No summary available.
ግንቦት 29 ቀን 2011 ዓ.ም ዳኞች፡- ተኽሉት ይመስል ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነአ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራው ፀሐይ መንክር አመልካች- የኢፋዳሪ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዲይ ሚኒስቴር - ነ/ፈጅ ሸዋቀረው አስፊው - ቀረቡ ተጠሪ- አቶ ሱልጣን ጃቢር መሀመድ - ቀረቡ መዛገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ በመቃወም ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁን ተጠሪ በአመልካች ላይ በፋዳራለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ ነው።
ተጠሪ ያቀረቡት ክስ ይዖት፡- በሥሜ የተመዖገበ ሱልጣን ጃቢር በውጭ ሀገር ሥራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ በአመልካች ፍቃድ ተሰጥቶኝ በዘሁ መሰረት የንግድ ፈቃድ አውጥቼ እና ለሥራውም ዋስትና የሚሆን በብልክ አካውንት በባንክ ብር 281,200.00 አስቀምጨ ሥሰራ ቆይቼ መንግስት በ2007 ዓ.ም ሥራው ለጊዚው እንዱቆም መመሪያ ሲያስተላልፍ ሥራው ቆሞ የነበረ ቢሆንም ፈቃደን ግን እያሳደስኩ ቆይቻለሁ፤ ሥራው በአዱስ መልክ ሲፈቀድ 100,000.00 ድላር (መቶ ሺህ ድላር) ያሥያዛኩ ሲሆን አስቀድሞ ያስያዛኩትን ገንዖብ አመልካች እንዱለቅልኝ የጠየቅሁ ቢሆንም ከድርጅቴ ጋር ግንኙነት የላለው አቶ በድሩ ከማል የተባለ ግለሰብ አቤቱታ ስላቀረበ አንለቅልህም ብሎል፤
ስለሆነም አመልካች የያዖብኝን ብር 281,200.00 (ሁለት መቶ ሰማንያ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ብር) እንዱለቅ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስ ተጠሪ ክስ ያቀረቡት በ 3 ግለሰቦች በተቋቋመ የግል ማህበር በመሆኑ በግላቸው ክሥ ማቅረብ አይችለም፤ ተጠሪ ቀደም ሲል ሱልጣን ጃቢር በውጭ ሀገር የግል ሥራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ሥም ዚጎችን ለሥራ ሲልክ የቆየ ሲሆን ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ የዘህን ኤጀንሲ ሥም በመለወጥ ተጠሪን ጨምሮ 3 ግለሰቦች ሆነው የአክሲዮን ድርሻ በመያዛ በሰነድች ማረጋገጫና ምዛገባ የተመዖገበ ሱልጣን ጃቢር በውጭ ሀገር ሥራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ኃ/የተ/የግል ማህበር አቋቁመው መተዲደሪያ ደንብና መመስረቻ ፅሁፍ ለአመልካች ያቀረቡ በመሆኑ ይህ ማህበር እያለ ተጠሪ በግላቸው በቀድሞው ኤጀንሲ ስም ያቀረቡት ክስ ተቀባይነት የለውም፤ ተጠሪ ለአመልካች መስሪያ ቤት ገንዖቡ እንዱመለስ ጥያቄ ሲያቀርቡ አስተዲደራዊ ውሳኔ ለመስጠት እንዱቻል ማብራሪያ እንዱሰጡ የተፈለጉ ቢሆንም ባለመቅረባቸው የሚወሰደው አስተዲደራዊ ውሳኔ ሳይነገራቸው ያቀረቡት ክስ አግባብነት የለውም፤ በአጠቃላይ የዋስትና ገንዖቡን በተመለከተ ህጋዊ ሰውነት ያለው ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሥለሆነ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩ በዘህ መልኩ የቀረበለት የሥር ፍርድ ቤት ክርክር የተነሳበት የዋስትና ገንዖብ በሱልጣን ጃቢር ሥራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሥም ገቢ የተደረገ ነው? ወይስ አይደለም?
