የባልና ሚስት ፍቺ ተፈጽሞ የንብረት ክፍፍል እስከሚደረግ ድረስ በጋብቻ ውስጥ የተፈራ ንብረትም ሆነ ከዚህ ንብረት የሚገኝ ገቢ የጋራ ሆኖ የሚቆይ ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 89 www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. II
No summary available.
መስከረም 23 ቀን 2011 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውልስ አርሺሶ አመልካች፡- አቶ አህፈሮም ግርማይ -ቀረቡ።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ ሀበን ፍስሐዬ የቀረበ -የለም።
መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥል ያለው ፍርድ ተሰጥቷል።
የነገሩ አመጣጥ የባልና ሚስት ንብረት ክርክርን የሚመለከት ነው። ጉዲዩ የተጀመረው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምድብ ችልት ነው።
በአሁን አመልካች እና ተጠሪ መካከል ያለው ጋብቻ መፍረሱን ተከትል የአሁን ተጠሪ በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጽፈው ባቀረቡት የክስ አቤቱታ በአሁን ተጠሪ ስም ከተመዘገበው የአስመጪና ላኪ ንግድ በተገኘ ገቢ እንዱሁም በብድር በተገኘ ገንዘብ የተገዛ የሰላዲ ቀጥር ኮድ-2-21508 አ.አ የሆነው መኪና እንዱሁም ላልች ንብረቶችን በመጥቀስ ክፍፍል እንዱደረግ ዲኝነት ጠይቀዋል።
የአሁን አመልካችም በበኩላቸው በሰጡት መልስ ከንግድ የተገኘውን ገቢ በተመለከተ ለትራንስፖርት፣ ለግብር እና ለትዲር ጥቅም ወጪ ወጥቶ የሚተርፍ ነገር የለም።
ተሽከርካሪው እዲ ያለበት በመሆኑ እዲው ታሳቢ ተደርጎና አመልካች የከፈለት ግምት ውስጥ ገብቶ ክፍፍለ ቢደረግ ተቃውሞ የላላቸው መሆኑን ገልጸው ተከራክረዋል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ጉዲዩን የተመለከተው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምድብ ችልት ግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ እንዱሁም አግባብ ካላቸው አካላት መግለጫዎችን ጠይቆ ከመረመራቸው በኃላ ከአስመጪነትና ላኪነት ተገኘ ከተባለው ገቢ ለትዲር ጥቅም እና ለተለያዩ ጉዲዮች ያወጡዋቸው ወጪዎች ተቀናሽ ተደርገው ሉከፈለ የሚገባው ገቢ ምን ያህል እንደሆነ በግልጽ በአሁን ተጠሪ አቤቱታ ላይ ያልሰፈረ በመሆኑ ጥያቄው ታልፎል። በሰላዲ ቁጥር 2-21506 አዱስ አበባ ለሆነው መኪና በጋራ ከተከፈለው ብር 11,530.72 /አስራ አንድ ሺህ አምስት መቶ ሰላሳ ብር ከሰባ ሁለት ሳንቲም/ ውስጥ ብር 5,765.15 /አምስት ሺህ ሰባት መቶ ስልሳ አምስት ብር ከአስራ አምስት ሳንቲም/ የአሁን አመልካች ለአሁን ተጠሪ እንዱከፍለ ሲል ወስኗል።
በዚህ ውሳኔ ላይ ቅሬታ የተሰማቸው የአሁን ተጠሪ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበዋል። ቅሬታቸውም መሰረት ያደረገው ከአስመጪነት እና ላኪነት የተገኘው ገቢ በአግባቡ ተጣርቶ ድርሻዬ አልተወሰነልኝም፣ ተሸከርካሪውን በተመለከተ በትዲር ወቅት በጋራ በብድር የተገዛ ሲሆን የብድሩን አከፊፈል በትዲር ዘመናችን ጀምሮ የጋራ ንብረታችን ክፍፍል ሳናደርግ በቆየንባቸው ጊዜዎች ውስጥ ተከፍል ያለቀ በመሆኑ መኪናው የጋራ ተብል ሉወሰን ሲገባው የሥር ፍርድ ቤት የፍቺ ውሳኔ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ የተከፈለውን ክፍያ የአሁን አመልካች /የሥር መልስ ሰጭ/ ከግላቸው እንዱከፍለ ያለአግባብ ግምት በመውሰድ ቀደም ሲል ከተከፈለው ገንዘብ ግማሽ ለአሁን ተጠሪ /ለይግባኝ ባይ/ እንዱተካ በማለት መኪናውን ለአሁን አመልካች /ለመልስ ሰጭ/ እንዱሆን የሰጠው ውሳኔ ተገቢነት የላለው በመሆኑ ሉሻር ይገባል የሚል ነው።
