ከወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ጽ/ቤት ያላገባ የሚል ማስረጃ መውሰድ በራሱ በሁለት ሰዎች መካካል የነበረውን የትዲር ሁኔታ ግንኙነት መኖሩን የሚያረጋግጠውን ማስረጃ የሚያስተባብል ስላለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 94-97
No summary available.
ግንቦት 28 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውልስ ኦርሺሶ አመልካች፡- አቶ አለማየሁ ተድላ- የቀረበ የለም።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ ሜሮን ፊንታዬ -ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲይ የቀረበው አመልካች የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች ተከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል። የክሳቸው ይዘትም፡ከአመልካች ጋር ጥር 22 ቀን 2003 ዓ.ም በባህላዊ መንገድ ጋብቻ ፈጽመው አብረው የቆዩ መሆኑን አሁን ግን በመካከላቸው በተፈጠረው አለመግባባት በትዲር መቀጠል የማይችለበት ደረጃ ላይ ስለደረሱ ፍርድ ቤቱ የማሰላሰያ ጊዜ መስጠት ሳያስፈልጋቸው በመካከላቸው ያለው ጋብቻ ፈርሶ የፍቺ ውሳኔ እንዱወሰንላቸው አመልካች ላይ ክስ አቅርበዋል። አመልካችም ለቀረበው ክስ የሰጡት መልስ ተጠሪ ጋር የፈጸሙት ጋብቻ እንደላለ ነገር ግን ተጠሪ ጋብቻ ተፈጸመበት ባለበት እለት ለተጠሪ ቀለበት ሲያደርጉwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የተዘጋጀው ዝግጅት የቀለበት ስነስርዓት እና ወደፉት እንደሚጋቡ ቃልኪዲን የገቡበት የመተጫጨት ስርዓት አለመሆኑን እና ይህ እውነትም ተጠሪ በራሳቸው ጥቅምት 27 ቀን 2007 ዓ.ም በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የወሳኝ ኩነቶች ጽ/ቤት ቀርበው ያላገቡ መሆናቸውን ገልጸዋል፤ ይህም ማስረጃ አለማግባታቸውን የሚገልጽ በተጠሪ እጅ የሚገኝ ሲሆን በዚህ ማስረጃ የሚያረጋግጡ መሆኑን ላልች ማስረጃዎች የሚያሳዩት ከተጠሪ ጋር ያላቸውን ግንኙነት የመተጫጨት ግንኙነት መሆኑን ለመተጫጨት መፍረሱ ምክንያት ተጠሪ ስለሆኑ አግባብ ባለው ህግ መሰረት ለአመልካች ወጪና ኪሳራ ሉከፍለ ይገባል በማለት የመከላከያ መልሳቸውን አቅርበዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማና ማስረጃ ከመዘነ በኋላ በቀን 9/2/2009 ዓ.ም በዋለው ችልት በአመልካችና ተጠሪ መካከል የትዲር ሁኔታ መኖሩን ስለተረጋገጠ በሁለቱም መካከል ጋብቻ አለ ብል ከወሰነ በኋላ ለዚህ ውሳኔ መነሻ የሆነው የፍቺ ጥያቄ በተመለከተ የአሁን አመልካች ከጅምሩ ምንም ጋብቻ የለንም ብለው የሚከራከሩ በመሆኑ የፍቺ ጥያቄው ላይ አዱስ መልስ እንዱሰጡበት ቀጠሮ መስጠት ሳያስፈልግ እንዱሁም የማሰላሰያ ጊዜ መስጠት ሳያስፈልግ በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 82 መሰረት ጋብቻቸው በፍቺ እንዱፈርስ ሲል የሰጠው ውሳኔ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ግራ ቀኙ ክርክር ከሰማ በኋላ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ስህተት የለበትም በማለት በውሳኔ አጽንቶታል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበውም ይህንኑ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። አመልካች ሰኔ 13 ቀን 2009 ዓ.