No summary available.
የሰበር መዛገብ ግንቦት 30 ቀን 2011 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው በእውቀት በላይ እንዲሻው አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች፡- አቶ ቢቂላ አያኖ ተጠሪ፡- አቶ አሉቢ ቂላ መዛገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ ላቀርብ የቻለው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዛገብ ታህሳስ 11 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችልት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ በማፅናት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ሉታረምልኝ ይገባል በማለት አመልካች ታህሳስ 15 ቀን 2011 ዓ.ም የተፃፈ 02 ገጽ የሰበር አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
ጉዲዩ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተጀመረ ሲሆን አመልካች ከዘህ በፉት ፍርድ ቤቱ ችልታ የላቸውም በማለት የሰጠው ውሳኔ ስህተት መሆኑ በመግለፅ የተደረገላቸው የህግ ክልከላ እንዱነሳ ወሳኔ ለሰጠው ፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርበው፣ አቤቱታ ለማቅረብ ችልታ የላቸውም በሚል ምክንያት ተቀባይነት ማጣታቸው መነሻ በማድረግ አቤቱታ በማቅረባቸው ነው። ለክርክሩ መነሻ የሆነው ተጠሪ ለፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባቀረበው አቤቱታ ወላጅ አባቴ አቶ ቢቂላ አያኖ (የአሁኑ አመልካች) በጣም ያረጁ እና ጆሮአቸው የማይሰማ በመሆኑ ነገሮችን ማስተዋልና ማስታወስ ስለማይችለ የፍርድ ክልከላ ይሰጥልኝ በማለት ባቀረበው አቤቱታ መሰረት ፍርድ ቤቱ በመዛገብ ቁጥር 2600/07 ታህሳስ 28 ቀን 2007 ዓ/ም በዋለው ችልት የአሁኑ አመልካች በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 351 መሰረት የፍርድ ክልከላ ሰጥቷል። ይህንን ክልከላ ተከትል ተጠሪ በመዛገብ ቁጥር 2600/07 የአመልካች ሞግዘት እንዱሆን ሾሞታል።
አሁን የቀረበው አቤቱታ አመልካች የተደረገባቸው ፍርድ ክልከላ እንዱነሳ ፣ክልከላውን ለሰጠው ፍርድ ቤት በመዛገብ አቤቱታ አቅርበው ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤትም አመልካች የፍርድ ክልከላ ከተሰጠባቸው በኋላ ክስ ለማቅረብ ችልታ የላቸውም በማለት በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 33(1) እና ፍ/ብ/ሕ/ቁ 377 መሰረት ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ አድርጎታል። አመልካች በተሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኝ አቤቱታ ያቀረቡ ቢሆንም የአመልካች አቤቱታ ባለመቀበል ሰርዜታል። ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በሥር ፍርድ ቤቶች የተሰጠ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች በቀን 15/04/2011 ዓ/ም የተፃፈ 2 ገፅ አቤቱታ አቅርበዋል ። የአቤቱታው ይዖት ባጭሩ ፡-አመልካች የህግ ክልከላ የተሰጠብኝ መሆኑን መሰረት በማድረግ ክልከላው ይነሳልኝ በማለት ያቀረብኩት አቤቱታ ሆኖ እያለ ፍርድ ቤቱ ክልከላ ይነሳ በማለት አቤቱታ ማቅረብ የሚችለት በፍ/ሕግ ቁጥር 377 ላይ የተገለፁት ግለሰቦች ናቸው በማለት አቤቱታዬን ወድቅ አድርጎታል። ይሁን እንጂ ክልከላ የተደረገበት ሰው ክልከላው በመቃወም አቤቱታ ማቅረብ እንደሚችል በፍ/ሕግ ቁጥር 355 ላይ ተገልፆ እያለ የስር ፍርድ ቤቶች ግንኙነት በላለው የህግ ድንጋጌ መሰረት አቤቱታዬን ውድቅ በማድረግ መወሰናቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለሆነ ሉሻር ይገባል የሚል ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በሰበር ችልት ላታይ ይገባዋል በመባለ ተጠሪ ቀርበው