በሙስና ወንጀልች አዋጅ መሰረት በተመሰረት ክስ ተከሳሹ እንዱከላከል ብይን ተሰጥቶ ይህ ብይን የተሰጠበት ድንጋጌ አማራጭ ቅጣትን ያስቀመጠ ሆኖ በተሻሻለው የፀረ-ሙስና ልዩ የስነ ስርአትና የማስረጃ ህግ (ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 3/1 ሁለተኛ ሀሳብ ላይ ከአራት አመት በላይ በሚል የተደነገገውን የፋዳራል ጠቅላይ ዐ/ህግ እና ብርጋዳር ጀነራል ሐድጉ ገ/ጊዮርጊስ እንደ መነሻ ቅጣት በመውሰድ የቅጣት መነሻቸው አራት ዓመት የሆነ በጽኑ እሥራት የሚያስቀጡ ወንጀልችን የሚመለከት እንደሆነ አድርጎ በመውሰድ ዋስትናን መፍቀድ ተቀባይነት የላለው ስለመሆኑ የተሻሻለው የጸረ-ሙስና ልዩ የሥነ-ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 4/1/ ተከሳሹ በፈፀመው የወንጀል ድርጊት ምክንያት የደረሰው የጉዲት መጠንን በተመለከተ አቃቤ ህግ ክስ በመሰረተበት የህግ አንቀጽ በተከሳሹ የወንጀል ድርጊት ምክንያት የደረሰውን የጉዲት መጠን አለመግለጹ ተከሳሽ በዋስትና ቢለቀቅ ዋስትናውን አክብሮ ላቀርብ አይችልም የሚል ግምት በመውሰድ የዋስትና መብትን የማያስከለክል ስለመሆኑ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 67
No summary available.
የሰ/መ/ ታሕሳስ 24 ቀን 2012 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ጳውልስ ኦርሺሶ ፀሐይ መንክር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- የፋዳራል ጠቅላይ ዐ/ህግ ተጠሪ፡- ብርጋዳር ጀነራል ሐድጉ ገ/ጊዮርጊስ መዛገቡ የተቀጠረው መርምሮ ፍርድ ለመስጠት ነው። በመሆኑም መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የዋስትና ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በወ/ይ/መ/ ላይ ሐምል 30/2011 ዓ.ም በዋለው ችልት ተጠሪ እንዱከላከለ ብይን የተሰጠባቸው ሁለቱም ድንጋጌዎች የዋስትና መብት የማያስከለክለ በመሆኑ በዋስ ሆነው ጉዲያቸውን እንዱከታተለ ሲል የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ነው።
ጉዲዩ የተጀመረው የአሁን አመልካች በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሁን ተጠሪን ጨምሮ በአራት ግለሰቦች ላይ አዋጅ ቁጥር 881/2007 በመጥቀስ ባቀረበው የሙስና ወንጀል ክስ ነው። ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር እና የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን ከሰማ በኋላ ሰኔ 07 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችልት የአሁን ተጠሪን በተመለከተ ክስ የቀረበበትን የአዋጁን አንቀፅ 9/1/ሀ/ለ/2/ ድንጋጌን በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 113/2/ መሰረት ወደ አንቀፅ 9/1/ሀ/ለ በመቀየር እንዱከላከለ ብይን ሰጥቷል።
ይህንኑ ብይን ተከትል ተጠሪ ባቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ላይ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ተጠሪ በሁለት ክሶች እንዱከላከለ የተባለ መሆኑን እና የሁለቱ ክሶች ቅጣት ሲደመር ከ10 ዓመት በላይ መሆኑን በመግለፅ የዋስትና ጥያቄውን በአዋጅ ቁጥር 434/1997 አንቀፅ 4 መሰረት ውድቅ አድርጓል።
ተጠሪ የዋስትና ጥያቄውን በሚመለከት በስር ፍ/ቤት የተሰጠውን ብይን በመቃወም ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታ አቅርበዋል። ከዋስትና አንፃር የተሰጠውን ብይን በይግባኝ የተመለከተው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትም ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ በአዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 3/1 ከአራት ዓመት በላይ እና ከአስር ዓመት በታች የሚያስቀጡ ተደራራቢ ወንጀልች ሲኖሩ እየተደመሩ ከ10 ዓመት በላይ የሚያስቀጣ ከሆነ ዋስትና ይከለክላል የሚለው የሕግ አገላለጽ በግልጽ እንደሚያሳየው ከአራት ዓመት በላይ የሚለው አገላለጽ መነሻ ቅጣቱ አራት ዓመት እና በላይ የሆነ ድንጋጌን የሚመለከት እንደሆነ የሚያሻማ አይደለም፤ ተደራራቢ ወንጀልች እየተደመሩ ከ10 ዓመት በላይ በሆነ ጊዚ ዋስትና ሉያስከለክል እንደሚገባ የድንጋጌው ሀሳብ ቢሆን ኖሮ ከአራት ዓመት በላይ የሚለው አገላለጽ ባላስፈለገ ነበር፤ ይህ ከሆነ ደግሞ የዘህ ድንጋጌ ዓላማ ከአራት ዓመት በላይ የሚያስቀጣ ተደራራቢ ወንጀልን የሚመለከት እንጂ ተጠሪ እንዱከላከል ብይን የተሰጠበት አንቀጽ 9/1/ሀ/ለ መነሻ ቅጣቱ አንድ ዓመት ቀላል እሥራት ወይም አንድ ዓመት ጽኑ እሥራት የሚለውን የሚጨምር ነው በሚል የሚተረጎም አይደለም፤ በይግባኝ ባይ ላይ የተለየ ከወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 67 አኳያ የዋስትና መብቱን የሚያስከለክል ምክንያት ባልቀረበበት ሁኔታ ተደራራቢ ወንጀልች ተደምረው ከ10 ዓመት በላይ ሉያስቀጣ የሚችል ነው በማለት የዋስትና መብት መከልከለ የአዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 2 ንኡስ ቁጥር 3/1 ድንጋጌን የሚቃረን ነው በማለት ተጠሪ ለብር 100,000 የሚበቃ ዋስ ሲያቀርቡ ከእስር እንዱፈቱ ሲል ወስኗል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም መሰረታዊ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል ሲሆን ይዖቱም፡- የተሻሻለው የፀረ-ሙስና ልዩ የሥነ ሥርዓትና ማስረጃ አዋጅ ቁጥር 434/1997 አንቀፅ 4/1 / በአዋጅ ቁጥር 882/2007 እንደተሻሻለው / የድንጋጌው ይዖት ሉተረጎም የሚገባው ከ4 ዓመት በላይ እና ከ10 ዓመት በታች የሚያስቀጡ ተደራራቢ ወንጀልች የእያንዲንደ ተደራራቢ ወንጀል የቅጣት ጣሪያው ከ4 ዓመት በላይ እና ከ10 ዓመት በታች የሚያስቀጡ ሲሆን እንደሆነ እና መደመር ያለባቸው ተደራራቢ ወንጀልች የቅጣት ጣሪያቸውን እና የወንጀልችን ክብደት መሰረት በማድረግ እንደሚደመሩ ሕጉ ሲረቀቅ መነሻ ከተደረጉት ምክንያቶች እና ከወንጀልቹ ክብደት አኳያ መረዲት እየተቻለ ይግባኝ ሰሚ ጠቅላይ ፍርድ ቤት 4 ዓመት የተባለውን እንደመነሻ ቅጣት ወስድ ተጠሪን በዋስትና መልቀቁ ከህጉ መንፈስ ውጭ ከመሆኑም በላይ የአዋጁን ተፈፃሚነት ከጥያቄ የሚያስገባ ነው፤ በዘህ አዋጅ እና በላልችም የሙስና ወንጀልች ድንጋጌዎች መነሻቸው አራት ዓመት እና ከዘያ በላይ የሆኑ የሙስና ወንጀልች የለም፤ በሙስና ወንጀል የዋስትና ክርክር ጊዚ ክስ የቀረበበት ድንጋጌ ጣሪያ ቅጣት ላታይ እንደሚገባ የፋ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልት በሰ.መ. ላይ ትርጉም የሰጠ በመሆኑ 4 ዓመት የተባለው የቅጣቱ ጣሪያ በሚለው ሉወሰድ ሲገባው በሕጉ ባልተደነገገበት ሁኔታ 4 ዓመትን እንደመነሻ ቅጣት መወሰደ አግባብ አይደለም፤ ከዋስትና አሰጣጥ አንፃር የቀረበው የክስ ብዙት ከግንዙቤ ሉገባ እንደሚገባ ይኸው ሰበር ችልት በሰ.መ. ላይ ትርጉም የሰጠ በመሆኑ እና ተጠሪ እንዱከላከለ ብይን የተሰጠው እስከ 10 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ሉያስቀጡ በሚችለ ሁለት ወንጀልች በመሆኑ ተደራራቢ ክሱ ከሚያስከትለው ቅጣት አንፃር የዋስትና ጥያቄው በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 67/ሀ መሰረት ላታይ ሲገባው መታለፈ አግባብ ስላልሆነ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ተሽሮ ተጠሪ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዲያቸውን እንዱከታተለ ሉወሰን ይገባል የሚል ነው።
የአመልካቹ የሰበር አቤቱታ በሰበር አጣሪው ችልት ተመርምሮ የአሁን ተጠሪ በአዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 9/1/ ስር በሁለት ወንጀልች እንዱከላከለ ብይን ተሰጥቶ እያለ የስር ፍርድ ቤት በዋስትና እንዱለቀቁ የመወሰኑን አግባብነት ከአዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 9/1፤ አዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀፅ 2 እና በሰ.መ. ላይ ከተሰጠው አስገዲጅ ትርጉም አኳያ ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ በዘህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል። ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የተጠሪ መልስ ይዖት በአጭሩ፡- በተጠቀሰው ድንጋጌ ውስጥ 4 ዓመት የተባለው መነሻ ቅጣት ለመሆኑ ህጉ በግልፅ ያስቀመጠ በመሆኑ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ውሳኔ የሚነቀፍ አይደለም፤ ዋስትና ሉከለከል የሚችለው ከ4 ዓመት በላይ በሆነ ተደራራቢ ወንጀል ለመሆኑ ሕጉ በግልጽ አስቀምጧል፤
