አንድ ድርጊት ከመፈፀሙ በፉት፣ ሲፈፀም ወይም ድርጊቱ ከተፈፀመ በኃላ ዐቃቤ ህግ ስላቀረበው ክስ ማስረጃ ይሆነኛል በማለት በሕጉ አግባብ ያቀረበውን ማስረጃ በማስረጃነት ላቀርብ የማይችልና ተቀባይነት የላለው (Inadmissible evidence) ነው የሚል ግልፅ ክልከላ የሚያደርግ የሕግ ድንጋጌ በላለበት የማስረጃው አስረጂነት ዋጋ ሳይታይና ሳይመዖን በደፈናው ማስረጃው ከተከሳሾች ጋር አብሮ ተከሳሽ የነበረ ነው፤ የተከሳሾችን የመከላከል መብት ይጎዲል በሚል ምክንያት ተቀባይነት የላለው ነው በማለት ውድቅ ማድረግ የማስረጃ ተቀባይነት፤አግባብነትና ምዖና መርህን፤ የክርክር አመራርና የዲኝነት አሰጣጥ ስርዓትን ያልተከተለ ስለመሆኑ ወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 108-122፣የሙስና ወንጀልች አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 8 እና የተሻሻለው የጸረ ሙስና ልዩ የሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 434/1997 አንደተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 41፣43
No summary available.
ሐምል 15 ቀን 2011 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው በዔውቀት በላይ እንዲሻዉ አዲነ ሃይለ ነጋሽ እስቲበል አንደዓለም አመልካች:- የፋዳራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተጠሪዎች፡-
ይህ የሰበር አቤቱታ ላቀርብ የቻለው አመልካች መስከረም 22 ቀን 2011 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ መጋቢት 18 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠው ብይን በማጽናት የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ሐምል 12 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለቱ ነው።
ጉዲዩ በሙስና ወንጀል ተከሶ የነበረን ሰው ምስክር ስለማድረግ በሚመለከት የቀረበ የማስረጃን ተቀባይነት ( Admissibility ) ክርክርን የሚመለከት ነው። የአሁን አመልካች በአሁን ተጠሪዎች ላይ በስር ፍ/ቤት አቅርቦባቸው የነበሩት ክሶች ሶስት ሲሆኑ ይዖታቸውም፡- 1ኛ ክስ፡- ተጠሪዎች የአዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 32/2 ድንጋጌን በመተላለፍ 1ኛ ተጠሪ የብሓራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግልት ሰራተኛነቱን በመጠቀም ለሀገራዊ ስራ ነው በሚል ሙለጌታ ተመስገን እና ኑርሁሴን ጠይብ የተባለ ሰዎችን በመመልመል በ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች አማካኝነት ሀሰተኛ የሆኑ የኢምባሲ መታወቂያዎች እና ላልች ሰነድችን በማዖጋጀት የማይገባ ብልጽግና ለማግኘት ከባድ የአታላይነት ወንጀል ፈጽመዋል። በ2ኛ ክስ የአዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 23/2/ ድንጋጌን በመተላለፍ በ1ኛ ክስ በተገለጸው ሁኔታ ሀሰተኛ ሰነድ እንዱዖጋጅ ካደረጉ በኋላ በሀሰተኛ ስም ከየመን እና ከአንጎላ ኤምባሲ ዔቃዎች ፍተሻ ሳይከናወንባቸው እና ቀረጥ እና ታክስ ሳይከፈልባቸው ወደ አገር እንዱገቡ እና ለነጋዳ እንዱከፊፈለ በማድረግ በወንጀል ድርጊት እና በተገኘው ውጤት ሙለ ተካፊይ በመሆን ያልተገባ የገንዖብ ጥቅም በማግኘት በግብረአበርነት በፈጸሙት ሀሰተኛ ሰነድ መገልገል የሙስና ወንጀል ተከሰዋል የሚል ነው። 3ኛ ክስ 1ኛ ተጠሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/1/ሀ/ እና የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2007 አንቀጽ 166/1 ድንጋጌን በመተላለፍ በጉምሩክ ወንጀል የተጠረጠረን ዔቃ በማጓጓዛ ላይ የነበረን ተሽከርካሪ ፍተሻ እንዲይደረግበት እና እንዱያመልጥ በማድረግ ሀሰተኛ መረጃ ለጉምሩክ ኢንተልጀንስ ሰራተኞች በመስጠት የጉምሩክ ቁጥጥርን የማሰናከል ወንጀል ፈጽሟል የሚል ነው።
ክሱ ለተጠሪዎች ተነቦላቸው ተጠሪዎች መቃወሚያ በማቅረባቸው ዐቃቤ ሕግ መልስ እንዱሰጥበት በማድረግ ብይን ለመስጠት በተያዖው ቀነ-ቀጠሮ ዓቃቤ ሕግ ለፍ/ቤቱ ባቀረበው አቤቱታ 1ኛ እና 2ኛ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮችን ተከሳሽ አድርጎ ለማቅረብ በ2ኛ ተጠሪ ላይ የቀረበውን ክስ ደግሞ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 122/1 መሰረት በማንሳት ምስክር ለማድረግ እንዱፈቀድለት ጠይቋል።
ጉዲዩ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ዓቃቤ ሕግ ባቀረበው አቤቱታ ላይ 1ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች አስተያየት እንዱሰጡበት ካደረገ በኋላ ዓቃቤ ሕግ በክሱ ማስረጃ ዛርዛር በተ.ቁ 1 እና 2 ላይ የተመለከቱትን ምስክሮች በተከሳሽነት አካቶ ለማቅረብ ያቀረበው ጥያቄ ተገቢ በመሆኑ በዘህ ረገድ ክሱ ተሻሽል እንዱቀርብ ተፈቅድለታል፤ ሆኖም 2ኛ ተጠሪን ከተከሳሽነት ሰርዜ ምስክር አድርጎ ለማቅረብ የጠየቀውን በተመለከተ በአዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 8 እና የአዋጅ ቁጥር 882/2007 እና 434/97 አንቀጽ 43 ድንጋጌ በአዋጅ ቁጥር 882/2007 እንደተሻሻለው መሰረት ግብረአበርን ከክሱ ነጻ በማድረግ በምስክርነት አካቶ የመቅረብ መብት ተግባራዊ ላሆን የሚችለው ጉዲዩ ፍ/ቤት ከመቅረቡ በፉት ስለተፈጸመው ድርጊት እና ስለተባባሪዎቹ ሚና ግለሰብ ጠቃሚ ማስረጃ ከሰጠ ሲሆን ከዘህ ድንጋጌ ግለሰብ የሚጠቀመው ለክርክሩ አመራር ጠቃሚ ማስረጃ ከሰጠ እና የምርመራውን መንገድ መምራቱ ከተረጋገጠ ሲሆን በዘህ ደረጃ የሚሰጠው መረጃም ምስክሩ በገለልተኝነት ፍትሕን የመረዲቱን ሚና እንዱጫወት የሚረዲው ሲሆን ግለሰቡ በተከሳሽነት ከተካተተ በኋላ ያውም ክሱ ተሰምቶ አጠቃላይ የክርክሩን ሂደት በተረዲ እና ተከሳሽ ከላልች ተከሳሾች ጋር በመታሰሩ ምክንያት የሚያገኘውን