዊ አይደለም በማለት በዚህ ረገድ በክልለ ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት በፊ/መ/ በ21/07/2007 ዓ.ም ተሰጥቶ በአ.ብ.ክ.መ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ሰኔ 09 ቀን 2007 ዓ.ም የጸናው የውሳኔ ክፍል የተሻረ መሆኑን የሚያሳይ መሆኑን ተመልክተናል። ከዚህ አንጻር ሲታይ አመልካች ከተጠሪ ጋር ጋብቻ መስርተው የቆዩ መሆኑ በዚህ ሰበር ሰሚ ችልትም በመ/www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የመጨረሻ ፍርድ የተሰጠበት ጉዲይ ሲሆን አመልካች በዚህ መዝገብ ልጁ የተወለደው ከተጠሪ ሳይሆን ከሟች ሐጅ መሃመድ ሁሴን ነው በማለት ያቀረቡት ክርክር ስነ ስርዓታዊ በሆነ አግባብ በዚህ ሰበር ችልት ተቀባይነት ያገኘ ከመሆኑ ውጪ ጉዲዩ የመጨረሻ እልባት ያገኘ አይደለም። ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ በዚህ ረገድ የሰጠው ውሳኔ ህጻኑ የሟች ሃጅ መሐመድ ሁሴን ልጅና ወራሽ መሆኑን የሚያረጋግጥ አስቀድሞ የተሰጠው ማስረጃ በሕጉ አግባብ መቃወሚያ ቀርቦበት ሳይሰረዝ የተጠሪ ልጅ ነው በማለት መወሰኑ ስነ ስርዓታዊ አይደለም በማለት በዚህ ረገድ የተሰጠውን ውሳኔ ከመሻሩ ውጪ ተጠሪ በሕጉ አግባብ የሚያቀርቡትን መቃወሚያ ወይም ክርክር የገደበ አይደለም። በመሆኑም አመልካች በዚህ ረገድ ያቀረቡትን ክርክር ይህ ችልት በሰ/መ/ የሰጠውን ውሳኔ መሰረታዊ ይዘት፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 5 ድንጋጌ ሙለ ይዘትና ተጠሪ በሕጉ አግባብ ሉያቀርቡ የሚችለትን መቃወሚያ ክርክር ያላገናዘበ በመሆኑ አልተቀበልነውም። ላላው አመልካች አጥብቀው የሚከራከሩት ነጥብ የማስረጃ የማሰማት መብታቸው ያላግባብ ታልፎል የሚል ነው። ይሁን እንጂ አመልካች የሰው ምስክሮች እንዱያሰሙ መብታቸው የተጠበቀላቸው መሆኑን፣ ይህንኑ መብታቸውን ምስክር እስከመቀየር ድረስ ፍርድ ቤቱ ጠብቆላቸው ምስክሮችን እንዱያቀርቡ በተደጋጋሚ ታዘዘው በራሳቸው ጉድለት የተነሳ ሳያቀርቡ በመቅረታቸው የታለፈ መሆኑን የውሳኔው ግልባጭ የሚሳይ በመሆኑና አመልካችም ሕጋዊ ምክንያት ያላቸው ስለመሆኑ ያቀረቡት ማስረጃ ሳይኖር የስር ፍርድ ቤት በዚህ ረገድ ስህተት መፈፀሙን በመጥቀስ የሰበር ቅሬታ ማቅረባቸው ተቀባይነት የሚያገኝበትን የሕግ አግባብ አላገኘንም። በመሆኑም የማስረጃ ማሰማት መብት በሕጉ በተዘረጋው ስርዓት የሚከናወንና ይህንኑ በህጉ የተዘረጋውን ስርዓት መሰረት ተደርጎ የተከራካሪ ወገን መብት በፍርድ ቤት ሲጠበቅ ተከራካሪ ወገኑ ሕጋዊ ምክንያትና ማስረጃ በላለበት ሁኔታ በራሱ ጉድለት ማስረጃውን ሳያቀርብ የቀረ ተከራካሪ ወገን ማስረጃ የማሰማት መብት አልተጠበቀልኝም በማለት ቅሬታ የሚያቀርብበት የሕግ አግባብ የለም። በመሆኑም አመልካች በስር ፍርድ ቤት በተሰጣቸው በቂ ጊዜ ምስክሮቻቸውን ለማቅረብ ያልቻለት በራሳቸው ጉድለት ስለመሆኑ ተረጋግጦ የማስረጃ ማሰማት መብታቸው የታለፈ መሆኑን የክርክሩ ሂደት የሚያሳይ በመሆኑ በዚህ ረገድ ያቀረቡትን ቅሬታ ይህ ችልት ሉቀበል የሚችልበትን የሕግ አግባብ ሳላላገኘ አልፈነዋል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ወደ ዋናው ጉዲይ ስንመጣም አመልካች ከአብራካቸው የወለደት ህጸን ኢብራሑም/አቡበከር/ የተባለ ከሟች ሐጂ መሐመድ እንጂ ከአሁኑ ተጠሪ የወለድኩት አይደለም በማለት የሚከራከሩ ቢሆንም ተጠሪ በበኩላቸው አመልካች ጋር በፀና ጋብቻ ውስጥ ሁነው ህጻኑን የወለደ መሆኑን በመጥቀስ በሕጉ ግምት የሕጻኑ አባት እኔ ነኝ በማለት የሚከራከሩ መሆኑን፣ በአመልካችና በተጠሪ መካከል ከሕዲር 10 ቀን 1995 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 26 ቀን 1996 ዓ/ም ድረስ ጋብቻ የነበራቸው መሆኑን፣ በመ/ቁጥር 104/95 በሆነው አመልካች እስከ ሰኔ 18 ቀን 1995 ዓ/ም ድረስ ከሟች ሐጂ መሐመድ ሁሴን ጋር በጋብቻ ውስጥ የነበሩ መሆኑ መረጋገጡንና ህጻኑ ከሐጂ መሐመድ ሁሴን ሞት በኋላ አንድ አመት ቆይቶ ነሐሴ 25 ቀን 1996 ዓ/ም የተወለደ መሆኑን በፍሬ ነገር ደረጃ መረጋገጡን ተገንዝበናል። የበታች ፍርድ ቤት ህጻኑ የተጠሪ ልጅ ነው ወደሚለው ድምዲሜ የደረሱትም እነዚህን ፍሬ ነገሮችን መሰረት በማድረግና የደም ምርምራ አባት አለመሆኑን ለማረጋገጥ እንጂ አባትነትን ለማረጋገጥ በሕግ የተፈቀደ መንገድ አይደለም፣ በጋብቻ ውስጥ የተወለደ ልጅ አባት ነው ተብል የሚገመተው እናትዬውን ያስቀመጠው ባል ነው የሚለትን ምክንያቶችን በመያዝ መሆኑን ከውሳኔው ግልባጭ ተገንዝበናል።
በመሰረቱ የአንድ ሰው አባትነት የሚረጋገጥባቸው መንገድች በክልለ የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 79/1995 በአንቀጽ 136 ስር የተመለከቱ ሲሆን ከእነዚህም አንደ በፍርድ ቤት በሚሰጥ ውሳኔ አባትነት እንዱታወቅ ማድረግ መሆኑ በተጠቀሰው አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ (1) ስር ተመልክቷል። አባትነትን እንዱታወቅ ለማድረግ ከሚያስችለ ሁኔታዎች መካከልም አንደ በሕግ የታወቀ ግንኙነት መኖር መረጋገጡ እንደሆነ በቤተሰብ ሕጉ በአንቀጽ 137 ስር ተመልክቷል። የወረዲው ፍርድ በሰጠው ውሳኔ ላይ የአመልካቹን አባትነት በፍርድ ለማረጋገጥ መሰረት ያደረገውን የክልለን የቤተሰብ ሕግ ሲሆን ፍርድ ቤት በተጠሪው ምስክሮች በሰ/መ/ እንዱሁም በላልች የሰነድ ማስረጃዎች ከተረጋገጠው ፍሬ ነገር አንጻር የተጠሪ አባትነት በሕግ ግምት የሚወሰድበትና በዱ.ኤን.ኤ ምርመራም የሚስተባበልበት አግባብ የለም በሚል ምክንያት መሆኑን ከወረዲው ፍርድ ቤት የውሳኔ ግልባጭ ተገንዝበናል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
አመልካች የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው በማለት አጥብቀው ከሚከራከሩባቸው ነጥቦች መካከል አንደ እና ዋነኛው ህጻኑ ከሐጂ መሀመድ ሁሴን የተፀነሰ እና ከመወለደ ጊዜም ሆነ ከተፀነ በኋላ ከአመልካች ጋር በጋብቻ ተሳስረው በመኖር ላይ ያልነበሩ መሆኑን በመጥቀስ ነው። ይሁን እንጂ ክርክራቸውን በማስረጃ ያላስደገፈ ከመሆኑም በላይ ከተጠሪ ጋር የነበራቸውን የጋብቻ ግንኙነት ጊዜ ያላገናዘበ መሆኑን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።