ሉመለስ ይገባል? ወይስ አይገባም? የሚል ጭብጥ ይዜ ጉዲዩን በመመርመር ውሳኔ ሰጥቷል። በሰጠው ውሳኔ ተጠሪ ክፍያውን በግላቸው ገቢ ያደረጉት መሆኑን ስላስረደ በባንክ ገቢ ያደረጉትን ብር 281.200.00 (ሁለት መቶ ሰማንያ አንድ ሽህ ሁለት መቶ) አመልካች ከወጪና ኪሳራ ጋር እንዱለቅ (እንዱመልስ) በማለት ወስኗል። በዘህ ውሳኔ ላይ በአመልካች በኩል ይግባኙ የቀረበለት የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራቀኙን ክርክር ሰምቶ ውሳኔው ስህተት የለበትም በማለት አፅንቶታል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዘህ ነው። አመልካች የካቲት 18/2011 ዓ.ም ያቀረበው ማመልከቻ በአጣሪ ችልቱ ተመርምሮ ጉዲዩን ከኢትዮጵያ የውጪ ሀገር ስራ ስምሪት አዋጅ ቁጥር 923/2008 እና የውጪ ሀገር ስራ ሥምሪት አፈፃፀም መመሪያ አንጻር ለማጣራት ሲባል ለሰበር ችልት እንዱቀርብ እና ተጠሪም መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል። ተጠሪ በ26/07/2011 ዓ.ም በተፃፈ መልስ ውሳኔው ስህተት አልተፈፀመበትም ተብል እንዱፀና ጠይቋል። አመልካቹም የመልስ መልስ አቅርቧል። መዛገቡ ለምርመራ የተቀጠረውም በዘህ ሁኔታ ነው።
ከፍሲል ባጭሩ የገለጽነው የጉዲዩን አመጣጥ ሲሆን በበኩላችን ለሰበር ችልቱ የተያዖውን ጭብጥ ከግራ ቀኙ ክርክር፣ ቅሬታ ከቀረበበት ውሳኔና ተገቢነት ካላቸው የህጉ ድንጋጌዎች ጋር በማያያዛ መርምረናል።
እንደመረመርነው የውጪ ሀገር ስራ ስምሪት አዋጅ ቁጥር 923/2008 እና ይህን አዋጅ ለማስፈፀም የወጣው የውጪ ሀገር ስራ ሥምሪት አፈፃፀም መመሪያ ፈቃድ ስለመመለስና የዋስትና ገንዖብ ስለመልቀቅ ዛርዛር ድንጋጌዎችን ይዖዋል። በአዋጁ አንቀጽ 60(5) ሥር እንደተደነገገው ኤጀንሲው በማናቸውም ሁኔታ ሥራውን ሲያቆም ሚኒስቴሩ የዋስትናውን ገንዖብ የሚለቀው ከሰራተኛ መብትና ጥቅም ጋር የተያያዖ ጥያቄ ስልጣን በተሰጠው አካል በመታየት ላይ ካልሆነ እና በኤጀንሲው አማካኝነት ለስራ ወደ ውጪ አገር የተላኩ ሰራተኞች በሙለ የሥራ ውላቸው ከተቋረጠ ከ6 ወር በኃላ ነው። የመመሪያው አንቀጽ 23 የዋስትና ገንዖብ እንዱለቀቅ ጥያቄ ሲቀርብ መሟላት ስለሚኖርባቸው ሁኔታዎች ይዖረዛራል።
ከዘህም ላላ የአዋጁ አንቀጽ 78 የመሸጋገሪያ ድንጋጌዎችን የያዖ ሲሆን አስቀድሞ ሥራ ላይ በነበረው አዋጅ ቁጥር 632/2001 መሰረት ፈቃድ ተሰጥቷቸው የነበሩ ኤጀንሲዎች ስለሚኖርባቸው ኃላፉነት እና ፈቃደ ተሰርዜ ቢሆን እንኳ ኤጀንሲው ለሥራ ወደውጪ አገር የላካቸው ሰራተኞች ከሚያነሱት ማናቸውም የመብት ጥያቄ ነጸ እንደማይሆን ተመልክቷል።
ከፍሲል ከተጠቀሱት የህጉ ድንጋጌዎች መገንዖብ እንደሚቻለው የዋስትና ገንዖብ የሚያዖው በዋናነት ለሰራተኛው መብትና ደህንነት ዋስትና ማስከበሪያ እንዱውል ሲሆን ኤጀንሲው በሚኒስቴሩ የተሰጠውን ፈቃድ በመመለስ ለሥራ ወደ ውጪ አገር ለላካቸው ዚጎች መብትና ደህንነት ማስከበሪያ በባንክ ያስያዖው የዋስትና ገንዖብ እንዱለቀቅለት ጥያቄ ሲያቀርብ አሟልቶ ሉያቀርብ የሚገባቸው ሁኔታዎች በህጉ ተለይተው የተደነገጉ መሆናቸውን ነው።
