No summary available.
የሰበር መዛገብ ጥር 3ዐቀን 2ዐ11 ዓ.ም ዳኞች፡- ተኽሉት ይመሰል ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራው ፀሐይ መንክር አመልካች፡- አቶ መረሳ ወ/ማርያም ቀረቡ:: ወ/ሮ አብረኸት ገ/ፃድቃን ወኪል ቀረቡ:: ተጠሪ፡- ቄስ ወ/ጊዩርጊስ ኪዲኔ ጠ/መኮንን አምቦ :: መዛገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር አቤቱታ ላቀርብ የቻለው አመልካቾች የአሁን ተጠሪ ላይ በትግራይ ክልል ማዔከላዊ ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት አክሱም ምድብ ችልት የሽያጭ ውልን መነሻ በማድረግ የቀ ረበው ክስ ወፍጮውን እና መሬቱ ከነግንብ አጥሩ ለተከሣሽ የሸጡ በመሆኑ መሬቱን ተከሣሽ ሉለቅ አይገባም ተብል መወሰኑና እስከ ክልለ ሰበር ሰሚ ችልት መጽናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ነው በሚል በሰበር ለማሳረም አቤቱታ በመቅረቡ ነው።
በስር ፍ/ቤት ቀርቦ የነበረው ክስ በአጭሩ የሚያሳየው በወረዲ ታች ማይጨው ማይበራዛዬ ቀበላ ዓዱ ንፊስ ጎጥ ልዩ ቦታ ዓውደ ኩሐ በተባለ የኢንቨስትመንት ቦታ አዋሣኙ በክሱ የተገለፀውን ቦታ የእህል ወፍጮ ከነሙለ መሳሪያው በብር 2ዐ,ዐዐዐ.ዐዐ/ሃያ ሺ / ከሣሾች ለተከሣሽ የሸጡላቸውና ገንዖቡንም መቀበላቸውን ሆኖም ግን የተሸጠውን ወፍጮ ከኢንቨስትመንት ቦታው ላይ ሉያነሱ በተደጋጋሚ ተከሣሽን ቢጠይቋቸው ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ቢሰጡም ሉያነሱ ስላልቻለ አንስተው ቦታውን እንዱለቁልን ይወሰንልን በማለት አመልካቾች ክስ አቅርበዋል።
ተከሣሽ/ተጠሪ / በሰጡት መልስ ወፍጮውን የገዙሁት ከነመሬቱ ነው ለአስተዲደሩም ይህንኑ ገልፀው በቀን 12/1/2ዐዐ7 ዓ.ም. በቁጥር 51/11 በክስ የተገለፀ 4ዐ በ3ዐ ካ/ሜ የመጠቀም መብት የይዜታ ማረጋገጫ ተሰጥቶኛል። ስለዘህ ህጋዊ ይዜታዬ ነው። መሬቱንም በብር 2ዐ,ዐዐዐ.ዐዐ ተብል ተገምቶ መቅረቡ መሬቱ በገንዖብ አይገመትም ህጋዊነትም የለውም የሚል መልስ በማቅረብ ክሱ ውድቅ እንዱሆንላቸው ጠይቀዋል።
ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ ምስክሮችን በመስማት ጉዲዩን መርምሮ ቤትና ቦታውን ከነወፍጮው የሸጡ መሆኑን ስለተረጋገጠ መሬቱን ተከሣሽ የሚለቁበት ምክንያት የለም በማለት መወሰኑን የውሣኔው ግልባጭ ያሳያል።
አመልካች ይግባኝ ብለው ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረቡ ቢሆንም ይግባኝ ቅሬታቸው ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱን ተመልክተናል።
አመልካቾች በስር ፍ/ቤቶች ውሣኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመ በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ ሲለ ግንቦት 27 ቀን 2ዐ1ዐ ዓ.ም. የተፃፈ 5 ገጽ አቤቱታ አቅርበዋል። ይዖቱም በአጭሩ፡ክርክር ያስነሳውን ይዜታ ስፊቱ 4ዐበ3ዐ የሆነውን ቦታ በሄክታር 125 ተለክቶ በብር 187.5 ሂሣብ በመክፈል ከ2ዐዐ2 – 2ዐ52 ዓ.ም. ድረስ የሚፈለገውን ፍርማሉቲ በማሟላት በቦታው ላይ 4 ክፍል ቤት ያረፈበትን በሉዛ አዋጅ መሰረት በኢንቨስትመንት ተረክበን በቁጥጥር ስር አድርገን እየተጠቀምንበት ነበር።
በይዜታው ላይ ብዘ መዋለ ንዋይ አፍሰን 6 ወፍጮ ተክለን በውክልና ለአሁን ተጠሪ እንዱያስተዲድሩ ጥቅማጥቅም እየሰጡን የሚፈለግ የመንግሥት ክፍያ እየከፈለ ለ2 ዓመት ቆይተዋል። ቦታውን እና በላዩ ላይ ያለ ንብረቶችን ተጠሪ እንድንሸጥላቸው ስለጠየቁን በብር 27ዐ,ዐዐዐ.ዐዐ የሸጥንላቸው መሆኑ በመግለጽ የጣቢያው ጽ/ቤት ለወረዲው ጽ/ቤት ድጋፍ እንዱሰጠን በማለት ጠይቀን የወረዲው አስተዲደር የገጠር የሉዛ መሬት አይሸጥም አይለወጥም በማለት ያገደት በመሆኑ በላዩ ላይ የሰፈረውን ወፍጮ ድንጋዩና ዔቃዎችን ከነመለዋወጫው በብር 2ዐ,ዐዐዐ.ዐዐ/ሃያ ሺ ብር/ ሸጠንላቸው እያለ ከ2 ዓመት በኋላ የወረዲውን አስተዲደር በማሳሳት በሉዛ የተረከብንበትን ቦታ ከግለሰቦች ጋር በመመሳጠር ይህን ቦታ ያለአግባብ ሉቀሙን ችለዋል።