መረጃ እና የቀሪ ተከሳሾችን የክርክር አመራር ከተረዲ በኋላ ወደ ምስክርነት እንዱቀየር መፍቀደ የክርክሩን ሚዙናው አሰራር የሚጎዲ የተከሳሾችን የመከላከል ሕገ መንግስታዊ መብት የሚሸረሽር በመሆኑ የዓቃቤ ሕግ ጥያቄ በቀጥታ የሙስና አዋጁን ልዩ የስነ-ስርዓት የማስረጃ ሕጉን መሰረት ያላደረገ ቢሆንም ጥያቄው ሉመዖን የሚገባው ችልቱ በዋነኝነት ከሚመራበት ለጉዲዩ የበለጠ አግባብነት ካለው ከአዋጅ ቁጥር 882/2007 አንጻር ላሆን ስለሚገባ ዓቃቤ ሕግ 2ኛ ተጠሪን ምስክር አድርጎ ለማቅረብ ያቀረበው ጥያቄ አግባብነት የለውም በማለት በአብላጫ ድምጽ ውድቅ አድርጎታል።
አመልካች ይህን ትዔዙዛ በመቃወም ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታ አቅርበዋል። ይግባኙ የቀረበለት ፍ/ቤት ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ ግብረአበር ከክስ ነጻ ተደርጎ ማስረጃ የሚሆነው ጉዲዩ ፍ/ቤት ከመቅረቡ በፉት ጠቃሚ ማስረጃ ከሰጠ ስለመሆኑ በሕጉ ከማረጋገጣችንም በላይ ሕጉም ይህን ያደረገው በዓላማ በመሆኑ እና አሁን ክስ ይነሳለት የተባለው ግለሰብ ግን ከግብረአበሮቹ ጋር አብሮ በፍ/ቤት ክስ ቀርቦበት የግብረአበሮቹን የክርክር አመራር ከተረዲ በኋላ ስለሆነ የስር ፍ/ቤት የሰጠው ብይን ሉነቀፍ አይገባም በማለት አጽንቶታል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል ሲሆን ይዖቱም በአዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 8 እና አዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 43 … ጉዲዩ ፍ/ቤት ከመቅረቡ በፉት … የሚለው መስፈርት የተቀመጠው በምርመራ ወቅት በወንጀል ተሳታፉ የሆኑ ሰዎችን ማስረጃ የሆኑ ሰነድችን በማምጣት ሆነ ምስክር በመሆን ምርመራውን እንዱያግዘ እና ለፍትሕ ተባባሪ እንዱሆኑ በማድረግ በምርመራው የተጠናከረ ማስረጃ ለማግኘት ሲባል የተቀመጠ ማበረታቻ ነው፤ በልላ አገላለጽ አንድ ጠቋሚ ወይም በወንጀለ ውስጥ ተሳትፍ የነበረው ሰው ወደ ምስክር ሉዜር ይገባል የሚል ጥያቄ ቢያቀርብ ጥያቄው ተቀባይነት የሚያገኝበት መስፈርት ብቻ እንጂ ዓቃቤ ሕግ አንድ ጊዚ ክሱን ፍ/ቤት ካቀረበ በኋላ ክሱን በመሰረዛ ወደ ምስክር ማዜር አይችልም የሚል ክልከላ ያስቀመጠ ድንጋጌ አይደለም፤ ዓቃቤ ሕግ በራሱ ውሳኔ በየትኛውም ደረጃ ላይ የሚገኝን ጉዲይ አስመልክቶ ተከሳሽን ከክስ ነጻ በማውጣት ወደ ምስክር ለማዜር ይህ መስፈርት በየትኛውም ሕግ በአስገዲጅነት አልተቀመጠም፤ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልትም በሰ.