አራት ዓመት እንደቅጣት ጣሪያ ሉወሰድ አይገባም፤ አመልካች ተከላከል የተባልኩበት የሕግ አንቀጽ የቅጣት መነሻ የአንድ ዓመት ቀላል እስራት ነው፤ አመልካች የጠቀሳቸው የሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔዎች ከጉዲዩ ጋር ተያያዥነት የላላቸው ሲሆን በ2007 ዓ.ም በወጣ አዋጅ ላይም ተፈጻሚ አይሆኑም፤ የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት አተረጓጎም አዋጅ ቁጥር 881/2007 አፈፃፀምን የሚከለክል አይደለም፤ በአዋጅ ቁጥር 434/1997 እና በተሻሻለው አዋጅ መካከል ልዩነት ካለ አዱሱ ሕግ ተፈፃሚ ላሆን ይገባል፤ በሰበር ችልት ማስቀረቢያ ነጥብ ላይ የተጠቀሱት የሰበር ውሳኔዎች አሁን ከቀረበው ጉዲይ ጋር ተመሳሳይ በሆነ ጉዲይ ላይ የተሰጠ ትርጉም ሳይሆን መነሻ እና መድረሻ ቅጣቱ በግልፅ ተለይቶ ባልተጠቀሰ ድንጋጌ ከመሆኑም በላይ በተሻሻለ ሕግ ላይ የተሰጡ በመሆናቸው አሁን ለቀረበው ጉዲይ ተፈፃሚነት የላቸውም፤ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 67/ሀ ድንጋጌ መሰረት የቀረበው ክርክር በስር ፍርድ ቤት ያልተነሳ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም፤ በመሆኑም የቀረበው ቅሬታ ውድቅ ተደርጎ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ውሳኔ ሉፀና ይገባል የሚል ነው።
አመልካች ነሐሴ 15/2011 ዓ.ም በተፃፈ የመልስ መልስ ክስ በቀረበበት አዋጅም ሆነ በወንጀል ህጉ መነሻ ቅጣቱ 4 ዓመት የሆነ ድንጋጌ የላለ በመሆኑ ሕግ አውጪው የማይፈፀም ሕግን ያወጣል ብል መውስድ የሕጉን መንፈስ እና ዓላማ የተከተለ አይደለም፤ ክስ የቀረበበት አዋጅ የሰበር ችልቱ በሰ.መ. ላይ የሰጠውን ትርጉም የሚያጠናክር በመሆኑ ለቀረበው ጉዲይ አግባብነት የለውም ልባል አይገባም፤ ተጠሪ እንዱከላከለ ብይን የተሰጠባቸው ሁለቱም አንቀፆች የቅጣት ጣሪያ ሰበር ችልቱ በተጠቀሰው መዛገብ ላይ የሰጠው ትርጉም ለአዋጅ ቁጥር 881/2007 ተፈፃሚ ላደረግ ይገባል፤
የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 67/ሀ/ ድንጋጌን አስመልክቶ የተሰጠው ውሳኔ የሕግ ትርጉም በመሆኑ እና የሰበር ክርክር የሕግ አተረጓጎምን የሚመለከት በመሆኑ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ሉመለከተው ሲገባው ያለፈውን ጉዲይ ማቅረቡ ተገቢ ነው በማለት የሰበር አቤቱታው በማጠናከር ተከራክሯል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባዋል ተብል የተያዖውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዖብ እንደሚከተለው መርምሮታል።
ከክርክሩ ሑደት መገንዖብ የተቻለው የስር ከፍተኛው ፍ/ቤት ተጠሪ በአዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀፅ 9/1/ሀ/ለ/1/ ድንጋጌ በሁለት ክሶች እንዱከላከለ ብይን የተሰጠ እና የሁለቱም ክሶች ቅጣት ሲደመር ከ10 ዓመት በላይ በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 434/1997 አንቀፅ 4 መሰረት የዋስትና ጥያቄው ተቀባይነት የለውም በማለት ውድቅ ያደረገው መሆኑን፤ ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ደግሞ በአዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 3/1 ከአራት ዓመት በላይ የሚለው አገላለጽ ከአራት ዓመት በላይ የሚያስቀጣ ተደራራቢ ወንጀልን የሚመለከት እንጂ ተጠሪ እንዱከላከል ብይን የተሰጠበትን አንቀጽ 9/1/ሀ/ለ መነሻ ቅጣቱ አንድ ዓመት ቀላል እሥራት ወይም አንድ ዓመት ጽኑ እሥራት የሚለውን የሚጨምር ነው በሚል የሚተረጎም አይደለም በማለት የተጠሪን የዋስ መብት የጠበቀ መሆኑን ነው።
በመሆኑም የዘህን ችልት ምላሽ የሚፈልገው የክርክሩ መሰረታዊ ጭብጥ፡-
በአዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 3/1 ላይ ከአራት ዓመት በላይ እና ከ10 ዓመት በታች የሚያስቀጡ ተደራራቢ ወንጀልች ሲኖሩም እየተደመሩ ከ10 ዓመት በላይ የሚያስቀጣ ከሆነ ዋስትናን ይከለክላል በማለት የተቀመጠው ሀሳብ መነሻ ቅጣትን የሚመለከት ነው? አይደለም?
ተከሳሹ እንዱከላከል ብይን የተሰጠበት የሕግ አንቀጽ አማራጭ ቅጣትን ባስቀመጠ ጊዚ የዋስትናን መብት ጥያቄን ለመወሰን ሲባል ተፈጻሚ የሚሆነው የትኛው የቅጣት አማራጭ ነው?
የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ከወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 67 አኳያ የዋስትና መብቱን የሚያስከለክል መከራከሪያ ባልቀረበበት ሁኔታ የተጠሪ የዋስትና መብት ሉከለከል አይገባም ማለቱ ተገቢ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለት ናቸው።
በመሆኑም ከላይ ለተያዘት መሰረታዊ የክርክሩ ጭብጦች ምላሽ መስጠት ያስችለን ዖንድ የሙስና ወንጀልችን አስመልክቶ በሐገራችን የወጡትን ሕጎች እና በየጊዚው የወጡትን የማሻሻያ አዋጆች ሕግ አውጪው ሉያሳካው ከፈለገው ግብ እና ከዋስትና መብት መሰረታዊ መርሆዎች እና ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ መመርመር አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
በመሰረቱ የጸረ ሙስና ልዩ የሥነ-ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 236/93 እንደተሻሻለ / አዋጅ ቁጥር 239/93 አንቀጽ 51/2 / በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ የተያዖ ሰው የዋስትና መብት አይኖረውም በማለት ግልጽ ክልከላ ያደረገ አዋጅ የነበረ ሲሆን ሕግ አውጪው አስቀድሞ ባወጣው የሙስና ወንጀልች ሕግ ዋስትናን በግልጽ ክልከላ / ገደብ / ያደረገ መሆኑን፤ በሂደት በወጣው የተሻሻለው የጸረ ሙስና ልዩ የሥነ-ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 4/1/ በሙስና ወንጀል የተያዖ ሰው በዋስ እንዱለቀቅ ማመልከት ይችላል፤ ሆኖም የተከሰሰበት ወንጀል ከ10 ዓመት በላይ ሉያስቀጣ የሚችል ከሆነ በዋስትና መልቀቅ አይቻልም በማለት የሙስናን ወንጀል ቅጣት መጠንን መሰረት በማድረግ ዋስትናን ለመፍቀድ ወይም ለመንፈግ እንደመስፈርት በማስቀመጥ በዋስ የመለቀቅ መብት በመርህ ደረጃ ሕገ-መንግስታዊ መብት መሆኑን ያመላከተ ነው።
በቀጣይነት የወጣው የተሻሻለው የጸረ ሙስና ልዩ የሥነ-ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 3/1 ይህንኑ ሕገመንግስታዊ መብት የበለጠ በማስፊት በሙስና ወንጀል የተያዖ ሰው በዋስ እንዱለቀቅ ለፍ/ቤት ማመልከት እንደሚችል ሆኖም የተከሰሰበት ወይም የተጠረጠረበት ወንጀል ከ10 ዓመት በላይ በሆነ ጽኑ እሥራት ሉያስቀጣ የሚችል ከሆነ በቀደሙት አዋጆች እንደተመለከተው በዋስትና መለቀቅ የማይችል መሆኑን፤ ከአራት ዓመት በላይ እና ከ10 ዓመት በታች የሚያስቀጡ ተደራራቢ ወንጀልች ሲኖሩም እየተደመሩ ከ10 ዓመት በላይ የሚያስቀጣ ከሆነ ግን ዋስትና የሚከለክለ መሆኑን ይደነግጋል።
በሙስና ወንጀል የተያዖን ሰው የዋስትና መብትን አስመልክቶ በተለያየ ጊዚ የወጡት ሕጎች ከላይ በዛርዛር የተገለጹት ሲሆኑ እነዘህ ሕጎች ሉያሳኩት የፈለጉት መሰረታዊ ዓላማ ከኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገመንግስት እና በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕጉ ላይ ዋስትናን አስመልክቶ ከተደነገጉት ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ እንደሚከተለው መርምረነዋል።
በመሰረቱ የተያዘ ሰዎች በሕገ-መንግስቱ ጥበቃ ከተደረጉላቸው መብቶች አንደ የዋስትና መብት ነው።
የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግሥት በአንቀጽ 19/6 የተያዘ ሰዎች በዋስትና የመፈታት መብት ያላቸው መሆኑን በመርህ ደረጃ ያስቀመጠ ሲሆን ይህ በሕገ መንግሥቱ የተከበረው መሰረታዊ መብት ሉነፈግ፣ ሉገደብ ወይም በቂ የሆነ የዋስትና ማረጋገጫ እንዱቀርብ የሚደረገውም አግባብነት ባላቸው ላልች ዛርዛር ሕጎች መሰረት በልዩ ሁኔታ ስለመሆኑ ከድንጋጌው ይዖት መገንዖብ ይቻላል። በዖመናዊው የሕግ አስተሳሰብም በዋስ ለመለቀቅ ከሚያበቁ ምክንያቶች መካከል ጎልቶ የሚታየው ማንኛውም በወንጀል የተከሰሰ ሰው በፍ/ቤት የጥፊተኝነት ውሳኔ ሳይሰጥበት ሉቀጣ አይገባውም የሚለው ነው።
በሕገ-መንግስቱ ልዩ ጥበቃ የተሰጠው ይህ መብት መሰረታዊ ዓላማውም ተከሳሹ በተከሰሰበት ወንጀል ጥፊተኝነቱ ሳይረጋገጥበት በእስር እንዲይቆይ ማድረግ ነው። በመሆኑም የዋስትና መብት መርሁ መፍቀድ ሲሆን ልዩ ሁኔታው ደግሞ መከልከል ነው።
ይህን መሰረታዊ መብት አስመልክቶ የመወሰን ስልጣን እና ኃላፉነት የተሰጣቸው ፍ/ቤቶችም በወንጀል ጉዲይ ተጠርጥሮ ክስ የቀረበበት ሰው የሚያቀርበውን የዋስትና መብት ጥያቄ እና ከሣሽ የሆነው ዓቃቤሕግም በጉዲዩ ላይ የሚሰጠውን አስተያየት በሕገመንግስቱ ዋስትናን አስመልክቶ ከደነገገው መሰረታዊ ዓላማ እና በላልች ልዩ ሕጎች ከተደነገጉት ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ በጥንቃቄ መርምረው ውሳኔ መስጠት ይጠበቅባቸዋል። ይህንኑ ተግባራዊ ሲያደርጉም በመርህ ደረጃ የዋስትናን መብት መፍቀድ ያለባቸው ሲሆን በሕጉ ተለይተው በተቀመጡ ምክንያቶች ግን የዋስትናን መብት በልዩ ሁኔታ ሉነፍጉ ይችላለ። እነዘህም ምክንያቶች መርማሪው ፕሉስ ምርመራውን ገና ያላጠናቀቀ ሲሆን በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 59፤ ተከሳሽ ፈጽሞታል የተባለው ወንጀል በዋስትና ለመለቀቅ የሚከለክል ሲሆን በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 63 የሕግ ክልከላን መሰረት በማድረግ እና በላልች ልዩ ሕጎች፤ ወይም ተከሳሹ ፈጽሞታል የተባለው ወንጀል በዋስ መለቀቅን የማይከለክል ቢሆንም ተጠርጣሪው ቢለቀቅ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 67 የተገለፁትን ተግባራት ይፈጽማል ተብል ሲታመን ነው። የዋስትና መብትን አስመልክቶ በሕገመንግስቱ እና በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕጉ ላይ የተቀመጡት መሰረታዊ መርሆዎች በዛርዛር የተገለጹት ሲሆኑ በሙስና ወንጀል የተጠረጠረን ወይም የተከሰሰን ሰው አስመልክቶ በየጊዚው ተሻሽለው የወጡት ሕጎች ከዋስትና መብት መሰረታዊ መርሆዎች ጋር ተገናዛበው ሲታዩ ሉያሳኩ የፈለጉት መሰረታዊ ዓላማ ምንድነው የሚለውን ቀጥለን እንመልከት።
የጸረ ሙስና ልዩ የስነስርዓት እና የማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 236/93 እንደተሻሻለ / አዋጅ ቁጥር 239/93 አንቀጽ 51/2 / በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ የተያዖ ሰው የዋስትና መብት አይኖረውም በማለት ግልጽ ክልከላ አድርጎ የነበረ አዋጅ ቢሆንም የዋስትና መብት በሕገመንግስቱ እና ኢትዮጵያ በተቀበለቻቸው ዓለምዓቀፍ ስምምነቶች ጥበቃ የተደረገለት መሰረታዊ መብት መሆኑ ታምኖበት በሂደት በወጣው የተሻሻለው የጸረ ሙስና ልዩ የስነስርዓት እና የማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 4/1 በሙስና ወንጀል የተያዖ ሰው በዋስ እንዱለቀቅ ማመልከት ይችላል፤ ሆኖም የተከሰሰበት ወንጀል ከ10 ዓመት በላይ ሉያስቀጣ የሚችል ከሆነ በዋስትና መለቀቅ እንደማይችል በመግለጽ በሙስና ወንጀል የተከሰሰ ሰው በተከሰሰበት ሕግ ላይ ያለውን የቅጣት መጠን መሰረት በማድረግ የዋስትና መብትን በከፉል የፈቀደ መሆኑን ከድንጋጌው ይዖት መገንዖብ ይቻላል። የአዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 4/1 ድንጋጌ ከፍተኛ ቅጣት ሉያስቀጣ በሚችል የሙስና ወንጀል የተከሰሰ ሰው በዋስ ከመልቀቅ ይልቅ በእስር ሆኖ ጉዲዩን እንዱከታተል ማድረግ፤ በልላ በኩል ከ10 ዓመት በታች ሉያስቀጣ በሚችል የሙስና ወንጀል የተከሰሰ ሰው በእስር ከማቆየት ይልቅ በዋስ ሆኖ ጉዲዩን እንዱከታተል ማድረግ የዋስትና መብት ሕገመንግስታዊ ሽፊን የተሰጠው መሰረታዊ መብት መሆኑ ታምኖበት ሕግ አውጪው የዋስትና መብትን አስመልክቶ አስቀድሞ በነበረው አዋጅ ላይ አስቀምጦት የነበረውን ፍጹም ክልከላ በተወሰነ ደረጃ በመተው የዋስትና መብትን በተወሰኑ የሙስና ወንጀልች ላይ የፈቀደ መሆኑን አመላካች ነው።
በተሻሻለው የጸረ ሙስና ልዩ የስነስርዓት እና የማስረጃ ሕግ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 3/1 በሙስና ወንጀል የተያዖ ሰው በዋስ እንዱለቀቅ ለፍ/ቤት ማመልከት ይችላል፤ ሆኖም የተከሰሰበት ወይም የተጠረጠረበት ወንጀል ከ10 ዓመት በላይ በሆነ ጽኑ እሥራት ሉያስቀጣ የሚችል ከሆነ በዋስትና መለቀቅ አይችልም። ከአራት ዓመት በላይ እና ከ10 ዓመት በታች የሚያስቀጡ ተደራራቢ ወንጀልች ሲኖሩም እየተደመሩ ከ10 ዓመት በላይ የሚያስቀጣ ከሆነ ዋስትና ይከለከላል በማለት ይደነግጋል። በድንጋጌው የመጀመሪያ ሐሳብ ላይ የተቀመጠው እና የተከሰሰበት ወይም የተጠረጠረበት ወንጀል ከ10 ዓመት በላይ በሆነ ጽኑ እሥራት ሉያስቀጣ የሚችል ከሆነ በዋስትና መለቀቅ አይችልም የሚለው ሐሳብ በአዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 4/1 የተከሰሰበት ወንጀል ከ10 ዓመት በላይ ሉያስቀጣ የሚችል ከሆነ በዋስትና መለቀቅ አይችልም በማለት ከተገለጸው ሀሳብ ጋር ተመሳሳይ በመሆኑ በዘህ ረገድ የአዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 3/1 የመጀመሪያ ሀሳብ የተለየ ነገር የለውም። በአዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 3/1 ላይ የተቀመጠው ሁለተኛው ሀሳብ በዘህ መዛገብ ለተያዖው ጉዲይ አግባብነት ያለው የክርክሩ ጭብጥ በመሆኑ በድንጋጌው ላይ የተቀመጠው ሁለተኛ ሀሳብ መሰረታዊ ዓላማ ከድንጋጌው ይዖት፤ አግባብነት ካላቸው የሙስና ወንጀል ድንጋጌዎች እና ከመደበኛው የወንጀል ሕጉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ መመርመር አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
ተጠሪ እንዱከላከለ ብይን የተሰጠው በአዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9/1/ሀ/ለ ሲሆን ይህ ደግሞ ከአንድ ዓመት በማያንስ ቀላል እሥራት እና ከሶስት ሺህ ብር በማይበልጥ መቀጮ ወይም ከአሥር ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እሥራት እና ከአሥር ሺህ ብር በማይበልጥ መቀጮ የሚያስቀጣ ነው።
በኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወንጀል ሕግ የቀላል እሥራት እና የጽኑ እሥራት ቅጣት መጠን በሚገባ ተለይቶ ተቀምጧል። የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 106/1 ቀላል እስራት ከ10 ቀን እስከ ሶስት ዓመት የሚያስቀጣ መሆኑን፤ የዘሁ ሕግ አንቀጽ 108/1 ድንጋጌ ደግሞ ጽኑ እሥራት ከአንድ ዓመት እስከ 25 ዓመት የሚደርስ እና በሕጉ ተገልጾ የተደነገገ ሲሆንም በዔድሜ ልክ የሚያስቀጣ እንደሆነ ይደነግጋል።
የአዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 3/1 ድንጋጌ የመጀመሪያ ሀሳብ ላይ የተከሰሰበት ወይም የተጠረጠረበት ወንጀል ከ10 ዓመት በላይ በሆነ ጽኑ እሥራት ሉያስቀጣ የሚችል ከሆነ በዋስትና መለቀቅ አይችልም በማለት የተገለጸ በመሆኑ ይህ ሀሳብ የሚመለከተው በጽኑ እሥራት የሚያስቀጡ ወንጀልችን ነው። በዘሁ ድንጋጌ ላይ የተቀመጠው ሁለተኛ ሀሳብ የድንጋጌው የመጀመሪያ ሀሳብ በአራት ነጥብ ከተቋጨ በኋላ ይህንኑ ሀሳብ ተከትል ከአራት ዓመት በላይ እና ከ10 ዓመት በታች የሚያስቀጡ ተደራራቢ ወንጀልች ሲኖሩም እየተደመሩ ከ10 ዓመት በላይ የሚያስቀጣ ከሆነ ዋስትና ይከለከላል በማለት የተገለጸ በመሆኑ እና በልዩ ሁኔታ ከወንጀለ ከባድነት የተነሳ በሕጉ ልዩ ክፍል ተደንግጎ ሲገኝ ወይም በቀላል እስራት የሚያስቀጡ ተደራራቢ ወንጀልች ሲኖሩ ወይም ወንጀለኛው በተደጋጋሚ ሲቀጣ እስከ አምስት ዓመት ሉደርስ እንደሚችል እንደተጠበቀ ሆኖ ቀላል እሥራት የሚያስቀጣው ከ10 ቀን እስከ ሶስት ዓመት በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 3/1 ሁለተኛ ሀሳብ ላይ ከአራት ዓመት በላይ እና ከ10 ዓመት በታች የሚያስቀጡ ተደራራቢ ወንጀልች በማለት የተገለጸው ሀሳብ ከአራት ዓመት በላይ በጽኑ እሥራት ሉያስቀጡ የሚችለ ወንጀልችን የሚመለከት እንጂ የቅጣት መነሻቸው አራት ዓመት የሆነ በጽኑ እሥራት የሚያስቀጡ ወንጀልችን የሚመለከት እንዲልሆነ ከድንጋጌው አቀራረጽ እና ይዖት መገንዖብ ይቻላል።
በአዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 3/1 ከአራት ዓመት በላይ የሚያስቀጡ ተደራራቢ ወንጀልች ተፈጽመው በተገኙ ጊዚ በሚል የተገለጸው ሁለተኛ ሀሳብ መነሻ ቅጣትን የሚመለከት አይደለም ካልን በቀላል እሥራት የሚያስቀጡ ወንጀልች የፈለገውን ያህል ተደራርበው ቢገኙ ላላ ሕጋዊ ምክንያት እስካልቀረበ ጊዚ ድረስ ተደራራቢ ወንጀልች ናቸው በሚል ምክንያት የተከሰሰውን የዋስትና መብት መከልከል የማይቻል መሆኑ፤ ሆኖም ከአራት ዓመት በላይ እና ከ10 ዓመት በታች በሆነ ጽኑ እሥራት የሚያስቀጡ ተደራራቢ ወንጀልች ሲኖሩ እና እየተደመሩ ከ10 ዓመት በላይ የሚያስቀጣ ከሆነ ግን የተከሰሰውን ሰው የዋስትና መብት የሚከለከል መሆኑን የሚያሳይ ነው።
ከላይ የተመለከተውን የሕጉን ትንታኔ መነሻ በማድረግ በሙስና ወንጀል ሕግ አዋጅ ቁጥር 881/2007 ላይ ከአራት ዓመት በላይ እና ከ10 ዓመት በታች የሚያስቀጡ ወንጀልች መኖር አለመኖራቸውን በተመለከተ አዋጁን እንደተመለከትነው በአዋጁ አንቀጽ 13/4/ለ የተመለከተው ወንጀል ተፈጽሞ ሲገኝ እንደነገሩ ሁኔታ በቀላል እስራት እና በመቀጮ ወይም ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት፤
በአዋጁ አንቀጽ 13/7 የተመለከተው ወንጀል ተፈጽሞ ሲገኝ ከሶስት ዓመት እስከ 7 ዓመት እና ከብር 10,000 እስከ 50,000 መቀጮ፤ በአዋጁ አንቀጽ 17/2 የተመለከተው ወንጀል ተፈጽሞ ሲገኝ ከአንድ ዓመት በማያንስ ቀላል እስራት እና ከሶስት ሺህ ብር በማይበልጥ መቀጮ ወይም ከ7 ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት እና ከ 20,000 በማይበልጥ መቀጮ፤ በአዋጁ አንቀጽ 16/1 ላይ የተመለከተው ወንጀል ተፈጽሞ ሲገኝ ከአንድ ዓመት እስከ 10 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንደሚያስቀጣ ይደነግጋል። ከእነኚህ ድንጋጌዎች ይዖት መገንዖብ የሚቻለው ድንጋጌዎቹን በመተላለፍ የተከሰሰ ሰው ከአራት ዓመት በላይ እና ከ10 ዓመት በታች በሆነ ጽኑ እሥራት ሉቀጣ እንደሚችል አመላካች ድንጋጌዎች መሆናቸውን ነው።
ይህንኑ መሰረት በማድረግ በእጃችን ያለውን ጉዲይ እንደመረመርነው አመልካች ለዘህ ሰበር ሰሚ ችልት ባቀረበው ክርክር መነሻቸው አራት ዓመት እና ከዘያ በላይ የሆኑ የሙስና ወንጀልች የለም በማለት የሚከራከር ቢሆንም ከላይ በዛርዛር በተገለጹት ድንጋጌዎች የተከሰሰ ሰው ከአራት አመት በላይ እና ከ10 ዓመት በታች በሆነ ጽኑ እሥራት ሉቀጣ እንደሚችል አመላካች ድንጋጌዎች በመሆናቸው እና በአዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 3/1 ሁለተኛ ሀሳብ ላይ ከአራት ዓመት በላይ እና ከ10 ዓመት በታች የሚያስቀጡ ተደራራቢ ወንጀልች በማለት የተገለጸው ሀሳብ ከአራት ዓመት በላይ በጽኑ እሥራት ሉያስቀጡ የሚችለ ወንጀልችን የሚመለከት እንጂ መነሻ ቅጣትን የሚመለከት ባለመሆኑ አመልካቸ በዘህ ረገድ ያቀረበው መከራከሪያም ሆነ ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በድንጋጌው ከአራት ዓመት በላይ እና ከ10 ዓመት በታች የሚያስቀጡ ተደራራቢ ወንጀልች በሚል የተገለጸው የሕጉ አገላለጽ መነሻ ቅጣቱ አራት ዓመት እና በላይ የሆነን ድንጋጌን የሚመለከት ነው በማለት የደረሰበት መደምደሚያ ተቀባይነት ያለው አይደለም።
በልላ በኩል አመልካች ለዘህ ችልት ባቀረበው ክርክር የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ.መ. በሙስና ወንጀል የዋስትና ክርክር ጊዚ ክስ የቀረበበት ድንጋጌ ጣሪያ ቅጣት ላታይ እንደሚገባ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም የተሰጠበት በመሆኑ 4 ዓመት የተባለው የቅጣቱ ጣሪያ ሉወሰድ ይገባል በማለት የሚከራከር ከመሆኑ አኳያ ተጠቃሹ የሰበር ሰሚ ችልት ወሳኔ ከጉዲዩ ጋር ተያያዥ መሆን አለመሆኑን እንደሚከተለው መርምረናል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ.መ. ሐምል 28 ቀን 2003 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ዋስትናን በሚመለከት የሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም የወንጀል ሕግ አንቀጽ 676/1 በመተላለፍ ከባድ የእምነት ማጉደል የሙስና ወንጀል ፈጽሟል በማለት የተከሰሰን ሰው በሚመለከት የተሰጠ ውሳኔ ሲሆን ድንጋጌው የሚመለከተው ተፈጸመ የተባለውን የወንጀል ድርጊት እና ቅጣቱን የሚመለከት እንጂ አማራጭ ቅጣት አልተቀመጠበትም፤ በድንጋጌው ጥፊተኛ የተባለም ሰው ከአምስት ዓመት እስከ 25 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት እና ከብር 100,000 በማይበልጥ መቀጮ የሚያሰቀጣ መሆኑን ይገልጻል፤ ይህንኑ ድንጋጌ እና የአዋጅ 434/97 አንቀጽ 4 ድንጋጌን መሰረት በማድረግ በመዛገቡ የተሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉምም ተከሳሹ የተከሰሰበትን ዛቅተኛ የቅጣት መነሻ መውሰድ የአዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 4 ድንጋጌን ውጤታማ በሆነ ሁኔታ ተፈጻሚ የማያደርግ እና ሕግ አውጭው የፀረሙስና ልዩ የሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕግን በማውጣት ለማሳካት የሚፈልገውን ግብ የማያሳካ ነው የሚል ነው። ይህ አስገዲጅ ትርጉም አንድ ቅጣት ብቻ ተለይቶ የተቀመጠበትን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 676/1 በሚመለከት የተሰጠ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም እንጂ ተከሳሹ የተከሰሰበት የሕግ አንቀጽ አማራጭ ቅጣትን ያስቀመጠ በሆነ ጊዚ ለዋስትና ጉዲይ ሲባል ፍ/ቤቱ የትኛውን የቅጣት አማራጭ መውሰድ እንዲለበት በመግለጽ የሰጠው የሕግ ትርጉም የለም። በመሆኑም አመልካች በዘህ ውሳኔ ላይ የተሰጠው የሕግ ትርጉም ለጉዲዩ አግባብነት አለው በማለት ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት ያለው አይደለም። በሰ.መ. የተሰጠው ውሳኔም አስቀድሞ በሰ.መ. የተሰጠውን ውሳኔ መሰረት በማድረግ የተሰጠ ውሳኔ በመሆኑ፤ አዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 58 አዋጁ በስራ ላይ ከመፈጸሙ በፉት የተፈጸሙ ወንጀልች በነባሩ የስነምግባር እና የጸረ ሙስና ልዩ የስነስርዓት እና የማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 434/97 መሰረት ፍጻሜ ያገኛለ የሚል በመሆኑ እና አመልካች ፈጸሙት የተባለው የሙስና ወንጀል አዋጅ ቁጥር 882/2007 ከወጣ በኋላ በመሆኑ ተጠቃሾች የሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔዎች ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸው አይደለም።
ተጠሪ እንዱከላከለ ብይን የተሰጠበት የአዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 9/1/ሀ/ለ/1/ እንደነገሩ ሁኔታ ከአንድ ዓመት በማያንስ ቀላል እስራት እና ከሶስት ሺህ ብር በማይበልጥ መቀጮ ወይም ከ10 ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እሥራት እና ከአሥር ሺህ ብር በማይበልጥ መቀጮ ያስቀጣል በሚል አማራጭ ቅጣትን ያስቀመጠ በመሆኑ፤ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰመ. ም ሆነ በሰ.መ. በሰጠው ውሳኔ ተከሳሽ የተከሰሰበት የሕግ አንቀጽ አማራጭ ቅጣትን ባስቀመጠ ጊዚ ለዋስትና ጉዲይ ሲባል ሉያዛ የሚገባው ቅጣት የትኛው እንደሆነ ገዢ ትርጉም ያልሰጠበት በመሆኑ ለዋስትና ጉዲይ ሲባል ሉወሰድ የሚገባው የቅጣት አማራጭ የትኛው ነው የሚለው በጥንቃቄ ላታይ ይገባዋል።
ተጠሪ እንዱከላከለ ብይን የተሰጠው በአዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9/1/ሀ/ለ ሲሆን ይህ ደግሞ ከአንድ ዓመት በማያንስ ቀላል እሥራት እና ከሶስት ሺህ ብር በማይበልጥ መቀጮ ወይም ከአሥር ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እሥራት እና ከአሥር ሺህ ብር በማይበልጥ መቀጮ የሚያስቀጣ ነው። ከላይ በዛርዛር ካስቀመጥናቸው የሕጉ ትንታኔዎች አኳያ ፍ/ቤቱ ቀላል የእስራት ቅጣት አማራጩን የሚወስድ ከሆነ የተጠሪ የዋስትና መብት የሚፈቀድ ሲሆን ፍ/ቤቱ የጽኑ እሥራት አማራጭን የሚወስድ ከሆነ ደግሞ የተጠሪ የዋስትና መብት የሚከለከል ይሆናል። በመሆኑም ፍ/ቤቱ ለዋስትና ጉዲይ ሲባል በድንጋጌው ከተቀመጡት ሁለት የቅጣት አማራጮች ውስጥ የትኛውን አማራጭ ተግባራዊ ማድረግ እንዲለበት ተከሳሹ ፈጽሞታል ከተባለው ድርጊት፤ ከሙስና ወንጀል አዋጆች ልዩ ባሕርይ እና ከዋስትና መብት መሰረታዊ ዓላማ ጋር በማገናዖብ መለየት ይኖርበታል።
በያዛነው ጉዲይ የሥር ከፍተኛው ፍ/ቤት ተጠሪ አስቀድሞ ክስ የቀረበባቸውን የአዋጁን አንቀፅ 9/1/ሀ/ለ/2/ ድንጋጌን በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 113 በመለወጥ በአንቀፅ 9/1/ሀ/ለ እንዱከላከለ ብይን ሲሰጥ እንደምክንያት ያስቀመጠው በተጠሪ አድራጎት ደረሰ የተባለው የጉዲት መጠን ተጠሪ በተከሰሱበት የሕግ አንቀጽ የተቀመጠ አይደለም በሚል ነው። ተጠሪ ፈጽመውታል በተባለው የወንጀል ድርጊት ምክንያት ደረሰ የተባለው የጉዲት መጠን በዓቃቤሕግ ክስ ላይ የተገለጸው አይደለም የሚባል ከሆነ ተጠሪ ይከላከለ ከተባለበት የአዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 9/1/ሀ/ለ ላይ ከተቀመጡት የቀላል እሥራት እና የጽኑ እሥራት የቅጣት አማራጮች ውስጥ የዋስትና መብት ሕገመንግስታዊ ሽፊን የተሰጠው መሰረታዊ መብት ከመሆኑ አኳያ ለዋስትናው ጉዲይ ሲባል የቀላል እሥራት አማራጭን መውሰድ ተመራጭ ሆኖ አግኝተነዋል። ተጠሪ ይከላከለ ከተባለበት የአዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 9/1/ሀ/ለ ላይ ከተቀመጡት የቀላል እሥራት እና የጽኑ እሥራት የቅጣት አማራጮች ውስጥ ለዋስትናው ጉዲይ ሲባል የቀላል እሥራት አማራጭ የተወሰደ በመሆኑ እና በአዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 3/1 በቀላል እሥራት የሚያስቀጡ ወንጀልች የፈለገውን ያህል ተደራርበው ቢገኙ ዋስትናን ለማስከልከል የሚያስችል ላላ ሕጋዊ ምክንያት እስካልቀረበ ጊዚ ድረስ ተደራራቢ ወንጀልች ናቸው በሚል ምክንያት የተከሰሰውን ሰው የዋስትና መብት መከልከል አይቻልም።
በልላ በኩል አመልካች ለዘህ ሰበር ሰሚ ችልት ባቀረበው ክርክር ተጠሪ እንዱከላከለ ብይን የተሰጠው እስከ 10 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ሉያስቀጡ በሚችለ ሁለት ወንጀልች በመሆኑ ተደራራቢ ክሱ ከሚያስከትለው ቅጣት አንፃር የዋስትና ጥያቄው በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 67/ሀ መሰረት ላታይ ሲገባው መታለፈ አግባብ አይደለም በማለት የሚከራከር ከመሆኑ አኳያ የስር ይግባኝ ሰሚው የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ከወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 67 መሰረት የዋስትና መብቱን የሚያስከለክል መከራከሪያ ባልቀረበበት ሁኔታ የተጠሪን የዋስትና መብት መከልከል አግባብ አይደለም በማለት የሰጠው ውሳኔ አግባብ መሆን አለመሆኑን ቀጥለን እንመልከት።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የዲኝነት ስልጣኑ የተመለከተው የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ተጠሪ የተከሰሱበትን የሕግ አንቀጽ በብይን ሲቀይር ተጠሪ በጠበቃቸው አማካኝነት የዋስትና መብት እንዱፈቀድላቸው ጠይቀዋል። ከሳሽ የሆነው ዓቃቤሕግ በዋስትና ጥያቄው ላይ በሰጠው አስተያየት ተጠሪ እንዱከላከለ ብይን የተሰጠው በሁለት ክሶች በመሆኑ እና የዋስትና መብት ቢጠበቅላቸው ቅጣቱን በመሸሽ የዋስትና ግዳታቸውን አክብረው ስለማይቀርቡ የዋስትና ጥያቄው ተቀባይነት ሉያገኝ አይገባም በማለት የተቃወመ ስለመሆኑ የከፍተኛው ፍ/ቤት የሰጠው ብይን በግልጽ የሚያሳይ በመሆኑ አመልካች የተጠሪ የዋስትና መብት በሕግ ባይከለከልም ዋስትናን ሉያስከለክለ በሚችለ ሁኔታዎች ሉነፈግ ይገባል በማለት የተከራከረ መሆኑን መገንዖብ ይቻላል። የስር ከፍተኛው ፍ/ቤት የተጠሪን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ያደረገው በአዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 4 መሰረት በመሆኑ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 67 በተገለጸው አግባብ የተጠሪን የዋስትና መብት ለማስከልከል የሚያስችለ ሁኔታዎች መኖር አለመኖራቸውን መመርመር አላስፈለገውም ነበር። ተጠሪ የስር ከፍተኛው ፍ/ቤት የዋስትና መብታቸውን በመከልከል በሰጠው ብይን ቅር በመሰኘት ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታ አቅርበው በተደረገው የቃል ክርክር አመልካች ባቀረበው ክርክር ተጠሪ ጥፊተኛ ሆነው ቢገኙ ሉወሰድ የሚችለው ቅጣት ከባድ ላሆን እንደሚችል ግምት ከተወሰደ የክሶችን ብዙት እና ከባድነት መነሻ በማድረግ የዋስትና መብት ሉከለከለ ይገባል በማለት የተከራከረ ስለመሆኑ የስር ይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍ/ቤት መዛገብ አስቀርበን ተመልክተናል። በመሆኑም የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 67 መሰረት ዋስትናን ለማስከልከል የሚያስችል መከራከሪያ አልቀረበም ማለቱ አመልካች በስር ከፍተኛው ፍ/ቤትም ሆነ በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ዋስትናን በሚመለከት ያቀረበውን ክርክር ያላገናዖበ ሆኖ አግኝተነዋል። ስለሆነም አመልካች በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 67 መሰረት የተጠሪ የዋስትና መብት ሉከለከል ይገባል የሚል ክርክር ያቀረበ በመሆኑ የተጠሪ የዋስትና መብት በሁኔታ ሉከለከል ይገባል? ወይስ አይገባም? የሚለውን እንደሚከተለው መርምረነዋል።
የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 67 ድንጋጌ ተከሳሹ በዋስትና ወረቀት የተመለከቱትን ግዳታዎች የማይፈጽም የማይመስል እንደሆነ የዋስትና ጥያቄው ውድቅ ላደረግ እንደሚችል ይደነግጋል። ሆኖም ይህ ድንጋጌ ፍ/ቤቱ ግምቱን መነሻ የሚያደርግባቸው ሁኔታዎች ምን እንደሆኑ በግልጽ አላመላከተም። በመሆኑም አንድ ተከሣሽ የዋስትና መብት ቢከበርለት ግዳታውን የሚፈጽም እንደማይመስል ግምት የሚወሰደው በቂ እና ሕጋዊ ልባል በሚችል ምክንያት ላሆን ይገባል። እነዘህም ምክንያቶች ከተለያዩ ከባቢያዊ ሁኔታዎችና ከጉዲዩ ልዩ ባሕርይ አንፃር ፍርድ ቤቱ ሉገነዖበው የሚችለው ነጥብ ነው ተብል የሚታሰብ ነው።
በያዛነው ጉዲይ የስር ከፍተኛው ፍ/ቤት ተጠሪ አስቀድሞ ክስ የቀረበባቸውን የአዋጁን አንቀፅ 9/1/ሀ/ለ/2/ ድንጋጌን በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 113 በመለወጥ በአንቀፅ 9/1/ሀ/ለ በሁለት ክሶች እንዱከላከለ ብይን ሲሰጥ እንደምክንያት ያስቀመጠው በተጠሪ አድራጎት ደረሰ የተባለው የጉዲት መጠን ተጠሪ በተከሰሱበት የሕግ አንቀጽ የተቀመጠ አይደለም በሚል ነው። በተጠሪ የወንጀል ድርጊት ምክንያት ደረሰ የተባለው የጉዲት መጠን በዓቃቤሕግ ክስ ላይ የተገለጸው አይደለም የሚባል ከሆነ ተጠሪ በዋስትና ቢለቀቁ ዋስትናውን አክብረው ሉቀርቡ አይችለም የሚል ግምት የሚያሲዛ ሆኖ አላገኘነውም።
በመሆኑም ተጠሪ የዋስትና መብታቸው በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 67 መሰረት ሉከለከል አይገባም።
ሲጠቃለል የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ፍ/ቤት የተጠሪን የዋስትና መብት በመፍቀድ የሰጠው ውሳኔ ተገቢ ነው በማለት በውጤት ደረጃ ተቀብለነዋል። ስለሆነም ተከታዩን ውሳኔ በአብላጫ ድምጽ ሰጥተናል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. ሐምል 30 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ከላይ በፍርድ ሐተታው ላይ በተገለጸው ምክንያት በውጤት ደረጃ ጸንቷል።
በዘህ መዛገብ ከተሰየምን ዳኞች ውስጥ ሶስት ዳኞች የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የተጠሪ የዋስትና መብት በአዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 3/1 መሰረት ሉከለከል አይገባም በማለት የሰጠው ውሳኔ ተገቢ ነው ከሚል መደምደሚያ ላይ የደረስን በመሆኑ፤ ከችልቱ ዳኞች ውስጥ አራት ዳኞች አመልካች በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 67 መሰረት የተጠሪ የዋስትና መብት በሁኔታ ሉከለከል ይገባል በማለት መከራከሪያ ያቀረበ ቢሆንም የተጠሪ የዋስትና መብት በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 67 መሰረት ሉከለከል አይገባም ከሚል መደምደሚያ ላይ የደረስን በመሆኑ ተጠሪ በልላ ወንጀል የሚፈለጉ ካልሆነ በቀር በዋስ ሆነው ጉዲያቸውን ሉከታተለ ይገባል በማለት ወስነናል።
ትዔዙዛ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. ሐምል 30 ቀን 2011 ዓ.ም ተጠሪ እንዱያስይዘ ካዖዖው የዋስትና መጠን በተጨማሪ ተጠሪ ከሐገር እንዲይወጡ ታዝል። ይጻፍ፤ ትዔዙዘ ለሚመለከታቸው አካላት ይድረሳቸው።
የማይነበብ የሁለት ዲኛ ፊርማ አለበት።
ሰ/ኃ የሀሳብ ልዩነት እኔ ስሜ በተራ ቁጥር 3 ሥር የተሰየምኩት የችልቱ ዲኛ ከላልቹ የችልቱ ዳኞች በሃሣብ የሚለየኝ በፍሬ ጉዲዩ በአመልካች ተከላከል የተባለበት የህግ ድንጋጌዎች ዋስትና መብትን የሚያስነፍግ አይደለም በሚል በአብላጫው ድምጽ የተሰጠውን የውሣኔ ክፍል የምደግፍ በመሆኑ በዘህ ላይ ልዩነት የለኝም።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ያየው ፍ/ቤት በእርግጥ በሕግ ጉዲይ ዋስትና የሚያስነፍግ አይደለም በማለት ውሣኔ መስጠቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ሕግ ዋስትና በሚያስፈቅድ ጉዲይ ዋስትና መፍቀድ የሚችል ቢሆንም ዋስትና ሉፈቀድ አይገባም በማለት የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 67 ተጠቅሶ ክርክር ካለ ይህንንም መመልከት ይጠበቅበታል።