የስር ፍ/ቤት በሽያጩ ውል ላይ የተመለከተው የወፍጮ ቤትና ዔቃዎች በብር 2ዐ,ዐዐዐ.ዐዐ/ሃያ ሺ ብር/ መሸጡን እየተመለከተና በሁለቱ ወገኖች ፊርማ የተፈረመ የሰነድ ማስረጃ አቅርበን እያለ የሰጠው ውሣኔ ስህተት ስለሆነ እንዱሻርልን እና የተፈፀመው የህግ ስህተት እንዱታረምልን የሚል ሰፉ አቤቱታ አቅርበዋል።
አቤቱታውን የመረመረው የሰበር አጣሪ ችልትም በግራ ቀኙ የተደረገው የወፍጮ ሽያጭ ውል የአመልካችን አጠቃላይ ይዜታ ስለማጠቃለል አለማጠቃለለ ግራ ቀኙ በተገኙበት ለማጣራት በሚል ጭብጥ በመያዘ መዛገቡ ለዘህ ችልት ላቀርብ ችሎል።
አቤቱታው ከማስቀረቢያ ነጥቡ ጋር ለተጠሪ እንዱደርሳቸውና መልሳቸውን እንዱያቀርቡ በተሰጠው ትዔዙዛ መሰረት ሰኔ 29 ቀን 2ዐ1ዐ ዓ.ም. የተፃፈ 5 ገጽ መልስ አቅርበዋል። ይዖቱም በስር ፍ/ቤት ውሣኔ ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለ በመሆኑ ውሣኔው እንዱፀናላቸው ጠይቀዋል።
አመልካችም የመልስ መልስ አቅርበው የጽሁፍ ክርክሩ በዘህ ተጠናቋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል እኛም አቤቱታውን መልሱን እና የመልስ መልሱን ከስር ፍ/ቤት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ መርምረናል።
እንደመረመርነውም አመልካች በስር ፍ/ቤት አቅርበውት የነበረው ክስ ወፍጮ ሸጨለት ወፍጮውን ሉያነሳልኝ አልቻለም በመሆኑም እንዱያነሳልኝ ይወሰንልኝ የሚል ነው። ተጠሪ በበኩላቸው ወፍጮውን የገዙሁት ከኢንቨስትመንት መሬቱ ጋር በመሆኑ ወፍጮውን ላነሳ አይገባኝም በማለት ተከራክረዋል።
ክርክር ያስነሳው ወፍጮ ያረፈበት መሬት አመልካች ለወፍጮ ሥራ አገልግልት በኢንቨስትመንት የመሬት ኪራይ ውል መሆኑም በግራ ቀኙን አላከራከረም። እያከራከረ ያለው ወፍጮው የተሸጠው መሬቱን ጨምሮ ነው ወይስ ወፍጮው ብቻ ነው የሚለው ሲሆን በግራ ቀኙ መካከል ሐምል 18 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም. የተፈረመው የሽያጭ ውል የእህል ወፍጮ ሽያጭ ውል መሆኑን ያሳያል።
ከዘህ የሽያጭ ውል መረዲት የሚቻለው አመልካች 5 ቋት የሚሰራ 1 ቋት የተበላሸ ወፍጮዎችን ለተጠሪ በብር 2ዐ,ዐዐዐ.ዐዐ/ሃያ ሺ ብር/ የሸጡ መሆኑን ነው። አመልካችም በዘህ ውል መሰረት ገንዖቡን መቀበላቸውን ገልፀው ተጠሪ ግን በሽያጭ ውለ መሰረት ወፍጮውን ከኢንቨስትመንት መሬቱ ላይ አላነሳልኝም የሚል ነው። ውለ በግልጽ የወፍጮ ቋት ሽያጭ የተፈፀመ መሆኑን የሚያሳይ ከሆነ ተጠሪ እንደሚለት ወፍጮው በመሸጡ የኢንቨስትመንት የኪራይ መሬቱን የተጠሪ ሉያደርግ ይችላል አይችልም የሚለውን መመልከት ተገቢ ነው።
በቅድሚያ ለወፍጮ ሥራ መሬት መከራየት በተሻሻለው ትግራይ ክልል የኢንቨስትመንት የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 239/2ዐዐ6 ውስጥ የሚካተት ነው ወይንስ አይደለም የሚለውን መመልከት ተገቢ ነው። በዘሁ መሰረት ከላይ በተገለፀው አዋጅ አንቀጽ 2 ‛ትርጓሜ“ በሚለው ስር ንዐስ አንቀጽ 9 ‛የእርሻ ኢንቨስትመንት“ ማለት በአዛርዔት መስኖ፣በእንሰሳት ሃብት ልማት፣ በተፈጥሮ ሀብት ልማት፣ በአግሮ ኢንደስትሪና በላልች ተዙማጅ የልማት ሥራዎች የሚካሄድ ኢንቨስትመንት ነው በማለት የደነገገ በመሆኑ ከአስተዲደሩ ጋር በገጠር ይዜታ መሬት ላይ በውል የተደረገው የወፍጮ ሥራ ኢንቨስትመንት በአዋጁ የሚፈቀድ መሆኑን መረዲት ችለናል።
በመሆኑም አመልካች የክልለ የኢንቨስትመንት አዋጅ በሚፈቅደው ሥራ ተሰማርተው እንዱሰሩ ክርክር ያስነሳውን መሬት ለ5 ዓመት የተከራዩ በመሆኑ ይህን የተከራዩትን የኢንቨስትመነት መሬት ማስተላለፍ ይችላለ? ወይስ አይችለም? የሚለውን በተመለከተ በአዋጅ አንቀጽ 24 ስር በተመለከተው መልኩ የገጠር መሬት የእርሻ ኢንቨስትመንትን መብት ከሚተላለፍበት ስርአት ውጭ ለ3ኛ ወገን ማስተላለፍ የተከለከለ ስለመሆኑ በአንቀጽ 22/5 ስር በግልጽ የተመለከተ ከመሆኑም ላላ በአንቀጽ 26/4 ስር ከሚመለከተው አካል እውቅና ውጭ የተከራየውን መሬት ወደ 3ኛ ወገን አስተላልፍ ሲገኝ የኪራይ ውለ የሚያቋርጥ ድርጊት መሆኑን ይደነግጋል። በመሆኑም ከላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች የምንረዲው የእርሻ የኢንቨስትመንት መሬትን በሚመለከተው አካል እውቅና በሕግ አግባብ መብት ከሚተላለፍበት ስርአት ውጭ በሽያጭ ለ3ኛ ወገን ማስተላለፍ የማይቻል መሆኑን ነው።
ግራ ቀኙ በክርክራቸው እያነሱ ያለትም መጀመሪያ ከነመሬቱ ወፍጮውን አመልካች ሉሸጡ ተጠሪ ሉገዘ የተስማሙ ቢሆንም አስተዲደሩ መሬት መሸጥ እንደማይቻል የገለፀላቸው በመሆኑ የወፍጮ ቋት ሽያጭ ውል የፈፀሙ ስለ መሆኑን አንስተዋል። ከዘህም መረዲት የምንችለው በኪራይ ለኢንቨስትመንት ሥራ የተገኘ መሬት መሸጥ የማይቻል መሆኑን ነው።
በመሆኑም በግራ ቀኙ መካከል የተፈረመው የወፍጮ ቋት ሽያጭ ሆኖ እያለ በውለ ያልተመለከተ እና በሕግም የእርሻ የኢንቨስትመንት መሬትን በሽያጭ ለ3ኛ ወገን ማስተላለፍ በግልጽ ክልከላ የተደረገበት መሆኑ ተደንግጎ እያለ እንዱሁም በግራ ቀኙ መካከል የተፈረመው የሽያጭ ውል የወፍጮ ቋት የሽያጭ ውል ስምምነት መሆኑን በግልጽ እያመለከተ የኢንቨስትመንት የኪራይ ውል የተደረገበትን መሬት ተጠሪ እንደገዘ በማድረግ የኪራዩን መሬት አይለቅም ተብል በስር ፍ/ቤት መወሰኑ እና በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት መጽናቱ ውለን እና የክልለን የመሬት አስተዲደር አጠቃቀም አዋጅን ያላገናዖበ እንዱሁም አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት ወደ 3ኛ ወገን የሚተላለፍበትን የህግ አግባብ ያልተከተለ ሆኖ በመገኘቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ በመገኘቱ ሉሻር ይገባል ብለን ተከታዩን ውሣኔ ሰጥተናል።
ውሣኔ
የትግራይ ክልል የማዔከላዊ ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት አክሱም ምድብ ችልት በመ/ቁ/ 23586 ጥር 23 ቀን 2ዐ1ዐ ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው ውሣኔ ፣ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ/ 1ዐ3245 ሚያዛያ ዐ5 ቀን 2ዐ1ዐ ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው ትዔዙዛ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ በመገኘቱ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ሐምል 18 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም. በተደረገ ውል አመልካች ለተጠሪ የሸጡት የእህል ወፍጮ እንጂ የኢንቨስትመንት መሬቱን አይደለም ብለናል።
በመሆኑም ተጠሪ በእህል ወፍጮ ሽያጭ ውለ መሰረት የገዘትን ወፍጮዎች አመልካች በኪራይ ውል ከያዘት ኢንቨስትመንት መሬት ላይ እንዱያነሱና መሬቱን ለአመልካች እንዱያስረክቡ ተወስኗል።
በዘህ ሰበር ችልት ግራ ቀኙ ላወጡት ወጪ የየራሳቸውን ይቻለ።
የውሣኔው ትክክል ግልባጭ ለስር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
መዛገቡ ውሣኔ ስላገኘ ተዖግቷል ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
ትዔዙዛ ውሣኔው ሲፃፍ ቆይቶ ዙሬ የካቲት 13 ቀን 2ዐ11 ዓ.ም. ተነቧል።
ሰ/ኃ የማይነበብ የ5 ዳኞች ፊርማ አለበት።
የሰ/መ/ ግንቦት 30 ቀን 2011 ዓ.ም.
ዳኞች- ተኽሉት ይመስል ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነአ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራው ፀሐይ መንክር አመልካች- የገቢዎች ሚኒስቴር ተጠሪ- አቶ አስራት አሰግድ መዛገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና ይግባኙ የቀረበለት የፋ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሳኔና ብይን የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አቤቱታ ስላቀረበ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው አመልካች በተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ነው።
የክሱ ይዖት፡- በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፕርት እና ልጀስቲክስ አገልግልት ድርጅት በቃሉቲ ወደብ ተርሚናል የመጋዖን ሰራተኛ ሆኜ ስሰራ በወ/ሮ ኤደን ወንዱፍራው ስም ከደባይ ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በቃሉቲ ጉምሩክ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት እንዱፈፀምባቸው ካስገቧቸው ዔቃዎች ውስጥ የኮንትሮባንድ ዔቃዎች በመያዙቸው ለገቢዎችና ጉሙሩክ ቃሉቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ30/12/2008 ዓ.ም ጥቆማ ሰጥቼ ብር 382,241.60 የሚያወጡ የኮንትሮባንድ ዔቃዎች በቁጥጥር ስር እንዱውለ አድርጌያለሁ፤ የተከሳሽ መ/ቤት ሥራ አስኪያጅ ሽልማት የሚገባኝ መሆኑን ገልጾ ፍርም እንድሞላ የተደረገ ሲሆን በዘሁ አግባብ በ29/03/2009 ዓ.ም ፍርም ሞልቼ የጠቋሚ መለያ ቁጥር AAKc/230/03/09 ተሰጥቶኛል፤
የምስጋና ደብዲቤም አግኝቻለሁ፤ ነገር ግን የጠቋሚውን ፍርም ከሞላሁ በኃላ በመመሪያ ቁጥር 78/2004 መሰረት 40% ወሮታ ክፍያ ብር 152,896.61 ተጠሪ እንዱከፍለኝ በተደጋጋሚ ጠይቄ ሉከፍለኝ ፈቃደኛ ስላልሆነ ይህን ገንዖብ እንዱከፍል ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
ተጠሪ ለክሱ በሰጠው መልስ በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 53 እና 132 መሰረት ራሱ በሚጠብቀው መጋዖን ውስጥ ዔቃ እንዲይወጣ መያዘ የሥራ ግዳታውን ተወጥቷል የሚያስብል እንጂ በመመሪያው መሰረት ወሮታ የሚያስከፍል ጥቆማ ሰጥቷል ስለማይባል ክሱ ውደቅ ይደረግልን፤
የጥቆማ ፍርሙ በ10 ቀን መሞላት ነበረበት ወይም ከአቅም በላይ ያልሞላ መሆኑን ቀርቦ ማስረዲት አለበት፤ የጥቆማ ክፍያ አያሰጥም እንጂ ይሰጣል ቢባል እንኳ የጥቆማ ፍርሙን በ10 ቀን ውስጥ ስላልሞላ እንዱሁም ከሳሽ ጥቆማ ባያደርግ ኖሮ ኃላፉነት አልተወጣም ተብል ተጠያቂ ይሆን ስለነበር ክፍያ ሉጠይቅ አይገባም በማለት ተከራክሯል።
ክሱ በሚሰማበት ጊዚ አመልካች ባይቀርብም ተጠሪ ቀርበው የአመልካች ሰራተኛና የመጋዖን ኃላፉ አለመሆናቸውን፤ አይደለም የመጋዖን ሰራተኛ የፀጥታ አስከባሪዎችም ወሮታ የሚከፈላቸው መሆኑን፤
እቃው ይለቀቅ ተብል የመልቀቂያ ቅጽ (release form) የተሞላለት ስለሆነ ጠቁመው ባያስይዘት ኖሮ ምንም ኃላፉነት እንደማይመጣባቸው፤ ጥቆማ የሰጡት በግንባር ቀርበው በመሆኑ በ10 ቀን ውስጥ ፍርም አልሞላም የሚለው ክርክር እንደማይመለከታቸው፤ ይመለከታቸዋል ቢባል እንኳ ዔቃው የተያዖባት ግለሰብ ጠፍታ እርሷ ባለችበት ዔቃውን ለማስፈተሽ ተብል በመጠባበቅ የቆየ በመሆኑ እንደ በቂ ምክንያት ሉወሰድ እንደሚገባ ተከራክረዋል።
ጉዲዩ በዘህ መልኩ የቀረበለት የሥር ፍርድ ቤት የአሁን አመልካች ለተጠሪ የወሮታ ክፍያ ለመክፈል ይገደዲል? ወይስ አይገደድም? የሚል ጭብጥ በመያዛ ክርክርና ማሰረጃውን መርምሮ ውሳኔ ሰጥቷል። በሰጠው ውሳኔ ተጠሪ የአመልካች ሰራተኛ ወይም፣ የህግ አስከባሪ አባል ባለመሆናቸው የሥራ ግዳታቸውን ተወጥተዋል ተብል የወሮታ ክፍያ አያገኙም የሚባልበት የህግ ምክንያት አልተገኘም፤ አመልካች ጠቅሶ የሚከራከረው የጉሙሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 56 እና 132 ድንጋጌዎችም ተጠሪ ግዳታቸውን ስለተወጡ ክፍያ አያገኙም የሚያስብለ አይደለም፤ በተለይም ተጠሪ ለግለሰቧ ዔቃዎቹ እንዱለቀቁላት የመልቀቂያ ፍርም (release form) ተሰጥቶ እንደነበር ተከራክረው በማስረጃም ያረጋገጡ ሲሆን አመልካች ይህን ክድ ስላልተከራከረም፤ በዘህ መልኩ እንዱለቀቅ የተፈቀደ ዔቃ ላይ ደግሞ በተጠሪ ላይ ኃላፉነት ያስከትል ነበር ማለት ስለማይቻል አመልካች የሚያቀርበው ክርክር ተቀባይነት የለውም፤ በ 10 ቀን ውስጥ የጥቆማ ፍርም አልሞለም የተባለውን በተመለከተም የቀረቡት ማስረጃዎች ተጠሪ በግንባር ጥቆማ ያቀረቡ መሆኑን የሚያስረደ በመሆኑ ተቀባይነት የላለው ሲሆን መሙላት ነበረባቸው ቢባል እንኳ ተጠሪ የጠቋሚ ቅፅ እንዱሞለ መደረጉና ቅጹ በአመልካች ኢንስፓክሽን ኦፉሰር ተረጋግጦ መፈረሙ ስለተረጋገጠ ተጠሪ እንደሚለት ቅፁን ሳይሞለ የቆዩት ዔቃዎቹ ሳይፈተሹ በመቆየታቸው በበቂ ምክንያት መሆኑን ያስረዲል ስለሆነም በዘህም ረገድ የቀረበው ክርክር ተቀባይነት የለውም። በአጠቃላይ ዲኝነት የተጠየቀበትን 40% የወሮታ ክፍያ ብር 152,896.65 አመልካች ለተጠሪ ሉከፍል ይገባል በማለት ወስኗል።
ይህን ውሳኔ በመቃወም አመልካች ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ ቅሬታውን ቢያቀርብም ውሳኔውን ሉያስነቅፍ የሚችል ምክንያት አልተገኘም ተብል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 337 መሰረት ይግባኙ ተሰርዝል።
የሰበር አቤቱታው ለዘህ ፍርድ ቤት የቀረበው በዘህ ነው። አመልካች ጥር 22 ቀን 2011 ዓ.ም ያቀረበው ማመልከቻ በአጣሪ ችልቱ ተመርምሮ ተጠሪ የወሮታ ክፍያ ተጠቃሚ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን አከራካሪ ነጥብ ለይቶ ለመወሰን የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ትርጉም አግባብነት ለማየት ሲባል መዛገቡ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ እና ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል። ተጠሪ በሰጡት መልስ የሥር ፍርድ ቤቶች ያሳለፈት ውሳኔ የህግ ስህተት አልተፈፀመበትም ተብል እንዱፀና የጠየቁ ሲሆን አመልካችም ክርክሩን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከፍሲል ባጭሩ የገለጽነው የጉዲዩን አመጣጥ ነው። በበኩላችን የግራ ቀኙን ክርክር ከተገቢው የህጉ ድንጋጌ ጋር በማያያዛ በሥር ፍርድ ቤቶች በተሰጠው ውሳኔ የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን መርምረናል።
እንደመረመርነው ተጠሪ የወሮታ ክፍያ ተጠቃሚ ሉሆኑ ይገባል? ወይስ አይገባም? የሚለውን ጭብጥ ለመወሰን ይቻል ዖንድ የህገ ወጥ ዔቃዎች መረጃ አሰጣጥ፣ አያያዛ እና ወሮታ ክፍያን ለመወሰን ተሻሽል የወጣውን መመሪያ ቁጥር 78/2004 ይዖት መመርመሩ ተገቢ ነው። በመመሪያው አንቀጽ 2(7) መሰረት ‛የወሮታ ክፍያ“ ማለት ለጠቆሙ ወይም ለያዘ ወይም ለተባበሩና ድጋፍ ለሰጡ ሰዎች የሚሰጥ ክፍያ ሲሆን የባለሥልጣኑን ሰራተኛ እና የህግ አስከባሪ አካል አባልን/ሰራተኛን እንደማይጨምር ተደንግጓል። ከዘህ ድንጋጌ መገንዖብ የሚቻለው ክፍያው የማይመለከታቸው የባለሥልጣኑን ሰራተኛ እና የህግ አስከባሪ አካል አባልን/ሰራተኛን መሆኑን መረዲት ይቻላል።
በተያዖው ጉዲይ ተጠሪ በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፕርት እና ልጀስቲክስ አገልግልት ድርጅት በቃሉቲ ወደብ ተርሚናል የመጋዖን ሰራተኛ መሆናቸውን ገልፀው የኮንትሮባንድ ዔቃዎች መኖራቸውን ተጠራጥረው ለገቢዎችና ጉሙሩክ በማሳወቅ ብር 382,241.60 የሚያወጡ የኮንትሮባንድ ዔቃዎች ስላስያዘ 40% ወሮታ ክፍያ ብር 152,896.61 እንዱከፈላቸው እንዱወሰን የጠየቁ ሲሆን አመልካች በበኩለ ተጠሪ ራሳቸው በሚጠብቁት መጋዖን የሚጠበቅባቸውን ኃላፉነት ተወጥተዋል ከሚባል በቀር በመመሪያው መሰረት ወሮታ የሚያስከፍል ሥራ ሰርተዋል ስለማይባል ክሱ ውደቅ እንዱደረግ ተከራክሯል።
የስር ፍርድ ቤት ጉዲዩን መርምሮ ተጠሪ የአመልካች ሰራተኛ ወይም፣ የህግ አስከባሪ አባል ባለመሆናቸው የሥራ ግዳታቸውን ተወጥተዋል ተብል የወሮታ ክፍያ አያገኙም የሚባልበት ምክንያት አለመኖሩን፤ አመልካች የሚከራከርበት የጉሙሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 56 እና 132 ድንጋጌዎችም ተጠሪ ግዳታቸውን ስለተወጡ ክፍያ አያገኙም የሚያስብለ አለመሆናቸውን፤ ዔቃዎቹ እንዱለቀቁም የመልቀቂያ ፍርም (release form) ተሰጥቶ እንደነበር በማረጋገጥ ዲኝነት የተጠየቀበትን 40% የወሮታ ክፍያ አመልካች እንዱከፍል ወስኗል። ይኸው መደምደሚያ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ተቀባይነት አግኝቷል።
የፋዳራለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና ይግባኝ ሰሚው የከፍተኛ ፍርድ ቤት ከፍሲል የተጠቀሰው መደምደሚያ እና ውሳኔ ላይ የደረሱት ፍሬ ነገር ለማጣራት እና ማስረጃ ለመመዖን በህግ በተሰጣቸው ሥልጣን መሰረት ነው።በኢፋዳሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 80(3)(ሀ) እና በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀፅ 10 ስር እንደተደነገገው የዘህ ሰበር ሰሚ ችልት ስልጣን በመጨረሻ በተላለፈው ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈፅሞ ሲገኝ ማረም እንጅ ፍሬ ነገርን መመርመር አይደለም።
ፍሬ ነገሩን ለማጣራት እና ማስረጃ ለመመዖን በህግ ስልጣኑ የተሰጣቸው የሥር ፍርድ ቤቶች በህጉ አግባብ ክርክሩን በመምራትና ማስረጃውን በመመዖን ከፍ ሲል የተመለከተው መደምደሚያ ላይ ደርሰዋል። የህገ ወጥ ዔቃዎች መረጃ አሰጣጥ፣ አያያዛ እና ወሮታ ክፍያን ለመወሰን ተሻሽል የወጣውን መመሪያ ቁጥር 78/2004 አንቀጽ 2(7) ለ‛የወሮታ ክፍያ“ ከሰጠው ትርጉም አንጻርም ተጠሪ ክፍያ ሉጠይቁ አይገባም የሚባል አይደለም። ስለሆነም በዘህ መልኩ ጉዲዩ ታይቶ አመልካች ለተጠሪው ወሮታ የመክፈል ኃላፉነት አለበት ተብል መወሰኑ ህጉን የተከተለ ነው ከሚባል በቀር የሚነቀፍ ሆኖ አላገኘነውም።
ነገር ግን የኃላፉነቱን መጠን በተመለከተ ተጠሪ የኮንትሮባንድ ዔቃውን ይዖው ለገቢዎችና ጉሙሩክ ቃሉቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሪፕርት ማድረጋቸውን ክርክሩ ስለሚያሳይ የወሮታ አበል ሉከፈላቸው የሚገባው የህገ ወጥ ዔቃዎች መረጃ አሰጣጥ፣ አያያዛ እና ወሮታ ክፍያን ለመወሰን ተሻሽል በወጣው መመሪያ ቁጥር 78/2004 አንቀፅ 19(ለ) መሰረት 10% ነው። ከዘህ አንፃር ውሳኔው ሉቃና የሚገባ ሆኖ አግኝተነዋል። ተከታዩንም ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ 6886 ግንቦት 6/2010 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የፋ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ በ02/05/2011 ዓ.ም ያሳለፈው ብይን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት በአብላጫ ድምፅ ተሻሽሎል።
አመልካች በተጠሪ ለተያዘት ብር 382,241.60 የሚያወጡ የኮንትሮባንድ ዔቃዎች የወሮታ ክፍያ በመመሪያ ቁጥር 78/2004 አንቀፅ 19(ለ) መሰረት የዔቃውን ዋጋ 10% ብር 38,224.16 (ሰላሳ ስምንት ሺህ ሁለት መቶ ሃያ አራት ብር ከ16/100) ከወጪና ኪሳራ ጋር አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍል ወስነናል።
በአጣሪ ችልቱ ጥር 23/2011 ዓ.ም አፈጻፀም እንዱታገድ የተሰጠው ትዔዙዛ ተነስቷል። ይህ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ መሰረት ይፈፀም ብለናል።
መዛገቡ ተዖግቷል ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
የማይነበብ የሶስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።
እኛ ስማችን በተራ ቁጥር ሶስት እና አምስት ላይ የተጠቀስን ዳኞች በዘህ ጉዲይ የአብላጫዉ ድምጽ ከሰጠዉ ዉሳኔ በሚከተለዉ ምክንያት ተለይተን የልዩነት ሀሳብ እናስቀምጣለን።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ የአሁን ተጠሪ በጉምሩክ አዋጅ እና መመሪያ መሰረት ለጠቋሚ የሚከፈለዉ የወሮታ ክፍያ እንዱከፈለዉ የጠየቀዉን ዲኝነት የሚመለከት ነዉ። የአሁን ተጠሪ ባቀረበዉ ክስ በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፕርትና ልጂስቲክስ አገልግልት ድርጅት በቃሉቲ ወደብ ተርሚናል የመጋዖን ሰራተኛ ሆኜ ስሰራ በወ/ሮ ኤደን ወንዱፍራዉ ስም ከደባይ ወደ ኢትዮጵያ ገብተዉ በቃሉቲ ጉምሩክ የጉምሩክ ስነሥርዓት እንዱፈጸምላቸዉ ካስገቧቸዉ ዔቃዎች ዉስጥ የኮንትሮባንድ ዔቃዎች በመያዙቸዉ ለገቢዎችና ጉምሩክ ቃሉቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጥቆማ አቅርቤ አስፈላጊዉን ፍርም የሞላሁኝ ቢሆንም የሕገወጥ ዔቃዎች መረጃ አሰጣጥ፣ አያያዛ፣ አመዖጋገብ እና የወሮታ ክፍያዎችን ለመወሰን ተሻሽል የወጣ መመሪያ ቁጥር 78/2004 መሰረት 40% የወሮታ ክፍያ እንዱከፈለዉ ዲኝነት ጠይቋል። የአሁን አመልካች ባቀረበዉ ክርክር ተጠሪ ራሱ በሚጠብቀዉ መጋዖን ዉስጥ የተጠቀሰዉ ዔቃ እንዲይወጣ ቁጥጥር ሥር እንዱዉል እና እንዱያዛ ማድረጉ የሥራ ግዳታዉን ተወጥቷል የሚያስብል እንጂ በመመሪያዉ መሰረት ለጠቋሚ የሚከፈለዉ ክፍያ የሚገባዉ አይደለም በማለት በዛርዛር ተከራክሯል።
የሥር ፍ/ቤቶች ግራ ቀኛቸዉን በማከራከር በሰጡት ዉሳኔ የአሁን ተጠሪ ያቀረበዉን የዲኝነት ጥያቄ በመቀበል በመመሪያዉ መሰረት 40% የወሮታ ክፍያ እንዱከፈለዉ ወስኗል። ይህ ሰበር ሰሚ ችልት የአብላጫዉ ድምጽ ደግሞ የሥር ዉሳኔ በማሻሻል 10% የወሮታ ክፍያ ለተጠሪ እንዱከፈለዉ ወስኗል።
በዘህ ምክንያት እኛ ስማችን ከፍ ሲል የተጠቀሰዉ ዳኞች ከአብላጫዉ ድምጽ በመለየት የሚከተለዉን የልዩነት ሀሳብ አስቀምጠናል።
በዘህ መሰረት መታየት ያለበት ጉዲይ ተጠሪ በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፕርትና ልጂስቲክስ አገልግልት ድርጅት በቃሉቲ ወደብ ተርሚናል የመጋዖን ሰራተኛ ሆኖ እያለ ከዘህ መጋዖን ገብቶ ሉወጣ ያለዉን ዔቃዎች ዉስጥ የኮንትሮባንድ ዔቃ መኖሩን ጠቁሞ በማስያዘ ምክንያት በመመሪያ ቁጥር 78/2004 አንቀጽ 19 መሰረት ለጠቋሚ የሚከፈለዉ ክፍያ ይገባዋል ወይስ አይገባዉም? የሚለዉ ነጥብ ነዉ።
እንደሚታወቀዉ በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 50 ዔቃዎችን ወደ ጉምሩክ ስለማስገባትን አስመልክቶ መደንገጉን መገንዖብ ይቻላል። በዘህ ድንጋጌ ንዐስ አንቀጽ 1 ሥር ‹‹የጉምሩክ ወደብ የደረሰ ማናቸዉም ዔቃ ወደ ጊዚያዊ የጉምሩክ ዔቃ ማከማቻ ወይም ቦንድድ የጉምሩክ መጋዖን መግባት አለበት›› በማለት ይደነግጋል። እንዱሁም የዘህ ድንጋጌ ንዐስ አንቀጽ 2 እንደሚደነግገዉ ‹‹ማናቸዉም ወደ ጊዚያዊ የጉምሩክ ዔቃ ማከማቻ የገባ ዔቃ ዛርዛር ሁኔታዉ እየተገለጸ በመጋዖኑ መዛገብ ላይ ይመዖገባል›› በማለት ተደንግጓል። ማናቸዉም ወደ ቦንድድ ጉምሩክ መጋዖን የሚገባ ዔቃ በመጋዖን ዱክሉራሲዮን ተመዛግቦ ለባለስልጣኑ መቅረብና መፈቀድ እንዲለበት በዘህ ድንጋጌ ንዐስ አንቀጽ 3 ሥር ተመልክቷል። በዘህ አግባብ ወደ ጉምሩክ መጋዖን የገባዉ ዔቃ በዘህ አዋጅ አንቀጽ 51 ሥር በተመለከተዉ የጊዚ ገደብ ዉስጥ አስፈላጊዉ የጉምሩክ ሥነሥርዓት ተከናዉኖበት ከማከማቻዉ መዉጣት እንዲለበት ተገልጾዋል። በዘህ አግባብ ወደ ጉምሩክ መጋዖን የገቡት ዔቃዎች ከመጋዖኑ የሚወጡበት ሁኔታ በአዋጁ አንቀጽ 52 መሰረት በጉምሩክ ሕጉ እና በዘህ ድንጋጌ ሥር ለተመለከቱት ዓላማዎች ሲባል ብቻ ተመዛግበዉ ከማከማቻዉ ወይም ከመጋዖኑ መዉጣት እንዲለባቸዉ ተጠቅሷል።
ከእነዘህ ሁኔታዎች መካከል አንደ ‹‹ዔቃዎቹ የሚፈለግባቸዉ ቀረጥና ታክስ ተከፍልባቸዉ ለአገር ዉስጥ ፍጆታ እንዱዉለ ሲለቀቁ›› መሆኑ ተመልክቷል። በዘህ መሰረት ወደ መጋዖን የገቡት ዔቃዎች በዱክላራሲዮኑ፤ በጭነት ማኒፋስት ወይም በትራንዘት ሰነድ ከተገለጸዉ መጠን በላይ በትርፍነት የተገኘ ዔቃ ዱክላራሲዮኑ ለቀረበለበት የባለስልጣኑ ቅርንጫፍ ወዱያዉኑ ሪፕርት መደረግ እንዲለበት እና በትርፍ ዔቃዉ ላይ ተገቢ ቀረጥና ታክስ እንዱከፈል መደረግ እንዲለበት በአዋጁ አንቀጽ 53 ሥር ተደንግጎ እናገኛለን። ወደ ጉምሩክ መጋዖን በገቡት ዔቃዎች ላይ ደግሞ የጉምሩክ ቁጥጥር መከናወን እንደሚገባ እና አስፈላጊዉ የጉምሩክ ሥነሥርዓት ተፈጽሞበት ከመጋዖኑ ሲለቀቅም መደረግ የሚገባቸዉን ተግባራት በዘህ አዋጅ አንቀጽ 56 ሥር ተጠቅሷል። ወደ ጉምሩክ መጋዖን የሚገባዉንና የሚወጣዉን ዔቃ በተመለከተ የጉምሩክ መጋዖን ሰራተኞች ዔቃዎቹን ባለስልጣኑ በሚያወጣዉ መመሪያ መሰረት የመመዛገብና በየጊዚ ሪፕርት ማድረግ ከተጣለባቸዉ የሥራ ግዳታዎች መካከል አንደ እንደሆነ በአዋጁ አንቀጽ 132 (2) ሥር ተመልክቷል።
በዘህ መሰረት አሁን ወደ ተያዖዉ ጉዲይ ስንመለስ በወ/ሮ ኤደን ወንድፍራዉ ስም ከደባይ አገር ወደ ኢትዮጵያ የገባዉ ዔቃ የአሁን ተጠሪ በሚሰራዉ የጉምሩክ መጋዖን ሲገባ እና ሲወጣ በአዋጁ አንቀጽ 50፣52፣ 53፣ 56 እና 132 (2) ሥር የተመለከተዉን አስፈላጊዉን የጉምሩክ ስነስርዓት እንደአስፈላጊነቱ መፈጸም ይገባዉ ነበር። በወ/ሮ ኤደን ስም የተመዖገበዉ ዔቃ ወደ መጋዖን ሲገባ በሕጉ በተመለከተዉ አግባብ ያልተመዖገበ እና ከመጋዖኑ ሲወጣም ደግሞ በትርፍነት የተገኙት ዔቃዎች ተገቢዉ ቀረጥና ታክስ ሳይከፈልባቸዉ ሉወጣ እንደነበር መገንዖብ ተችሎል። ይህ ማለት የአሁን ተጠሪ የሚሰራበት መጋዖን በሕጉ የተጣለበትን የሥራ ግዳታ ሳይወጣ መቅረቱን የሚያስገነዛብ ጉዲይ ነዉ።
ይህ ከሆነ ጉዲዩ የሚመለከታቸዉ የመጋዖኑ ሰራተኞች በሕግ የተጣለባቸዉን የሥራ ግዳታቸዉን ባለመወጣታቸዉ ተጠያቂነትን ሉያስከትልባቸዉ የሚገባዉ ጉዲይ ነበር። በዘህ አንጻር ሲታይ የአሁን ተጠሪ የሚሰራበት የጉምሩክ መጋዖን በሕግ የተጣለበትን ግዳታ ሳይወጣ በመቅረቱ ተጠሪ ደግሞ ይህን ሁኔታ በማወቁ ለሚመለከተዉ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ቃሉቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመጠቆም ማሳወቁ በመጋዖኑ በራሱ እና በላልች የመጋዖኑ ሰራተኞች ላይ የተጣለዉን የሥራ ግዳታን ተወጥቷል የሚያስብል ነዉ።
በዘህ መመሪያ አንቀጽ 4 መሰረት ‹‹በአገሪቱ የጉምሩክ ክልል በየትኛዉም ሥፍራ ሕገወጥ ዔቃ መኖሩን የሚያዉቅ ማንኛዉም ሰዉ ወዱያዉኑ በአቅራቢያዉ ለሚገኝ የባለስልጣኑ መስሪያ ቤት ወይም ሕግ አስከባሪ አካል ማሳወቅ አለበት›› በማለት ይደነግጋል። በዘህ አግባብ ጥቆማ ያደረገ ማንኛዉም ሰዉ ደግሞ በመመሪያ አንቀጽ 16 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት የወሮታ ክፍያ እንደሚፈጸምለት ተመልክቷል። በዘህ አግባብ አሁን የተያዖዉ ጉዲይ ሲታይ የአሁን ተጠሪን ጨምሮ ላልች የጉምሩክ መጋዖን ሰራተኞች የሚሰሩት ሰራተኞች በሕግ የተጣለባቸዉን የሥራ ግዳታ ባለመወጣታቸዉ በወ/ሮ ኤደን ስም ተመዛግቦ የገባዉ ዔቃ ዉስጥ በትርፍነት የተገኘዉ ተገቢዉን ቀረጥና ታክስ ሳይከፈልበት ሉወጣ ሲል ተጠሪ ደርሶበት ለሚመለከተዉ የጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመጠቆም ማሳወቁ ተጠሪ በእሱ እና በላልች የመጋዖኑ ሰራተኞች ላይ የተጣለዉን የሥራ ግዳታ ተወጥቷል ከሚባል በስተቀር በመመሪያ ቁጥር 78/2004 መሰረት ሕገወጥ ዔቃ በተመለከተ መረጃ በመስጠት በመጠቆም አስይዝል ተብል የወሮታ ክፍያ ይገባዋል የሚያስብል የህግ መሰረት የለም። በመሆኑም የአሁን ተጠሪ ያቀረበዉ የወሮታ ክፍያ ጥያቄ የህግ ድጋፍ የለዉም ብለናል።
ሲጠቃለል የሥር ፍ/ቤቶች በዘህ ጉዲይ በመመሪያ ቁጥር 78/2004 አንቀጽ 19 መሰረት ለተጠሪ የወሮታ ክፍያ ሉከፈለዉ ይገባል በማለት የሰጡት ዉሳኔ ከፍ ሲል በተጠቀሰዉ መሰረት የአዋጁንና የመመሪያዉን ዓላማና መንፈስ ያላገናዖበ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመባቸዉ ስለሆኑ መሻር ይገባቸዉ ነበር ብለን የአብላጫዉ ድምጽ ከሰጠዉ ዉሳኔ በመለየት የልዩነት ሀሳባችን አስቀምጠናል።
መዛገቡ ተዖግቷል።
የማይነበብ የሁለት ዳኞች ፊርማ አለበት ።
No topics extracted.