በተያዖው ጉዲይ የሥር ፍርድ ቤት ክርክር የተነሳበት የዋስትና ገንዖብ አስቀድሞ በሱልጣን ጃቢር ሥራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ሥም ገቢ የተደረገ መሆን አለመሆኑን የሚመለከት ጭብጥ በመያዛ የወሰነ ቢሆንም በህጉ ከተቀመጡት ሁኔታዎች አንጻር ተገቢው ጭብጥ ተይዜ በዘሁ አንጻር ክርክርና ማስረጃው ታይቶ በአግባቡ ተገናዛቦ የተሰጠ ውሳኔ ባለመሆኑ ተቀባይነት የሚኖረው አይደለም።
ይልቁንም በህጉ አግባብ ዋስትና ያስያዖው ኤጀንሲ ፈቃደን መመለስ አለመመለሱ፤ አስቀድሞ የተሰጠ ፈቃድ ካልተመለሰ ፈቃድ ሳይመለስ የዋስትና ገንዖበ ሉመለስ የሚገባ ስለመሆን አለመሆኑ፤
እንዱሁም ኤጀንሲው ለሥራ ወደ ውጪ አገር ለላካቸው ዚጎች መብትና ደህንነት ማስከበሪያ በባንክ ያስያዖው የዋስትና ገንዖብ እንዱለቀቅለት ሉያሟላ የሚገባቸው ሁኔታዎች የተሟለ መሆን አለመሆኑ ሁለ ከክርክርና ማስረጃው አንጻር ታይቶና በአግባቡ ተገናዛቦ ውሳኔ ላሰጥበት ይገባ ነበር።
በአጠቃላይ ለጉዲዩ አወሳሰን ጠቃሚ የሆኑ ፍሬ ነገሮች ከህጉና ከማስረጃው አንፃር በአግባቡ እንዱጣሩ ሳይደረግ ተጠሪ ክፍያውን በግላቸው ገቢ ያደረጉት መሆኑን አስረድተዋል በሚል ምክንያት ብቻ ገቢ ያደረጉትን ብር 281.200.00 (ሁለት መቶ ሰማንያ አንድ ሽህ ሁለት መቶ) አመልካች ሉለቅ ይገባል በማለት በሥር ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ ስህተት የተፈጸመበት ነው ብለናል። ይግባኝ ሰሚው ችልትም ይህን ሳያርም ማለፈ የሚነቀፍ ነው። ስለሆነም ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ ሰኔ 29 ቀን 2010 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በ04/06/2011 ዓ.ም የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የፋዳራለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተዖጋውን መዛገብ በማንቀሳቀስ ዋስትና ያስያዖው ኤጀንሲ ፈቃደን መመለስ አለመመለሱን፤ አስቀድሞ የተሰጠው ፈቃድ ካልተመለሰ ፈቃድ ሳይመለስ የዋስትና ገንዖበ ሉመለስ የሚገባ ስለመሆን አለመሆኑ፤ እንዱሁም ኤጀንሲው ለሥራ ወደ ውጪ አገር ለላካቸው ዚጎች መብትና ደህንነት ማስከበሪያ በባንክ ያስያዖው የዋስትና ገንዖብ እንዱለቀቅለት ሉያሟላ የሚገባቸው ሁኔታዎች የተሟለ መሆን አለመሆኑን ሁለ በመመርመር ጉዲዩን በአግባቡ አጣርቶ ተገቢውን ውሳኔ እንዱሰጥ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343(1) መሰረት መልሰናል። የውሳኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዛገቡ ተዖግቷል ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.