ነገር ግን የወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ 67 በሥር ፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ተነስቶ የነበረ እና ፍ/ቤቱ በዘህ ላይ ግራ ቀኙን ሳያከራክር እና ዓቃቤ ሕግ አለኝ የሚለውን የሕግ ግምት የሚያስጥለ ማስረጃዎችን እንዱያቀርብ፤ተከሣሽም በዐቃቤሕግ የተነሳበትን የሕግ ግምትን እና የቀረበበትን ማሰረጃ የሚያስተባብለ መከላከያ እንዱያቀርብ ሳይደረግ ሕጉ ዋስትና መብትን አያስከለክልም በሚል ዋስትና መፈቀደ ተገቢ ሆኖ ስላላገኘሁት፤እንዱሁም የፋዳራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሥር ፍ/ቤት ውሣኔን በመሻር ዋስትና ሉፈቀድ አይገባም ብል ሲወስን በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 67 የተነሳውን መከራከሪያ በሥር ፍ/ቤት የተነሳ በመሆኑ የሥር ፍ/ቤት አከራክሮ ውሣኔ ያላሳረፈበት መሆኑን ከጉዲዩ ከተረዲ ወደ ሥር ፍ/ቤት ተመልሶ በዘህ ድንጋጌ መሰረት ክርክር ተደርጎበት ውሣኔ እንዱሰጥ መመለስ ሲገባው በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 67 መሰረት የቀረበ ጥያቄ የለም በማለት ወደ ፋደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዲዩ በተጠቀሰው ድንጋጌ መሰረት ተገቢ ክርክር ተደርጎበት ከቀረበው ክርክር እና ማሰረጃ አንፃር ተጣርቶ ዋስትና የመፍቀድ ወይም የመከልከል ውሣኔ ላሰጥ የሚገባው የነበረ ሆኖ ይህ ሳያደረግ የሥር ፍ/ቤትን ውሣኔ በማጽናት መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመ ሆኖ ስላገኘሁት ከወዱሁ በሥር ፍ/ቤት የወ/መ/ሥ/ሥ/ቁ.67 ላይ የተሰጠ ውሣኔ ሳይኖር በዘህ ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩ ባለበት ደረጃ የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 67 ድንጋጌን በማንሳት ዋስትና ሉፈቀድ ይገባል በሚል በአብላጫው ድምጽ ሉወሰን አይገባም ነበር በማለት ከባልደረቦቼ በሃሣብ ተለይቻለሁ።
የማይነበብ የአንድ ዲኛ ፊርማ አለበት ሰ/ኃ
ስማችን በሁለተኛ እና በአራተኛ መስመር ላይ የተጠቀሰው ዳኞች ከወንጀል ህግ ሥነሥርዓት ቁጥር 67 አንፃር በተሰጠው የውሳኔ ክፍል የምንስማማ ሲሆን አብላጫው ድምፅ የአዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀፅ 3(1) ድንጋጌ አተረጓጎምን አስመልክቶ በጠቀሰው ምክንያት እና በደረሰበት ድምዲሜ ያልተስማማን በመሆኑ የልዩነት ሀሳባችንን በሚከተለው መልኩ አስፍረናል።
በመሰረቱ በአብላጫ ድምፅም እንደተገለፀው በዋስ የመለቀቅ መብት ህገ መንግስታዊ መርህ ሲሆን በህግ በተደነገጉ ልዩ ሁኔታዎች ፍርድ ቤት ዋስትና ላለመቀበል የሚችል ለመሆኑ የኢ.ፍ.ዳ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀፅ 19(6) ድንጋጌ ያስገነዝባል። የዋስትና መብትን በተመለከተ በህግ በልዩ ሁኔታ ገደብ ከተጣለባቸው ሁኔታዎች ውስጥ አንደ ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ ወይም የተከሰሱ ሰዎችን የሚመለከት ነው። ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ የተሻሻለው የፀረ ሙስና ልዩ የስነ ስርዓትና የማስረጃ ህግ አዋጅ ቁጥር 434/1997 አንቀፅ 4(1) ከአስር ዓመት በላይ ሉያስቀጣ በሚችል የሙስና ወንጀል የተከሰሰ ሰው በዋስትና ሉለቀቅ እንደማይችል ይደነግጋል።
ይህንኑ አዋጅ ለማሻሻል የወጣው የተሻሻለው ልዩ የፀረ ሙስና የሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ህግ /ማሻሻያ/ አዋጅ ቁጥር 882/2007 በአንቀፅ 3(1) ስር ከአስር ዓመት በላይ በሆነ ፅኑ እስራት በሚያስቀጡ ወንጀልች የተከሰሰን ሰው ጉዲይ በተመለከተ ከላይ የሰፈረውን ድንጋጌ ቃል በቃል ከደገመ በኋላ ቀጥል ባለው ዓረፍተ ነገር ከአስር ዓመት በታች በሆነ እስራት የሚያስቀጡ ወንጀልችን አስመልክቶ አዱስ ሀሳብ አስፍሯል። ይህም ከአራት ዓመት በላይ እና ከአስር ዓመት በታች የሚያስቀጡ ተደራራቢ ወንጀልች ሲኖሩ እየተደመሩ ከአስር ዓመት በላይ የሚያስቀጣ ከሆነ ዋስትና ይከለከላል የሚል ነው።
ግራ ቀኙን ለዚህ ሰበር ችልት ክርክር ያበቃውም ይኸው በማሻሻያ አዋጁ ውስጥ የተጨመረው አዱስ ሀሳብ አተረጓጎምን የሚመለከት እንጂ ክስ በቀረበበት ወይም ተከላከል በተባለበት አንቀፅ ስር አማራጭ ቅጣት በተቀመጠ ጊዜ ለዋስትና ሲባል የትኛው ቅጣት መታየት አለበት የሚል ባለመሆኑ ለቀረበው ጉዲይ እንደ ዋና ጭብጥ ተደርጎ በአብላጫው ድምፅ መያዙ አግባብ አይመስለንም። ያም ሆኖ ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ ተከሳሹ ለሚያቀርበው የዋስትና ጥያቄ ፍርድ ቤቶች ተከሳሹ በቀረበበት የሙስና ወንጀል ክስ ጥፋተኛ ሆኖ ቢገኝ ሉጣልበት የሚችለውን የቅጣት ጣሪያ መነሻ በማድረግ ውሳኔ ሉሰጡ እንደሚገባ ይኸው ችልት በሰ/መ/ቁ/63344 ላይ አስገዲጅ የህግ ትርጉም የሰጠ በመሆኑ ዝቅተኛው ቅጣት የሚያዝበት አግባብ የለም። በእርግጥ አብላጫው ድምፅ ይህ የሰበር ችልቱ ትርጉም አሁን ለቀረበው ጉዲይ ተፈፃሚነት የለውም ብሎል። ሆኖም ትርጉሙ የተሰጠው የሙስና ወንጀልን ልዩ ባህሪ መሰረት በማድረግ ከዋስትና ጋር በተያያዘ መነሻ ላደረግ የሚገባን ነጥብ ያመለከተ እንጂ የቅጣት ዓይነትን ለይቶ የተሰጠ ባለመሆኑ አሁን ለቀረበው ጉዲት ተፈፃሚነት የለውም ልባል አይገባም። እናም እነዚህ ነጥቦች ታሳቢ ተደርገው የቀረበውን ጉዲይ በሚከተለው መልኩ ተመልክተናል።
በፍዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አተረጓጎም መሰረት በድንጋጌው ውስጥ የተጠቀሰው አራት ዓመት መነሻ ቅጣታቸው አራት ዓመት እና በላይ የሆኑ ወንጀልችን የሚመለከት ነው የሚል ሲሆን በተጠሪ ጠበቃ በኩል ተመሳሳይ አረዲድ መኖሩን ከቀረበው ክርክር መረዲት ይቻላል። አመልካች በበኩለ ከአራት ዓመት በላይ ተብል የተጠቀሰው መነሻ ቅጣትን ሳይሆን የእያንዲንደን ተደራራቢ ወንጀልችን ጣሪያ ቅጣት የሚመለከት ነው የሚል ነው።
የድንጋጌውን አተረጓጎም ልዩነት በአግባቡ ለመፍታት ይረዲ ዘንድ ጉዲዩን ከሶስት አበይት ነጥቦች አኳያ ማየቱ ተገቢ ይሆናል። የመጀመሪያው ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ የዋስትና መብትን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች እድገታዊ አመጣጥን የሚመለከት ነው።
በኢ.ፍ.ዳ.ሪ. መንግስት የሙስና ወንጀልን በተመለከተ ልዩ የሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ህግ መጀመሪያ የታወጀው በአዋጅ ቁጥር 236/1993 ነው። ይህ አዋጅ በታወጀ በ20 ቀኑ በአዋጅ ቁጥር 239/1993 የተሻሻለ ሲሆን ማሻሻያ አዋጁ በአንቀፅ 2 ስር በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ የተያዘ ሰው የዋስትና መብት የላለው መሆኑን ደንግጓል። ይህንኑ አዋጅ ለማሻሻል የወጣው አዋጅ ቁጥር 434/1997 ደግሞ ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ የዋስትና መብት የከለከለው ከአስር ዓመት በላይ በሆነ እስር ሉያስቀጣ በሚችል የሙስና ወንጀል የተጠረጠረ ወይም የተከሰሰን ሰው መሆኑን በአንቀፅ 4 ስር ደንግጓል። በመጨረሻም ይህንን አዋጅ ለማሻሻል የወጣው አዋጅ ቁጥር 882/2007 ደግሞ ከአስር ዓመት በታች በሆነ እስራት የሚያስቀጡ ሆነው ነገር ግን ከአራት ዓመት በላይ እና ከአስር ዓመት በታች በሆነ እስራት በሚያስቀጡ ተደራራቢ ወንጀልች የተከሰሰ ሰው የተደራራቢ ወንጀልቹ ድምር ቅጣት ከአስር ዓመት በላይ የሚያስቀጣ በሆነ ጊዜ ዋስትና የሚከለከል መሆኑን ደንግጓል።
የድንጋጌዎቹ የእድገት አመጣጥ የሚያሳየው መጀመሪያ በሙስና ወንጀል የተጠረጠረ ወይም የተከሰሰ ሰው ሙለ በሙለ ዋስትና ተከለከለ፤ ቀጥል ከአስር ዓመት በላይ በሆነ እስራት ሉያስቀጣ በሚችል ወንጀል የተጠረጠረ ወይም የተከሰሰ ሰው ብቻ ተከለከለ፤ በመጨረሻም ከአስር ዓመት በታች በሆነ እስራት የሚያስቀጡ ተደራራቢ ወንጀልች የተከሰሰ እና የተደራራቢ ወንጀልቹ ድምር ቅጣት ከአስር ዓመት በላይ የሆነ ተከሳሽ ብቻ እንዱከለከል መደረጉን ያስገነዝባል። ከዚህ የእድገቱ አመጣጥ አንፃር አዋጅ ቁጥር 882/2007 በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 434/1997 ከአስር ዓመት በታች በሆነ እስራት የሚያስቀጡን ወንጀልችን በተመለከተ በተቃራኒ ንባብ እውቅና ተሰጥቶት የነበረውን የዋስትና መብትን በልዩ ሁኔታ የሚገድብ እንጂ አብላጫው ድምፅ በገለፀው አኳኋን የዋስትና መብትን በተሻለ የሚያሰፋ ድንጋጌ አይደለም። ከልዩ ህጎች የሚጠበቀው ዋስትና መፍቀጃ ምክንያቶችን መዘርዘር ሳይሆን በህገ መንግስቱ የተረጋገጠው መብት ሉገደብ የሚችልበትን ልዩ ሁኔታን ብቻ ለይቶ ማስቀመጥ ነው። ከተጠቀሱ አዋጆች የእድገት ሂደትም መገንዘብ የሚቻለው ከጊዜ ወደ ጊዜ ዋስትና የሚያስከለክለ ልዩ ሁኔታዎች ብቻ እየተለዩ መምጣቸውን ነው።
አዋጅ ቁጥር 434/1997 ከአስር ዓመት በላይ በሆነ እስራት ሉያስቀጣ በሚችል የሙስና ወንጀል የተከሰሰ ሰው በዋስትና ሉለቀቅ እንደማይችል ከመደንገጉ ውጭ ከአስር ዓመት በታች በሆነ እስራት በሚያስቀጣ ወንጀል ስለ ተከሰሰ ሰው ያለው ነገር የለም። እናም ከፍርድ በፊት ያለመታሰር መብት ህገ መንግስታዊ መርህ በመሆኑ የድንጋጌውን ተቃራኒ ንባብ በመውሰድ ከአስር ዓመት በታች በሆነ እስራት በሚያስቀጣ ወንጀል የተጠረጠረ ወይም የተከሰሰ ሰው በመደበኛው የወንጀል ህግ ሥነ-ሥርዓት ሉቀርቡ የሚችለ የዋስትና መቃወሚያዎች እንደተጠበቁ ሆነው ያለ አንዲች ቅድመ ሁኔታ በዋስትና የመለቀቅ መብት ይኖረዋል ማለት ይቻላል።