የከፍተኛ ፍርድ ቤቱም የሥር ፍርድ ቤት ቅሬታ በቀረበባቸው ነጥቦች ላይ የሰጠው ውሳኔ በአግባቡ መሆን አለመሆኑን ለማጣራት ይግባኙ መልስ ሰጭን ያስቀርባል በማለት ክርክራቸውን የሰማ ሲሆን የአሁን አመልካች /መልስ ሰጭ/ ጋብቻ ከፈጸምንበት ጊዜ ጀምሮ የፍቺ ውሳኔ እስከተሰጠበት ድረስ የአስመጪና ላኪ ንግድ ተሰርቶ የተገኘው የተጣራ ገቢ ብር 197,453.77 /አንድ መቶ ዘጠና ሰባት ሺህ አራት መቶ ሃምሳ ሶስት ብር ከሰባ ሰባት ሳንቲም/ መሆኑን ከገቢዎች ከቀረበው ማስረጃ ማረጋገጥ የሚቻል ሲሆን ለትዲር እና ተያያዥ ወጪዎች ይኸው ገንዘብ ወጥቷል። በመሆኑምwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የአሁን ተጠሪ /ይግባኝ ባይ/ ያቀረቡት ቅሬታ ተቀባይነት የለውም። መኪናውን በተመለከተ የአሁን አመልካች /መልስ ሰጭ/ ከፍቺ በኃላ ከፍተኛውን እዲ የከፈልኩና በመኪናው ላይ እዲ የላለበት ስለሆነ የሥር ፍርድ ቤት ይህንኑ ግምት ውስጥ በማስገባት መኪናውን ለአሁን አመልካች/ ለመልስ ሰጭ/ ይገባል ማለቱ በአግባቡ ነው።
የአሁን ተጠሪ /ይግባኝ ባይ/ መኪናውን በጋራ ልካፈል ይገባል የሚለ ካሆነ ከፍቺ በኃላ በግል የከፈልኩትን ብር 237,497.16 / ሁለት መቶ ሰላሳ ሰባት ሺህ አራት መቶ ዘጠና ሰባት ብር ከአስራ ስድስት ሳንቲም/ ተመላሽ አድርገውልኝ መኪናው ተሸጦ ብንካፈል ተቃውሞ የለኝም በማለት ተከራክረዋል።
የይግባኝ ሰሚው ክፍተኛ ፍርድ ቤትም ግራ ቀኙ ያሰሙትን ክርክራቸውን ከመረመረ በኃላ ከአስመጪነትና ላኪነት ጋር የተያያዘውን ክርክር በተመለከተ በአግባቡ ሳይጣራ የተሰጠ ውሳኔ ስለሆነ በመልስ ሰጭ /በአሁን አመልካች/ ስም ተመዝግቦ ከሚገኘው የአስመጪና ላኪ ንግድ ተገኘ የተባለውን ገቢ በተመለከተ የተጣራ ገቢው ምን ያህል እንደሆነ ከተጣራው ገቢ ላይ የወጣ ወጪ መኖር አለመኖሩን፣ አለ ከተባለ መጠኑ ምን ያህል እንደሆነና ግራ ቀኙ ሉከፍለት የሚችለት ተራፉ ገንዘብ /ንብረት/ መኖር አለመኖሩን የግራ ቀኙ ቀኙን ክርክር፣ የተሰበሰበውን ማስረጃ እንዱሁም እንደ አግባብነቱ ላላ ተጨማሪ ማስረጃ በማስቀረብ ጭምር ተገቢ ነው ያለውን ውሳኔ እንዱወሰን ጉዲዩን በፍትሒብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 343 /1/ መሰረት መልሶታል። መኪናውን በተመለከተ ደግሞ መልስ ሰጭ /የአሁን አመልካች/ ከፍቺ በኃላ የመኪናውን የብድር እዲ የከፈለ ከመሆኑ ውጭ ይኸው የገንዘብ ምንጭ ከግራ ቀኙ የጋራ ሀብት ያልተገኘ ይልቁንም መልስ ሰጭ / የአሁን አመልካች/ በግላቸው ከላላ የገንዘብ ምንጭ በተገኘ ገቢ የተከፈለ መሆኑን በማንሳት ያቀረቡት ክርክርም ሆነ ማስረጃ የለም። መልስ ሰጭ /የአሁን አመልካች/ ከግል ገቢያቸው የከፈለ መሆኑን አላስረደም ከተባለ ደግሞ ለመኪናው መግዣ ግራ ቀኙ የተበደሩትን ገንዘብ በተመለከተ የተከፈለውንና ከግራ ቀኙ የጋራ ሀብት የተገኘ ነው ተብል ግምት የሚወሰድ በመሆኑ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው መኪና ግራ ቀኙ የጋራ ሀብት ነው ተብል ተወስኗል በማለት ውሳኔውን ደምድሟል።
ውሳኔውን በመቃወም የአሁን አመልካች ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበው በፍትሒብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 337 መሰረት ተዘግቶባቸዋል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ውሳኔዎቹን ለማስለወጥ ሲሆን አመልካች በጠበቃቸው በኩል በውሳኔዎቹ ላይ ተፈጽሞብኛል ያለዋቸውን ቅሬታ ነጥበችን ዘርዝረው አቅርበዋል።
የሰበር አቤቱታውን አጣሪው መርምሮ ክርክር የተነሳበት መኪና በብድር ገንዘብ የተገዛ መሆኑ ባልተካደበትና ተጠሪም እዲው የጋራ ሆኖ ንብረቱን በጋራ ለመካፈል እየጠየቁ እያለ እዲው የጋራ ሳይባል ንብረቱ ብቻ የጋራ ነው የመባለ አግባብነት መጣራት ያለበት መሆኑ ስለታመነበት ጉዲዩ ለሰበር ችልት ይቅረብ ሲል ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው በጠበቃቸው በኩል በ19/08/2010 ዓ/ም የተጻፈ ዝርዝር መልስ አቅርበው የተከራከሩ ሲሆን የአመልካች ጠበቃም ግንቦት 10 ቀን 2010 ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ አቅርበዋል።
የነገሩ አመጣጥና የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተመለከተውን የሚመስል ሲሆን መኪናው የጋራ ነው ተብል የተወሰነው እዲው ከባልና ሚስት ገቢ የተከፈለ በመሆኑ ነው ወይስ አይደለም? የሚል ጭብጥ ተይዞ ጉዲዩ እንደሚከተለው ተመርምሯል።
ለክርክሩ ምክንያት የሆነው መኪና አመልካችና ተጠሪ በትዲር ውስጥ አብረው እያለ በብድር በተወሰደ ገንዘብ የተገዛ መሆኑ ግራ ቀኙን አላከራከረም። ግራ ቀኙን እያከራከረ ያለው ከመኪናው እዲ አከፊፈል ጋር የተያያዘ ነው። የአሁን አመልካች መኪናውን ለመግዛት ከተወሰደው እዲ ከፍተኛው የተከፈለው የአመልካችና ተጠሪ ጋብቻ በፍቺ ከፈረሰ በኃላ በመሆኑ መኪናው ለአመልካች የግል ልባል ይገባል። የግል የማይባል ከሆነ ደግሞ ተጠሪ እዲውን ተጋርተው መኪናው የጋራ ላሆን ይችላል በማለት የሚከራከሩ ሲሆን ተጠሪ ደግሞ ፍቺ ከተፈጸመ በኃላ የንብረት ክፍፍል ሳይደረግ ባለበት ሁኔታ ከአስመጪነትና ላኪነት ከተገኘው ገቢ እዲው ተከፍል ያለቀ በመሆኑ ተጠሪ የሚጋሩት እዲ የለም፣ መኪናው የጋራ ነው በማለት ተከራክረዋል። ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን የሰላዲ ቁጥር ኮድ 2- 21508 አ.አ የሆነ ተሽከርካሪ በተመለከተ አበዲሪ /አዱስ ብድርና ቁጠባ ተቋም/ አመልካችና ተጠሪ ተለያይተው መኖር ከጀመሩበት ከጥር 13 ቀን 2006 ዓ/ም ጀምሮ ከጠቅላላ ብድር ምን ያህል እንደተከፈለ ተጠይቆ በቁጥር አ/ብ/ቁ/ተ/ ሚያዚያ 25 ቀን 2008 ዓ/ም በሰጠው ማስረጃ ከ13/05/2006 ዓ/ም በኃላ በጥቅለ ብር 238,469.29 /ሁለት መቶ ሰላሳ ስምንት ሺህ አራት መቶ ስልሳ ዘጠኝwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ብር ከሃያ ዘጠኝ ሳንቲም/ መከፈለን የገለጸ መሆኑን ተያይዞ ከቀረበልን የሥር ፍርድ ቤት የውሳኔ ግልባጭ ለመመልከት ተችሎል። ይህ የመኪና ብድር ገንዘብ የተከፈለው የንብረት ክፍፍል ውሳኔ ከመሰጠቱ አስቀድሞ ነው። በዚህ ጊዜ የአመልካችና የተጠሪ የንግድ ሥራ የሚሰራበት የአስመጪነትና ላኪነት የንግድ ሥራ እንቅስቃሴ በአሁን አመልካች አማካይነት ሲከናወን የነበረ መሆኑን አመልካች አይክደም። ይህ ከሆነ የከፍተኛ ፍርድ ቤት በውሳኔው ላይ እንዲስቀመጠውም እዲው የተከፈለው የባልና ሚስት የጋራ ከሆነው ከንግድ ሥራው ነው ተብል ግምት የሚወሰድ ነው። አመልካች እዲው የተከፈለው ከንግድ ሥራው አይደለም፣ ከግል ንብረቴ ወይም ገንዘብ ነው የሚል ክርክር አላቀረቡም። ከዚህ አንጻር አላስረደም። አንድ ተከራካሪ ወገን ስለሚከራከርበት ፍሬ ነገር የማስረዲት ግዳታ እንዲለበት የፍትሒብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 255 