በመሰረቱ በጋብቻ ውስጥ የተፀነሰ ወይም የተወለደ ልጅ አባቱ ነው የሚባለው ባልየው ስለመሆኑ በክልለ የቤተሰብ ሕግ በአንቀጽ 137 እና 138 ስር ተመልክቷል።
ህጻኑ የተፀነሰው ወይም የተወለደው አመልካች እንደሚከራከሩት ከላላ ሰው ጋር በጋብቻ ውስጥ ባለበት ጊዜ መሆኑ አልተረጋገጠም። ይልቁንም ከተጠሪ ጋር ጋብቻ ውስጥ የነበሩ መሆኑ በሚገባ የተረጋገጠ ጉዲይ ነው። አባትነትን በሕግ ግምት ወይም በመቀበል መንገድች ለመወሰን ክርክር ሲነሳ የባህሪ ወሳኝ ቅንጣት (DNA) ውጤት እንደ መከላከያ ማስረጃ እንዱቀርብ በሕጉ በግልጽ የተቀመጠ ድንጋጌ የላለ በመሆኑ ዲኝነት ሰጪ የሆነው ፍርድ ቤት በሕጉ የተረዘረጋውን ስርዓት ተከትልና ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ አስፈላጊ መሆኑን ሲያምንበት ተግባራዊ ሉያደርገው የሚችለው መሆኑን ከክልለ የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 79/95 አንቀፅ 183(1) እና 155(1(ሀ)) ድንጋጌዎች ይዘት የምንረዲው ጉዲይ ነው። ከዚህ አንጻር ስንመለከተው የዘር የባህሪ ወሳኝ ቅጣት (DNA) ምርመራ ውጤት በሕጉ በተመለከተው አግባብ በሕጋዊ ምክንያቶች ለማስረጃነት የሚቀርብ እንጂ በሕግ የተቀመጠውን ግምት እናት ስለካደች ብቻ ለማስረጃነት የሚቀርብ ማስረጃ ነው ብል ድምዲሜ የሚያዝበት አይደለም። በተያዘው ጉዲይ አመልካች የዘር የባህሪ ወሳኝ ቅጣት (DNA) ምርመራ ውጤት ለማስረጃነት እንዱቀርብ በስር ፍርድ ቤት ያልጠየቁ ከመሆኑም በላይ በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ ላይም ይህንኑ በቅሬታ ነጥብነት ጠቅሰው የጠየቁት ዲኝነት ካለመኖሩም በላይ ይህ ችልት ግራ ቀኙን በቃል ሲያነጋግራቸውም ተጠሪ ወጣ ገባ ይል ነበር የሚል ቃል ለችልቱ በማስታወቅ የምራመራ ሂደቱ እንዱከናወን ፍላጎት የላላቸው መሆኑን የገለፁ ሲሆን ተጠሪ ግን ፈቃደኝነታቸውን የገለፁ መሆኑ ችልቱ ተገንዝቧል። በዚህም ምክንያት የዘር የባህሪ ወሳኝ ቅጣት (DNA) ምርመራ ሳይደረግ በጉዲዩ ላይ ውሳኔ የመሰጠቱን ጉዲይ በተመለከተ አጣሪው ችልት በጭብጥነት የያዘው የክርክሩን ሂደትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ያላገናዘበ ከመሆኑም በላይ የህፃኑን በሕግ ግምት የተጠሪ ልጅ መሆኑን መሰረት ያላደረገ፣ በክልለ የቤተሰብ ህግም በአንቀፅ 181 እና 183(1) ድንጋጌዎች በተመለከተው አግባብ ምርመራው እንዱደረግ የሚያስገድደ ሕጋዊ ምክንያቶች ስለመኖራቸው ያለመረጋገጡን መሰረት ያላደረገ ሁኖ ተገኝቷል።
የስር ፍርድ ቤት አመልካች ከሟች ሐጂ መሀመድ ሁሴን ጋር እስከ ሰኔ 18 ቀን 1995 ዓ/ም ድረስ ጋብቻ ውስጥ እንደነበሩ ማስረጃ እንዲላቸው፣ ከተጠሪ ጋርም ከህዲር 10 ቀን 1995 ዓ/ም ጀምሮ ሕጋዊ ጋብቻ የነበራቸው መሆኑን የጊዜ መደራረብ መኖሩን ተገንዝቦ ሕጻኑ ከሟች ሐጂ መሀመድ ሁሴን ሉወለድ አይችልም ወደሚለው ድምዲሜ የደረሰው በሕጉ የተመለከተውን የእርግዝና ጊዜ መሰረት አድርጎ ስለመሆኑ ከውሳኔ ይዘት ተገንዝበናል። በእርግጥ የልጀ አባት ነህ ተብል በሕግ አባትነት የሚሰጠው ሰው ልጁ ከመወለደ በፉት በ300ኛውና በ180ኛው ቀናት መካከል ባለው ጊዜ ውስጥ ከልጁ እናት ጋር የሩካቤ ስጋ ግንኙነት ላለመፈፀሙ በማያጠራጥር ሁኔታ ያስረዲ እንደሆነ የተባለውን ልጅ ልጄ አይደለም ለማለት እንደሚቻል በክልለ የቤተሰብ ሕግ አንቀፅ 179 ስር የተመለከተ ሲሆን የተጠቃሹ ቤተሰብ ሕግ አንቀፅ 139 በአንጻሩ ጋብቻ ከተፈጸመ ከ180 በኋላ ወይም ጋብቻው ከፈረሰ በ300 ቀናት ውስጥ የተወለደ እንደሆነ ልጁ በጋብቻው ውስጥ እንደተፀነሰ ይቆጠራል በሚል በንኡስ ቁጥር አንድ ስር ከመንደንገጉም በላይ ለዚህ ተቃራኒ የሆነ የማስረጃ ተቀባይነት የላለው መሆኑን ጭምር አስገዲጅነት ባለው ሁኔታ በንዐስ ቁጥር ሁለት ስር በግልጽ አስፍሯል። ከዚህ አንጻር ሲታይ አመልካች ከሟች ሐጂ መሀመድ ሁሴን ጋር የነበራቸው ጋብቻ ሰኔ 18 ቀን 1995 በሞት ከፈረሰ በኋላ ህፃኑን ጋብቻው ከፈረሰ በ300ኛው ቀን ውስጥ የወለደት ሳይሆን ይህ በሕጉ የተመለከተው ጊዜ ከአለፈ በኋላ ነሐሴ 25 ቀን 1996 ዓ/ም የወለደ መሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ በተጠቃሹ የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 139(2) ድንጋጌ አግባብም ተቃራኒ ማስረጃ ለማቅረብ የሚችለበት የሕግ አግባብ የለም።
አመልካች የሕጻኑን ከተጠሪ መወለድ ክደው የሚከራከሩ መሆኑ ሲታይም የመካድ ክርክር እያቀረቡ ያለ መሆኑን የሚያስገነዝብ ሁኖ ከተጠሪ ጋር በጋብቻ ተሳስረው በነበሩበት ሁኔታ ልጁ የተጠሪ ልጅ አይደለም በማለት የሚያቀርቡት ተገቢነት የላለው መሆኑን ከክልለ የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 79/95 አንቀፅ 185(5) እና 190 ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ የምንረዲው ጉዲይ ሆኖ አግኝተናል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ሲጠቃለልም በእነዚህ ሁለ ምክንያቶች ተጠሪ ከአመልካች ጋር በጋብቻ ተሳስረው በነበሩበት ጊዜ ህፃን አቡበከር /እብራሑም/ ከአመልካች ወልደዋል ተብል የህጻኑ አባት ናቸው ተብል የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት የሚቻልበትን የሕግ አግባብ ስላላገኘን ተከታዩን ወስነናል።
በሐብሩ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/9 በ29/07/2009 ዓ/ም ተሰጥቶ በሰሜን ወል መስተዲድር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 2112 በ28/09/2009 ዓ/ም ፣ በአ.ብ.ክ.መ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ አጣሪ ችልት በሰ/መ/ቁ 03- 19077 ሐምል 24 ቀን 2009ዓ.ም የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።፡
የስር ፍርድ ቤቶች ሕፃን አቡበከር /ኢብራሑም/ የተጠሪ ልጅ ነው በማለት በሰጡት ውሳኔ የተፈፀመ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለም ብለናል።
በዚህ ፍ/ቤት ለተደረገው ክርክር ግራ ቀኙ ያወጡት ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