ሆኖም ከአስር ዓመት በታች በሆነ እስራት የሚያስቀጡም ሆነው በርካታ ተደራራቢ ወንጀልች ሉፈፀሙ የሚችለበት እድል መኖሩ በመዘንጋቱ በአዋጁ ሽፋን አልተሰጠውም።
እናም ከድንጋጌው ይዘት መረዲት የሚቻለው ከዋስትና አንፃር የአዋጅ ቁጥር 882/2007 ዋነኛ ትኩረት ይህንኑ ከአስር ዓመት በታች በሆነ እስራት በሚያስቀጡ ተደራራቢ ወንጀልች የተከሰሱ ሰዎችን ጉዲይ መልክ ማስያዝ ነው ብል መውሰድ ይቻላል።
የድንጋጌዎቹ የእድገት አመጣጥ ይህን የሚመስል ከሆነ ቀጥል ላታይ የሚገባው ሁለተኛው አበይት ነጥብ የድንጋጌው የቃላት አጠቃቀም ዘዬ ነው። ከላይ እንደተመለከተው የድንጋጌው ዋና ዓላማ ከአስር ዓመት በታች በሆነ እስራት ሉያስቀጡ በሚችለ ተደራራቢ ወንጀልች የተከሰሱ ሰዎችን የዋስትና ሁኔታ መምራት ነው። ይህ ከሆነ በድንጋጌው ውስጥ “ከአራት ዓመት በላይ እና ከአስር ዓመት በታች የሚያስቀጡ ተደራራቢ ወንጀልች” የሚለው አገላለፅ ለምን አስፈለገ የሚለው በአግባቡ ሉጤን የሚገባው ነጥብ ይሆናል። ከድንጋጌው የቃላት አጠቃቀም በጥቅለ መገንዘብ የሚቻለው የህግ አውጭው ዓላማ ከአስር ዓመት በታች በሆነ እስራት በሚያስቀጡ ተደራራቢ ወንጀልች የተከሰሱትን ሁለንም ተከሳሾች ዋስትና መከልከል አለመሆኑን ነው። ይልቁንም ዋስትና መከልከል የተፈለገው እያንዲንደ ተደራራቢ ወንጀል ከአራት ዓመት በላይ እና ከአስር ዓመት በታች በሆነ እስራት የሚያስቀጣ ሆኖ የተደራራቢ ወንጀልቹ ድምር ቅጣት ከአስር ዓመት በላይ በሆነ ወንጀል የተከሰሱትን ሰዎችን ብቻ ነው።
የድንጋጌው መልዕክት ይህ ከሆነ ከአራት ዓመት በላይ የተባለው የሚያመለክተው የተደራቢ ወንጀለን መነሻ ቅጣት ነው ወይስ ጣሪያ ቅጣት የሚለው ቀጥል የሚታይ ሶስተኛው አበይት ነጥብ ይሆናል። የዚህን ሀረግ ትክክለኛ ትርጉም ለመረዲት የሙስና ወንጀልን በሚደነግገው መደበኛ የወንጀል ህጉ እና በአዋጅ ቁጥር 881/2007 ስር ለእያንዲንደ የሙስና ወንጀል የተቀመጠውን ቅጣት መጠን በጥንቃቄ በመፈተሽ ከላይ ከሰፈረው ድንጋጌ ተግባራዊ አፈፃፀም ጋር አዛምድ ማየትን ይጠይቃል።
በዚሁ መሰረት በወንጀል ህጉም ሆነ በአዋጅ ቁጥር 881/2007 ውስጥ መነሻ ቅጣቱ አራት ዓመት እስራት የሆነ የሙስና ወንጀል የለም። መነሻ ቅጣታቸው ከአራት ዓመት በላይ እና ከአስር አመት በታች የሆኑት ሁለት ብቻ ናቸው። አንደ መነሻው አምስት አመት ሲሆን ላላኛው ደግሞ መነሻ ቅጣቱ ሰባት ዓመት የሆነ ነው። የእነዚህ ሁለቱ ቅጣቶች ጣሪያ ቅጣት እንደ ወንጀለ ዓይነት የሚለያይ ቢሆንም መዲረሻው ግን ከአስራ አምስት እስከ ሃያ አምስት ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ነው።
በዚሁ አግባብ በድንጋጌው ውስጥ “ከአራት ዓመት በላይ” የሚለው ሀረግ የሚያሳየው የእያንዲንደን ተደራራቢ ወንጀል መነሻ ቅጣት ነው የሚባል ከሆነ ጣሪያ ቅጣቱ ቢያንስ አስራ አምስት ዓመት ፅኑ እሰራት ይሆናል። ጉዲዩ ይህ ከሆነ በአዋጅ ቁጥር 434/1997 አንቀፅ 4(1) እና ይህ ሰበር ችልት በሰ/መ/ቁ/63344 ላይ ከሰጠው አስገዲጅ ትርጉም አኳያ የድንጋጌው ጣሪያ ቅጣት ከአስር ዓመት በላይ በመሆኑ እና በራሱ ከመነሻው ዋስትናን የሚያስከለክል በመሆኑ ስለ ተደራራቢ ወንጀል ማንሳት አያስፈልግም። በመሆኑም “ከአራት ዓመት በላይ” የሚለው ሀረግ መነሻ ቅጣትን የሚያሳይ ነው የሚለው አተረጓጎም የድንጋጌውን ተግባራዊ አፈፃፀም ትርጉም የሚያሳጣ በመሆኑ የሚያስኬድ አይደለም።
በአንፃሩ መነሻ ቅጣታቸው ምንም ይሁን ምን ጣሪያ ቅጣታቸው ግን ከአራት ዓመት በላይ እና ከአስር ዓመት በታች የሆኑ በአዋጁ ብቻ ከሃያ አንድ በላይ ድንጋጌዎች እንዱሁም ከአራት ዓመት በታች ጣሪያ ቅጣት ያላቸው ወደ አራት ድንጋጌዎች መኖራቸውን ለመገንዘብ ተችሎል። በተለያየ ምክንያት አንድን የህግ ድንጋጌን መተርጎም ቢያስፈልግ ከመተርጎሚያ ስልቶች ውስጥ አንደ ህጉን ማወጀ ካስፈለገበት መሰረታዊ ዓላማ አንፃር ድንጋጌው ተግባራዊ ላሆን በሚችልበት አግባብ መተርጎም(Purposive Interpretation) ስለመሆኑ የህግ አተረጓጎም መሰረተ ሀሳብ ያስገነዝባል።
ከዚህ አኳያ የህግ አውጭው ዓላማ ነው ተብል ከላይ የተመለከተው ተግባራዊ ላሆን እና በአግባቡ ከግብ ሉደርስ የሚችለው በድንጋጌው ውስጥ “ከአራት ዓመት በላይ” ተብል የተጠቀሰው ሀረግ የእያንዲንደን ተደራራቢ ወንጀልች ጣሪያ ቅጣት የሚመለከት ነው በሚል ሲተረጎም ስለመሆኑ መረዲት ይቻላል።
የድንጋጌው ትርጉም ይህ ከሆነ የአሁን ተጠሪ እንዱከላከለ ብይን በተሰጠባቸው እያንዲንደ ድንጋጌ ስር ያለው ጣሪያ ቅጣት ከአስር ዓመት የማይበልጥ ፅኑ እስራት ሲሆን የሁለቱ ተደራራቢ ወንጀል ጠቅላላ ቅጣት ከአስር ዓመት በላይ በመሆኑ በፀረ ሙስና ልዩ የሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ህግ(ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀፅ 3(1) መሰረት ዋስትና የሚያስከለክል ነው። እናም የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ አረዲድ የህጉን መንፈስ የተከተለ በመሆኑ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የተከተለው አተረጓጎም ከዚህ አኳያ ሉቃና ይገባ ነበር በማለት ከስራ ባልደረቦቻችን የተለየ አቋም ይዘናል።
የማይነበብ የሁለት ዲኛ ፊርማ አለበት።
ሰ/ኃ የሰ.መ.
ሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- ሀለቃ ንጉሴ አብርሃ ተጠሪ፡- የትግራይ ክልል ፍትሕ ቢሮ መዛገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ነው። በመሆኑም መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
የሰበር አቤቱታው ላቀርብ የቻለው አመልካች ሰኔ 07 ቀን 2011 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ በትግራይ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የቃፍታ ሁመራ ወረዲ ፍ/ቤት በመ.ቁ 1800/11 በቀን 16/07/2011 ዓ.ም አመልካች በሕግ እንደሚፈለግ አውቆ ሆነ ብል ሲደበቅ የነበረ እና ሕግን በተከተለ የመጥሪያ ስነ ስርዓት መጥሪያ የተላከለት መሆኑ ስለተረጋገጠ ጉዲዩ ዲግም እንዱታይለት ያቀረበው አቤቱታ ተገቢ አይደለም ሲል የሰጠው ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ. ሚያዛያ 28 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠው ትዔዙዛ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
ጉዲዩ በላለሁበት ታይቶ የተሰጠ ውሳኔ ይነሳልኝ በሚል የቀረበን አቤቱታ የሚመለከት ነው።
አመልካች በስር ፍ/ቤት ባቀረቡት አቤቱታ በቃፍታ ሁመራ ቀበላ ዓዱሹሁ ነዋሪና ባለትዲር እና ገበሬ መሆናቸውን፤ ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው ወደ ሕግ አካል ቀርበው የማያውቁ መሆኑን፤ የመጥሪያ ትዔዙዛ ሳይሰጣቸው በስርቆት ወንጀል የአራት ዓመት ፍርደኛ ነህ ተብለው በቀን 25/06/2011 ዓ.ም ከመኖሪያ ቤታቸው በፕሉስ የተያዘ መሆኑን በመግለጽ ከሕግ ውጪ በላለሁበት ታይቶ የተሰጠው ውሳኔ ተነስቶ ጉዲያቸው ባለበት እንዱታይ ይወሰንላቸው ዖንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
ተጠሪ በሰጠው መልስ አመልካች የተከሰሱበት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 669/3/ለ ድንጋጌ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 162 መሰረት በላለበት መታየት የሚችል መሆኑን፤ በፕሉስ መጥሪያ እንዱቀርቡ ታዜ ሉቀርቡ ያልቻለ መሆኑን፤ በአድራሻቸው እንደላለ የሚገልጽ ማስረጃ አመልካች ከሚገኙበት አድራሻ የቀረበ መሆኑን፤ በጋዚጣ ጥሪ ተደርጎላቸውም ስላልቀረቡ ጉዲያቸው በላለበት ታይቶ ውሳኔ ያገኘ መሆኑን በመግለጽ አቤቱታው ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
ፍ/ቤቱም ጉዲዩን መርምሮ አመልካች በተደጋጋሚ እንዱያቀርቡ ታዜ በአድራሻቸው እንደላለ ማስረጃ ቀርቧል፤ በመቀጠልም በመቃልህ ጋዚጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ሉቀርቡ አልቻለም፤ አመልካች በክሱ ላይ በተገለጸው እና መደባይ ዙና ወረዲ ቀበላ ዓዱ ጸጉራ ቀጠና ወይና አምባ በሚባለው አድራሻ እንዲለ እና ለግዚው ተሰውረው እንደነበር የሚገልጽ ማስረጃ ከቀበላው ጸጥታ አስተዲደር ቀርቧል፤ ይህ ማረጋገጫም አመልካች በሕግ የሚፈለጉ መሆኑን እያወቁ ሆን ብለው ሲደበቁ እንደነበረ የሚያሳይ ነው፤ ዓዱ ጎሹ በሚባል ቦታ ነው የነበርኩት በማለት የሚከራከሩ ቢሆንም ማስረጃ አላቀረቡም፤
ለአመልካች የደረሰው መጥሪያ ሕግን የተከተለ የመጥሪያ ስነ ስርዓት በመሆኑ አቤቱታቸው ተቀባይነት የለውም በማለት ውድቅ አድርጎታል። አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ ያቀረቡ ቢሆንም አቤቱታቸው በትዔዙዛ ውድቅ ተደርጓል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም መሰረታዊ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል ሲሆን ይዖቱም፡- አመልካች ገበሬ ባለትዲር እና የልጆች አባት መሆኔ በስር ፍ/ቤት ተረጋግጧል፤