ም በፃፈት አቤቱታ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶችን ዘርዝረው አቅርበዋል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ በመደረጉ ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት በታዘዘው መሰረት ነሐሴ 23 ቀን 2009 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርበዋል። አመልካችም አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ በመስጠት ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለክርክሩwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ከተያዘው ጭብጥ አንፃር መርምረናል። በመሰረቱ ጋብቻ ስለመፈፀሙ በቀዲሚነት ላቀርብ የሚገባው የጋብቻ ምስክር ወረቀት ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 94 ድንጋጌ ሲያስቀምጥ ጋብቻ ስለመኖሩ ይኸው ማስረጃ ከላለ የጋብቻ ግንኙነት ስለመኖሩ በትዲር ሁኔታ ማረጋገጥ ስለመቻለም የተጠቀሰው ሕግ በአንቀጽ 95 ደንግጓል። ይህ የጋብቻ መኖር አለመኖርን በተመለከተ ላቀርብ የሚገባው የማስረጃ አይነትና ቅደም ተከተለ ነው። የትዲር ሁኔታ መኖር ማለት ምን ማለት እንደሆነም ሕጉ በአንቀጽ 96 ስር አስቀምጧል። በዚህም መሰረት የትዲር ሁኔታ ማለት አንድ ወንድና አንዱት ሴት የትዲር ሁኔታ አላቸው የሚባለት ራሣቸውን እንደባልና ሚስት የሚቆጥሩና የሚኖሩ ከመሆናቸውም በላይ ቤተዘመድቻቸውና ማህበረሰቡ እንደባልና ሚስት የሚቀበሎቸው ሁነው ሲገኙ መሆኑ ተደንግጓል። ይህንኑ በሕጉ የተመለከተውን ትርጓሜ ማስረዲት ከተቻለ ፍርድ ቤቱ ጋብቻ ተፈጽሟል ሲል የሕግ ግምት እንደሚወሰድ ተጠቃሹ ሕግ በአንቀጽ 97/1/ ስር በግልጽ አስቀምጧል።
ይህ የሕግ ግምት በማስረጃ መረጋገጥ በሚገባቸው ፍሬ ነገሮች ላይ የተመሰረተ ነው።
በዚህ አግባብ የተወሰደውን የሕግ ግምት ላላኛው ተከራካሪ ወገን ማፍረስ የሚችልበት አግባብም በዚሁ ሕግ በአንቀጽ 97/2/ ተመልክቷል።
የአሁን ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ያሰሟቸው ምስክሮች ጥር 22 ቀን 2003 ዓ.ም አመልካችና ተጠሪ በባህላዊ መንገድ ጋብቻ መፈጸማቸው፤ጋብቻው ከመፈጸሙ በፉት አመልካች በአካባቢው ባህልና ወግ መሰረት መስከረም 22 ቀን 2003 ዓ.ም የአገር ሽማግላዎችን ወደ ተጠሪ ቤተሰቦች በመላክ ሽማግላዎቹ ልጃችሁን ለልጃችን ስጡ በማለት ጥያቄ አቅርበው የተፈቀደላቸውና የሰርጉ ቀን የተወሰነ መሆኑ፤በሰርጉ ላይ ቀለበት የማድረግ ስነስርዓት ሲፈጸም አመልካች የዘላለም ሚስቴ ናት በማለት ቃልኪዲን ገብተው የተዘጋጀው ምሳ ከተበላ በኋላ አመልካች ወደ ተከራዩት ቤት መሄዲቸው ከዚያ ግዜ ጀምረው ከአሜሪካ ወደ አገር ቤት ሲመለሱም አብረው በዚሁ ቤት አንድ ላይ ይኖሩ እንደነበር በዝርዝር ያስረደ ስለመሆናቸው ፍሬ ጉዲዩን የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ስልጣን የተሰጣቸው የስር ፍርድ ቤቶች ያረጋገጡት ጉዲይ ነው። አመልካች አጥብቀው የሚከራከሩት ተጠሪ በቀን 27/02/2007 ዓ.ም ከወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ጽ/ቤት ያላገባ የሚል ማስረጃ መውሰዲቸው በራሱ በአመልካች እና ተጠሪ የጋብቻ ግንኙነት አለመኖሩን ያረጋግጣል የሚል ነው። ነገር ግን ከጥቅምት 27 ቀን 2007 ዓ.ም በፉት በአመልካችናwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በተጠሪ የነበረውን የትዲር ሁኔታ ግንኙነት መኖሩን በማስረጃ የተረጋገጠውን የሚያስተባብል አይደለም በማለት የስር ፍርድ ቤቶች የደረሱበት ድምዲሜ የሚነቀፍበት ህጋዊ ምክንያት አልተገኘም። በመሆኑም በዚህ ረገድ የአመልካች አቤቱታ ተቀባይነት የለውም።
ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሁኖ ስላልተገኘ ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 126385 ጥቅምት 9 ቀን 2009 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 185798 ግንቦት 17 ቀን 2009 ዓ.ም በውሳኔ ያጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.