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ያስረዲለ። ከዚህ ጋረ በተያያዘ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ሰሚ ችልትም በሰበር መዝገብ ላይበፍትሐብሕር ክርክር አንድ መብት ወይም ግዳታ አለ ብል የሚከራከር ወገን መብቱ ወይም ግዳታው ስለመኖሩ የማስረዲት ሸክም ያለበት ስለመሆኑ አስገዲጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል። ይህም ትርጉም በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2/1/ መሰረት በየትኛውም ደረጃ በሚገኙት ፍርድ ቤቶች ላይ አስገዲጅነት እንዲለው በግልጽ ተደንግጎ እንመለከታለን። ስለሆነም አመልካች የመኪናው የብድር ገነዝብ ከፍቺ በኃላ የተከፈለ በመሆኑ ተጠሪ የተከፈለውን ገንዘብ እስካልተኩ ድረስ መኪናው የጋራ ላሆን አይገባም በማለት የሚከራከሩት ክርክር ከላይ በዝርዝር ከተመለከተው አንጻር ሲታይ ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም። የሰበር አጣሪውም እዲው በዚህ መልክ የተከፈለ መሆኑን ከሥር ፍርድ ቤት ክርክርና ይዘት በአግባቡ ሳይመለከት ከፍቺ በኃላ አመልካች የግል ገንዘብ እንደከፈለ አድርጎ ተጠሪ እዲውን ሳይከፍለ መኪናውን እንዱካፈለ መባለ ተገቢ እንዲልሆነ አድርጎ የያዘው ጭብጥ አግባብነት ያለው ሆኖ አልተገኘም።
ይህ በእንዱህ እንዲለ የባልና ሚስት ፍቺ ተፈጽሞ የንብረት ክፍፍል እስከሚደረግ ድረስ በጋብቻ ውስጥ ያፈሩት ንብረትም ሆነ ከዚህ ንብረት የሚገኝ ገቢ የጋራ ሆኖ እንደሚቆይ ከተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 89 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንረዲው ነው።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በልላ በኩል አመልካች ከአስመጪነትና ላኪነት ጋር በተያያዘ የተገኘውን ገቢ በተመለከተ ጉዲዩ ተጣርቶ እንዱወሰን ወደ ሥር ፍርድ ቤት መመለሱ አግባብ እንዲልሆነ በሰበር ቅሬታቸው ያነሱትን አጣሪው በጭብጥነት ያልያዘ ሲሆን ይህ ችልት ይህን ቅሬታ እንደተመለከተው ከሆነ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩ ተጣርቶ እንዱወሰን መመለሱ በአግባቡ ነው በሚል ታልፎል።
ሲጠቃለልም የክፍተኛ ፍርድ ቤቱ የሰጠው ውሳኔም ሆነ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የሰጠው ትዕዛዝ የሚነቀፍ ሆኖ ስላላገኘነው የተፈጸመ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የለም ብለን የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
146781 በቀን 30/02/2010 ዓ/ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍትሒብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 348 /1/ መሰረት ፀንቷል።
ክርክር ለተነሳበት መኪና የተወሰደ ብድር ገንዘብ ከአመልካችና ከተጠሪ ገቢ የተከፈለ በመሆኑ መኪናው የጋራ ነው ተብል የተወሰነው ውሳኔ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም ተብል ተወስኗል።
የዚህን ችልት ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
የውሳኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይድረሳቸው።
ጉዲዩ ውሳኔ ስላገኘ መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.