መ. ክስ የቀረበ ቢሆንም ዓቃቤ ሕግ ተከሳሽ የነበረን ሰው ወደ ምስክርነት ማዜር እንደሚችል በመግለጽ ትርጉም ሰጥቶበታል፤ ዓቃቤ ሕግ 2ኛ ተጠሪን ከተከሳሽነት አውጥቶ ወደ ምስክር ያዜረበት አግባብ ግለሰቡ ተከሶ ፍ/ቤት ከቀረበ እና በኋላም በመታሰሩ ምክንያት ያገኘውን ዔውቀት ለማስመስከር እና የተከሳሾችን የመከላከል መብት በመሸርሸር የክርክሩን ሚዙናዊ አሰራር ለመጉዲት ሳይሆን ግለሰቡ ቀድሞውንም በወንጀለ አብሮ የተሳተፈ እና ይህንኑም ክስ ከመመስረቱ በፉት ተጠርጣሪ በሆነበት ጊዚ በምርመራ ክፍል ስለተፈጸመው የወንጀል ድርጊት እና ስለተባባሪዎቹ ሚና የራሱንም ተሳትፍ በመጨመር የሰጠውን የተከሳሽነት ቃል በሙለ ቃል በቃል የምስክርነት ቃለንም ሲሰጥ ከመድገም ውጪ ከላልች ተከሳሾች ጋር በመታሰሩ ምክንያት የቀየረው ወይም የጨመረው ቃል በላለበት የወንጀለ ዋና ፈጻሚ በሆኑ ሰዎች ላይ ውሳኔ ለማሰጠት እና ይህንንም በልላ መንገድ በተሰበሰቡት ማስረጃዎች ብቻ ለማሳካት በቂ ባለመሆኑ ምክንያት ነው፤ ዓቃቤሕግ የ2ኛ ተጠሪ ክስ እንዱነሳ የጠየቀው በተናጠል ሳይሆን ምስክር መሆኑን እንደ ቅድመ-ሁኔታ በማስቀመጥ የነበረ ሲሆን 2ኛ ተጠሪን ወደ ምስክር ለማዜር ክስ መነሳቱ አስፈላጊ በመሆኑ ወደ ምስክር መዜሩን ፍ/ቤቱ ከፈቀደ ክስ እንዱነሳለት በሚል እሳቤ እንጂ ተከሳሹ ወንጀል አልፈጸመም በሚል እሳቤ ክሱ እንዱነሳለት ብቻ ተፈልጎ አይደለም፤ በመሆኑም የስር ፍ/ቤቶች እነኚህን ሁኔታዎች ሳያገናዛቡ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች በስር ፍ/ቤት የሰው ማስረጃ ከመስማቱ በፉት በወ/መ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 122/1 መሰረት በቀን 04/07/2010 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ መሰረት በ2ኛ ተከሳሽ ላይ ያቀረብነው ክስ እንዱነሳ እና በቀሪ ተጠርጣሪዎች ላይ ማስረጃ ለማድረግ የስር ፍ/ቤት የአሁን አመልካችን ጥያቄ ውድቅ የማድረጉን አግባብነት በሰ/መ/ ከተሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ጋር በማገናዖብ ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ በዘህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል። ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል። 2ኛ ተጠሪ በጋዚጣ ጥሪ ተደርጎለት ስላልቀረበ መልስ በጽሐፍ የመስጠት መብቱ ታልፎል።
1ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች የሰጡት መልስ ይዖት በሙስና ወንጀልች አዋጅ ላይ በግልጽ እንደተመለከተው ተከሳሹ ከላልች ተከሳሾች ጋር ክስ ቀርቦበት አብሮ ታስሮ ወደ ምስክርነት ሉቀየር የሚችልበት የሕግ መሰረት የለም፤ 2ኛ ተጠሪ አብሮን ክስ ቀርቦበት የነበረ እና ስለተከሰስንበት ወንጀል አብሮን ተከሳሽ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ከእኛ የሰማውን መረጃ ወደ ምስክርነት ቀይሮ እኛን በሚጎዲ መልኩ እንዱመሰክር መፍቀድ በራሳችን ጉዲይ እኛን የሚጎዲ የምስክርነት ቃል እንዱሰጥ የማስገደድ ያህል ነው፤ አመልካች የጠቀሰው የሰበር መዛገብም ለጉዲዩ ተፈጻሚ ላሆን አይገባም፤ አመልካች 2ኛ ተጠሪን በምስክርነት ማቅረብ የፈለገበት ምክንያት በአቤቱታው ላይ እንደገለጸው ሳይሆን ሆን ብል ከተጠሪዎች ጋር እንዱታሰር በማድረግ ተከሳሾች ነን በሚል ግለሰቡ ነገ በምስክርነት ይቀርብብናል የሚል ጥርጣሬ በላለበት ከእኛ ያገኘውን መረጃ እና እውቀት ተጠቅሞ እኛን ለመጉዲት ታስቦ የተደረገ በመሆኑ የስር ፍ/ቤቶች 2ኛ ተጠሪ በምስክርነት ላቀርብ አይገባም በማለት የሰጡት ውሳኔ ተገቢ ስለሆነ ሉጸና ይገባል የሚል ነው።