የጽሁፍ ክርክራቸው ተለዋውጠዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዖት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙ ፅሐፍ ክርክር የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። ለክርክሩ መነሻ የሆነው የአሁኑ ተጠሪ አባት የሆኑት የአሁኑ አመልካች በጣም ያረጁ እና ጆሮአቸው የማይሰማ በመሆኑ ነገሮችን ማስተዋልና ማስታወስ ስለማይችለ የፍርድ ክልከላ ይሰጥልኝ በማለት ባቀረበው አቤቱታ መነሻነት ፍርድ ቤቱ በመዛገብ በቀን 28/04/2007 ዓ/ም በዋለው ችልት በአቶ ቢቂላ አያኖ ንብረት ላይ በፍ/ህግ ቁጥር 351(1) የፍርድ ክልከላ የሰጠ መሆኑ በውሳኔው ላይ አስፍሯል። ከዘህ በኋላ አመልካች የህግ ክልከላ የተሰጠብኝ ያለአግባብ ነው ችልታ አለኝ በማለት ክልከላው ይነሳልኝ አቤቱታ አቅርበው ፍርድ ቤቱ ክልከላ ይነሳ በማለት አቤቱታ ማቅረብ የሚችለት በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 377 ላይ የተገለፁት ግለሰቦች ናቸው በማለት ውሳኔ ሰጥቶ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ተቀባይነት አግኝቷል።
በመሰረቱ በህግ ችልታ ያለው ማንኛውም ሰው ክስ ማቅረብ እንደሚችል በፍ/ሥ/ስ/ሕግ ቁጥር 33(1) ተመልክቷል። የፍ/ህግ ዓንቀፅ 377 ስር እንደተመለከተው አእምሮው ከጎደለው ሰው በቀር ስለክልከላው ፍርድ እንዱሰጥ ለመጠየቅ የሚችለት ሰዎች በማንኛውም ጊዚ የክልከላው ውሳኔ እንዱቀር ለዳኞች ጥያቄ ለማቅረብ ይችላለ በማለት ተመልክቷል። ከዘሁ ድንጋጌ በመቀጠል ክልከላ እንዱወሰን ያደረጉት ምክንያቶች በቀሩ ጊዚና የተከለከለ ሰው ንብረቱን ለመምራትና ለማስተዲደር የሚችል የሆነ እንደሆነ ዳኞች የክልከላው ውሳኔ ማስቀረት (ማንሳት) እንዲለባቸው በፍ/ህግ ዓንቀፅ 378 ተደንግጓል ።በልላ በኩል በፍ/ሕግ ቁጥር 355 እንደተመለከተው አእምሮው ጎደል ወይም ድውይ የሆነው ሰው እራሱ ፣ከባልና ሚስት ደህነኛው ከስጋ ወይም ከጋብቻ ዖመድች አንደ ወይም ዓቃቤ ህግ ዳኞች ስለክልከላው በሰጡት ፍርድ ላይ አቤቱታ ማቅረብ እንደሚችለ ተመልክቷል።
No specific laws extracted.
No topics extracted.
ስለሆነም ከላይ ከተጠቀሱት የህግ ድንጋጌዎች ይዖትና መንፈስ መረዲት የሚቻለው በፍርድ ክልከላ የተደረገለት ሰው ንብረቱን ለመምራትና ለማስተዲደር የሚችል የሆነ እንደሆነ ክልከላው ቀሪ እንዱሆን መጠየቅ እንደሚችል ፍርድ ቤቶችም ይህንን ተከትለው ውሳኔ መስጠት እንዲለባቸው የተደነገገ በመሆኑ አመልካች በተደረገለት ክልከላ ምክንያት ላላ አዱስ ክስ ማቅረብ የማይችል ቢሆንም የተደረገለት ክልከላ እንዱነሳለት ግን ከላይ በተጠቀሰው ህግ መሰረት የሚፈቀድለት በመሆኑ የተደረገለት ክልከላ እንዱነሳለት ላቀረበው አቤቱታ ፍርድቤቱ አመልካች የክስ አቤቱታ ለማቅረብ ችልታ የላቸውም በማለት መዛገቡን መዖጋቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ውሳኔ በመሆኑ ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
በጉዲዩ ላይ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትበመ/ ሰኔ 06 ቀን 2010 ዓ/ም ተወስኖ ፣ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ታህሳስ 11 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችልት በትእዙዛ የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
በአመልካች ክልከላ እንዱነሳላቸው አቤቱታ ማቅረብ የሚችለ በመሆናቸው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተዖጋውን መዛገብ በማንቀሳቀስ በጉዲዩ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ ውሳኔ እንዱሰጥበት ተመልሶለታል ።ይፃፍ።
በዘህ ችልት ክርክር ለወጣው ወጭና ኪሳራ ግራ ቀኙ የራሳቸውን ይቻለ።
መዛገቡ ተዖግቷል፤ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
ሳ/ፀ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት።