አንድ ወንጀል ክስ እንዱሻሻል ትእዙዛ የሚሰጠዉ በክስ ማመልከቻ ፍርም ወይም በክሱ ማመልከቻ ላይ ስለወንጀለ አስፈላጊ ዛርዛር ዉስጥ ስህተት ሲገኝ ወይም ሳይጠቀስ ሲቀርና ይህም መሰረታዊ ነገር ሆኖ ሲገኝ ስለመሆኑ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህግ አንቀጽ 111፣112፣118 እና 119/1/ 171521 የፋዳራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ እና ወ/ሮ ትርሃስ መስፍን ገ/እግዘአብሓር ታኅሳስ 23 ቀን 2012 ዓ/ም ልዩ ልዩ 77. የእርሻ የኢንቨስትመንት መሬት በሚመለከተው አካል እውቅና በሕግ አግባብ መብት ከሚተላለፍበት ስርአት ውጭ በኪራይ ለኢንቨስትመንት ሥራ የተገኘ መሬት በሽያጭ ለ3ኛ ወገን ማስተላለፍ የማይቻል ስለመሆኑ የተሻሻለው ትግራይ ክልል የኢንቨስትመንት የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 239/2ዐዐ6 አንቀጽ 2፣22/5/፤24፣26/4/
No summary available.
ታህሳስ 23 ቀን 2012 ዓ/ም ዳኞች ፤- እትመት አሰፊ ጳውልስ ኦርሺሶ ፀሐይ መንክር መላኩ ካሳዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- የፋዳራል ጠቅላይ ዓቃቤህግ - አቶ ብርሃኑ ታደለ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ ትርሃስ መስፍን ገ/እግዘአብሓር - የቀረበ የለም።
መዛገቡ ተመርምሮ ቀጥል ያለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ለዘህ የሰበር ክርክር መነሻው አመልካች በቁጥር 3-3367/1862/07 በ18/06/2011 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ችልት በኮ/መ/ቁ225717 በቀን 24/02/2009 ዓ.ም የሰጠው ብይን እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይህንኑ በማጽናት በኮ/መ/ቁ.
218556 ህዲር 13 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው በማለት በመጠየቁ ነው።
የነገሩ አመጣጥ የወንጀል ክስን የሚመለከት ነው።የአሁን አመልካች /የሥር ከሳሽ/ በቁጥር 2/515/1868/07 በ23/07/07 ዓ.ም ጽፍ ያቀረበው ክስ በ1996 የወጣውን የኢትዮጵያ ፋዳራላዊ ዱሞክራሲዊ ሪፐብላክ የወንጀል ህግ አንቀጽ 385 (1) (ለ) ሥር የተመለከተውን በመተላለፍ ተከሳሽ ተከሳለች የሚል ነው።የክሱ ዛርዛር፡- ተከሳሽ /የአሁን ተጠሪ/ ጥቅምን ወይም መሻሻልን ለማግኘት በማሰብ በልደታ ክፍለ ከተማ ቀበላ 12/45 ክልል ልዩ ቦታው የኢሚግሬሽን የዚግነት ጉዲይ ዋና መመሪያ ውስጥ በቀን 19/06/07 በግምት ከቀኑ 8.00 ሰዓት ሲሆን ተከሳሽ ዚግነቷ ኤርትራዊ ሆኖ እያለ በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ንፊስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዲ 12 የነዋሪዎች መታወቂያ በማውጣት ቁጥሩ EP 2378734 የሆነ የኢትዮጵያ ፒስፕርት በማውጣቷ ተከሳሽ የማይመለከታትን ትክክለኛ ሰነድ በመገልገል ወንጀል ተከሳለች የሚል ነው።
ተከሳሽ ቀርባ የእምነት ክህደት ቃል ከሰጠች በኋላ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ችልት በኮ/መ/ቁ.225717 በሆነው በቀን 24/02/2009 ዓ.ም በዋለው ችልት በሰጠው ብይን በቀን 4/11/2008 ዓ.ም በዋለው ችልት አቃቤ ህግ ያቀረበው ክስና ክርክር እና የተጠቀሰው ድንጋጌ የማይጣጣም በመሆኑ ክሱን አሻሸል እንዱያቀርብ ትዔዙዛ እንደተሰጠ፣ይሁን እንጂ ዐቃቤህግ በቀን 10/02/2009 ዓ.ም በተጻፈ መልስ ክሱ በአግባቡ የቀረበ፣የተከሳሽ ድርጊትም ሉወድቅበት በሚችል የወንጀል ህግ ድንጋጌ መሰረት የቀረበበ መሆኑ ክስ የሚሻሻልበት አግባብ የለም ማለቱን ገልጾ ዐቃቤህግ በፍርድ ቤቱ የተሰጠውን ትዔዙዛ ተገቢነት የለውም የሚል ከሆነ በይግባኝ የሚያስተካክል ከመሆን ባለፈ ትዔዙዛ አልፈጽምም መባለ ተገቢ ሆኖ አልተገኘም።ይህ ችልትም ቀደም ሲል በዘህ ፍርድ ቤት የተሰጠን የክስ ይሻሻል ትዔዙዛ የማንሳት ሥልጣን የላለው በመሆኑ እንደትዔዙዘ ዐቃቤህግ ክሱን ባለማሻሻለ መዛገቡ ሉዖጋ ይገባል ሲል ደምድሞታል።
በዘህ ብይን የአሁን አመልካች ቅር ተሰኝቶ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረበ ሲሆን ከፍተኛ ፍርድ ቤቱም የሥር ፍርድ ቤት ክስ እንዱሻሻል ያስተላለፈው ትዔዙዛ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነሥርዓት ህግ ቁጥር 119 (1) ክስ እንዱለወጥ ወይም እንዱጨመር ወይም አዱስ ክስ እንዱዖጋጅ ፍርድ ቤት ማዖዛ የሚችል መሆኑን ህጉ የሚፈቅድ በመሆኑ የሥር ፍርድ ቤት ይህን ትዔዙዛ ማዖዘ የሚነቀፍ ስላልሆነ የይግባኝ ቅሬታው መልስ ሰጪን አያሰቀርብም ሲል ወስኗል።
አመልካች የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችልት የሰጠው ብይን እንዱሁም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው በማለት በቁጥር 3-3367/1862/07 በቀን 18/06/2011 ዓ.ም የተጻፈ አቤቱታ አቅርቧል።የአቤቱታው ይዖትም በአጭሩ፡- የሥር ፍርድቤቶች ተጠሪዋ የውጭ ዚጋ ወይም ኤርትራዊ ሆና እያለ እና ለኢትዮጵያዊያን ብቻ የሚያገለግል የነዋሪዎች መታወቂያ ተጠቅማ ፒስፕርት አውጥተው ባለበት ሁኔታ አመልካች ይህን በሚያሳይ እንዱሁም የወንጀል ድንጋጌውን በሚገልጽ መልኩ ተጠሪ ለእርሷ አገልግልት የማይውል ነው ልባል አይገባም ወይም የክሱ ፍሬ ነገርና የወንጀል ድንጋጌው አይጣጣምም ተብል የተሰጠው ውሳኔ የወንጀል ህጉን አንቀጽ 385(1) (ለ) ሲተረጉሙ መሰረታዊ የህግ ስህተት መፈፀማቸውን ስለሚያሳይ እንዱታረምልን የሚል ነው።
የሰበር አቤቱታውን አጣሪው መርምሮ አመልካች በሥር ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ በመሰረተው የወንጀል ክስ ላይ የተመለከተው የወንጀል ህግ አንቀጽ እና ዛርዛሩ የማይመጣጠን በመሆኑ አመልካች ክሱን አሻሽል እንዱያቀርብ በሥር ፍርድ ቤት በሰጠው ትዔዙዛ መሰረት አመልካች ለማሻሻል ፈቃደኛ አልሆነም፤ቀደም ሲል ክስ እንዱሻሻል የተሰጠውን ትዔዙዛ ማንሳት አይቻልም በሚል የተዖጋበትን አግባብነት ከመሰረታዊ ክርክር አመራር ሥነ-ሥርዓት እና ከወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ ለመመርመር ለሰበር ያስቀርባል ሲል ትዔዙዛ ሰጥቷል።
ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላት ቀርባ ሐምል 9 ቀን 2011 ዓ.ም በሰጠችው መልስ የሥር ፍርድ ቤት የቀረበው ክስ ስህተት ያለበት ነው ብል ያመነ በመሆኑ ክስ እንዱሻሻል በሰጠው ትዔዙዛ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም በማለት ተከራክራለች።አመልካቹም በ24/11/2011 ዓ.ም የተጻፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
የነገሩ አመጣጥና የክርክሩ ሂደት ከላይ እንደተመለከተው ሲሆን በሥር ፍርድ ቤቶች ብይንም ሆነ ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል? ወይስ አልተፈጸመበትም? የሚል ጭብጥ ተይዜ ጉዲዩ እንደሚከተለው ተመርምሯል።የሥር ፍርድ ቤት የቀረበውን ክስ አመልካች እንዱያሻሽል በ4/11/2008 ዓ.ም ትዔዙዛ መስጠቱ፣ዐቃቤ ህግም በ10/02/2009 ዓ/ም በተጻፈ መልስ ክሱ የተከሳሽ /የተጠሪ./ ድርጊት ሉወድቅበት በሚችል የወንጀል ህግ ድንጋጌ መሰረት የቀረበበ መሆኑ ክስ የሚሻሻልበት አግባብ የለም ሲል መከራከሩ የተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች ናቸው።የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልዲታ ምድብ ችልት መዛገብ ለመዛጋት መሰረት ያደረገው ዐቃቤ ህግ ክስ እንዱያሻሽል የተሰጠውን ትዔዙዛ የሚቃወም ከሆነ በይግባኝ ከሚያሳርም ውጪ ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ትዔዙዛ ሉያነሳ ስለማይችል መዛገቡ ተዖግቷል የሚል ነው።የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ብይን በተመለከተ ለሁለት ከፍል ማየት ተገቢ ነው።የመጀመሪያው ፍርድ ቤቱ ክስ እንዱሻሻል የሰጠውን ትዔዙዛ እራሱ ማንሳት ይችላል? ወይስ አይችልም? የሚለው ነው።የወንጀል ክርክር የሚመራበት ሥርዓት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ህግ በዛርዛር ተደንግጎ እንመለከታለን።የወንጀልን ጉዲይ የሚመለከት ችልትም በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ህግ ላይ የተደነገጉትን ድንጋጌዎች ተከትል የቀረበለትን ጉዲይ ይመለከታል ክርክሩንም ይመራል፣ችልቱንም ይቆጣጠራል፣ክርክሩ ሲጠናቀቅ ወይም ጉዲዩ ሲበስል ፍርድ ይሰጣል።ክርክሩን ከሚመራባቸው ሥልቶች መካካል አንደ ጉዲዩን በሚያይበት ጊዚ አስፈላጊ ነው ብል ያመነውን ትዔዙዛ መስጠት ነው።በተያዖው ጉዲይ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችልት አመልካች ባቀረበው ክስ ላይ የተገለጸው ፍሬ ነገር ከተጠቀሰው የህግ ድንጋጌ ጋር የማይጣጣም ነው በማለት ክሱ እንዱሻሻል በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ህግ ቁጥር 119(1) መሰረት ትዔዙዛ ሰጥቷል።አመልካች ክስ እንዱያሻሽል ትዔዙዛ ሲሰጥ የቀረበው ክስ የሚሻሻልበት ምክንያት አይኖርም በማለት ክስ ለማሻሻል ፈቃደኛ ባለመሆኑ ፍርድ ቤቱ አስቀድሞ የሰጠውን ትዔዙዛ አላነሳም ማለቱ ስህተት አይደለም።በያዛነው ጉዲይ ትዔዙዛ የሰጠው ፍርድ ቤት እራሱ ትዔዙዘን ለማንሳት የማይችልበት አንደኛው ምክንያት ክስ እንዱሻሻል በራሱ በኩል አምኖ ትዔዙዛ የሰጠ በመሆኑ የሰጠውን ትዔዙዛ ማንሳት ተገቢ ሆኖ ስለማይታይ ነው። ሁለተኛው ምክንያት ትዔዙዛ የሰጠው ፍርድ ቤት እራሱ ተመልሶ ትዔዙዘን የሚያነሳ ከሆነ የክርክር አመራር ሥርዓትን ያልተከተለ ስለሚሆንና ተገልጋዩም በፍርድ ቤቱ ላይ ያለውን አመኔታ የሚቀንስ ወይም የሚሸረሽር በመሆኑ ነው።ሶስተኛው ምክንያት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ህግ ቁጥር 184 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ፍርድ ቤቱ ክስ እንዱሻሻል የሰጠው ትዔዙዛ ይግባኝ ልባል የሚችል በመሆኑ ነው።ይግባኝ ልባል የሚችልበትም ፍርድ ቤቱ የቀረበው ክስ መሻሻል አለበት ብል ያመነ በመሆኑ ባዖዖው ትዔዙዛ መሰረት ካልተሻሻለ በስተቀር ክርክሩን ስለማያካሂድ ነው።ከእነዘህ ምክንያቶች ተነስተን ስናይ የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ትዔዙዛ አላነሳም ማለቱ የሚነቀፍ ሆኖ አልተገኘም።
በልላ በኩል ሁለተኛው መሰረታዊ ነገር ፍርድ ቤቱ የቀረበው ክስ ላይ ያለው ፍሬ ነገር እና የተጠቀሰው የህግ ድንጋጌ አይጣጣምም በማለት አመልካች ክስ እንዱያሻሽል ትዔዙዛ መስጠቱ በክስ ላይ የተገለጸውን እና የተጠቀሰውን የህግ ድንጋጌንያገናዖበ ነው ወይ? የሚለው ላታይ የሚገባው ነው።
በመሰረቱ ፍርድ ቤት ክስ እንዱሻሻል ትእዙዛ የሚሰጠዉ በምን አግባብ ነዉ? ህጋዊ ውጤቱስ ምንድነዉ? የሚለው መታየት ያለበት ነው።የወንጀል ክስ ማመልከቻ አዖጋጃጀት አስመልክቶ ይዖቱና ዓይነቱ በምን አኳኋን እና ዛርዛር ሉኖረዉ እንደሚገባ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህግ አንቀጽ 111 እና 112 ላይ ተመልክቷል።ከነዘህ ድንጋጌዎች ይዖት መገንዖብ የሚቻለዉ ክሱ በዛርዛር እንዱገለጽ ከሚጠበቅባቸዉ መሰረታዊ ፍሬ ነገሮች ዉስጥ በክሱ የተጠቀሰዉ የወንጀል ህግ ድንጋጌ እና ተከሳሹ የፈጸመው የወንጀል ተግባር የክሱ ፍሬ ነገር ከህጉ አነጋገር ጋር በጣም የተቀራረበ መሆን እንዲለበት ነዉ።የክሱ አዖገጃጀትና ዛርዛር ይዖት ላይ መገለጽ የሚገባው መሰረታዊ ነገር ባለመገለጹ ተከሳሹን ያሳሳተው እንደሆነ ወይም ትክክለኛ ፍርድ ለመስጠት የማይቻል ከሆነ ደግሞ ፍርድ ቤቱ በራሱ አስተያየት ወይም ማመልከቻ በቀረቡለት ጊዚ እንደነገሩ ሁኔታ ክሱ እንዱለወጥ፣እንዱጨመር ወይም አዱስ ክስ እንዱዖጋጅ ትእዙዛ መስጠት እንደሚችል በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህግ አንቀጽ 118 እና 119/1/ ድንጋጌዎች ይዖት ያስገነዛባለ።ስለሆነም ክስ እንዱሻሻል ትእዙዛ የሚሰጠው በክስ ማመልከቻ ፍርም ወይም በክሱ ማመልከቻ ላይ ስለወንጀለ አስፈላጊ ዛርዛር ውስጥ ስህተት ሲገኝ ወይም ሳይጠቀስ ሲቀርና ይህም መሰረታዊ ነገር ሆኖ ሲገኝ እንደሆነ እንገነዖባለን።በዘህ ምክንያት ፍርድ ቤቱ ክስ እንዱሻሻል ትእዙዛ ሰጥቶ ዐቃቤ ህግ የተሻሻለ ክስ አዖጋጅቶ ያላቀረበ እንደሆነ ተከሳሽ ለጊዚዉ እንደሚለቀቅ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 122/3/ ድንጋጌ ይገልጻል።ስለሆነም በፍርድ ቤቱ ትእዙዛ መሰረት ክሱ ተሻሽል ያልቀረበ እንደሆነ ውጤቱ መዛገቡን ለጊዚው በመዛጋት ተከሳሹን መልቀቅ እንደሆነ ህጉ በግልጽ ደንግጓል።
የክስ ማመልከቻ እንዱሻሻል የሚደረገው ከላይ በተገለጸው አግባብ በክሱ ዛርዛር ላይ መገለጽ የሚገባው መሰረታዊ ጉዲይ ሳይገለጽ የቀረ እንደሆነ ወይም ደግሞ ያለአግባብ የተገለጸው ነገር ተከሳሹን የሚያሳስት ነው ተብል ሲታሰብ ነው።
በእጃችን ያለውን ጉዲይ ስንመለከት የዐቃቤ ህግ ክስ ተከሳሽ /የአሁን ተጠሪ/ ጥቅምን ወይም መሻሻልን ለማግኘት በማሰብ በልደታ ክፍለ ከተማ ቀበላ 12/45 ክልል ልዩ ቦታው የኢሚግሬሽን የዚግነት ጉዲይ ዋና መምሪያ ውስጥ በቀን 19/06/07 በግምት ከቀኑ 8.00 ሰዓት ሲሆን ተከሳሽ ዚግነቷ ኤርትራዊ ሆኖ እያለ በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ንፊስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዲ 12 የነዋሪዎች መታወቂያ በማውጣት ቁጥሩ EP 2378734 የሆነ የኢትዮጵያ ፒስፕርት በማውጣቷ ተከሳሽ የማይመለከታትን ትክክለኛ ሰነድ በመገልገል ወንጀል ህግ አንቀጽ 385(1) (ለ) ሥር የተደነገገውን በመተላለፍ ተከሳለች የሚል ነው።በዘህ ክስ ላይ የተገለጹት ፍሬ ነገሮች በወንጀል ህግ አንቀጽ 385(1) (ለ) ሥር ከተቀመጠው ጋር ይጣጣማለ? ወይስ አይጣጣሙም? የሚለውን መመልከት ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል።የወንጀል ህግ አንቀጽ 385 (1) (ለ) ወደ ሀሰት የተለወጠውን ወይም መስል የተሰራውን ሰነድ ወይም ለእርሱ አገልግልት ያልታሰበውን ወይም እርሱን የማይመለከተውን ትክክለኛ ሰነድ እያወቀ የተገለገለበት እንደሆነ በቀላል እሥራት ወይም በመቀጮ ይቀጣል ሲል ይደነግጋል።ቀጥል ያለው ፒራግራፍም /አንቀጽ/ ተጨማሪ ዛርዛር ነጥቦችንና ቅጣታቸውን ያስቀምጣል።በያዛነው ጉዲይ የአቃቤ ህግ ክስ ተጠሪ ኤርትራዊ ሆና እያለች በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ንፊስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዲ 12 የነዋሪዎች መታወቂያ በማውጣት ቁጥሩ EP 2378734 የሆነ የኢትዮጵያ ፒስፕርት በማውጣቷ የማይመለከታትን ትክክለኛ ሰነድ በመገልገል ተከሳለች የሚል ነው።ተጠሪ የኢትዮጵያን ፒስፕርት ለማውጣት የተጠቀመችው ከላይ የተጠቀሰው ክፍለ ከተማ የወረዲ 12 ነዋሪ እንደሆነች በማድረግ ያወጣችውን መታወቂያ ደብተር በመጠቀም ነው።ይህ ደግሞ በወንጀል ህግ አንቀጽ 385 (1) (ለ) ሥር ከተቀመጡት ነጥቦች መካከል "እርሱን የማይመለከተውን ትክክለኛ ሰነድ እያወቀ የተገለገለበት እንደሆነ" የሚለው ከአቃቤ ክስ ጋር የሚጣጣም ነው። በመሆኑም የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች /ዐቃቤ ህግ/ ባቀረበው ክስ ላይ የተገለጸው ፍሬ ነገር ከተጠቀሰው የህግ ድንጋጌ ጋር አይጣጣምም ሲል የደረሰው ድምዲሜ የተሳሳተ ነው።ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ይህንን ሳያርም ማለፈ ሲታይ የሚነቀፍ ሆኖ ተገኝቷል።
ሲጠቃለልም የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችልት ክስ እንዱሻሻል ሲል የሰጠው ትዔዙዛ በክሱ ላይ የተመለከቱትን ፍሬ ነገሮች እና የተጠቀሰውን የህግ ድንጋጌን በአግባቡ ያላጤነ ሆኖ በመገኘቱ እንዱሁም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ይህንን ሳያርም ማለፈ ሲታይ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።በመሆኑም ቀጥል ያለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
ፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ችልት በኮ/መ/ቁ. 225717 በቀን 24/02/2009 ዓ.ም አመልካች ክስ አላሻሽልም ብሎል በማለት መዛገቡ እንዱዖጋ ሲል የሰጠው ብይን እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትይህንኑ በማጽናት በኮ/መ/ቁ. 218556 ህዲር 13 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 195 (2 )(ሀ) መሰረት ተሰርዝል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችልት ክስ እንዱሻሻል ሲል የሰጠው ትዔዙዛ በክሱ ላይ የተመለከቱትን ፍሬ ነገሮች እና የተጠቀሰውን የህግ ድንጋጌን በአግባቡ ያላጤነ ሆኖ በመገኘቱ እና ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለትም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ይህንን ሳያርም ማለፈ ሲታይ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ተብል ተወስኗል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችልት ክስ እንዱሻሻል በ4/11/2008 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠሁትን ትዔዙዛ በራሴ አላነሳም ሲል የደረሰው ድምዲሜ ተገቢ ነው ብለናል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችልት የዖጋውን መዛገብ በማንቀሳቀስ ክርክሩን ሰምቶ ተገቢውን ውሳኔ እንዱሰጥበት በማለት በወንጀለኛመ ቅጫ ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 195 (2) (ሀ) መሰረት ጉዲዩን መልሰንለታል።ይጻፍ።
መዛገቡ ተዖግቷል ይመለስ ።
No topics extracted.