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራቀኙን ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ፤ ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች እና በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባል ተብል ከተያዖው ነጥብ ጋር በማገናዖብ እንደሚከተለው መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዖብ የሚቻለው አመልካች በስር ፍ/ቤት 2ኛ ተከሳሽ በነበረው 2ኛ ተጠሪ ላይ አቅርቦት የነበረውን ክስ በማንሳት /በማቋረጥ/ ፤ ላልችን በተከሳሽነት በማካተት እና በላልች ምክንያት ጭምር ክሱን በማሻሻል 2ኛ ተጠሪን ምስክር አድርጏ ለማቅረብ ያቀረበውን አቤቱታ ፍርድ ቤቱ በ2ኛ ተጠሪ ላይ የቀረበውን ክስ መነሳት ተቀብል 2ኛ ተጠሪ ከላልች አመልካቾች ጋር ተከሶ የነበረ በመሆኑ ምስክር ሆኖ ላቀርብ አይችልም በማለት መወሰኑን እና ይኸው በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት መጽናቱን የሚመለከት በመሆኑ በወንጀል ክስ ክርክር ምክንያት የዐቃቤ ሕግ ምስክር ተቀባይነት የላለው ምስክር (Inadmissible evidence) ነው የሚለውን ለዘህ ችልት ያስቀርባል ሲባል ከተያዖው ነጥብ አንጻር መርምረናል።
የአገራችን የፍትሕ ስርዓት በአንድ መጽሐፍ ስር የተጠቃለለ ዛርዛር የማስረጃ ሕግ የላለው ቢሆንም በተለያየ ሁኔታ የማስረጃን ተቀባይነት፣ የማስረጃን አግባብነት፤ አመራመርና ምዖና መርሆችን የሚደነግጉ የማስረጃ ሕግ ድንጋጌዎች በሕገ መንግስቱና በላልች የይዖትና የስነ-ስርዓት ሕግ ውስጥ በተበታተነ ሁኔታ ተደንግገው ይገኛለ። ከነዘህም ውስጥ የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ እና የተሻሻለው የጸረ ሙስና ልዩ የሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 434/1997 ተጠቃሽ ነው።
በመሰረታዊነት የአንድን ጉዲይ ዓይነት መሰረት በማድረግ የክርክሩን ጭብጥ ለማስረዲት ላቀርብ የሚገባዉ የማስረጃ ዓይነት (Admissibility) በልዩ ሁኔታ በህግ እስካልተወሰነ ድረስ በተከራካሪ ወገኖች ክሱን ወይም ክርክሩን ያስረደልኛል ወይም ይከላከለልኛል የሚሎቸዉን ማንኛዉንም ዓይነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችለ ስለመሆኑ፣ በዘህ መልኩ በተከራካሪ ወገኖች የሚቀርብ ማስረጃ ደግሞ የተያዖዉን የክስ (ክርክር) ጭብጥ ለማስረዲት አግባብነት ያለው መሆኑ (Relevancy) እስከተረጋገጠ ድረስ የክርክሩን ጭብጥ ለማስረዲት ብቃት አለዉ ተብል እንደሚገመት፣ ጉዲዩን የያዖዉ ፍርድ ቤትም ግራ ቀኝ ያቀረቧቸዉን ማስረጃዎች ለእያንዲንደ ማስረጃ ተገቢዉን ዋጋ በመስጠት ማስረጃዎችን ከነሙለ ይዖታቸዉ መመዖን እንደሚገባዉ የማስረጃ አቀባበል እና ምዖና መርህ ያስገነዛባል። ስለሆነም አንድ ማስረጃ ተቀባይነት የላለው ለፍርድ ሥራ በግብዓትነት መቅረብ የላለበት ነው ወይም ማስረጃው ቀርቦ ከመዛገቡ ጋር ቢያያዛ እንኳን ዳኞች የማስረጃውን ይዖት፣ ተዓማኒነትና ክብደት ለመወሰንና በፍርድ ሥራ በግብዓትነት መጠቀም የላለባቸው መሆኑን የሚገልጽ፤ማስረጃው በማስረጃነት ቀርቦ ከመመርመርና ከመመዖን የሚከለክለው ግልጽ ከልካይ የሆነ የሕግ ድንጋጌ ሉኖር ይገባል።
ወደያዛነው ጉዲይም በዋነኛነት በወንጀል ክስ ጉዲይ ምክንያት በምስክርነት የሚጠሩ ሰዎች መመስከር የሚጠበቅባቸው ውሳኔ ስለሚሰጥበት ፍሬ ነገር ተገቢ የሆኑትን በቀጥታም ሆነ ቀጥታ ባልሆነ መንገድ ስለሚያውቃቸው ፍሬ ነገሮች (የወ/መ/ሕ/ስ/ስ/ቁ.137(1)) በመሆኑ በወንጀል ጉዲይ የቀረበን አንድ ማስረጃን ውድቅ ላደረግ የሚችለው በማስረጃነት እንዲይቀርብ ሕግ የከለከለው (Inadmissible ) ሲሆን እና በፍርድ ቤት ተመዛኖ ተቀባይነት ሲያጣ ነው። ከዘህ ውጪ የወንጀልም ሆነ የሥነሥርዓት ሕጉ የወንጀል ክስን ለማስረዲት ወይም ለመከላከል መቅረብ የሚገባቸውን የማስረጃ ዓይነቶች ለይተው አልደነገጉም። ከዘህ አንጻር አመልካች ከላልች ተጠሪዎች ጋር በ2ኛ ተጠሪ ላይ አቅርቦት የነበረውን ክስ ማንሳቱን ፍርድ ቤቱ ተቀብል አመልካች አሻሽል በሚያቀርበው በዘሁ ክስ 2ኛ ተጠሪን ምስክር አድርጎ ለማቅረብ ያቀረበውን አቤቱታ ግን ያልተቀበለው ስለመሆኑ የሰጠው ምክንያት ደግሞ አመልካች ግብረአበርን ከክስ ነጻ በማውጣት በምስክርነት ተግባራዊ ላሆን የሚችለው ጉዲዩ ፍርድ ቤት ከመቅረቡ በፉት ነው እንጂ ክስ ቀርቦ ከተሰማና ከላልች ተከሳሾች አጠቃላይ የክርክሩን አካሄድ ከተረዲ በኋላ ላቀርብ የሚገባ አይደለም፤ አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 8 ፤ አዋጅ ቁጥር 882/2007 ና 434/97 አንቀጽ 43 ድንጋጌዎች መሰረት ያላደረገ ነው የሚል ነው። ይህም የሚመለክተው 2ኛ ተጠሪ ምስክር ሆኖ እንዲይቀርብ የህግ ክልከላ አለ ወይም በህጉ ምስክር አድርጎ ለማቅረብ አልተመለከተም በማለት ውድቅ ማድረጉን የሚያመለክት ነው።
የሙስና ወንጀልችን የሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 8 ሆነ የተሻሻለው የጸረ ሙስና ልዩ የሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 434/1997 አንደተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 41 የሚደነግጉት ከወንጀለ ልዩ ባህሪ አንጻር በምርመራ ወቅት ፤ጉዲዩ ፍርድ ቤት ከመቅረቡ በፉት ባለት ጊዚያት፤ በወንጀል ድርጊቱ ተካፊይ የሆነ ሰው በአዋጁ የተመለከቱት ሁኔታዎች ተሟልተው ሲገኙ ላቀርብበት ከነበረበት ክስ ነጻ ስለሚወጣበት ሁኔታ ነው። ስለሆነም ስለወንጀለ በሰጠው ጠቃሚ መረጃ መሰረት ምርመራውን በማገዘ ምክንያት ፍርድ ቤት ክሱ ከመቅረቡ በፉት የሚያገኘው ነው። በፍርድ ቤት ምስክር አድርጎ የማቅረብ ጉዲይ አመልካች ምርመራው ተጠናቅቋል ብል ሲያምን በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 108-122 እንደተመለከተው የክስ ማመልከቻውን አዖጋጅቶ ሲያቀርብ የሚገልጸው ነው። የአመልካች አቤቱታም ለስር ፍርድ ቤት የቀረበው በዘሁ የክርክር ደረጃ ላይ ሲሆን የስር ፍርድ ቤት ከክስ በፉት ያለውን የሙስና ወንጀልችን የሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 8 እና የተሻሻለው የጸረ ሙስና ልዩ የሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 434/1997 አንደተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 41 መሰረት በማድረግ የደረሱበት ድምዲሜ ህጉን ያላገናዖበ ከመሆኑም ባሻገር ድንጋጌዎቹ በዋናነት ግብረአበርን ከክስ ነጻ ማድረግን እንጂ በፍርድ ቤት የሚቀርብ ክስ ላይ ምስክር ማድረግን የሚመለከቱ አይደለም። በሰ/መ/ የተሰጠው ፍርድም የሚስገነዛበው ተካሰሽ የነበረን ሰው ዐቃቤ ሕግ ክሱን በማንሳት ምስክር አድርጎ ማቅረቡንና ይሀም የሚጥሰው ህግ አለመኖሩን በመግለጽ ክርክሩን አይቶ ማስረጃውን በመመዖን መወሰኑን ነው።
በአጠቃላይ አንድ ድርጊት ከመፈፀሙ በፉት፣ ሲፈፀም ወይም ድርጊቱ ከተፈፀመ በኋላ ዐቃቤ ህግ ስላቀረበው ክስ ማስረጃ ይሆነኛል በማለት በሕጉ አግባብ ያቀረበውን ማስረጃ በማስረጃነት ላቀርብ የማይችልና ተቀባይነት የላለው (Inadmissible evidence) ነው የሚል ግልፅ ክልከላ የሚያደርግ የሕግ ድንጋጌ ከላለ ማስረጃው ቀርቦ፣ በሕጉ አግባብ ተመዛኖ፣ የማስረጃው ትክክለኛነትና ህጋዊነት ተጣርቶ የሚወሰን እንጂ የማስረጃው አስረጂነት ዋጋ ሳይታይና ሳይመዖን በደፈናው ማስረጃው ከተከሳሾች ጋር አብሮ ተከሳሽ የነበረ ነው፤ የተከሳሾችን የመከላከል መብት ይጎዲል በሚል ምክንያት ተቀባይነት የላለው ነው በማለት ውድቅ ማድረጉ የማስረጃ ተቀባይነት፤አግባብነትና ምዖና መርህን፤ የክርክር አመራርና የዲኝነት አሰጣጥ ስርዓትን ያልተከተለ በመሆኑን መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው። በዘህም መሰረት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ መጋቢት 18 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠውን ብይን በማጽናት የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ሐምል 12 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በወ/መ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 195/2/ለ/2 መሰረት ተሸሯል።
አመልካች 2ኛ ተጠሪን ምሰክር አድርጎ ለማቅረብ ያቀረበው አቤቱታ በልዩ ሁኔታ በህግ ያልተከለከለ በመሆኑ ተቀባይነት ያለው (Admissible) ማስረጃ ነው።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ የጀመረውን ክርክር ቀጥል ማስረጃዎቹን ሰምቶ ለእያንዲንደ ማስረጃ ተገቢዉን ዋጋ በመስጠት ማስረጃዎችን በመመዖን ተገቢውን ዲኝነት እንዱሰጥበት በማለት መልሰን ልከንለታል።ይጻፍ።
መዛገቡ ተዖግቷል።
No topics extracted.