አመልካች በወንጀል ጥፊተኛ መባላን ያወቅኩት በቀን 25/06/2011 ዓ.ም በፕሉስ ከተያዛኩ በኋላ ነው፤
ከዘህ ቀን በፉት ለመርማሪ ፕሉሰ የሰጠሁት ቃል የለም ክስ እንደቀረበብኝ አልተነገረኝም፤ በምኖርበት አካባቢም የተለጠፈ መጥሪያ የለም፤ አመልካች በመርማሪ ፕሉስ ፉት ቀርቤ ትክክለኛ ስሜን እና አድራሻዬን ባልሰጠሁበት ሁኔታ እና ትክክለኛ ስሜም አለቃ ንጉሰ አብርሃ ተክለ አብዛጊ ሆኖ ሳለ አቶ ንጉሰ አብርሃ ተክለ ተብል በመቃልህ ጋዚጣ መታወጁ አግባብ አይደለም፤ በስር ፍ/ቤት የተሰጠው ፍርድ አመልካችን የሚመለከት መሆኑ ሳይረጋገጥ በላለሁበት የተሰጠው ፍርድ ተነስቶ ጉዲዩ ባለሁበት እንዱታይ ያቀረብኩትን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች በተጠቀሰው አድራሻ የሚገኝ ስለመሆኑ ፕሉስ ቃል ከሰጠ ያስመዖገበው አድራሻ ስለመኖሩ እንዱሁም በአድራሻው የማይገኝ ከሆነም ማረጋገጫ እንዱቀርብ ሳይደረግ፤ የጋዚጣ ጥሪውም በአመልካች ማመልከቻ በተጠቀሰው አግባብ ስለመደረጉ ሳይረጋገጥ ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ መደረጉ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ. ከሰጠው ውሳኔ ጋር በማገናዖብ ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ በዘህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል። ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የተጠሪ መልስ ይዖት በአጭሩ፡- ስነ ስርዓቱ በሚያዖው መሰረት መጥሪያ ለአመልካች እንዱደርሰው ተደጋጋሚ ትዔዙዛ ለፕሉስ ተልኳል፤ ፕሉስ ለፍ/ቤቱ በሰጠው ምላሽ አመልካች በአድራሻው እንደላለ እና ሉያቀርቡት እንደማይችለ በመግለጽ ምላሽ በመስጠቱ በጋዚጣ እንዱጠራ ተደርጓል፤ አመልካች በጋዚጣ ተጠርቶ ስላልቀረበ ጉዲዩ በላለበት ታይቷል፤ አመልካች በአድራሻው የነበረ መሆኑን በማስረጃ አላረጋገጠም፤ አመልካች በላለበት ጉዲዩ ታይቶ የተሰጠው ውሳኔ የመጥሪያ አሰጣጥ ስርዓትን የተከተለ በመሆኑ የስር ፍ/ቤቶች የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ የሰጡት ውሳኔ ሉጸና ይገባል የሚል ነው። አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው። ይህ ችልትም በሰበር አጣሪ ችልት ለተያዖው ጭብጥ ምላሽ ከመሰጠቱ በፉት ከመነሻውም ቢሆን አመልካች የተከሰሱበት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 669/3/ለ በላለበት የሚታይ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዛ ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምሮታል።
በመሰረቱ የተከሰሱ ሰዎች በሕግ ከተጠበቁላቸው መብቶች መካከል አንደ የተከሰሱበት ጉዲይ በፍርድ ቤት ሲታይ በችልት ተገኝቶ የቀረበባቸውን ማስረጃ የመመልከት፣ የቀረበባቸው ምስክሮችን የመጠየቅ፣ ለመከላከል የሚያስችላቸውን ማስረጃ የማቅረብ ወይም የማስቀረብ እንዱሁም ምስክሮቹ ቀርበዉ እንዱሰሙላቸው የመጠየቅ መብት ነዉ። ኢትዮጲያ የተቀበለችው ዓለም አቀፍ የሲቪል እና የፕለቲካ መብቶች ስምምነት አንቀጽ 14 ድንጋጌም የተከሰሱ ሰዎች ፍትህ የማግኘት እና በገለልተኛ ፍ/ቤት የመዲኘት እና በአካል ተገኝቶ የመከራከር መብት እንዲላቸው ይደነግጋል።
ከላይ የተመለከቱት ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው በልዩ ሁኔታ በግልጽ በሕግ ከተመለከቱትና ከተፈቀደት በስተቀር በመርህ ደረጃ የወንጀል ክስ የሚታየዉም ሆነ ክርክር ተደርጎ ዉሳኔ የሚሰጠዉ ተከሳሽ በችልት በተገኘበት ነዉ። በልዩ ሁኔታ ሕግ ፈቅድ ጉዲዩ ተከሳሽ በላለበት የሚታየዉም ከአሥራ ሁለት ዓመት በማያንስ ጽኑ እሥራት የሚያስቀጡ ወይም በመንግስት ኢኮኖሚ ላይ የሚፈጸሙ ወንጀልች ሆነዉ በጽኑ እስራት ወይም ከብር 5,000 በላይ የሚያስቀጡ ከባድ ወንጀልችን የሚመለከቱ ወንጀልችን ብቻ ስለመሆኑ ከወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 162(2) ድንጋጌ ይዖት መገንዖብ ይቻላል። ሕጉ እነዘህን ወንጀልች አስመልክቶ በልዩ ሁኔታ ተከሳሽ በላለበት እንዱታዩ የፈቀደበትና አብዙኛዎችን ወንጀልች ተከሳሽ እስካልተገኘ ድረስ ወይም በአግባቡ መጥሪያ ደርሶት በችልት ቀርቦ የመከራከር መብቱን እስካልተወ ድረስ ጉዲዩ እንዲይታይ የደነገገበት ዓላማ በአንድ በኩል ተከሳሽ ከባድ ወንጀል ፈጽሞ ከፍትሕ በመሰወሩ የወንጀለ ተጎጂዎችን ፍትሕ የማግኘት መብት ለማረጋገጥ ሲሆን በልላ በኩል ደግሞ ሕጉ ለይቶ ባስቀመጣቸው ከባድ ወንጀልች ውጪ ባለት ጉዲዮች የተከሳሽ በችልት ተገኝቶ የመከራከር መብት ከሚጣስ ይልቅ ተከሳሽ እስኪገኝ ድረስ የፍርድ ሂደቱ እንዲይካሄድ ስለመሆኑ ከላይ በዛርዛር ከተደነገጉት ድንጋጌዎች ይዖት መገንዖብ ይቻላል።
በያዛነው ጉዲይ አመልካች የተከሰሱበት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 669/3/ለ ድንጋጌ ከአንድ ዓመት በማያንስ ቀላል እሥራት ወይም ከአሥራ አምስት ዓመት የማይበልጥ ጽኑ እሥራት የሚያስቀጣ ነው። ይህ ድንጋጌ አማራጭ ቅጣቶችን የያዖ ሲሆን በዘህ ድንጋጌ መሰረት ክስ የቀረበበት ተከሳሽ አንድም በቀላል እሥራት አልያም በአማራጭ ከተቀመጠው የጽኑ እሥራት ቅጣት ከ12 ዓመት በታች ወይም ከአሥራ ሁለት ዓመት በላይ በሆነ ጽኑ እሥራት ሉቀጣ እንደሚችል እንገነዖባለን። በመሆኑም በዘህ ድንጋጌ መሰረት የተከሰሰ ተከሳሽ አስመልክቶ ተመራጭ የሚሆነው የፍርድ ሂደት የወንጀለ ተጎጂዎችን ፍትሕ የማግኘት መብት ለማረጋገጥ ሲባል ከአሥራ ሁለት ዓመት በላይ በሆነ ጽኑ እሥራት ሉቀጣ እንደሚችል ከወዱሁ ግምት በመውሰድ ጉዲዩን በላለበት ማየት ነው? ወይስ የተከሳሽ በችልት ተገኝቶ የመከራከር መብት ከሚጣስ ይልቅ ተከሳሽ እስኪገኝ ድረስ የፍርድ ሂደቱ እንዲይካሄድ ማድረግ?
የሚለው በጥንቃቄ ታይቶ ምላሽ ሉሰጠው ይገባል።
በአካል ፍ/ቤት ተገኝቶ የመከራከር መብት ለተከሰሱ ሰዎች በሕገመንግስቱ አንቀጽ 20/4 እና ኢትዮጲያ በተቀበለችው ዓለም ዓቀፍ የሲቪል እና የፕለቲካ መብቶች ስምምነት አንቀጽ 14 ላይ የተጠበቀላቸው መሰረታዊ መብት በመሆኑ፤ አመልካች የተከሰሱበት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 669/3/ለ ከባድ የስርቆት ወንጀል ሕግ አውጪው ሉያሳካው ያሰበው ልዩ ዓላማ ኖሮት ለብቻው የሕግ ማዔቀፍ የወጣለት ሳይሆን በመደበኛው የወንጀል ሕግ የተደነገገ በመሆኑ፤ ይህ ድንጋጌም አማራጭ ቅጣቶችን የየዖ በመሆኑ፤ በዘህ ድንጋጌ መሰረት አመልካች ጥፊተኛ ቢባለ በቀላል እሥራት፤ ከ12 ዓመት በታች በሆነ ጽኑ እሥራት ወይም ከአሥራ ሁለት ዓመት በላይ በሆነ ጽኑ እሥራት ሉቀጡ የሚችለ በመሆኑ ተመራጭ የሚሆነው የፍርድ ሂደት አመልካች በድንጋጌው የተቀመጠው ከፍተኛ ቅጣት ሉቀጡ ይችላለ ብል ከወዱሁ በማሰብ ጉዲዩን በላለበት እንዱታይ ማድረግ ሳይሆን የተከሳሽ በችልት ተገኝቶ የመከራከር መብት ከሚጣስ ይልቅ ተከሳሽ እስኪገኝ ድረስ የፍርድ ሂደቱ እንዲይካሄድ ማድረግ ነው። በመሆኑም አመልካች የተከሰሱበት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 669/3/ለ ተከሳሹ በላለበት ላታይ የሚችል አይደለም። የስር ፍ/ቤት ጉዲዩን በዘህ አግባብ በማየት አመልካች የተከሰሱበት የሕግ ድንጋጌ በላለበት የሚታይ አይደለም በማለት አመልካች እስኪገኙ ድረስ የፍርድ ሑደቱ እንዲይካሄድ ማድረግ ሲገባው አመልካች የተከሰሱበት ድንጋጌ በላለበት የሚታይ እንደሆነ ግምት በመውሰድ የሰጠው የጥፊተኝነትም ሆነ የቅጣት ውሳኔ እና አመልካች ጉዲያቸው ባለበት ያቀረቡትን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ስለሆነም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ.
ሚያዛያ 28 ቀን 2011 ዓ.ም በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 195/2/ለ/2 መሰረት ተሽሯል።
ከላይ በፍርድ ሐተታው ላይ በተገለጸው ምክንያት አመልካች የተከሰሱበት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 669/3/ለ ድንጋጌ ተከሳሽ በላለበት ላታይ የሚችል አይደለም በማለት ወስነናል።
ስልጣን ያለው ላላ ችልት አመልካች ባለበት ክርክሩን እንዱያይ እና ዓቃቤሕጉም ክሱን ስልጣን ላለው ፍ/ቤት እንዱያቀርብ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 202 መሰረት ተወስኗል።
ትዔዙዛ
-የሚመለከተው ማረሚያ ቤት አመልካች በላለበት ታይቶ በስር ፍ/ቤቶች የተሰጠው የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ ተሽሮ አመልካች ባለበት ጉዲያቸው እንዱታይ የተወሰነ መሆኑን አውቆ በዘህ ችልት እንዱያስይዘ የተወሰነውን የዋስትና ገንዖብ ማስያዙቸው ሲረጋገጥ በልላ ጉዲይ የማይፈለጉ መሆኑን አረጋግጦ ከእሥር እንዱለቅ ታዝል።
-መዛገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዖግቷል። ይመለስ።
No topics extracted.